በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ ከ5,000 በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ 2,400 ሄክታር ሰብል ወደመ!
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ እና ሰበታ ሃዋስ ወረዳዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ አዋሽ ወንዝ በመሙላቱ ከ5,000 በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ2,400 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
የኢሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ተስፋዬ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ባሳለፈነው ቅዳሜ ምሽት አዋሽ ወንዝ በአራት አቅጣጫዎች ሞልቶ በመፍሰሱ ወሬርሶ ቀሊና እና ሙሉ ሳተዩ በተባሉ ሁለት ቀበሌዎች ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ አስገድዷል።ከፍተኛ መጠን ያለው ሰብል እና እንደ ዶሮ፣ ፍየል እና በግ ያሉ እንስሳት በጎርፉ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የጠፉት አጠቃላይ የእንስሳት ብዛት አሁንም በመጣራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የሰበታ ሀዋስ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አሸናፊ ንጉሴ በበኩላቸው የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ወደ አዋሽ ባሎ ቀበሌ በመግባቱ 240 አባወራዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውንና በሰብል እንዲሁም በእንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል። አያይዘውም የአከባቢው ነዋሪዎች ጎርፉን ይባባሳል በሚል በስጋት ላይ መውደቃቸውን ጠቁመዋል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa

❤16😭3👍1
ከናይሮቢ አዲስ አበባ በአውቶብስ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ!
ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን 'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ።ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት እሁድ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን 'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' ዳይሬክተር ሚካኤል ጄምስ ማቺዮ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በአንድ ጉዞ 7 ሺህ 500 የኬንያ ሽልንግ እንደሚያስከፍል የተናገሩት ዳይሬክተሩ ለደርሶ መልስ ጉዞ ዋጋ 15 ሺህ የኬንያ ሽልንግ (16 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ገደማ) መሆኑን ገልጸዋል።እንደ አቶ ሚካኤል ገለጻ አቢሲኒያ ሌግዠሪ በየቀኑ ወደ በናይሮቢ እና በአዲስ አበባ መካከል የሕዝብ ማመላለስ ሥራዎችን ይሠራል።
ባለፈው ዕሁድ ሥራውን በይፋ ሲጀምር ሰባት ተሳፋሪዎች ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ትኬት ቆርጠው ነበር።
"እሁድ የሙከራ ጉዞ ነበር፤ነገር ግን በደንብ ማስታወቂያ ስላልተሠራ ቀጥታ የሚጓዙ ተሳፋሪዎች አልተገኙም" የሚሉት አቶ ሚካኤል "ባሱ 46 ሰዎች የመያዝ አቅም ቢኖረውም ቀጥታ አዲስ አበባ የሚሄዱት ሰባት ሰዎች ብቻ ነበሩ" ብለዋል።
'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል አውቶብሶቹ አስተናጋጆች፣ ራሳቸውን የቻሉ የሴቶችን እና የወንዶች መጸዳጃ፣ በውስጣቸው የኢንተርኔት እና 'ስክሪንን' ጨምሮ የመዝናኛ አግልግሎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
Via BBC

❤60👍8🔥2😁2
Forwarded from ALX Ethiopia
🚀 Want to become a Virtual Assistant? Join our live Telegram session to learn about the programme, how to apply, and get your questions answered!
Don’t miss it - happening this Saturday, 3 ነሐሴ 2017 (August 9, 2025) starting at 11፡00 (5:00 PM) in our Telegram group
👉🏾 t.me/virtualassistantapplicationguide
#ALXEthiopia #ALXAfrica #ALXTribe #AIwithALX #VirtualAssistant

❤8👍1
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል በፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሁለት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች በፈፀሙት ስልጣንን ያለ አግባብ መገልገል ወንጀል ጥፋተኛ ሆነዉ በመገኘታቸዉ በጽኑ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላለፈ።
አንደኛ ተከሳሽ የሆኑት በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የምዝገባና ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታምሩ ግንበቶ እና 2ኛ ተከሳሽ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የውጪ ዜጎች ቁጥጥርና ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጅላሉ በድሩ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 9(1) (ሀ) መተላለፋቸው ተመላክቷል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሙስና ጉዳዮች ችሎትም ተከሳሾቹ ጥፋተኝነታቸዉ በሰዉ እና በሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ 1ኛ ተከሳሽ ታምሩ ግንበቶ በ8 አመት ፅኑ እስራት እና 1 ሺህ ብር፤ 2ኛ ተከሳሽ ጅላሉ በድሩ ደግሞ በ4 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።
ተጨማሪ ያንብቡ
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8754

Addis standard
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል በፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30/ 2017 ዓ/ም፦ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሁለት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች በፈፀሙት ስልጣንን ያለ አግባብ መገልገል ወንጀል ጥፋተኛ ሆነዉ በመገኘታቸዉ በጽኑ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላለፈ። አንደኛ ተከሳሽ የሆኑት በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የምዝገባና ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር…
❤18😁2
በአዲስ አበባ ስድስት ወራት ውስጥ ቡና በኪሎ በአማካኝ 900 ብር ጨምሯል ተባለ
ከስድስት ወራት በፊት በከተማዋ በብዙ ካፌ እና ሬስቶራንቶች ፣የጀበና ቡና መሸጫ ቦታዎች አንድ ኪሎ ቡና 400 ብር እንደሚገዙ ለፊደል ፖስት የተገነዘበ ሲሆን አሁን ላይ አንድ ኪሎውን ለመግዛት 1,300 ብር ድረስ እያወጡ ይገኛሉ።
Via:- ፊደል ፓስት
@Yenetube @Fikerassefa

❤32👍15🔥3😭3
ከፍተኛ ንፋስና በረዶ በቢሾፍቱ የአበባና ፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ!
በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ በደረሰው ከፍተኛ ንፋስና በረዶ የተቀላቀለበት ከባድ ዝናብ፣ በአካባቢው በሚገኙ የአበባና የፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ። ይህ ያልተጠበቀ የአየር ሁኔታ በተለይ ለዘርፉ አምራቾች ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሏል።
በዚህም ከትናንት በስቲያ (ሰኞ) ሁለት ዋና ዋና እርሻዎች ላይ የሚገኙት ግሪን ሐውሶች ሙሉ በሙሉ መዉደማቸዉን ለካፒታል የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ከእነዚህ ሁለት እርሻዎች በተጨማሪ፣ ሌሎች ስምንት የሚሆኑ እርሻዎችም ከፍተኛ የሚባል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተጠቁሟል ።
በደረሰው አደጋ ምክንያት በአካባቢው የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የእርሻ ስራዎችን ይበልጥ ተፅዕኖ ዉስጥ እንደሚጥለው ተገልጿል ።
በአደጋው የተጎዱት አምራቾች አሁን ባለው ሁኔታ ውስጥ ተጨማሪ ጫናዎች እንዳሉባቸው ገልጸዋል። በተለይም በቀጣይ ወራቶች ዉስጥ ወደ ስራ ካልተመለሱ አሁን በባንክ ላይ ያለባቸው ብድር እና ለመንግስት የሚከፍሉት ግብር ከፍተኛ ጫና እንደሚሆናቸው አስረድተዋል።
ይህን ተከትሎ በፍጥነት ወደ ስራ ካልተመለሱ እነዚህን ግዴታዎች ለመወጣት እንደሚቸገሩ እና ተጨማሪ ኪሳራ እንደሚደርስባቸው ስጋታቸውን ለካፒታል ገልጸዋል። በእርሻ ማሳዎች ላይ አሁን የደረሰው ጉዳት መጠን ለማወቅ ዝርዝር ጉዳዮች እየተጣሩ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል።
Via Capital

❤32😭10
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤2
Forwarded from YeneTube
በ 25% ዲስካውንት ለገበያ አቅርበናል!
📌 ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
✅ መገልገያዎች
👉 ሦስት ሊፍት
👉 ባለ 3 ፎቅ የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
📌 የካሬ አማራጮች
👉ባለ 1መኝታ - 63 ካሬ
👉ባለ 2 መኝታ - 86 እስከ 103 ካሬ
👉ባለ 3 መኝታ - 132 እስከ 146 ካሬ
👉1 መኝታ 63ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2መኝታ 86 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 946,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 9,460,000 ብር
👉3መኝታ 114 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,219,800 ብር
ሙሉ ክፍያ 12,198,000 ብር
ለበለጠ መረጃ
☎️ +251976195835
Telegram username
@Ruthtemersales
What's app
https://wa.me/251976195835
TEMER PROPERTIES
Create | Construct | Deliver
#TemerProperties #Temerrealestate
📌 ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
✅ መገልገያዎች
👉 ሦስት ሊፍት
👉 ባለ 3 ፎቅ የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
📌 የካሬ አማራጮች
👉ባለ 1መኝታ - 63 ካሬ
👉ባለ 2 መኝታ - 86 እስከ 103 ካሬ
👉ባለ 3 መኝታ - 132 እስከ 146 ካሬ
👉1 መኝታ 63ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2መኝታ 86 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 946,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 9,460,000 ብር
👉3መኝታ 114 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,219,800 ብር
ሙሉ ክፍያ 12,198,000 ብር
ለበለጠ መረጃ
☎️ +251976195835
Telegram username
@Ruthtemersales
What's app
https://wa.me/251976195835
TEMER PROPERTIES
Create | Construct | Deliver
#TemerProperties #Temerrealestate
❤2
Forwarded from ALX Ethiopia
🚀 Want to become a Virtual Assistant? Join our live Telegram session to learn about the programme, how to apply, and get your questions answered!
Don’t miss it - happening this Saturday, 3 ነሐሴ 2017 (August 9, 2025) starting at 11፡00 (5:00 PM) in our Telegram group
👉🏾 t.me/virtualassistantapplicationguide
#ALXEthiopia #ALXAfrica #ALXTribe #AIwithALX #VirtualAssistant
Don’t miss it - happening this Saturday, 3 ነሐሴ 2017 (August 9, 2025) starting at 11፡00 (5:00 PM) in our Telegram group
👉🏾 t.me/virtualassistantapplicationguide
#ALXEthiopia #ALXAfrica #ALXTribe #AIwithALX #VirtualAssistant
YeneTube
ከናይሮቢ አዲስ አበባ በአውቶብስ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ! ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን 'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ።ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት እሁድ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን 'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' ዳይሬክተር ሚካኤል ጄምስ ማቺዮ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአንድ ጉዞ 7 ሺህ…
"ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እውቅና ውጪ ነው"
ቢቢሲ አማርኛ፤ "ከናይሮቢ - አዲስ አበባ በአውቶብስ የሕዝብ ትራንስፖርት ተጀመረ" በሚል ያሰራጨው ዘገባ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እውቅና ውጪ ነው።
ቢቢሲ አማርኛ በድረገጹ፣ "አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት፣ ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን አስታወቀ" ሲል ዘግቦ፣ ይህንን መረጃ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህጋዊነቱን ሳያረጋግጡ ሌሎችም ሚዲያዎች አሰራጭተዋል።
ሆኖም ይህንን ጉዳይ በሀገሪቱ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ላይ በአዋጅ ሀላፊነት የተሰጠው ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የማያውቀው መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን ።
እንደ ሀገር በ2018 በጀት አመት በሁለቱ ሀገራት መካከል ትስስር ለመፍጠር፣ ይህንን አገልግሎት ለመጀመር እቅድ የተያዘ ቢሆንም፣ ሂደቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል የትብብር ስምምነት መፈራረም፣ ታሪፍ በጋራ መወሰንና ሌሎች የዲፕሎማሲ ጉዳዮች የሚፈልግ በመሆኑ ከሚመለከተው መንግስታዊ መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር የሚሰራበት መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር!

😁9❤6
ልዩ መረጃ
የሱዳን ጦር በሱዳን ዳርፉር በኒያላ አየር ማረፊያ ሲያርፍ የነበረ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አይሮፕላን ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተሰማ።
የሱዳን ጦር የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አውሮፕላን በዳርፉር ግዛት ስትራቴጅካዊቷ ኒያላ ከተማ ሲያርፍ ኢላማ አድርጓል ሲል የሱዳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።
አውሮፕላኑ የኮሎምቢያ ቅጠረኛ ተዋጊዎችን ይዞ እንደነበር እና ሲያርፍ በትናንትናው ዕለት August 6/2025 በሱዳን ጦር ጥቃት እንደደረሰበት ዘገባው ጠቅሷል። በጥቃቱ ከ40 በላይ የኮሎምቢያ ቅጥረኛ ወታደሮች/Colombian mercenaries/ መሞታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ኒያላ አየር ማረፊያ በጄኔራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ቁጥጥር ስር ይገኛል።
የሱዳን ጦር አረብ ኢምሬትስ ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ድጋፍ ታደርጋለች ብሎ ያምናል።
አዩ ዘሀበሻ

❤23👍7🔥1
የኢትዮጵያ ጦር ለሶማሊያ ወታደሮች ሰጠ የተባለው ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው?
በሶማሊያ ጌዶ ክልል የሚገኘው የኢትዮጵያ ሠራዊት የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ወታደሮች በቅርቡ ከያዙት የድንበር ከተማ፣ በለድ ሀዋ በሦስት ቀን ውስጥ ለቅቀው እንዲወጡ ለአገር ሽማግሌዎች መናገራቸው ተገለፀ።
ከተማዋ በለድ ሀዋ ቁልፍ የሶማሊያ የድንበር ከተማ ስትሆን ኢትዮጵያን እና ኬንያን የምታዋስን እና የኢትዮጵያ ሠራዊት የሚገኝባት ነች።
ባለፉት ሳምንታት የሶማሊያ የከፊል ራስ ገዝ ክልል ጁባላንድ ታጣቂዎች እና የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ወታደሮች በአካባቢው ውጊያ አካሂደው፣ የሶማሊያ መንግሥት ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም. ከተማዋን በቁጥጥሩ ስር አውሏል።
ከፍተኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መኮንኖች ከሶማሊያ የጎሳ መሪዎች ጋር በዶሎ ከተማ መነጋገራቸውን እና የሶማሊያ ፌደራል መንግሥቱ ወታደሮች ከበለድ ሀዋ በሦስት ቀን ውስጥ ለቅቀው እንዲወጡ ማዘዛቸውን የአገር ሽማግሌዎች ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል።
በሶማሊያ የፌደራል መንግሥት የጌዶ አስተዳዳሪ የሆኑት አብዱላሂ አብዲ ጃማ (ሺምቢር) በዶሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሠራዊት በበለድ ሀዋ የሚገኘውን የሶማሊያ መንግሥት ኃይል በሦስት ቀናት ውስጥ ለቅቆ እንዲወጣ በአገር ሽማግሌዎች እንደተነገራቸው ገልፀዋል።
የጌዶ አስተዳዳሪ አብዱላሂ አብዲ ጃማ (ሺምቢር) ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በጥምረት የሚሠራ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ሠራዊት በኩል ተላለፈ በተባለው ትዕዛዝ ምክንያት ከበለድ ሀዋ የሚወጣ የፌደራል ጦር የለም ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
👇👇
https://www.bbc.com/amharic/articles/c5y3edzy2zyo

1❤21😁5👍1
YeneTube
Photo
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ካመነጨሁት ሀይል 33.2 በመቶው የተገኘው ከህዳሴ ግድቡ ነው አለ።
በበጀት ዓመቱ ከተገኘው ሀይል 93 በመቶው ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የተቀረው 7 በመቶ ደግሞ ለውጪ ሀገራት የተሸጠ መሆኑ ተነግሯል።
ተቋሙ ይህንን ያለው የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን እና የ2018 በጀት ዓመት እቅዱን በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው።በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 29,480 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨቱን ተናግሯል።
ይህም ካቀድኩት በላይ ነው ያለው ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 25,423 ጊጋ ዋት ሰዓት የማምረት እቅድ ነው የነበረኝ ብሏል።ከሀይል ሽያጩ 75.4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ ተናግረዋል።
ከመነጨው ሀይልም 33.2 በመቶው የተገኘው ከህዳሴ ግድቡ መሆኑን ያብራሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው ኢንጅነር አሸብር ባልቻ 93 በመቶው የመነጨው ሀይል ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የተቀረው 7 በመቶ ደግሞ ለውጭ ሀገራት የተሸጠ ነው ብለዋል።ለሀገር ውስጥ ከቀረበው 93 በመቶ ሀይል 60 በመቶው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሸጠ፣ 27 በመቶው ለዳታ ማይኒንግ እና 6 በመቶው ደግሞ ለኢንዱስትሪዎች የተሸጠ መሆኑን ከተቋሙ ሰምተናል።
ከአጠቃላይ የመነጨ ሀይል 7 በመቶው ለውጭ ሽያጭ መቅረቡን ያስረዱት ሀላፊው ለውጭ ሀገራት በሽያጭ ከቀረበው 5 በመቶው ለኬኒያ እና 2 በመቶው ለጅቡቲ እንደተሸጠ ተናግረዋል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በተጠናቀቀው በጀት አመት ችግር ሆነውብኛል ስላላቸው ጉዳዮችም አንስቷል።
የመሰረተ ልማት ስርቆት ሲፈትነኝ ቆይቷል ያለው ተቋሙ፤በ43 የሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በተፈፀመ ስርቆት ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶብኛል ብሏል።በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የሰላም እጦት እንደልብ ስራዎችን ተዘዋውሬ መስራት እንዳልችል ያደረገኝ ሌላኛው ችግር ነው ሲል ተናግሯል።
Via Sheger

😁24❤20👍2