የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በነፃ የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ መስጠት መጀመሩን ተናገረ፡፡ ትናንት በነፃ መሰጠት የጀመረው ምርመራ እስከ ነገ ይቀጥላል ተብሏል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ #ንዋይ_ፀጋዬ ለሸገር እንደተናገሩት ለምርመራው ይሄንኑ ብቻ የሚሰራ የስፔሻሊስት ሀኪሞች #ቡድን ተዘጋጅቶ እየሰሩ ነው፡፡
እድሜያቸው #ከ35ዓመት በላይ ከሆኑ መቶ ሺህ ሴቶች 42 ያህሉ በበሽታው እንደሚጠቁ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ብዙ ጊዜ ሴቶች ደረት፣ ብብት አካባቢ እባጮችን ሲያዩ ጡታቸው አካባቢም የተለየ የቆዳ ቀለም ሲኖር ቀድመው የካንሰር ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ በሽታው ቢገኝባቸው እንኳን #በፍጥነት ህክምናውን ወስደው #ለመዳን ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
በመሆኑም እስከ #ነገ በሚሰጠው የጡት ካንሰር #ነፃ ምርመራ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ በሚገኘው የመድሀኒያለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኝታችሁ መመርመር ትችላላሁ ተብላችኋል፡፡
እድሜያችሁ ከ35 አመት በላይ የሆናችሁ ሴቶች ሁሉ የእረፍት ቀናችሁን ተጠቅማችሁ የነፃ ምርመራውን እድል እንድትጠቀሙ ተጋብዛችኋል ፡፡ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ 250 አልጋ ያለው የካንሰር ህክምና ተቋምም እየገነባ መሆኑንም ሰምተናል፡፡
ምንጭ:- ሸገር FM 101.1
@YeneTube @Fikerassefa