YeneTube
Photo
የ1 ዓመት ከ8 ወር እድሜ ያለውን ሕጻን በማገት ሁለት ሚሊዮን ብር የጠየቁ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ!
በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አፍሪካ ሕብረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፤ የአንድ ዓመት ከስምንት ወር እድሜ ያለውን ሕጻን በማገት ሁለት ሚሊዮን ብር የጠየቁ እና በወንጀሉ ተባብረዋል የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ፋኑኤል ብርሃነ የተባለን የ1 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያለውን ሕጻን ሐምሌ 30 ቀን 20017 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 1 ሰዓት ከ40 ገደማ ከመኖሪያ ቤቱ በሥውር በመውሰድ ወደ ወላጅ አባቱ ስልክ መደወላቸው ተገልጿል፡፡ለአባቱ ሕጻኑን እንዳገቱት በመግለፅ እና ሁለት ሚሊዮን ብር በአካውንት ገቢ እንዲያደርጉ በመጠየቅ በቤተሰብ ላይ ጭንቀትና ድንጋጤን ፈጥረዋል፡፡
አቶ ብርሃነ ገ/ፃዲቅ የተባሉት የሕጻኑ ወላጅ አባትም ስለ ሁኔታው በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ በወቅቱ አሳውቀዋል።የሕጻኑ መጥፋት ሪፖርት የደረሰው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የቄራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የምርመራ እና የክትትል ክፍሉ ተቀናጅተው በተደረገ ከፍተኛ ጥረት፤ ካህሳይ ተክላይ የተባለውን እና ከሕጻኑ ወላጅ አባት ጋር ዝምድና ያለውን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ ገልጿል፡፡
የወንጀሉ አቀነባባሪ ነው ተብሎ ተጠርጥሮ በተያዘው በካህሳይ ተክላይ ላይ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ሥራ በሕጻኑ እገታ ከሚገኝ ገንዘብ የጥቅም ተካፋይ ለመሆን በመስማማት፤ ወንጀሉን የተባበሩ ፊሊሞን ገ/ማርያም፣ ተክሊት ህሉፍ እና ምህረት ዕድሉ የተባሉ ተጨማሪ ሦስት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ተነግሯል፡፡
እነዚህ ተጠርጣሪዎች የተያዙት ወንጀሉ በተፈፀመ በማግሥቱ ሳሪስ አካባቢ በሚገኘው ማራኪ በተባለ ሆቴል ውስጥ አልጋ ክፍል በመከራየት ሕጻኑን ይዘው በተሸሸጉበት ወቅት ፖሊስ ባደረገው ክትትል ነው ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ በወንጀሉ የተጠረጠሩት አራት ግለሰቦች በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ፖሊስ አስታውቋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

❤53🔥1😭1
Forwarded from YeneTube
ናቲ ስፒች ላንጉጅ ቴራፒ ኪሊኒክ
Nati Speech language therapy clinic
ከእርስዎ ወይም ከቤተሰብዎ ከንግግር ጋር በተያያዘ ችግር ያለበት ሰው ያውቃሉ?
እንግዲያውስ ናቲ የንግግር የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ለእርስዎ የሚሆን መፍትሔ ይዞልዎት መጥቷል ከንግግር ከቋንቋ እንዲሁም ከተግባቦት ጋር በተያያዘ ህክምና ወይም ስልጠና ከፈለጉ ወደ ናቲ የንግግርና የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ይምጡ ወይንም ይደውሉ እፎይ የሚሉበትን ምላሽ ያገኛሉ
“አለመናገር ጨዋነት አይደለም እክል እንጂ”
👉አድራሻ፡ መገናኛ ሾላ አባይ ባንክ የካ ሚካኤል ቅርንጫፍ ያለበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205
ከመምጣትዎ በፊት ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ
☎️ስልክ፡- 09- 08- 78- 26 -52
👉በተጨማሪም በነዚህ አማራጮች ያገኙናል
👉የቴሌግራም ገጽ ፡- https://tttttt.me/Nslt19
👉የቲክቶክ ገጽ፡-https://vm.tiktok.com/ZM69FtgrR/
👉 የፌስቡክ ገጽ፡-https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
👉በ YouTube ገፅ:-https://youtube.com/@natigetnet1989?si=_81wKG_5Ev45AZvY
👂👂በነፃ
የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በየትኛውም ክልል ለሚኖሩ በነፃ

❤11
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት የግል አልሚዎች እንዲሳተፉ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱ ተገለጸ
በዘርፉ ያለውን የኃይል ስብጥር ለማሳደግና የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት የግል አልሚዎች እንዲሳተፉ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡
በየዓመቱ የሀገሪቱ የኃይል ፍላጎት በአስር በመቶ እያደገ መሆኑን ያነሱት የተቋሙ የትራንስሚሽን እና ቢዝነስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አንዷለም ሲዓን፤ ከታሪፍ ማሻሽያው ጎን ለጎን የግል አልሚዎች እንዲሳተፉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ይሁን እንጂ በሀገሪቱ ያለው ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ የታሪፍ ምጣኔ የግል አልሚዎችን የሚያበረታታ ባለመሆኑ እስከ አሁን የሚፈለገው ውጤት አለመገኘቱ ተገልጿል፡፡
ከአሁን ቀደም ተቋሙ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወስዶት የነበረውና በተቋሙ የፋይናንስ ቁመና ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ የቆየውን ብድር መንግሥት ወደ ራሱ መውሰዱም ተነስቷል፡፡
ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ተቋሙ የመክፈል አቅሙንና ገቢውን ያገናዘበ ብድር ከባንኩ በመውሰድ ፕሮጀክቶችን በራሱ አቅም ለማስፈፀም እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

❤12
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ጋር የነበረውን የንግድ እገዳ ለተጨማሪ 90 ቀናት አራዘሙ
ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ፕላትፎርማቸው ላይ የእገዳውን ማራዘሚያ የሚያዝዘውን የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ መፈረማቸውን የገለፁ ሲሆን "የስምምነቱ ሌሎች አካላት በሙሉ እንደነበሩ ይቀጥላሉ" ብለዋል። የቻይና ንግድ ሚኒስቴር በበ
ኩሉ ቀረጥ የማቆም ውሳኔው መራዘሙን በተመሳሳይ ጊዜ አስታውቋል።
ማስታወቂያው ከዚህ ቀደም የተሰጠው ጊዜ ከማብቃቱ ጥቂት ሰዓታት በፊት ነው የወጣው።
ይህ ባይሆን ኖሮ ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ምርቶች ላይ ቀድሞውንም ከፍ ያለውን 30% ቀረጥ ልታሳድግ ትችል ነበር፣ ቻይናም በበኩሏ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች ላይ አፀፋዊ ቀረጥ በመጨመር ምላሽ ልትሰጥ ትችል ነበር ተብሏል።
ይህ እረፍት ሁለቱ ሀገራት ልዩነቶቻቸውን እንዲፈቱ ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ምናልባትም በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ መካከል ለሚደረግ ጉባኤ መንገድ ሊከፍት ይችላል።
ትራምፕ ሚያዝያ ወር ላይ ቀረጥ መጣል ከጀመሩ በኋላ ቻይና ለአንዳንድ የአሜሪካ ኩባንያዎች የሚውሉ ድርብ ጥቅም ያላቸውን እቃዎች ወደ ውጭ መላክን የገደበች ሲሆን ሌሎችን ደግሞ ወደ ቻይና እንዳይገቡ ወይም ኢንቨስት እንዳያደርጉ ከልክላለች።
በግንቦት ወር በጄኔቫ በተደረገ ስብሰባ ወደ ኋላ ለማፈግፈግ እና መነጋገራቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል፡ የአሜሪካ ቀረጥ ወደ 30 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን የቻይና ደግሞ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ብሏል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ድርድሮች ቀጥለዋል ሲል የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው።

❤20👎4😁1👀1
በአፋር ክልል 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ዓመት ዕድሜ ያለው የሰው ቅሪተ አካል ተገኘ!
በአፋር ክልል "ሌዲ ገራሩ" በተባለው የጥናት ቦታ 2.8 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያለው የአዲስ የአውስትራሎፒቴከስ እና የሆሞ ዝርያዎች ቅሪተ አካላት ተገኘ።የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ የሳይንቲስቶች እና የተመራማሪዎች ቡድን 13 ጥርሶችን በማግኘት በሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ሂደት ያልተጠናውን ጊዜ ለመረዳት የሚረዱ መረጃዎች መሰብሰባቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ጥርሶቹ የተገኙት ከዚህ በፊት የሰው ልጅ ቅሪተ አካል በተገኘበት አከባቢ ሲሆን የቅሪተ አካል አጥንቶቹ ሙሉ ስላልሆኑ በእነዚህ 13 ጥርሶች የተወከሉት የአውስትራሎፒቲከስ እና የሆሞ ዝርያዎች ስያሜ ገና እንዳልተሰጣቸው ተገልጿል።
በኔቫዳ ዩኒቨርሲቲ የፓሊዮአንትሮፖሎጂስት እና ረቡዕ ዕለት በኔቸር ዕትም ላይ የወጣው የምርምር ስራ መሪ የሆኑት ብራያን ቪልሞር “ይህ የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ታሪክ ቀስ በቀስ እየተለዋወጠ የመጣ የአንድ ዝርያ ታሪክ ብቻ አለመሆኑን ያረጋግጣል” ብለዋል።
ቪልሞር አክለውም “ይልቁንም የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ሂደት ልክ እንደሌሎች ህይወት ያላቸው ነገሮች ነው፤ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ዝርያዎች ያሉት እና አብዛኛዎቹም በተመሳሳይ ጊዜ ይኖሩ ነበር” ብለዋል።
Via AS

❤30😁29👎5👍2🔥1
ኢትዮጵያ የተቀበሩ ፀረ ሰው ፈንጂዎችን ለማስወገድ የጊዜ ገደቡ ለአራተኛ ጊዜ እንዲራዘምላት ጥያቄ አቀረበች!
በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በጦርነት ወቅት ተቀብረው የቀሩ የፀረ ሰው ፈንጂ ቅሪቶችን ለማስወገድ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለአራተኛ ጊዜ እንዲራዘም ጥያቄ አቀረበ፡፡
እ.ኤ.አ. በ2004 ኢትዮጵያ ያፀደቀችውና የኦታዋ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን እ.ኤ.አ. በ1997 የፀደቀውን የፀረ ሰው ፈንጂዎች ጥቅም፣ ምርት፣ ግብይትና ክምችትን ለማስወገድና ለማገድ የወጣ ስምምነት መፈረሟ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ በስምምነቱ አንቀጽ 5 መሠረት በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ፀረ ሰው ፈንጂዎችን ማስወገድ፣ ወይም መወገዳቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዕርምጃዎችን የመውሰድ ግዴታ እንዳለባት ተደንግጓል፡፡
https://ethiopianreporter.com/144396/

❤19👍4
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለ2017 ሀገራዊ የመጅሊስ ምርጫ ከ13 ሚሊዮን በላይ ሙስሊሞች ምዝገባ ማድረጋቸውን አስታወቀ!
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሀገራዊ የመጅሊስ ምርጫ ምዝገባ ለማጠናቀቅ እና የምርጫ ኩነቶች ዝግጅትን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም ምርጫውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ላለፉት አምስት ወራት የቅድመ ዝግጅት ሲደረግ እንደነበረና በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ በኡለማዎች፣ በምሁራን፣ በወጣቶች፣ በሴቶች እና በሥራ ማህበረሰቦች፤ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበረ የምርጫ አስፈጻሚ ቦርዱ ሰብሳቢ ዶ/ር አብዱልአዚዝ ኢብራሂም ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ለምርጫው ይመዘገባል ተብሎ የተጠበቀው በተለይም ዕድሜው ከ18 በላይ የሆነ እንዲሁም በዕድሜ በመለየት እና ወቅቱ ክረምት ከመሆን እና ማህበረሰቡ በምርጫ ዙሪያ ያለውን ሁኔታ መረዳት እጥረትን ጨምሮ ከ8 እስከ 10 ሚሊዮን ሕዝብ እንደነበረ አንስተዋል።
ነገር ግን በ2017 በሚካሄደው የመጅሊስ ምርጫ በአጠቃላይ 13 ሚሊዮን 151 ሺሕ 889 ሕዝብ ተመዝግቦ፤ ለምርጫ ራሱን ዝግጁ ማድረጉን ሰብሳቢው ለአሐዱ ተናግረዋል።በዚህም መሠረት ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች ላይ ምርጫው እንደሚካሄድ ገልጸው፤ የትግራይ ክልል ምርጫ ባለው የሰላም አለመረጋጋት ምክንያት በክልሉና በክልሉ የምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሠረት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አስታውቀዋል።
ከ60 ሺሕ በላይ መስጅዶችን ለምዝገባ ሲጠቀሙባቸው እንደነበረ ገልጸው፤ ከእነዚህ ውስጥ 49 ሺሕ 92 መስጂዶች ምርጫ እንደሚከናወንባቸው ገልጸዋል።ምርጫው በግልጸኝነት፣ በፍትሐዊነት፣ በአካታችነትና በአሳታፊነት ለማሳካት ስፊ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ቴክኖሎጂን ጭምር በመጠቀም ሲሰራበት ስለመቆየቱ ተናግረዋል።
ምርጫውን ለማስፈጸም ከተቋቋመው የምርጫ አስፈጻሚ አካላት እንደየእርከናቸው በአጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ 155 ሺሕ 101 ያህል ሰዎች በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ደረጃ ስልጠና መውሰዳቸውንም አክለዋል።"ፍትሐዊነትን ከማስፈን አንፃርም በመቶዎች ከሚቆጠሩ አቤቱታ አቅራቢዎች ጋር ውይይቶች ተደርገው መቀራረብና መረዳዳት ተችሏል" ብለዋል።
በመሆኑም "ምርጫው ነገ ነሐሴ 9 ቀን 2017 ከጁምአ ሰላት በኋላ በመላ ሀገሪቱ ተጀምሮ እንደየ አካባቢው ሁኔታ እስከ እሁድ ነሐሴ 11 ቀን 2017 ድረስ የመስጂድ ደረጃ ምርጫ ይካሄዳል" ብለዋል።
ከዚያ በመቀጠልም የወረዳ ምክር ቤት፣ የዞን ምክር ቤት፣ የየክልል ምክር ቤቶች እና የፌደራል መጅሊስ ምክር ቤት ከነሐሴ 11 2017 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ባሉት ጊዜያት ውስጥ እንደየ ክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ተካሄዶ፤ ነሐሴ 30 ቀን 2017 እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል።
መላው ሙስሊም ማህበረሰብ ቀደም ሲል በምዝገባ ያሳየውን ፍቃደኝነት እና ተነሳሽነት አሁንም የምርጫ ግብ የሆነውን መሪዎቹን መምረጥ፣ ሁሉም በነቂስ ወጥቶ እንደየ ማህበረሰብ ክፍሉ ዑለማዕ፣ ምሁሩ፣ ወጣቱ፣ ሴቱ እና የሥራ ማህበረሰብ በየ መስጂዱ ወጥቶ መሪዎቹን እንዲመርጥ የምርጫ አስፈጻሚ ቦርዱ ሰብሳቢ ዶ/ር አብዱልአዚዝ ኢብራሂም ጥሪ አስተላልፈዋል።
Via Ahadu

❤31👎10👍2🔥1
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤3
የአሜሪካ ሴናተር ቴድ ክሩዝ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሶማሊላንድ እውቅና እንዲሰጡ ያቀረቡትን ጥሪ የሶማሊላንድ ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች አደነቁ!
የሶማሊላንድ ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የአሜሪካ ሴናተር ቴድ ክሩዝ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሶማሊላንድ እንደ እውቅና እንዲሰጡ ያቀረቡትን ጥሪ በደስታ ተቀብለዋል። ጥሪውም ለብዙ አስርት አመታት ሲታገሉለት ለነበረው እውቅና ትልቅ ድጋፍ እንደሆነ ገልጸዋል።
የሴኔቱ የአፍሪካ እና ግሎባል ጤና ፖሊሲ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ሴናተር ቴድ ክሩዝ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ በጻፉት ደብዳቤ፣ ሶማሊላንድን “ለአሜሪካ ወሳኝ የደህንነት እና የዲፕሎማሲ አጋር” በማለት ያሞካሹ ሲሆን፣ “እውቅና እንዲሰጣትም” አሳስበዋል።
በደብዳቤያቸው፣ ሶማሊላንድ በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ያላትን ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ፣ ጠንካራ የጦር ሃይል እና ለፀረ-ሽብርተኝነትና ፀረ-ወንበዴ ዘመቻዎች ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ጠቅሰዋል። በተጨማሪም “ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ እና ከመሳሰሉ ተቀናቃኞች ከፍተኛ ጫና ቢደርስባትም” ሶማሊላንድ “ከአሜሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኗን” ገልጸዋል።
የሴናተር ክሩዝ ደብዳቤ የቀረበው የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ ኢሮ ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት ባቀዱት ጉዞ ዋዜማ ላይ ነው። በዚህ ሳምንት፣ ሚኒስትሩ አብዲራህማን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት፣ ፕሬዝዳንቱ ወደ አሜሪካ በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፋዊ ጉዞ ያደርጋሉ።

❤18😁2🔥1
የሲኖትራክ ተሸከርካሪ የጥራት ጉድለት ሳይሻሻል ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ታግዷል - የጉምሩክ ኮሚሽን
የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ያለበትን የጥራት እና የቴክኒክ ችግር እስኪያሻሽል ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መታገዱን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።
የጥራት ጉድለቱ በየጊዜው የሰው ሕይወት ብሎም ንብረት እንዲጠፋ ምክንያት በመሆኑ፤ አምራች ድርጅቱ ማሻሻያ እስከሚያደርግ ድረስ ተሸከርካሪው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ መከልከሉን ነው የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዘሪሁን አሰፋ ለኢቢሲ ዶትስትሪም የተናገሩት።
ክልከላው ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉንም ገልፀዋል።በዚህም ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ ምንም ዓይነት የማስገቢያ ፈቃድ እንዳልተሰጠ አረጋግጠዋል።

👍35❤20😁10
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤4👎1
የፑቲን እና የዶናልድ ትራምፕ ውይይት
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ብራዲሚር ፑቲንና የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አላስካ ሪቻርድ ኤር ቤዝ ተገኝተው ከፍትኛ እቀባበል አደረጉላቸው ።
ብራድሚር ፑቱንን አላስካ ሪቻርድ ጆይት ኤር ፖርት ሄድ እያጨበመቡ የትቀበሏቸው ዶናልድ ትራምፕ ሲሆኑ ለብራድሚር ፑቲን ክብር የአየር ላይ ትሪዒትም ቀርቧል።
በዩኩሬንና በሩሲያ እጅግ እውዳሚ ጦርነት ለማስቆም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተስፋ ሳይቆርጡ በአደረጉት ጥረት ትናንት የአሜሪካና የሩሲያ ፕሬዝዳቶች ችግሩን ለመፍታትና ጦርነቱን ለማስቆም ውይይት አድርገዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከፑቲን ጋር ሙሉ ለሙሉ ስምምነት ላይ ባይደርሱም በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ እንደተስማሙ እና ውይይቱ አበረታች እንደነበር ጠቅሰዋል።
ፑቲን ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅሰው አድናቆት ሰጥተዋል።
ነገር ግን ጦርነቱን ለማስቆም ራሺያ ዘላቂ እና አስተማማኝ ዋስትና ትፈልጋለች ብለዋል።

1❤18🔥3😭1
ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ማንነታቸው ባልታወቁና ጭምብል ባደረጉ ሰዎች መወሰዱ ተጠቆመ!
ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ላለፉት አራት ቀናት ማለትም ከነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓም ጀምሮ ሥራ ባለመግባቱ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደወልለትም ሆነ ከቤተሰቦቹ ለማጣራት ቢሞከርም ማግኘት አልተቻለም።
በሥራ ላይ እያለ የገባበት በመጥፋቱ የሥራ ባልደረቦቹም ሆኑ የሚቀርቡት ጓደኞቹ በእጅ ስልኩ ላይ ቢደውሉም ማግኘት አልተቻለም።
ጋዜጠኛ ዮናስ በሚኖርበት በሸገር ከተማ ኮዬ ፌጬ ኮንዶሚኒዬም በመሄድ በተደረገ ማጣራት፣ ጋዜጠኛው የተወሰደው ረቡዕ ምሽት ፊታቸውን በጭምብል በሸፈኑ ሰዎች መሆኑን ባካባቢው ካሉ የጥበቃ ሠራተኞች ለማወቅ ተችሏል።
የጥበቃ ሠራተኞቹ ተጨማሪ መረጃ መስጠት ባለመቻላቸው፣ ጋዜጠኛ ዮናስ፣ እነማን እንደወሰዱትና የት እንደተወሰደ ማወቅ አልተቻለም።
Via Reporter

2❤14😭14

❤10👀1