YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አቶ ኢሳያስ ዳኛው‼️

መርማሪ ፖሊስ በአቶ #ኢሳያስ_ዳኛው አዲስ የምርመራ መዝገብ ላይ ይግባኝ ጠየቀ። አቶ ኢሳያስ ኢትዮ-ቴሌኮም የኤን ፒ ጅኦ (NPGO) ኃላፊ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ኢዲኤም(edm) ከተባለው አማካሪ ድርጅት ጋር የስራ ማማከር ውል ያለጨረታ ተዋውለዋል፤ ለ12 አማካሪዎችና ለድርጅቱ ሰራ አስኪያጅ በሰዓት ከ125-150 ዶላር ከ2001 ዓ.ም ጀመሮ እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ለ44 ሰዓት ያለአግባብ ክፍያ እንዲፈጸም አድርገዋል ይላል መርማሪ ፖሊስ።

እንዲሁም ይላል መርማሪ ፖሊስ ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር የተደረገው ውል ከህግና መመሪያ ውጭ እንዲሻሻል ተጠርጣሪው አድርገዋል በማለት አዲስ የምርመራ መዝገብ የከፈተባቸው ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በ50ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡

መርማሪ ፖሊስ በዛሬው ችሎት በተጠርጣሪው ላይ በሙስና ወንጀል መሳተፋቸውን ለጥርጣሬ የሚያበቁ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በአዲሱ የምርመራ መዝገብ ላይ ማያያዙን በማስረዳት በጉዳዩ ላይ በቂ ምርመራ ለማድረግ እና ተጨማሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቆችም በበኩላቸው የደንበኛቸውን የዋስትና መብት ለመከልከል እና አስር ቤት ለማቆየት ካለሆነ በስተቀር እስካሁን ደረስ የቀረበ ክስ አለመኖሩን ለፍርድ ቤቱ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ 1ኛ ወንጀል ችሎትም መዝገቡን መርመሮ በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ወሳኔ ለመስጠት ለ13/06/2011 ዓ.ም ቀጠሮ መያዙን ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@YeneTube @FikerAssefa