YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለመጣው ለውጥ ዋጋ ለከፈሉ እና አስተዋፅኦ ላደረጉ የቤት እና የገንዘብ ሽልማት ሊሰጥ ነው፡፡

••>የሪፍት ቫሊ ዩንቨርስቲ ፣ ሶደሬ ሪዞርት ፣ የሪፍት ቫሊ ሆስፒታል፣ የቀርሽ ማይክሮ ፋይናንስና የናፍያድ ትምህርትቤቶች ባለቤት የሆኑት ባለሃብቱ ድንቁ ደያሳ በጥሬ ገንዘብ እና ቤት ሰርተው ሊሰጡ ነው፡፡

••>ድጋፉ ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና ፍትህ ሲታገሉ ለነበሩ የተመረጡ እና በእስር ላይ የቆዩ እንዲሁም በአስር ቆይታቸው ግፍ የተፈጠመባቸው እና የተለያየ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም ለህዝቡ ነፃነት ሲታገሉ የነበሩና በአነስተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ የኦሮሞ አርቲስቶች መሆኑ ታውቋል፡፡

••>ባለሃብቱ ከዚህ ቀደም ከኢትዮ ሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ12 ሚሊየን ብር በላይ እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዉ በተግባር ከ28 ሚሊየን ብር በላይ የሰጡ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃይ ወገኖች በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ትምህርት የሚሰጥበትን ሙሉ የከፍተኛ የትምህርት ማእከል ከአብራኩ ከወጣሁት ህዝብ አይበልጥብኝም በማለት ለተፈናቃይ ወገኖች ሙሉ በሙሉ በመልቀቅ እስከ አሁኑ ተፈናቃይ ወገኖች በዚሁ ኮሌጅ እየኖሩ ከመንግስት የሚደረግላቸዉን የመጨረሻ እርዳታ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙም ታወቋል፡፡

••>ባለሀብቱ በ2008ዓ.ም መጨረሻ በሶደሬ ሪዞርት ሆቴል በተደረገዉ የኦሮሞ አባገዳ ምክር ቤት ላይ አባዱላ በመሆን የተመረጡ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡

#ሸገር_ታይምስ
@Yenetube @Fikerassefa