#ሰኔ_16
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ 11 የፖሊስ አመራሮች በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም አቃቤ ህግ ገለፀ፡፡
ጉዳዩን የሚከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የፖሊስ አመራሮቹ በሰኔ 16ቱ የቦምብ ጥቃት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲካሄድባቸው ነበር፡፡
©EBC
@YeneTube @Fikerassefa

#ሰኔ_16 ⬇
አቶ ብርሃኑ ጃፋር ቦንብ የወረውሩትን አካላት በመኪና በመሸኘት እና ጥላሁን ጌታቸው ቦምብ በመወርወር የተጠረጠሩት ግለሰቦች ላይ ፍድር ቤቱ የሰባት ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
©FBC

#አቶ_ተስፋዬ_ኡርጌ #ሰኔ~16⬇️
በብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ናቸው ተብለው በሰኔ 16ቱ የቦምብ ጥቃት በመምራትና በማስተባበር ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፌደራል ፖሊስ ምርመራ ላይ የሚገኙት አቶ ተስፋዬ ዑርጌ በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ከተከሰተው ግጭት የጦር መሳሪያና የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት መርማሪ ፖሊስ ገለጸ።
የፌደራሉ የመጀመሪያ ተረኛ 1ኛ የወንጀል ችሎት መርማሪ ፖሊስ ያከናወናቸውን ስራዎች አድምጧል።
በዚህም መርማሪ ፖሊስ በአዲስ አበባ እና በክልል የሚገኙ ተባባሪ ተጠርጣሪዎችን መያዣ የማውጣት፣ የምስክር ቃል የመቀበል እና ሌሎች ስራዎች ማከናወኑን ገልጿል።
በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር በተፈጸመው ጥቃት በመነሻነት እጃቸው አለበት የተባሉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከሃገራቱ ጋር እየተወያየ መሆኑንም ጠቅሷል።
የቀሪ ምስክሮችን ቃል ለመቀበል፣ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች ላይ ከተጠርጣሪው ጋር ግንኙነትና እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎችን የማጣራት ስራ እና ሌሎች ቀሪ ስራዎችን ለማከናወንም 14 ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል።
የተጠርጣሪ ጠበቃ በበኩላቸው በቅድሚያ ተጠርጣሪውን የማረሚያ ቤት ልብስ በማልበስ በምስል አስደግፈው የሚለቁና የግለሰቡን ስም እየጠቀሱ ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ የሚያቀርቡ የሚዲያ አካላት እንዲያስተካክሉ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ ብለዋል።
በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት አላቸው ያላቸውን አካላት አጠናቅቄያለሁ እያለና አቃቢ ህግ ክስ ለመመስረት ጊዜ እየጠየቀ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊጠይቅ አይገባም በማለትም ተቃውመዋል።
ከዚህ ባለፈም መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ስራውን በፍጥነት እየሰራ አይደለም በማለት ፍርድ ቤቱ ከፍትህ ገጽታ አኳያ ሊያየው እንደሚገባም ተቀውሟቸውን አሰምተዋል።
ከዚህ ባለፈም ተጠርጣሪ የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው ምርመራው ቢቀጥል የሚፈጥረው ችግር የለም በማለትም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርም ጠይቀዋል።
መርማሪ ፖሊስም ተጠርጣሪው በዋስ ቢወጡ የምርመራ ሂደቱን በማደናቀፍ ማስረጃ ሊያሸሹ ይችላሉ በማለት ዋስትናውን ተቃውሟል።
ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ማንኛውም ሚዲያ የሁለቱን ወገን ጉዳይ በሚዛናዊነት እንዲያቀርብ በማለትና ዋስትናውን በማለፍ ለፖሊስ ተጨማሪ 8 ቀን ሰጥቷል።
©FBC
@yenetube @yenetube

⬆#ሰኔ_16 ጉዳይ እና ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ጉዳይ⬇
ሰኔ 16 በመስቀል አደባባይ የተፈጸመውን የቦምብ ጥቃት እና የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ግድያን የምርመራ ውጤት በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ ጠቅላይ አቃቤ ማስታወቁን የኢትዮዽያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
©Etv
@Yenetube @Fikerassefa

Update #ሰኔ_16 አቃቢ ህግ በሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ወንጀል አምስት ግለሰቦች ላይ ክስ መሰረተ⤵️
ጠቅላይ አቃቢ ህግ በሰኔ 16ቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦምብ አፈንድተዋል ያላቸው አምስት ግለሰቦች ላይ ክስ መሰረተ፡፡
አምስቱ ግለሰቦች ጌቱ ግርማ፣ ብርሃኑ ጃፈር፣ ጥላሁን ጌታቸው፣ ባህሩ ቶላ እና ደሳለኝ ተስፋዬ ናቸው አቃቤ ህግ ቦምብ በማፈንዳት ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው፡፡
ክሱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት የተከፈተ ሲሆን ክሱን ለእያንዳንዳቸው በችሎት እንዲደርስ ይደረጋል ተብሏል፡፡
የጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደሚያመላክተው አንደኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ ከሁለተኛ ተከሳሽ ጋር ሱሉልታ ላይ በመገናኘት ሰልፉን የጠራው ገለልተኛ ወገን ሳይሆን ኢህአዴግ ነው ኤችአር 128 የተባለውን በአሜሪካ ኮንግረስ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆን ያደርጋል የሚል ምክንያቶችን በመግለጽ ቦምቡን በመወርወር እንዲበተን እናድርግ በማለት እንዲዘጋጅ መግለጹን በክሱ ተመላክቷል፡፡
ለሦስተኛ ተከሳሽ ደውሎም ቦምብ የሚወረውር ሰው አንዲፈልግ ተልዕኮ መስጠቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡
ሁለተኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ጃፈር ደግሞ በሚያዝያ ወር 2010 ዓመተምህርት ሁለት ኤፍ 1 እና አንድ የጭስ ቦምብ ያለው መሆኑን ለአንደኛ ተከሳሽ መግለጹን የጠቀሰው አቃቤ ህግ ሱሉልታ ከተማ ተገናኝተው ቦምቡን የድጋፍ ሰልፉ ላይ በመወርወር ጥቃት ለማድረስ በመነጋገር ቦምቡን መወርወር የሚችሉ ልጆች እንዲዘጋጁ ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር ተነጋግረዋል ሲል አቃቤ ህግ በክሱ ጠቅሷል፡፡
ሦስተኛ ተከሳሽ ጥላሁን ጌታቸው በድጋፍ ሰልፉ ላይ ቦምብ እንዲያፈነዳ በአንደኛ ተከሳሽ ተገልጾለት ለአራተኛ ተከሳሻ በመደወል ቦምብ ለመወርወር ማቀዱን በመግለጽ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት እንዲገናኙ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
አራተኛ ተከሳሽ ባህሩ ቶላ በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት መስቀል አደባባይ ቦምቡን ለመወርወር ማቀዱን በመጥቀስ በሁኔታው ለመወያየት አስኮ የተቀጣጠሩ ሲሆን ከዚያም ቡራዩ ላይ በአምስተኛ ተከሳሽ ቤት ተገናኝተዋል፡፡
ከተገናኙ በኋላም በአምስተኛ ተከሳሽ ቤት ያደሩ ሲሆን አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች በሰኔ 16 2010 ዓመተምህረት ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ላይ ሁለተኛ ተከሳሽ በሚያሽከረክረው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ2 262335 አዲስ አበባ በሆነ መኪና ውስጥ ሁለት ኤፍ 1 ቦምብ እና አንድ የጭስ ቦምብ በመያዝ አንደኛ ተከሳሽ ቤት ማስቀመጣቸውን በክሱ ተጠቅሷል፡፡
ያስቀመጡትን ቦምብም በዚሁ ተሸከርካሪ ጭነው አዲስ አበባ ውንጌት አካባቢ ከሦስተኛ፣ ከአራተኛ እና ከአምስተኛ ተከሳሽ ጋር በመገናኘት ፒያሳ አካባቢ የገቡ ሲሆን በምን መልኩ ጥቃቱን ማድረስ እንዳለባቸው መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡

የተጠናከረ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ለዋልታ ቲቪ የተናገሩት ቅንጫቢ⤵️
📌"ኦነግ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ከኢትዮዽያ መንግስት ጋር ትጥቁን #ፈቶ #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው ተብሎ የሚነገረው መሰረተ ቢስ ወሬ ነው"
📌"እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት #ስምምነት_የለም። የታጠቀው ኣአካል ትጥቅ ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ የምንፈታበት ምክን ያት የለም።"
📌"ትጥቅ መፍታት የሚባል #sensitivity ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈቱ መባልም አንፈልግም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ኦነግ ያለው ሚና ምን እንደሚሆን ነው የተስማማነው።"
📌አቶ ዳውድ #ሰኔ_16 በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራ ድርጅታቸው እንዳልተሳተፈ ገልፀዋል። #በቡራዩና_በአዲስ አበባ በተፈጠሩ ግጭቶችም ኦነግ #አለመሳተፉን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።
📌#በቤኒሻንጉል፣ #በወለጋና #በከፋ በተፈጠሩ ግጭቶች #ኦነግ መሳተፉንና አለመሳተፉን ለማረጋገጥ ማጣራት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።
📌አቶ ዳውድ በበደኖና በአርባ ጉጉ #በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ #በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የኦነግ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።