YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ ቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች እየታሸጉ መሆኑ ተነገረ

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየታሸጉ መሆኑ ተገልጿል። በተለይም በወጣቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ እነዚህ ቤቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ፣ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

ይህ መታሸግ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተስተዋለ ቢሆንም፣ በተለይም በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ የሚገኙ በርካታ የቢንጎ ቤቶች በዛሬው ዕለት መታሸጋቸው ካፒታል ተመልክቷል።

አንዳንድ የጨዋታ ቤቶቹ ባለቤቶች እንደተናገሩት፣ መታሸጉ የተፈጸመው “አዋኪ ድርጊት” ፈጽመዋል በሚል ምክንያት ነው። በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እነዚህ አጫዋቾች፣ እርምጃው ቀጣይነት እንደሚኖረው እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

ምንም እንኳ እነዚህ ቤቶች ዋነኛ ተግባራቸው የቢንጎ ጨዋታ ማቅረብ ቢሆንም፣ ከጨዋታው በተጨማሪ የጫት መጠቀሚያ እና ለህገወጥ ወንጀሎች መነሻ ቦታዎች እንደሆኑ እና ይህንንም መንግስት ለማስቆም በሚል እርምጃውን እየወሰደ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

በተለይ በአዲስ አበባ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በስፖርት ውድድር ላይ የሚደረጉ የውርርድ (ቤቲንግ) ጨዋታዎችን ከማሸግ ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንዲገኝ የሚታወቅ ሲሆን አሁን የቢንጎ ቤቶች መታሸግ ከዚህ ጋር ግንኙነት ያለው ስለመሆኑ ግን እስካሁን በይፋ የተረጋገጠ ነገር የለም።
44👍13👎3
ሀገራችን ኢትዮጵያ የራሷን ጦርነት ሳትቋጭ የፕሮክሲ ጦርነት ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች።

የሱዳን እርስ በእርስ ጦርነት ስንት ሀገሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ ?

https://youtu.be/rs3JTbs89vg
13😁12👍1
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
3
YeneTube
Photo
ለዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች እየቀረበ ያለዉ ሀይል ተፅዕኖ እያሳደረበት እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልገሎት ገለፀ

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልገሎት  ወደ ሶስት ያህል ለሆኑ የዳታ ሴንተሮች ሀይል እያቀረበ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ ተናግረዋል።

አገልግሎቱ ለእነዚህ የዳታ ሴንተሮች ከ 10 እስከ 20 ሜጋ ዋት ሀይል እየወሰዱ እንደሚገኝ ተቋሙ የተጠናቀቀው በጀት አመት የስራ አፈፃፀም እና የ2018 አመት እቅዶቹ ዙሪያ ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ስራ አስፈፃሚዉ ይህንን የገለፁት።
የዳታ ማይኒንግ ዘርፍ ላይ ለሚገኙ ድርጅቶች ከፍተኛዉን ሀይል እያቀረበ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል መሆኑን የገለፁት ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ  ለድርጅቶቹ የሚቀርበዉ ሀይል ከፍተኛ መሆን በአገልግሎቱ ፍላጎት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሪፖርት እንደተገለፀዉ ከሆነ በተጠናቀቀው በጀት አመት አገልግሎቱ 16 ሺህ 2 መቶ 43 ጌጋ ዋት ሀይል ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በጅምላ መግዛቱን ያሳያል።

ይህ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የሀይል ፍላጎቱ 18.2 በመቶ ከፍ ማለቱን ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ መንግስት በዳታ ማይኒግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ድርጅቶች በቀጣይ የሚሰጠዉ ፍቃድ አለመኖሩን አስታዉሰዉ።
ሆኖም በአገልግሎቱ ላይ ለድርጅቶቹ እየቀረበ የሚገኘዉ ሀይል ተፅዕኖ መኖር በግልፅ የሚታይ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በበኩሉ በበጀት አመቱ ከዚህ ዘርፍ የመጣው ገንዘብ በተቋሙ አጠቃላይ ገቢ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ መሆኑን ይገልፃል።

ለመደበኛ ተጠቃሚዎች የኤሌክትሪክ ኃይል በመሸጥ ከተገኘው ገቢም የሚበልጥ መሆኑን ገልፆል።

ነገር ግን  ከአሁን በኋላ ለአዲስ የዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎች ፈቃድ እንደማይሰጥ እና ያሉትም  በሂደት እንዲወጡ የመግፋት ፍላጎት እንዳለው ይፋ አድርጓል።

@Yenetube @FikerAssefa
13😁8👍7👎2👀1
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል - የገንዘብ ሚኒስቴር

የገንዘብ ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል አለ፡፡

ነባሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከምጣኔ ውጭ ሌሎች ማሻሻያዎችን በማካተት ከ3 አስርት ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ በ2017 በጀት አመት ስራ ላይ መዋሉን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከነበረው ከ12 በመቶ በላይ ድርሻ በየዓመቱ በተከታታይ እየቀነሰ ከ7 በመቶ በታች መድረሱን ጠቅሶ፥ ከዚህ ጠቅላላ ቅናሽ 44 በመቶው የተጨማሪ እሴት ታክስ ድርሻ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ ህጉን አሁን ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ የቀጣይ ዓመታት ለውጦች ጋር እንዲጣጣም በማድረግ በመካከለኛ ዘመን የገቢ ስትራቴጂው መሰረት ተሻሽሎ በ2017 በጀት ዓመት ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል ብሏል፡፡

በማሻሻያው መሰረት በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን ነው የገንዘብ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
18👍9😁2
4 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን አስታወቀ!

ኮሚሽኑ በተቋሙ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ያለው የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን ገልጿል፡፡ኮሚሸኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በ2017 በጀት አመት 4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል ይህም ካለፈው አመት ጋርሲነጻጸር የ2.2 በመቶ እድገት አሳይቷል።

በበጀት አመቱ ለ 525 አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች ፈቃዶች እና 19 የማስፋፊያ ፈቃዶች መሰጠቱን ጠቁሞ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱት ውስጥ የውጭ ባለሃብቶች 308፣ 109 ለጣምራ ኢንቨስትመንት እና ከ98 በላይ ደግሞ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ሊሰጥ ችሏል። ይህም በተቋሙ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል።

በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ባሉ ኢንቨስትመንቶች 123 ሚሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ገቢ ያስገኙ ሲሆን ከዞኖቹ ውጪ ባሉ ኢንቨስትመንቶች 543.11 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል።ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው በ2017 በጀት አመት ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ በሚመረቱ ምርቶች በመተካት ስኬት እንዳስመዘገበ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
16😁12🔥2👎1
YeneTube
Photo
ወደ ሶማሊያ ሲጓዝ በፑንትላንድ ሀይሎች ተይዞ የነበረውና የተለቀቀው የጦር መሳሪያ የጫነ መርከብ አቅጣጫውን ወደ ጅቡቲ ቀይሮ መጓዙ ተነገረ!

“ሲ ወርልድ” የተሰኘው መርከብ በቅርቡ የጦር መሳሪያ ጭኖ ከቱርክ፥ ኢዝሚር ግዛት ወደ ሶማሊያ ሲጓዝ፥ በሶማሊያ ሰሜናዊ ግዛት በፑንትላንድ ሀይሎች ተይዞ ከተለቀቀ በኋላ፥ አቅጣጫውን በመቀየር ወደ ጅቡቲ መጓዙን ከስፍራው የወጡ ዘገባዎች አመላከቱ። የመጀመሪያ መድረሻው ሞቃዲሾ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በአቅራቢያው ወደምትገኘው ጅቡቲ አቅጣጫውን ቀይሯል።

የጭነት መርከቡ በፑንትላንድ የባህር ኃይል ፖሊስ (PMPF) ተይዞ መክረሙ ከሰሞኑ ሲዘገብ ቆይቷል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ መርከቡ የጦር መሳሪያ እገዳ ከጥቂት አመታት በፊት የተነሳላት የሶማሊያን ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አቅጣጫ አድርጎ እየተጓዘ ነበር።

በወቅቱ የወጡ ተጨማሪ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ የጦር መሳሪያው በሶማሊያ “TURKSOM” በመባል በሚታወቀው ወታደራዊ ካምፕ የሚውል ነው። “TURKSOM” የሶማሊያና ቱርክ ጥምር ወታደራዊ ማሰልጠኛ በአል-ሻባብ ላይ በሚደረገው ውጊያ ለሚሰለጠኑት የ “ጎርጎር” ወታደሮች ማሰልጠኛ ስፍራ እንደሆነ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ፣ በርካታ በሱማሊያ የሚሰራጬ ዘገባዎች፣ መርከቡ በወቅቱ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ሞቃዲሾን ትቶ አቅጣጫውን ወደ ጅቡቲ መቀየሩን ጠቁመዋል።
ሞቃዲሾም ሆነ አንካራ እስካሁን ባለው ሁኔታ ላይ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጡም።

ከሶስት ሳምንታት በፊት የፑንትላንድ የባህር ኃይል ፖሊስ በኮሞሮስ ባንዲራ ስር ይጓዝ የነበረውን ይህን  “ሲ ወርልድ” የተባለ የጭነት መርከብ ከቱርክ የተላከ ወታደራዊ መሳሪያ ጭኖ ለሶማሊያ ጦር (SNA) ለማድረስ በሚል ሲጓዝ በቦሳሶ ወደብ ነበር የተያዘው ።

በፑንትላንድ ባለስልጣናት መግለጫ መሰረት፣ የቱርክ አምባሳደር ወደ ሶማሊያ ባደረጉት ጉብኝት፣ በመርከቡ ላይ ያለው የጦር መሳሪያ፣ የቱርክ መንግስት ንብረት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካቀረቡ በኋላ የፑንትላንድ ባለስልጣናት መርከቡን ለመልቀቅ ወስነዋል።ነገር ግን፥ ትላንት የወጣው የጋሮዌ ዘገባ መርከቡ ለምን ወደ ጅቡቲ እንዳቀና አልገለጸም።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
25👍1
ሂልተንን ጨምሮ አራት ሆቴሎች 564 ሚሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገቡ!

ሂልተን ሆቴልን ጨምሮ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር የሚተዳደሩ አራት የቱሪዝም ዘርፍ ድርጅቶች፣ በ2017 የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት 564.2 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘታቸው ተገለጸ። ይህ ውጤት ከታቀደው የትርፍ ግብ በ37 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ባደረገዉ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ፣ የስፓ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ (ፍል ዉሃ)፣ የጊዮን ሆቴሎች ኢንተርፕራይዝ፣ ሂልተን ሆቴል እና የገነት ሆቴልን ያካተተውን የሆቴል ዘርፍ አፈጻጸም ላይ ትኩረት አድርጓል።

ድርጅቶቹ በድምሩ 2.1 ቢሊዮን ብር ገቢ በማሰባሰብ ከታለመው 114 በመቶ ማሳካት ችለዋል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ እያደገ የመጣውን የገበያ ፍላጎት እና የቱሪስቶች ፍሰት በመጠቀም ንግዳቸውን እንዲያሰፉ አሳስቧል።

ለዘላቂ እድገት ሲባልም የደንበኞችን እርካታ ማሻሻል፣ ዘመናዊ የግብይት ስልቶችን መጠቀም፣ እንዲሁም ዲጂታል አገልግሎትና የቦታ ማስያዣ ስርዓቶችን ማዘመን እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ተሰጥቷል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
16😁5👎4👍3🔥1
ብሔራዊ ቲያትር የቲኬት ዋጋን ወደ 200 ብር አሳደገ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር የመግቢያ ትኬት ዋጋን ከ ስምንት ዓመት በፊት ከነበረበት 80 ብር ወደ 200 ብር ማሳደጉን አስታውቋል። ቲያትሩ ከ1948 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ኪነጥበብ ከፍ ማለት እና መከበር አለበት በሚል ዋጋዉን ለማሻሻል ጥናት ሲደረግ መቆየቱ ተገልጿል።

ይህ ውሳኔ የኪነጥበብን ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና የቲያትር ቤቱን አገልግሎት ለማሻሻል ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።የቲያትር ቤቱ ኃላፊዎች፣ የቲኬት ዋጋው ከዚህ ቀደም በጣም ዝቅተኛ ስለነበር፣ አሁን የተደረገው ጭማሪ ሳይሆን 'ማሻሻያ' ነው ሲሉ አብራርተዋል። የዋጋ ማሻሻያው "ማንንም የማይጎዳ መልኩ" መሆኑን በማስረገጥ፣ የቲኬት ዋጋው ለሁሉም ትያትሮች በ200 ብር መወሰኑን ገልጸዋል።

ኦንላይን ትኬት ሽያጭ እና ሌሎች ለውጦች
ከተመሠረተ 70 ዓመታትን ያስቆጠረው ብሔራዊ ቲያትር፣ አዳዲስ ለውጦችን በማምጣት ተመልካቹን ለማርካት መዘጋጀቱን አስታውቋል።ከለውጦቹ መካከል ተመልካቾች ከየቤታቸው ሆነው ትኬት መግዛት የሚያስችላቸውን 'ኦንላይን' የቲኬት ሽያጭ ሥርዓት ማመቻቸቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም፣ የቲያትር ቤቱ ኃላፊዎች በቀጣይ ሁሉም ክልሎች የሚሳተፉበት ሥልጠና በብሔራዊ ቲያትር እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህ የዋጋ ማሻሻያ እና ሌሎች ተያያዥ ለውጦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት እና ዘመናዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
42👎9😁3👍1
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
2😁2
በዎላይታ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በትናንትናው ዕለት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል።

በአደጋው ሰለባ የሆኑ ሰዎች የሴሬ ፍንጫዋ ቀበሌ ነዋሪና የአንድ ቤተሰብ አባልት ሲሆኑ፤ በቦርኮሼ ቀበሌ እና በሰሬ ፍንጫዋ ቀበሌ መካከል ባለዉ በፍንጫዋ አዋሳኝ ፏፏቴ አጠገብ ለሣር አጨዳ በሄዱበት በተከሰተው በመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

ከአደጋው ሕይወታቸው ካለፉት ሰዎች ውስይ የአንዲት ሴት ልጅ አስክሬን መገኘቱ የተገለጸም ሲሆን፤ የእናቷ እና የወንድ ልጅ አስክሬን ባለመገኘቱ የአከባቢው ማህበረሰብና የፀጥታ አካላት በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

የአየር መዛባትን ተከትሎ የሚመጣው የክረምት ወቅት ዝናብ እንደዚህ ዓይነትና ሌሎች አደጋዎች እንዳይከሰት በሁሉም አከባቢ ህብረተሰቡ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲል የወረዳው ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳስቧል።በአደጋው ቀጠና ያሉ ሰዎችን እንደዚህ ዓይነትና ሌሎች አደጋዎች እንዳይርስባቸው ወደ ሌላ ቦታ የማሸጋገር ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
8😭6
2
YeneTube
Photo
የአለም ባንክ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ዘርፍ በገንዘብ የመደገፍ ፍላጎት አለኝ ማለቱ ተሠማ።

በሌላ በኩል በሪል ስቴት አልሚዎች እና በቤት ገዥዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በድርድር መፍትሄ እንዲያገኙ የሚሰራ የግልግል ዳኝነት ቡድን እየተቋቋመ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ልማት ከተጀመረ 30 ዓመት ሆኖታል።

በእነዚህ ጊዜያት በርካታ ዜጎች የቤት ባለቤት መሆናቸው፤ የብዙዎች የአኗኗር ዘይቤም መቀየሩ ይጠቀሳል።የዚያኑ ያህል ዘርፉ ላይ የሚነሱ ችግሮችም አሉ።

አንዱ በሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰሩ ቤቶች አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ታሳቢ ያደረጉ አይደሉም፤ ውድ ናቸው የሚል ነው።የቤቶቹ ዋጋ እነዚህኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች ጥያቄ ሲቀርብ ይሰማል።

ባለፈው ሚያዝያ ወር የተመሰረተው የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ግን የቤቶቹ ዋጋ ውድ ነው በሚለው ሃሳብ አይስማማም።አቶ ከድር ሰይድ የማህበሩ ዋና ፀሃፊ ሲሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሪል ስቴት ቤቶች ባለቤት እንዲሆኑ መፍትሄው በአነስተኛ ወለድ ፤ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ የሚቀርበው ሌላው ቅሬታ ባሉት ጊዜ እና የጥራት ደረጃ ቤቶችን ሰርተው አያስረክቡም የሚል ነው።በዚሁ ምክንያት በአልሚውና እና በደንበኛው መካከል አለመግባባቶች ሲፈጠሩ አንዳንዴም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሲያመራ ይታያል።

የተባሉት ችግሮች እንደሚገጥሙ የሚናገሩት ዋና ፀሃፊው አቶ ከድር - የግልግል ዳኝነት አይነት ስራ የሚሰራ ቡድን ማህበሩ እያቋቋመ እንደሚገኝ ነግረውናል።ማህበሩ በቅርቡ ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር መወያየቱን የነገሩን አቶ ከድር በውይይቱ ባንኩ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ዘርፍ በገንዘብ መደገፍ እንደሚፈልግ ተረድተናል ብለዋል።የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አሁን ላይ 57 አባላት እንዳሉት ሠምተናል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
27🔥6
አየር መንገዱ ባለው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት በርከት ያሉ የሀገር ውስጥ በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ!

‎የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት በርከት ያሉ የሀገር ውስጥ በረራዎቹ ከትናንት ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም መስተጓጎል እንደገጠማቸው አስታውቋል።

በዛሬው ዕለትም ተመሳሳይ የአየር ፀባይ በተወሰኑ ጣቢያዎች ላይ ሰለተስተዋለ ወደ እነዚህ ጣቢያዎች የሚደረጉ በረራዎች ማድረግ አለመቻሉን አየር መንገዱ ለአሐዱ በላከው መግለጫ አመላክቷል።

የአየሩ ሁኔታ ሲሻሻል መደበኛ በረራዎች ወዲያውኑ የሚቀጥሉ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፤ በዚህ ምክንያት ለተፈጠረው የደንበኞች መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
17👎3
ብሔራዊ የአልኮልና አረቄ ፋብሪካ ምርቶቹን ወደ አለምአቀፍ ገበያዎች እንዲያስፋፋ ማሳሰቢያ ተሰጠ!

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የብሔራዊ የአልኮልና አረቄ ፋብሪካ ምርቶቹን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያዎች በማስፋፋት ሽያጩን እንዲያሳድግ መክሯል።

የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እንዳስታወቀው፣ ፋብሪካው ዕድገቱን ማስቀጠል እንዲችል የግብይት ሥራዎችን ማጠናከር፣ ወደ ውጭ ገበያ መግባትና የሀገር ውስጥ የስርጭት መረቡን ማሻሻል ይኖርበታል ብሏል።

በተጨማሪም፣ የፋብሪካውን ምርታማነትና የማምረት አቅም በማሳደግ እንዲሁም ገቢ የሚያስገኙ ንብረቶችን በአግባቡ በመጠቀም ትልቅ ዋጋ መፍጠር እንደሚችል አስረድቷል።

ይህ የተባለው የፋብሪካው 2017 በጀት ዓመት አፈፃፀሙ በተገመገመበት ወቅት ነዉ። መንግስታዊዉ ኩባንያው በዓመቱ ከታክስ በፊት 340 ሚሊዮን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ሲደርስ፣ አጠቃላይ ገቢው ደግሞ 2.6 ቢሊዮን ብር መሆኑም ተመላክቷል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
11😁6👎3👍1🔥1