YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የዩክሬይን ፕረዚደንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ ፕረዚደንት ትራምፕ በመጨው አርብ ከሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ሊያካሄዱት ያቀዱት ንግግር «የዩክሬንን ሉአላዊ ግዛት የሚቆርስ ነው» ሲሉ ተቃዎሞአቸውን አሰሙ።

ሁለቱም ፕረዚደንቶች የዩክሬይንን ግዛት በሩስያ ሥር እንዲቆይ የሚል ስምምነት ካደረጉ «ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ነውም ብለዋል።

ፕረዚደንቱ በተንቀሳቃሽ ምስል ተቀርጾ ባሰራጩት መልዕክታቸው «ዩክሬይን መሬቷን ለወራሪዎች አሳልፋ አትሰጥም» ሲሉ ተደምጠዋል። «ለግዛታዊ አንድነታችን የሚሆን ምላሽ በሕገ-መንግስታችን አለ» ያሉት ዘለንስኪ ከዚህ የሚያፈነግጥ የለም ሲሉ አክለዋል። በዩክሬይን ሰላምን ለማምጣት በሚደረጉ ውይይቶች ለመካፈል ዝግጁ ነን ያሉት ፕረዚደንት ዘለንስኪ ዩክሬይን ያገለለ ንግግር «ጸረ ሰላም ነው» ሲሉ ተቃውመዋል።

የፑቲንና የትራምፕ ንግግር በሩስያ የተያዙ የዩክሬይን ግዛቶችን በሩስያ ሥር እንዲቆዩ የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት ዘለንስኪ ይህ ደግሞ «ተግባራዊ ሊሆን የማችል » ብለውታል።

የሩስያው ፕረዚደንት ቭላድሚር ፑቲንና የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የፊታችን አርብ በአላስካ ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን የጀርመን ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
22😁3
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የንግድ ባንክን አዲስ ሎጎ አገዱ!

የንግድ ምልክቱን ለመቀየር 600 ሚሊየን ብር መድቦ ሲሰራ የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጨረሻው ሰአት አዲሱን ሎጎ ይፋ የማድረግ እቅዱን ሰርዟል።በምክንያት የተጠቀሰው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ስለ አዲሱ ሎጎ መተዋወቅ መረጃውን ከቀናት በፊት ከሰሙ በሀኋላ በሰጡት ትእዛዝ ነው።

አዲሱ ሎጎ ፈጠራ የጎደለው ነው የሚሉት ተቺዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩም ላሳለፉት ውሰኔ ይሄንኑ በምክንያት ጠቅሰው፤ ምልክቱ የኢትዮጵያን ፊደል አለማካተቱ በተጨማሪ ምክንያት ጠቅሰዋል ሲል ሪፖርተር ነው የዘገበው።

ከቅረብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ሃብት እየመደቡ የፋይናንስ ተቋማት የንግድ ምልክቶቻቸውን እየቀየሩ እና እያሻሻሉ ተስተውለዋል።ሆኖም የሚያስተዋውቋቸው ምልክቶች ከፍተኛ ትችትን ከማስተናገድ አልዘለሉም።

ግዙፍ መንግስታዊ የፋይናንስ ተቋም የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ስር ነቀል ለውጥ እያደረገ መሆኑ ይታወሳል።አሁን ያለው የንግድ ምልክቱ ለበርካታ አስርት አመታት ሲጠቀምበት የኖረ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
88😁32👍11👎5🔥2
የትግራይ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ በትግራይና አፋር ክልሎች አዋሳኝ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ አፈንጋጭ ታጣቂ ቡድን ዛሬ በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት አድርሷል በማለት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ከሷል።

ቢሮው፣ ታጣቂ ቡድኑ "ጠብጣብ" በተባለ ቦታ ላይ አደረሰው ባለው ጥቃት የአንድ የክልሉ ጸጥታ ኃይል አባል ሕይወት መጥፋቱን ገልጧል። ይህ አጥፊ ተግባር ከቀጠለ ቡድኑን በሚመሩና በሚያስተባብሩ አካላት ላይ ርምጃ እወስዳለሁ በማለት ያስጠነቀቀው ቢሮው፣ ደም መፋሰሱ ባስቸኳይ ይቁም በማለት ጥሪ አድርጓል።

[ዋዜማ]
@YeneTube @FikerAssefa
29😁9😭1
የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አፈጻጸም ከ71 በመቶ በላይ ደረሰ!

የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግንባታ አፈጻጸም 71 ነጥብ 47 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት፤ ኮይሻ ከዓባይ ግድብ በመቀጠል በኢትዮጵያ ሁለተኛው ግዙፍ የውኃ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነው።

የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፤ የግንባታው አፈጻጸም 71 ነጥብ 47 በመቶ ደርሷል ብለዋል።ግንባታው በ2021 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ አመላክተው፤ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በዓመት 6 ሺህ 460 ጊጋ ዋት ስዓት ኃይል ያማመንጨት አቅም እንደሚኖረው አስታውቀዋል።የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 201 ሜትር ቁመትና 1 ሺህ 12 ሜትር ርዝመት እንደሚኖረው መገለጹ የሚታወስ ነው።

Via Gazette Plus
@YeneTube @FikerAssefa
31👍8🔥7👎2
የሀበሻ ቢራ ዋና ባለድርሻ ከአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች ድርሻቸውን በ5,900 ብር ለመግዛት ጥያቄ አቀረበ!

የሀበሻ ቢራ ዋና ባለድርሻ የሆነው ባቫሪያ ኦቨርሲዝ ቢሩስ ቢ.ቪ. (BOB) የተባለ የውጭ ኩባንያ፣ ከአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖችን በአንድ (1 ሺህ ብር) አክሲዮን 5,900 ብር ለመግዛት ጥያቄ አቀረበ።ይህ ጥያቄ በኩባንያው የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ምዝገባ ዙሪያ ውዝግብ በነበረበት ወቅት ይፋ መሆኑን ካፒታል ለመረዳት ችሏል።

አብዛኛውን ድርሻ የያዘው ባቫሪያ ኦቨርሲስ ቢራ ፋብሪካ (BOB) ከአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች ለመግዛት ያቀረበው ይህ ዋጋ፣ ቀደም ሲል በዴሎይት ከተገመተው ዋጋ በ 34% ብልጫ አለው። የኩባንያው መረጃ እንደሚያሳየው፣ የሽያጩ ጊዜ እስከ ነሐሴ 31 ቀን 2025 ድረስ የተራዘመ ነው።

የኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች ግን ቅሬታቸውን በማንሳት፣ አነስተኛ ድርሻ ያላቸው ባለሀብቶች ትርፋቸውን ወደ ካፒታል እንዳይቀይሩ ወይም አክሲዮናቸውን በገበያ ላይ እንዳይሸጡ ሲከለከሉ፣ አብዛኛውን ድርሻ የያዘው ባቫሪያ ግን ድርሻውን እንዲያሳድግ ልዩ ዕድል ተሰጥቶታል የሚል ክስ አቅርበዋል።

ባለአክሲዮኖች ይህ እርምጃ ሕጋዊ መሠረት የለውም እና የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን ይጎዳል በማለት እየተከራከሩ ነው።የሀበሻ ቢራ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር መስፍን አቢ ቀደም ሲል በሰጡት ምላሽ፣ ባለአክሲዮኖች የ ESX ምዝገባ እስከሚጠናቀቅበት ህዳር 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲጠብቁ ወይም በጠቅላላ ጉባዔ የጸደቀውን የገንዘብ ትርፍ እንዲቀበሉ ሁለት አማራጮች እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
36👀1
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
😁1
Forwarded from YeneTube
በ 25% ዲስካውንት ለገበያ አቅርበናል!

📌 ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት        

👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል  
መገልገያዎች    
👉 ሦስት ሊፍት   
👉 ባለ 3 ፎቅ የመኪና ማቆሚያ ቦታ    
👉 ቴራስ    
👉  ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት    
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር

📌 የካሬ አማራጮች
👉ባለ 1መኝታ - 63 ካሬ
👉ባለ 2 መኝታ - 86  እስከ 103 ካሬ
👉ባለ 3 መኝታ - 132  እስከ 146 ካሬ        

👉1 መኝታ 63ካሬ=      
        10% ቅድመ ክፍያ 693,000 ብር       
                   ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር 
👉2መኝታ 86 ካሬ       
          10%ቅድመ ክፍያ 946,000 ብር       
                  ሙሉ ክፍያ 9,460,000 ብር       
👉3መኝታ 114 ካሬ     
           10%ቅድመ ክፍያ 1,219,800 ብር     
                   ሙሉ ክፍያ 12,198,000 ብር  

ለበለጠ መረጃ 
☎️ +251976195835

Telegram username
@Ruthtemersales

What's app
https://wa.me/251976195835

TEMER PROPERTIES
Create | Construct | Deliver
#TemerProperties #Temerrealestate
4
Forwarded from ALX Ethiopia
🚀 Want to become a Virtual Assistant? Join our live Telegram session to learn about the programme, how to apply, and get your questions answered!

Don’t miss it - happening this Saturday, 3 ነሐሴ 2017 (August 9, 2025) starting at 11፡00 (5:00 PM) in our Telegram group
👉🏾 t.me/virtualassistantapplicationguide

#ALXEthiopia #ALXAfrica #ALXTribe #AIwithALX #VirtualAssistant
1😭1
የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ ለሚገነባው የአፍሪካ ግዙፉ አውሮፕላን ማረፊያ 8 ቢሊዮን ዶላር ለማፈላለግ ስምምነት ፈረመ!

የአፍሪካ ልማት ባንክ ግንባታው ሲጠናቀቅ የአፍሪካ ትልቁ አውሮፕላን ማረፊያ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀውን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ከሚያስፈለገው 10 ቢሊየን ዶላር፣ 8 ቢሊዮን ዶላር ለማፈላለግ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተፈራረመ።

ስምምነቱን የአየር መንገዱ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ለማ ያደቻ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና (ዶ/ር) ዛሬ በአዲስ አበባ አከናውነዋል።በፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ፤ የአየር መንገዱ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ እና የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።

በስምምነቱ መሰረት ባንኩ 80 በመቶውን ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት የሚያፈላልግ ሲሆን 20 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።በሁለት ምዕራፍ የሚገነባ አየር ማረፊያው የመጀመሪያው ሲጠናቀቅ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የሚያስተናግድ ሲሆን፤ በሙሉ አቅም ወደ ስራ ሲገባ ደግሞ ቁጥሩ ውደ 110 ሚሊዮን ከፍ ይላል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
26👎8😁1
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከኖርዌው የማዕድን ኩባንያ የ3 ሚ. ዶላር ድርሻ ገዛ!

የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ በአኮቦ የማዕድን ድርጅት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ፈፀመ፡፡የፈንዱ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ በኢትዮጵያ የወርቅ ማውጣት ሥራ ላይ ከተሠማራው የኖርዌው አኮቦ የማዕድን ኩባንያ ሦስት ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 7.4 በመቶ ድርሻ መግዛቱን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ታዬ፤ “በአኮቦ ማዕድን የምናደርገው ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መስፋፋት ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ እመርታ ነው” ብለዋል፡፡

ውሳኔው ኢትዮጵያ ከክፍለ ዘመን በኋላ ወደ ዓለም አቀፍ የአክስዮን ገበያ እንድትመለስ ያደረገና ለቀጣይ የድንበር ተሻጋሪ ኢንቨስትመንቶች በር የከፈተ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ እንደዘገበው፤ ኢንቨስትመንቱ አኮቦ አዲስ ማዕድን ማውጫ ለመገንባት የሚያስፈልገውን ወጪ የሚደግፍ ሲሆን፤ ይህም የድርጅቱን ወርሃዊ የወርቅ ምርት ከ5-10 ኪሎ ግራም ወደ 50-80 ኪሎ ግራም ከፍ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
15
ስምና ሎጎዬን በመጠቀም አሳሳች መረጃች እየተሰራጨ ነው ሲል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ!

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዪ ግለሰቦች የማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመክፈት እና በገፃቸው የሚኒስትሩን ሎጉ በመጠቀም አሳሳች መረጃዎችን እያሰራጩ ይገኛል ሲል አስታውቋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተለይም ካናዳን ጨምሮ ህጋዊ የሥራ ስምሪት የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተገባባቸው የተለያዩ ሀገራት ለሥራ እንልካለን የሚሉ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች በሚያሰሩ ህገወጦች ሎጎውን እንደሚጠቀሙ አስታውቋል።

በዚህም ሎጎውን በማየት ከተቋሙ ፍቃድ የተሰጠቸው እየመሰላቸው በርካቶች እየተጭበረበሩ መሆናቸውን ያስታወቀው ሲሆን ህብረተሰቡ ከህገወጦች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ህጋዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለመዘርጋት ሁለትዮሽ ስምምነት በተፈራረመባቸው ሀገራት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ላይ እንዲሰሩ ፈቃድ ያላቸው የሥራና ሠራተኛ አገናኝ የሆኑ ከ1200 በላይ ኤጀንሲዎች ዝርዝርም ይፍ አድርጓል።

@YeneTube @FikerAssefa
7
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ከግዢ ዋጋ በላይ የሚሸጡባቸው ሀገራት ኢትዮጵያ እና ስሪላንካ ብቻ መሆናቸው ተገለጸ!

የተሽከርካሪዎች ዋጋ በዓለም ዙሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሲሄድ፣ በኢትዮጵያ እና ስሪላንካ ግን በተቃራኒው ያገለገሉ መኪናዎች ከገዙበት ዋጋ በላይ ይሸጣሉ።እንደ መረጃዎች ከሆነ ሁለቱ ሀገራት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ለዓመታት ከተጠቀሙባቸው በኋላም እንኳ ከገዙበት ዋጋ በላይ የሚሸጡባቸው ብቸኛ ሀገራት ናቸው።

የግሎባል ፌዴሬሽን ኦፍ ስሪላንካ ቢዝነስ ካውንስልስ ዋና ጸሐፊ ሳጂቭ ክሻትሪያ ራጃፑትራ እንደተናገሩት ፣ ይህ ሁኔታ ሰዎች በመጨረሻ ጥቅም ላይ የማይውሉ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ብዙ ገንዘብ እንዲያወጡ እንደሚያደርግ እና በመጨረሻም ብረት ክምር ብቻ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ይህን ችግር ለመፍታት ስሪላንካ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ውጭ በመላክ፣ ከሽያጩ የሚያገኘውን ትርፍ ደግሞ የአዲስ ተሽከርካሪዎችን የማስመጣት ግብር ለመቀነስ ልትጠቀምበት እንደምትችል ጠቁመዋል።

በአሁኑ ጊዜ ስሪላንካ ተሽከርካሪዎች ላይ እስከ 300 በመቶ ግብር ትጥላለች፣ በአገር ውስጥ ደግሞ ያገለገሉ መኪናዎች ዋጋ ከመጀመሪያው የግዢ ዋጋ እስከ ሦስት እጥፍ ከፍ ሊል እንደሚችል ተጠቁሟል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
35😁25
ናቲ  ስፒች ላንጉጅ ቴራፒ ኪሊኒክ
Nati Speech language therapy clinic

ከእርስዎ ወይም ከቤተሰብዎ ከንግግር ጋር በተያያዘ ችግር ያለበት ሰው ያውቃሉ?

እንግዲያውስ ናቲ የንግግር የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ለእርስዎ የሚሆን መፍትሔ ይዞልዎት መጥቷል ከንግግር ከቋንቋ እንዲሁም ከተግባቦት ጋር በተያያዘ ህክምና ወይም ስልጠና ከፈለጉ ወደ ናቲ የንግግርና የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ይምጡ ወይንም ይደውሉ እፎይ የሚሉበትን ምላሽ ያገኛሉ

“አለመናገር ጨዋነት አይደለም እክል እንጂ”

👉አድራሻ፡ መገናኛ ሾላ አባይ ባንክ የካ ሚካኤል ቅርንጫፍ ያለበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205
ከመምጣትዎ በፊት ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ

☎️ስልክ፡- 09- 08- 78- 26 -52  


  👉በተጨማሪም በነዚህ አማራጮች ያገኙናል
👉የቴሌግራም ገጽ ፡- https://tttttt.me/Nslt19

 👉የቲክቶክ ገጽ፡-https://vm.tiktok.com/ZM69FtgrR/
👉  የፌስቡክ ገጽ፡-https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
👉በ YouTube ገፅ:-https://youtube.com/@natigetnet1989?si=_81wKG_5Ev45AZvY

👂👂በነፃ

የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህክምና  በየትኛውም ክልል ለሚኖሩ በነፃ
11
MacBook Air 2020 (M1)
8x256GB
Cycle Count: 22
Size: 13.3"

DM: @adagioandante
2
YeneTube
Photo
ሶማሊያ ከአልሸባብ ጋር ሠርተዋል ያለቻቸውን ሁለት ወታደሮች በሞት ቀጣች!

የሶማሊያ የመከላከያ ሠራዊት ፍርድ ቤት ለሁለት አስርት ዓመታት የቀጠናው የደኅንነት ስጋት ሆኖ ከቆየው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ሁለት የሀገሪቱ ብሄራዊ ጦር ሠራዊት አባላት ላይ የሞት ቅጣት ውሳኔን አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ "የጦር ሠራዊት አባላቱ ለአንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን መግደል፤ ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር በቅርበት ሰርተዋል" ሲል ነው በትናንትናው ዕለት ውሳኔውን ያስተላለፈው።

የሞት ፍርድ ውሳኔው ግድያው በተፈፀመበት ቦታ ላይ የተላለፈም ሲሆን፤ ይህም ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር ለሚሰሩ መሰል ወታደሮች ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት የተደረገ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

'የኦክቶበር 14ኛ ሻለቃ ጦር' አባላት የሆኑት ሞሃመድ ሁሴን ቡሌ እና አዳን ኢሳቅ ያሮው የተባሉት ተከሳሾች፤ ከታጣቂ ቡድኑ ጋር በጋራ በመስራት የ83ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ የሆኑት ሴይዲ መሀመድ አሊ ለተገደሉበት ጥቃት ተጠያቂ ተደርገዋል።

ጦር አዛዡ በሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ውስጥ ከፍተኛ መኮንን የነበሩ ሲሆን፤ የተገደሉት በአልጋቸው ሥር በተጠመደ ፈንጂ መሆኑን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

የወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ከአልሸባብ ጋር ሲሰሩ መገኘታቸውን የገለጸ ሲሆን፤ ስለ ኦክቶበር 14 ብርጌድ ጠቃሚ መረጃ ለአልሸባብ በመስጠት ጦሩን አደጋ ውስጥ መክተታቸውንም ገልጿል፡፡

"ይህ ከወታደራዊ ፕሮቶኮሎች ጋር የሚጋጭ ነው" ሲል ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ያስታወቀ ሲሆን፤ በሶማሊያ ወታደራዊ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሰረት በወታደሮቹ ላይ የሞት ቅጣቱ እንዲፈጸም ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተዳከመበት ተነቃቅቶ በሶማሊያ ከባባድ ጥቃቶችን በመፈጸም ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ተነጥቆ የነበረባቸውን ቦታዎችም መልሶ በመቆጣጠር ለሀገሪቱ እና ለቀጣናው እንደ አዲስ ስጋት እየሆነ መምጣቱ እየተገለጸ ይገኛል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
19👍1
YeneTube
Photo
ኢትዮጵያና አሜሪካ ሕገ ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ለመቆጣጠር መምከራቸው ተገለጸ!

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ህገወጥ ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ማስተላለፊያ ግብይቶችን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም በገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ላይ በሚደረገው ቁጥጥር ያላቸውን ትብብር ለማጠናከርና የገንዘብ ዝውውሩ በመደበኛ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ መከናወኑን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል ተብሏል።በተጨማሪም በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ባንኩ አስታውቋል፡፡

ውይይቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም አራት ተቀማጭነታቸውን በአሜሪካ ያደረጉ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሚሰበስቡት ገንዘብ አማካኝነት በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ የማስመሰል እና ሕገወጥ ተግባራትን በገንዘብ በመርዳት ወንጀል ላይ ተሳትፈዋል ሲል በይፋ ከከሰሰ በኋላ ነው።

እነዚህ ኩባንያዎች ሸገይ ገንዘብ አስተላላፊ፣ አዱሊስ ገንዘብ አስተላላፊ፣ ራማዳ ፔይ እና ታጅ ገንዘብ አስተላላፊ ሲሆኑ የሚገኙትም በቨርጂኒያ እና ሚኒሶታ ግዛቶች ነው። ከእነዚህ ኩባንያዎች መካከል ታጅ ገንዘብ አስተላላፊ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 የ'ዩ.ኤስ. ባንክ ሴክሬሲ አክት' ን በመጣስ ጥፋተኛ እንደሆነ ማመኑን በዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ ካሊፎርኒያ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት መግለጫ ያመላክታል።

ይሄን ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ኢ-መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን የሚጠቀሙ የንግዱ ማህበረሰብ ገንዘባቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ መግለፃቸው ይታወሳል።

አቶ ማሞ ብሔራዊ ባንክ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸው “የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ታማኝነትን ሆነ ብሎ ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋን ለማዛባት በማለም መቀመጫቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ህገ ወጥ የገንዝብ ዝውውር አስተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚቀጥል” ገልጸዋል።

በዚህም የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት "ሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓትን ወደ ጎን በመተው በሕገ ወጥ እና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች" የባንክ ሒሳብ ማገዱን ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
19😁13👎4👍1🔥1