YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ሻሸመኔ_ከተማ

በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የሰዎች ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ።

አደጋው የደረሰው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር ሞሃመድ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በከተማዋ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ለይ መሆኑን የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።

በአደጋውም የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱንም አቶ አዲሱ ገልፀዋል።

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ላለፈ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎችም የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

ከአደጋው ጋር ተያይዞም አንድ የሻሸመኔ ከተማ የፀጥታና አስተዳደር በሮ ተሽከርካሪ በእሳት መጋየቱንም አቶ አዲሱ አስታውቀዋል።

ተሽከርካሪው ፀጥታ የማስከበበር ስራ ላይ በተሰማራበት ወቅት ቦምብ ጭኗል በሚል #በተሳሳተ_መረጃ በእሳት መጋየቱን አቶ አዲሱ ገልፀዋል።

ሆኖም ግን በተሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት ቦምብ እንዳልነበረ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ማረጋገጣቸውንም አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅትም አደጋው ጋር ተያይዞ ወጣቱን በመምሰል የህገ ወጥነት እንዲስፋፋ መንገድ የመዝጋት፣ የዝርፊያ እና በፍቅር አብሮ የኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች ላይ ጉዳት ለማድረስ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ምልክቶች መታየታቸውንም ገልፀዋል።

©FBC
@YeneTube @Fikerassefa