YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ምክር ቤቶቹ ዛሬ የፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱን መልቀቂያ #በመቀበል አዲስ የሪፐብሊኩን #ፕሬዚዳንት ይሾማሉ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመውም፥ ምክር ቤቶቹ በስብሰባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት #ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የሚያቀርቡትን መልቀቂያ በመቀበል አዲስ ፕሬዚዳንት ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ነበር አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስን በመተካት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት።

ሶስተኛው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ነገ ለሚተካቸው አራተኛ የኢፌደሪ ፕሬዚዳንት በምክር ቤቶቹ ፊት ስልጣን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል
©FBC
@yenetube @mycase27