YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#Ethiopia #Sport በዓምላክ ተሰማ የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን እንዲመራ ተመረጠ

በአፍሪካ ዋንጫ ወሳኝ ጨዋታዎችን እየዳኘ
የሚገኘው ኢትዮጵያዊው በዓምላክ ተሰማ
የፍፃሜው ጨዋታ እንዲመራ በካፍ የዳኞች
ኮሚቴ ተመርጧል።

በግብፅ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው
ውድድር ሁለት የምድብ፣ አንድ የሩብ ፍፃሜ እና
ትላንት ወደ ፍፃሜ ለማለፍ ወሳኝ የነበረው
የሴኔጋል እና ቱኒዚያን የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታን
የመራ ሲሆን የፊታችን ዓርብ በካይሮ ስታዲየም
በአልጄርያ እና ሴኔጋል መካከል የሚደረገውን
የፍፃሜ ጨዋታም የሚመራ ይሆናል። ይህም
በ1980 የአፍሪካ ዋንጫ #ናይጄርያ#አልጄርያ ያደረጉትን ጨዋታ ከመሩት ተስፋዬ ገብረየሱስ (አሁን የኤርትራ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ናቸው) በኋላ የፍፃሜ ጨዋታን የሚመራ ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል።

Via :- Soccer Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa