#የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ_ዋና_መስሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ የመጨረሻ #ወለል ኮንክሪት ሙሌት ተካሄደ።
የኮንክሪት ሙሌቱ በዛሬው እለት ሲካሄድ ግንባታውን የሚያካሂደው ተቋራጭ እና የባንኩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የንግድ ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ ከሶስት አመት በፊት የተጀመረ ሲሆን፥ በዛሬው እለትም የህንጻው 48ኛ ወለል የኮንክሪት ሙሌት ተካሂዷል።
የአራት አመት ተኩል ፕሮጀክት የሆነው የህንጻው ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
ሶስት ቢሊየን ብር ወጪ የተመደበለት ይህ ፕሮጀክት ለሃገሪቱ የግንባታ ዘርፍ የቴክኖሎጅ ሽግግር በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ነው የተነገረው።
የህንጻ ግንባታው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2025 አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ከያዛቸው እቅዶች መካከል አንደኛው ነው።
ምንጭ:- ፋና
@YeneTube @Fikerassefa