YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቻይና ያጋጠመው የሙቀት መጨመር የአየር ማቀዝቀዣዎች ሽያጭ እንዲጨምር ማድረጉ ተሰማ

አንድ አንድ ቻይናውያን ከፍተኛ ሙቀቱን ለመቋቋም አነስተኛ የአየር ማቀዝቀዣዎችን ይዘው በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ ተስተውለዋል።

ቻይና ከመጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮ ያሳለፈቻቸው ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበባቸው ቀናት ብዛት በጣም በርካታ መሆናቸውን የቻይና ሚቲዎሮሎጂ አስተዳደር ባለስልጣን ገልፆል። አስተዳደሩ ረቡዕ ዕለት እንደገለፀው ከሆነ በቻይና ውስጥ ያሉ 152 ብሄራዊ የአየር ሁኔታ ታዛቢዎች ከሀምሌ ወር አጋማሽ ጀምሮ ከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ የሙቀት መጠን መዝግበዋል።

እንዲሁም ሰዎች ወደ አየር ማቀዝቀዣ እና የአየር ሙቀት መጨመርን ለመቋቋም የሚያስችሉ መሳሪያዎች ግዢ ፊታቻን ያዞሩ ሲሆን በዚህም የኃይል ፍጆታን ለመቆጣጠር ወቅታዊ እርምጃዎችን እንዲወስድ ለሀገሪቱ የኃይል ኢንዱስትሪ ማስጠንቀቂያ ልኳል። ባለፈው ሳምንት ከ200 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባትን አካባቢ ሸፍኖ፣ በደቡብ ምዕራብ ከምትገኘው ቾንግቺንግ ከተማ አንስቶ እስከ ጓንግዙ የባህር ዳርቻ ድረስ ከፍተኛ ሙቀት ተመዝግቧል።

በሃቤይ እና ሁናን ማእከላዊ አውራጃዎችም የሙቀት መጠኑ እስከ 50 ዲግሪ ሴንትግራድ እንደሚደርስ ተንብዮ ነበር። በደቡባዊ ጂያንግዚ እና ጓንግዶንግ ግዛቶችም ተመሳሳይ የሙቀት መጠን ይጠበቃል።በቻይና ውስጥ የተከተሰተው ከፍተኛ መቀት የህይወትን ምቾት ከማሳጣት፣ የእርሻ መሬቶችን ከማቃጠል እና የእርሻ ገቢን ከመሸርሸር በተጨማሪ ከፍተኛ የአየር ሙቀት መጨመሩ የማምረቻ ማዕከላትን ሊጎዳ እና በቁልፍ ወደቦች ላይ ስራዎችን ሊያስተጓጉል ይችላል ተብሎ የተሰጋ ሲሆን የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችንም ሊጎዳ ይችላል ተብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
23👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
49 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ የሩሲያ አዉሮፕላን ተከሰከሰ!

43 መንገደኞችንና 6 ሠራተኞችን አሳፍሮ ይበር የነበረ አንድ የሩሲያ የመንገደኞች አዉሮፕላን ሩሲያን ከቻይና ጋር በሚያውስነዉ ድንበር አካባቢ ተከሰከሰ።አንቶኖቭ 24 (A-24) የተባለዉ አዉሮፕላን ዛሬ ጧት ሩሲያን ከቻይና ጋር ከሚያዋስነዉ ድንበር ላይ ከምትገኘዉ ብላጎቬሽሼንስክ ከተባለችዉ ከተማ ትይንዳ ወደተባለች ሌላ ከተማ መብረር ላይ ነበር።

አዉሮፕላኑ አሳፍሯቸዉ ከነበሩት ሰዎች በሕይወት የተረፈ መኖሩ ብዙ አጠራጥሯል።አዉሮፕላኑ በወደቀበት አካባቢ ቀድመዉ የደረሱ የአደጋ ሠራተኞች በእሳት የተቃጠለ የአዉሮፕላኑን ሥብርባሪ ማግኘታቸዉን አስታዉቀዋል።አዉሮፕላኑ ይበር በነበረበት አካባቢ «አስቸጋሪ» የዓየር ሁኔታ ነበር ከመባሉ በስተቀር የአደጋዉ ትክክለኛ መንስኤ አልታወቀም።

@YeneTube @FikerAssefa
😭1716
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፈው የበጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገቡን አሰታወቀ!

ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ ባጠናቀቀው የበጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማስመዝገብ የእቅዱን 99% ማሳካቱን አስታወቀ። ይህ ካለፈው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ72.9% ዕድገትን ያሳያል።

ኩባንያው ይህንን ያስመዘገበው የተለያዩ የንግድ አማራጮችን በመተግበር፣ የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና በማቆየት እንዲሁም ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰባቸውን የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች በማስፋፋትና በማጠናከር መሆኑን ጠቁሟል።

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 213.6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘቱን አስታውቋል፤ ይህም የእቅዱን 84.3% ያሳካ ነው። ይህ አፈፃፀም ካለፈው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ15.44 ሚሊዮን ዶላር (7.8%) ጭማሪ አሳይቷል።

ከተገኘው የውጭ ምንዛሪ ውስጥ 193.11 ሚሊዮን ዶላር ከአለም አቀፍ አገልግሎት የተገኘ ሲሆን፣ 66.6 ሚሊዮን ዶላር ከአለም አቀፍ የትራንዚት ትራፊክ፣ 5.62 ሚሊዮን ዶላር ከመሠረተ ልማት ማጋራት ኪራይ (Infrastructure sharing) የተገኘ ሲሆን፣ ከ14.42 ሚሊዮን ዶላር በላይ ደግሞ በቴሌብር ዓለም አቀፍ የሐዋላ አገልግሎት አማካኝነት ወደ ሀገር ውስጥ የገባ የውጭ ምንዛሪ መሆኑ ተገልጿል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
17👎10
🎁ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ
የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት

💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,000 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🛍️🛒ሱቆች ከ 70 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ

- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው

-እንዲሁም በ ግሩፕ ሆነው ለሚመጡ ደንበኞች ዳጎስ ያለ ቅናሽ አዘጋጅተን እየጠበቅኖት ነው

ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!

☎️0900025097

#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#WhatsApp
10
🇪🇹 ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 32 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ የውጭ የምንዛሪ ገቢ በመሰብሰብ ክብረ ወሰን ሰበረች

ይህ ገቢ የተገኘው መንግሥት በወሰዳቸው አዎንታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም ላይ ተናግረዋል።

በ2016 ዓ.ም ከተመዘገበው 24. 7 ቢሊየን ዶላር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ የታየበት ሆኗል።

@Yenetube @Fikerassefa
👎2612😁9🔥1
እነ ቀሲስ በላይ በሙስና ወንጀል "ሊፈረድብን አይገባም" በማለት ባቀረቡት ይግባኝ ላይ ውሳኔ ተሰጠ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙስና ወንጀል "ሊፈረድብን አይገባም" በማለት ባቀረቡት ይግባኝ ጥያቄ እና የዐቃቤ ሕግ የመልስ መልስ ላይ ውሳኔ ሰጠ።

ከአንድ ዓመት በፊት የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ፣ በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ እና አለምገና ሳሙኤል እንዲሁም የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ በተባሉ ተከሳሾች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦ ነበር።

በዚህም እነ ቀሲስ በላይ መኮንን ከአፍሪካ ህብረት ምንም አይነት የክፍያ ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ላይ ተከሳሾች በተለያየ መጠን ክፍያ እንዲፈጸምላቸው የሚል የ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት ለባንኩ መቅረቡ ተጠቅሶ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል።

በዚህ መልኩ የቀረበውን ዝርዝር ክስ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች ብቻ ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ከዚህም በኋላ በነበሩ የተለያዩ የችሎት ቀጠሮዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ላይ በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች እንዲሁም የተከሳሾቹን መከላከያ ማስረጃ ፍርድ ቤቱ መርምሮና አመዛዝኖ 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙሉ ድምጽ፤ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት በአብላጫ ድምጽ የጥፋተኛ ፍርድ ተሰጥቶ ነበር።

ከዚህም በኋላ የስር ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ ወንጀሉ የተፈጸመው በትብብር መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ እንዲሁም ተከሳሾች ያቀረቡትን የተለያዩ ቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን በመየያዝ በጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም በነበረ ቀጠሮ 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በዕርከን 21 መሰረት በ5 ዓመት ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ፤ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችን ደግሞ በዕርከን 17 መሰረት እያንዳንዳቸውን በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑ ይታወቃል።

ተከሳሾቹ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግባኝ ወንጀል ችሎት “በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ልንባል አይገባም” እንዲሁም “የስር ፍርድ ቤት የሰጠው የቅጣት መጠን ተገቢ አደለም" የሚል ይዘት ያለው አቤቱታ አቅርበዋል።

ችሎቱ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የይግባኝ አቤቱታ እና የዐቃቤ ሕግን የመልስ መልስ መርምሮ እነ ቀሲስ በላይ የሙስና አዋጅ 881/2007 አንቀጽ 32 (2) (3) መሠረት በከባድ ማታለል የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ልንባል አይገባም የሚለው አቤቱታቸው ውድቅ ተደርጎ የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠው የጥፋተኝነት ፍርድ ሥነሥርዓታዊ መሆኑን ጠቅሶ ፍርዱን አፅንቶታል።

በሌላ በኩል ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ በተከሳሾቹ ላይ ላይ በስር ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረው ቅጣት መጠንን በማማሻል ቀሲስ በላይ ከ5 ዓመት ወደ 3 ዓመት ከ7 ወር አስራት ተቀይሮላቸዋል።

ኢያሱ እንዳለ እና በረከት ሙላት የተባሉ ተከሳሾች ደግሞ በስር ፍ/ቤት የተወሰነባቸው 3 ዓመት ከ3 ወር የነበረው ቅጣት 3 ወር ብቻ ተቀንሶ 3 ዓመት ብቻ እንዲሆን ውሳኔ ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ ተከሳሾቹ አቅርበውት የነበረውን የቅጣት ገደብ ጥያቄ አልተቀበለውም።

FBC
@Yenetube @Fikerassefa
53👎5😁2👍1
4😁1
YeneTube
Photo
ከዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ማዕረግ የሚመረቁ ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመስተማር ከፈቀዱ ስልጠና ወስደው መምህር እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ከ2018 ጀምሮ ወደ ስራ ሊያስገባ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም በሚል ወደ ስራ ይገባል የተባለው አሰራር የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚታየውን የመምህራን እጥረት ለመቅረፍ ይረዳል ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር፡፡ይህ የተባለው የክረምት ልዩ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማሻሻያ ስልጠና ለማስጀመር በማሰብ ከ30 ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ አሰልጣኝ መምህራን እየተሰጠ ያለው ስልጠና በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ድኤታ አየለች እሸቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተፈጥሮ ሳይንስ መምህራን ስልጠና ያልተካፈሉ መምህራን፣ የማህበራዊ ሳይንስ መምህራን፣ የስራና ተግባር ትምህርት መምህራን በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ ብለዋል፡፡ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው ስልጠና ልምድ አግኝተናል ያሉት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ለ2ኛ ጊዜ የሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ስልጠና መምህራኑ በሚያስተምሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ተዘጋጅተናል ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2018 ጀምሮ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚታየው የመምህራን እጥረት ለመቅረፍና ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ በማሰብ አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም አዘጋጅቷል ያሉት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር ‎የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ(ዶ/ር) ናቸው፡፡

በከፍተኛ ነጥብ ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች መምህር የመሆን ፍላጎች ካላቸው ትምህርት ሚኒስቴር የሚያዘጋጀውን ፈተና ካለፉ የሚፈለገው ስልጠና ተሰጥቷቸው በመምህርነት እንዲሰማሩ ይደረጋል ብለዋል፡፡ለዚህ ፕሮግራም ጅማሮ አሁን ላይ 6 ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ሰምተናል፡፡

በዘንድሮው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማሻሻያ ስልጠና 84,000 ሰልጣኞች ይካፈላሉ፡፡ከ30 ዩኒቨርሲቲዎች 630 የሚሆኑ መምህራን ስልጠናውን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡ስልጠናው ሀምሌ 28 ይጀመራል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
😁7132👍8😭3🔥2👀1
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊደረግ የነበረው የምስክር አሰማም ሂደት እንዲታገድ ትዕዛዝ አስተላለፈ!

ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊደረግ የነበረው የምስክር አሰማም ሂደት እንዲታገድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የተከሳሾች ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ጠበቆች ከመጋረጃ ጀርባ ምስክር እንዳይሰማ የይግባኝ አቤቱታውን ያቀረቡት ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን ጠበቃው ተናግረዋል።

በወቅቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ያስታወሱት ጠበቃው፤ ይሁን እንጂ እስከ ሐምሌ 29 የሚቆይ ከሆነ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከመጋረጃ በስተጀርባ ያለውን ምስክር ለመስማት ለትናንት ሐምሌ 16 ቀጠሮ በመያዙ በተከሳሽ ላይ "የማይተካ ጉዳት ያደርሳል" በሚል ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በድጋሚ ደብዳቤ አቤቱታ ማቅረባቸውን አመልክተዋል።

በዚህም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊደረግ የነበረው የምስክር አሰማም ሂደት እንዲታገድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አስታውሰው ይህንኑ የእግድ ትዕዛዝ ይዘን ትናንት ሐምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ችሎት ላይ ምስክር ከመሰማቱ አስቀድሞ አቀረብን ብለዋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
42😁2
👀👀👀👀👀👀👀👀👀👀
"አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ"
      ቀን 18/11/17 የወጣ
0997473781/ 0997470384

የስራ መደብ:ነርስ ጂፒ ዶክተር ነርስ,ላብራቶሪ ቴክኒሻን
♦️ት/ት ደረጃ:diploma/degree
♦️ልምድ:0-5
♦️ደሞዝ:በድርጅቱ እስኬል

የስራ መደብ #አካዉንታንት ለ ድርጅቶች እና ሆቴሎች ላይ /ለአስመጭ/ለፍብሪካ
♦️የት/ደረጃ' ዲግሪ/ዲፕሎማ
♦️የስራ ልምድ'0-6ዓመት
♦️ደሞዝ' 6000-15000

NGO
♦️የት/ት ደረጃ ኤኒ ዲግሪ /ዲፕሎማ
♦️የስራ ልምድ  0አመት
♦️ደሞወዝ  25000 30000+

የስራመደብ: ስልክ ኦፕሬተር  በፈረቃ
♦️ት/ት ደረጃ:10/12/ዲፕሎማ
♦️ልምድ: 0አመት
♦️ደሞዝ: 9800 +

የስራ መደብ: የሽልማት አስተባባር
♦️የት/ደረጃ' ዲግሪ/ዲፕሎ
♦️የስራ ልምድ '0አመት
♦️ደሞወዝ  13500

የስራ መደብ:#  ጥፍር እና አይላሽ
♦️ት/ት ደረጃ:  10
♦️ልምድ: 0አመት
♦️ደሞወዝ  12000 +

የስራ መደብ #አየር መንገድ ውስጥ ሽያጭ
♦️የት/ደረጃ' 10/ ዲፕሎማ/ዲግሪ
♦️የስራ ልምድ' 0 ዓመት
♦️ደሞዝ' 10,000 +

የስራ መደብ #Reception ለሆቴል ,ድርጅቶች እና ለ ገስት ሀውስ/ለክሊኒክ/ሆስፒታል/ለድርጅት
♦️የት/ደረጃ 10/ degree/dip
♦️ፃታ' /ሴ
♦️የስራ ልምድ'0~1 ዓመት
♦️ደሞዝ' 7000+

የስራ መደብ  ሆስተስ
♦️የት/ደረጃ' 10+
♦️ፆታ' /ሴ
♦️ደሞዝ' 15000/ 20000

የስራ መደብ:# ሹፌር ህ1/ደረቅ1
♦️ት/ት ደረጃ 8/10
♦️ልምድ:የሰራ
♦️ደሞዝ:11.000
♦️ፆታ:ሴት

የስራ መደብ:#ካሸር ለድርጅት እና ለትለያዩ ተቁአማት##ለሆቴል#ለሱፕርማርኬት
♦️የት/ደረጃ' 10-ዲግሪ
♦️ልምድ:0-1
♦️ፆታ' ሴ
♦️ደሞዝ' 5500-10000+

የስራ መደብ #በያጅ GMF
♦️የት/ደረጃ'/10/ሰርተፉኬት
♦️ልምድ: የሰራ
♦️ደሞዝ' ማራኪ

የስራ መደብ: ጉዳይ አስፈፃሚ
♦️የት/ደረጃ' 10+
♦️የስራ ልምድ '0አመት
♦️ፆታ' ወ/ሴት
♦️ደሞዝ: 10500

⭐️የስራ መደብ:#የእሸጋ ሰራተኛ
የት/ት ደረጃ:10/ሰርተፍኬት
ልምድ:0አመት
ደሞዝ:በስምምነት

☎️  አድራሻ መገናኛ መተባበር
      ህንጻ 4 ፎቅ ቢሮ ቁ B421

📞 0997470384
📞 0997473781
15🔥1
🎁ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ  ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከባለ አንድ  እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ
የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት

    💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,000 ብር
    💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር  ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🛍️🛒ሱቆች ከ 70 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ

- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር  የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው

-እንዲሁም በ ግሩፕ ሆነው ለሚመጡ ደንበኞች ዳጎስ ያለ ቅናሽ አዘጋጅተን እየጠበቅኖት ነው

ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!

☎️0900025097

#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#WhatsApp
4
Forwarded from YeneTube
የ5 ሚሊየን ቅናሽ ተደረገ 😳😳
📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር

👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ

☎️09-89-26-43-80

           🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር

        📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
      ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር

         📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ

👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
      ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር

ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉በ6 ወር የምትረከቡት
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 የልጆች መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት

እድሉን ለመጠቀም
☎️09-89-26-43-80

Whatsup: 09-89-26-43-80
Telegram: @fiyami11
Email:hiwottadi22@icloud.com



 
12😭1
🚨 የማክሮን ውሳኔ፦ ፈረንሳይ ለፍልስጤም ሀገርነት በመስከረም ወር እውቅና እንደምትሰጥ አስታወቀች

"አሁን ላይ አፋጣኝ የሆነው ነገር በጋዛ ያለውን ጦርነት ማቆም እና ለሲቪል ሕዝብ እርዳታ መስጠት ነው" ሲሉ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት በኤክስ ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።

ውሳኔው ከተለያዩ ሀገራት ፈጣን ምላሽ አስተናግዷል፡-

🇮🇱 ኔታንያሁ፡ "እንዲህ ያለ እርምጃ ሽብርተኝነትን የሚያበረታታ እና ሌላ የኢራን ወኪል የመፍጠር አደጋ አለው"


🇺🇸 ሩቢዮ፡ "ይህ ግድ የለሽ ውሳኔ የሃማስን ፕሮፓጋንዳ ብቻ የሚያገለግል እና ሰላምን የሚያደናቅፍ ነው"


ፈረንሳይ ለፍልስጤም የመንግሥት እውቅና የምትሰጥ የመጀመሪያዋ የቡድን ሰባት ሀገር ትሆናለች።
69👍18👎9🔥2
“በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ በሚዲያ ዘመቻ በሚያካሄዱ ሰዎች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል” -ፌደራል ፖሊስ

የፌደራል ፖሊስ በውጭና በሀገር ውስጥ ሆነው በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ የሚዲያ ዘመቻ በሚያካሄዱት ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል ሲል አስታወቀ።ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር ሙከራ የሚያደርጉ ግለሰቦች እና ቡድኖችን ለሕግ የማቅረብ ሥራን አጠናክሬ እቀጥላለሁም ብሏል።

“በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያ እንዲሁም በሁሉም መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ አሰሳና ፍተሻ እንደሚካሄድ ገልጿል፤ ዋነኛ ትኩረቴ “በፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ” ነው ሲል አስታውቋል።ፌደራል ፖሊስ ይህንን ያስታወቀው በቀጣይ ሦስት ወራት (ከሐምሌ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶች ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በተዘጋጀ የፀጥታ ዕቅድ ላይ በተደረገ ውይይት መሆኑን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከሪፐብሊካን ጋርድ፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተውጣጡ ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ውይይቱን በመሩበት ወቅት በቀጣይ ሀገራችን ከሐምሌ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም የምታስተናግዳቸውን ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶች በሰላም እንዲከናወኑ ከእንግዳ አቀባበል ጀምሮ ስምሪቱን በተደራጀ መልኩ መምራትና ማስተባበር እንደሚያስፈልግ መናገራቸውንም መረጃው አካቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
32😁11👍5👎41🔥1
መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ75 ቀናት ኋላ ማምረት መጀመሩን አስታወቀ!

በትግራይ ክልል መቀለ አቅራቢያ የሚገኘው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ75 ቀናት በኋላ ስሚንቶ ማምረት መጀመሩን አስታወቀ።

መስቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በግብአት ማውጫ ሳይት (ኳሪ ሳይት) ላይ አጋጥሞት በነበረው ችግር ምክንያት ላለፉት 75 ቀናት ምንም አይነት ምርት እያመረተ እንዳልነበር ጠቁሞ አሁን ላይ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ስምምነት ላይ በመደረሱ ወደ ምርት መመለሱን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ለምርት ማቆሙ ዋነኛ ምክንያቴ ለስሚንቶ ምርት የምጠቀምባቸው የተለያዩ ጥሬ እቃዎች በተለያዩ ምክንያቶች በአግባቡ እና በወቅቱ ማግኘት ስላልቻልኩ ነው ሲል መግለጹን ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ላይ ባቀረብነው ዘገባ መግለጻችን ይታወሳል።

ፋብሪካው የጥሬ እቃ በማወጣባቸው አከባቢዎች እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በጊዜያዊነት እና በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው መንግታዊ እና ማህበረሰባዊ አካላት ጋር በመመካከር ለመፍታት ጥረት ባደርግም እስካሁን መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም ማለቱም በዘገባው ተካቷል።ነገር ግን ጥሬ እቃ በሚያወጣባቸው አከባቢዎች እያጋጠሙት ስላሉ ችግሮች በይፋ የገለጸው ነገር አልነበረም።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
19👍2
⚠️ ''ደሞዝተኛ እናድርግዎ''

🚨 በሳምንት ከ1,000 - 4,000 ብር ተከፋይ ይሁኑ

🌐 ከተከፈቱ ከአንድ ዓመት በላይ የሆኑ የLinkedin አካውንቶችን በማከራዬት በሳምንት ጠቀም ያለ ክፍያ ያግኙ !

⚠️መስፈርቶች

💠ከተከፈተ ከ1 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆነ
💠ምንም Friend (Connection) ባይኖረውም እንከራያለን

📮 የክፍያው መጠን በተከፈተበት ዓመት ቆይታ ይወሰናል።

☎️
+251934848429 ይደውሉልን

⬛️ በውስጥ መስመር ➡️
@linkedin_ethiop ያግኙን

🌐 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ➡️
@linkedin_ethiopiaa
8