YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲሱ መዋቅር መሰረት አምስት #ቋሚ ተጠሪዎችን መሾሙ ተገለፀ።

የቋሚ ተጠሪነት ሹመት #የተሰጣቸው አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ፣ አምባሳደር ዶክተር ቦጋለ ቶሎሳ፣ አምባሳደር ነገ ፀጋዬ እና አምባሳደር ደዋኖ ከድር ናቸው፡፡
በዚህም መሰረት፦

🔹አምባሳደር ወይንሽት ታደሰ- የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ

🔹አምባሰዳር ማህሌት ኃይሉ- የአውሮፓ፣ የአሜሪካ፣ የኤዥያ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ

🔹አምባሳደር በጋለ ቶሎሳ- የዳያስፖራ እና ቆንስላ ጎዳዮች ቋሚ ተጠሪ

🔹አምባሳደር ነጋ ፀጋዬ- የኃብት ማኔጅመንትና አገልግሎት ቋሚ ተጠሪ

🔹አምባሳደር ደዋኖ ከድር- የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ ሆነው ተሹመዋል።

አምባሳደር #ወይንሸት በሲዊዲን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛን ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን፥

አምባሳደር #ማህሌት ኃይሉ ደግሞ በኒውዮርክ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት ምክትል የሚስዮን መሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡

አምባሳደር #ዶክተር ቦጋለ ቶሎሳ በኩባ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም ወደ ዋናው መስሪያ ቤት ተመልሰውም የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው አገልግለዋል፡፡

አምባሳደር #ነጋ ፀጋዬ በፈረንሳይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፥ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል በመሆንም ሰርተዋል፡፡

አምባሳደር #ደዋኖ ከድር ደግሞ በኩባ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር ሆነው ቆይተዋል፡፡

ሁለቱም በተለያየ ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው አገልግለዋል።

ቋሚ ተጠሪዎች የመስሪያ ቤቱን የዕለት ተዕለት ስራ የመከታተልና ውሳኔ የማሳለፍ ሃላፊነት የሚኖራቸው ሲሆን በተለያዩ አገሮች በስፋት ይሰራበታል፡፡

በቀጣይም የዳይሬክተር ጀኔራሎች እና ሌሎች የሃላፊነት እርከኖች ድልድል ይፋ እንደሚያደርግም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ምንጭ ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@yenetube @mycase27