YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች የመግቢያ ቀን ይፋ #አደረገ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የትምህርት ሚኒስቴር የሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች የቅበላ ጊዜ ይፋ #አድርጓል

ሚኒስቴሩ የተማሪዎች የቅበላ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን እና የመቀበያ ጊዜውንም ወደፊት #እንደሚያሳውቅ መግለጹ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት የትምሀረት ሚኒስቴር በዛሬው እለት የሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች የቅበላ ጊዜ ይፋ ያደረገ ሲሆን፥ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በዩኒቨርስቲዎቹ በመገኘት እንዲመዘገቡና ትምህርት እንድትጀምሩ አስታውቋል።

ተማሪዎች ወደ #ተመደቡበት ተቋማት ሲሄዱም ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅና የስፖርት ትጥቅ አማልተው እንዲጓዙም ጠቁሟል።

©fbc
@yenetube @mycase27