YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አስር የቀድሞ መርማሪዎች አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል የሚል ክስ ቀረበባቸው። ‼️
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከ2002 እስከ 2010 ዓ.ም. ባሉት አመታት የፌድራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል መርማሪ የነበሩ አስር ሰዎችን በሰብዓዊ #መብት #ጥሰት መክሰሱን አስታወቀ።

የቀድሞዎቹ ፌድራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት በምርመራ ወቅት ተጠርጣሪዎችን በኤሌክትሪክ ገርፈዋል፤ በብረት ጉጠት የጣት #ጥፍር_ነቅለዋል፤ አፋቸው ውስጥ #ሽጉጥ ከተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ተከሳሾች በኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በአርበኞች ግንቦት ሰባት አባልነት የጠረጠሯቸውን ግለሰቦች «በግንብ ላይ በተሰካ ብረት ላይ ለረጅም ጊዜ እጃቸውን በካቴና በማሰርና በማንጠልጠል፤ ከግድግዳ ጋር በማጋጨት፣ ፊታቸውን በጥፊ በመምታት፣ የፊትንና የጺም ጸጉር ፒንሳ በሚመስል ነገር በመንጨት እንዲሁም ራሳቸውን በሚስትቱበት ወቅት ውኃ በመድፋት በግድ የአሸባሪ ድርጅቶች አባል መሆናቸውን እንዲያምኑ በማድረግ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ፈፅመዋል» ሲል የፌድራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።
አስሩ ተከሳሾች ኮማንደር ዓለማየሁ ኃይሉ፣ ዋና ሳጅን እቴነሽ አረፋይኔ ወልደ ሚካኤል፣ ዋና ሳጅን ኪዳኔ አሰፋ ሸማ፤ ዋና ሳጅን ርዕሶም ክህሽን፣ ኢንስፔክተር ፈይሳ ደሜ በዳዳ፣ ምክትል ኢንስፔክተር የሱፍ ሐሰን መኮንን፣ ምክትል ኢንስፔክተር ምንላርግልህ ጥላሁን፣ ረዳት ኢንስፔክተር መንግሥቱ ታደሰ አየለ፣ ረዳት ኢንስፔክተር ኃይሉ ሁንዴ እና ኢንስፔክተር ስንታየሁ ፈጠነ ለገሰ ናቸው።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስሩ የቀድሞ መርማሪዎች በአጠቃላይ 78 ክሶች እንደተመሰረተባቸው አስታውቋል። ከክሶቹ መካከል «እጃቸውን በካቴና በማሰር፣ በጣት እንዲቆሙ በማድረግ፣ በኤሌትሪክ ገመድ በመግረፍና በግንባር ግድግዳ በማስገፋት፣ በብልታቸው ላይ 2 እስከ 4 ሊትር ሃይላንድ ውኃ በማንጠልጠል ከ2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት እንዲቆዩ በማስደረግ፣ በኤሌክትሪክ በማስነዘር ፣ ብልታቸውን በፒንሳ በመሳብ የጭንቀት ህመም እና ተያያዥ ድብርት እንዲደርስባቸው አድርገዋል» የሚሉት ይገኙበታል።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስሩ ተከሳሾች «በቀዝቃዛና ጨለማ እስር ቤት ውስጥ በማሰር፣ በእግራቸው መሀል እንጨት አስገብቶ በመገልበጥ የውስጥ እግራቸውን በኤሌትሪክ ገመድ በመግረፍ፣ በምርመራ ክፍሉ በተዘጋጀ ሚስማር ላይ በማንጠልጠል ለረዥም ሰዓት እንዲቆዩ በማድረግ፤ አድካሚ እና ከባድ ስፖርት በማሰራት፤ አፍንጫ ውስጥ እስክሪብቶ በመክተት፣ መቀመጫቸውን እና ጀርባቸውን ውኃ እየደፉ በኤሌክትሪክ ሽቦ በመግረፍ፣ ጺማቸውን በመንጨት ፣ብልታቸውን በቀጭን ሲባጎ በማሰር በግል ተበዳዮች ላይ ሞራላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት አስከትለዋል» ብሏል።

ተከሳሾች በፌድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 12ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ክስ መቀበላቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል። በመጪው የካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም. ክሱ በችሎት የሚነበብ ሲሆን በተከሳሾች የዋስትና መብት ላይ ክርክር ይደረጋል።
ምንጭ፦ DW
@Yenetube @FikerAssefa