YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ማስተካከያ_ይደረግበት ቢሾፍቱ የተገነባው የውኃ ፓርክ በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው አለመሆኑን ማረጋገጥ ችለናል። በኬንያ #ሞንባሳ ከተማ #ዋይልድ_ወተር የተሰኘ ግዙፍ የውሃ ፓር እንዳለ ትሪፕ አድቫይዘር ጠቁሞናል።
@YeneTube @FikerAssefa
#ማስተካከያ ከአማራ ፓሊስ

ስለ ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ በህግ ጥላ ስር የመዋል ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያው የሚሰራጨው የተሳሳተ መረጃ መታረም ይገባዋል ።

ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ የኮሚሽኑ የኮሚኒኬሽንና ሚዲያ መምሪያ ኃላፊ ሲሆኑ ሰራዊት የመምራትም ሆነ የማሰማራት ኃላፊነት የላቸውም በዚህም የልዩ ኃይል ፖሊስ ስምሪት አሰጣጥ ላይ ሃሳብ ሰጥተው ታሰሩ የሚለው ፍፁም የተሳሳተ ሃሳብ ነው ።

መኮንኑ በክልላችን ሰኔ 15ት ቀን በተከሰተው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ወንጀል ኃላፊነታቸውንና የአመራር ልምዳቸው በሚጠይቀው ልክ አለመወጣታቸውና በጉዳዩ ላይ ዕውቅና አላቸው የሚል ማስረጃ የቀረበባቸው በመሆኑ በህግ ቁጥጥር ስር ሁነው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ።

የተጠረጠሩበት ወንጀልም የኮሚሽኑ ሁሉም የመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት በምርመራ ቡድኑ በግልፅ ተነግሯቸው እሳቸውም ኃላፊነታቸውን ያልተወጡበትን ምክንያት አቅርበዋል ።

ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው ፍትህ በሚሰጣቸው ውሳኔ ንፅናቸው የሚረጋገጥ ሁኖ እርስ በርሳችን የሚከፋፍሉ ዘጋባዎች መታረም ይገባቸዋል ።

ምንጭ ፦ አማራ ፓሊስ
@YeneTube @Fikerassefa