YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶች ምልክት እንዲለጠፍባቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ።

ቢው ከአገራዊ ጠቅላላ ምርት 1.4 በመቶ እንዲሸፍን መታቀዱ ተሰምቷል።የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈልባቸው በገንዘብ ሚኒስቴር የተመረጡ ምርቶች፣ ምልክት እንዲለጠፍባቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ፡፡

በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 (በተሻሻለው) አንቀጽ 29 እና 42 (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ‹‹የኤክሳይዝ ምልክቶች አስተዳደር ሥርዓትን ለመወሰን የወጣው መመርያ ቁጥር 1072/2017››፣ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው በተለይ በአልኮልና በትምባሆ ምርቶች ላይ የሚደረገውን ክትትልና ቁጥጥር የሚያጠናክር የኤክሳይዝ ምልክት እንዲለጠፍባቸው አስገዳጅ ሆኗል።

የአልኮል መጠጦች፣ አልኮል አልባ ቢራ፣ የወይን ጠጅ ወይም የተጣራ አልኮል የታከለበት ወይን ጠጅ፣ የአልኮል መጠናቸው ከ0.5 በመቶ በላይ የሆነ ተመሳሳይ ምርቶች የኤክሳይዝ ምልክት ሊደረግባቸው እንደሚገባ በመመርያው ተደንግጓል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
10👍7👎1
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ዶላር ውጪ በሌሎች ምንዛሬዎች ለመገበያየት እየሰራች መሆኑን ገለጸች!

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ዶላር ውጪ በሌሎች ምንዛሬዎች ለመገበያየት በሚያስችሏት እርምጃዎች ላይ እየሰራች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ።በዚህም በተለያዩ ጊዜያት ከሀገራት ጋር የተደረሱ ስምምነቶች መኖራቸውም ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፤ ውሳኔው ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር፣ የንግድ ሚዛንን ለመጠበቅ እና በአንድ ምንዛሪ ላይ የመመካትን አሉታዊ ተፅእኖ ለመከላከል ያለመ ነው።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ባሳለፍነው አርብ ዕለት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ እንደ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ካሉ ሀገሮች ጋር በምንዛሬያቸው እንዲገበያዩ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሷን ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው፤ መንግስት የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብርን ለማመቻቸት ከአሜሪካን ዶላር ውጪ በሌሎች ምንዛሬዎች ለመገበያየት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ እየሰራ ነው ብለዋል።

ይህ እርምጃ የሀገሪቱን የውጭ ገበያዎች መዳረሻ ለማስፋት ያለመ ነው ብለዋል። አክለውም ከአሜሪካ ዶላር ውጪ ተጨማሪ ምንዛሬዎች መኖራቸው አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ሲሉ ተናግረዋል።

Via AS/EBC
@YeneTube @FikerAssefa
29👍16😁9🔥1
ኬንያ ለአፍሪካ አገሮች የቪዛ ገደቦችን ሙሉ በሙሉ አነሳች!

ኬንያ ለአፍሪካ እና ለአብዛኛዎቹ የካሪቢያን አገሮች ዜጎች የቪዛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ መሰረዟን አስታውቃለች። ይህ ውሳኔ የኤሌክትሮኒክ የጉዞ ፈቃድ ረጅም ቅጾች መሙላት ወይም የቪዛ ክፍያ መክፈል ሳያስፈልግ ወደ ኬንያ መግባት ያስችላል።

ይህን ተከትሎ ብቁ ተጓዦችም ያለምንም ችግር ወደ ድንበር በመሄድ ወደ አገር ውስጥ መግባት ተብሏል።

የዚህ አዲስ ፖሊሲ ትልቁ ተጠቃሚዎች የአፍሪካ አገሮች ዜጎች ሲሆኑ፣ በኬንያ እስከ ሁለት ወራት ድረስ የመቆየት መብት አግኝተዋል። በተጨማሪም፣ የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አባል አገራት ዜጎች አሁን ባሉት የነጻ እንቅስቃሴ ፕሮቶኮሎች መሠረት እስከ ስድስት ወራት ድረስ መቆየት ይችላሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
42👎1
የሰራተኞች ማህበራት 'ፌስታል ይዘው ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞችን ማሳየት እንችላለን' አሉ!

የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን፣ አዲስ በታቀደው የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ገለጸ።

ኮንፌዴሬሽኑ፣ ፓርላማው ከፈቀደ ከስራ ሰዓት በኋላ ሆቴሎች አካባቢ ፌስታል ይዘው ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞችን ማሳየት እንደሚችል አስደንጋጭ በሆነ መልኩ አስታወቀ።

የኮንፌዴሬሽኑ ዋና ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ አሁን ያለው የኑሮ ውድነት ሰራተኞችን በቀን አንድ ጊዜ እንኳ በአግባቡ እንዳይመገቡ ማድረጉን ገልጸዋል።

በረቂቅ አዋጁ የገቢ ግብር መነሻ ከ2,000 ብር ጀምሮ በ15 በመቶ ግብር እንዲከፈል የቀረበው ሀሳብ፣ የኑሮ ውድነትን ያላገናዘበ እና ሰራተኞችን ለከፋ ችግር የሚዳርግ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አቶ ካሳሁን፣ አንድ ድርጅት ከትርፉ 35 በመቶ ግብር ሲከፍል፣ ሰራተኛው ደግሞ ከሚበላው ደሞዙ ላይ 35 በመቶ መክፈሉ ፍትሃዊ አይደለም በማለት የግብር ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ረቂቅ አዋጁ ለሁለት ዓመታት በጥናት ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል። የ2,000 ብር መነሻ የተደረገበት ምክንያትም የአገሪቱ የመክፈል አቅም ዝቅተኛ በመሆኑ እንደሆነ ተብራርቷል።

ሚኒስትሩ አሁን ያለው የኑሮ ውድነት በግብር ብቻ የመጣ ሳይሆን፣ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ምክንያትም እንደሆነ ጠቁመው፣ መንግስት የደሞዝ ጭማሪ በማድረግ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል። ሸገር እንደዘገበው የግብር መነሻውን ከዚህ በላይ ከፍ ማድረግ ከመንግስት ገቢ ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚፈጥርም አስጠንቅቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
41😭15
የገቢ ግብር መነሻ ገቢ ወደ 5,000 ብር ከፍ እንዲል ጥያቄ ቀረበ!

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ የኑሮ ውድነትን ታሳቢ በማድረግ የገቢ ግብር መነሻ ገቢ ከ2,000 ብር ወደ 5,000 ብር ከፍ እንዲል ጠንካራ ጥያቄ ቀርቧል። በአሁኑ ረቂቅ አዋጅ መሰረት፣ ከ2,000 ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር እንዲከፈል ሀሳብ ቀርቧል።

ይህ የተገለጸው በፓርላማው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተካሄደው ውይይት ላይ ሲሆን፣ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ፣ የአዋጁ ማሻሻያ የመንግስትን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።ከግብር ነፃ የሚሆነው ገቢ አሁን ባለው ማሻሻያ በ300% በማደግ ወደ 2,000 ብር ከፍ እንዲል የተደረገ ሲሆን፣ ከፍተኛው 35% ግብር የሚያርፍበት ገቢ ደግሞ ወደ 14,000 ብር ከፍ እንዲል ሆኗል።

በውይይቱ ወቅት፣ የገቢ ግብር መነሻው ከአምስት ሺህ ብር ጀምሮ እንዲሆን፣ ለአካል ጉዳተኞች በተለየ መልኩ ግብር እንዲቀነስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የሙያና የንግድ ዘርፎች አንፃር በደንብ እንዲታይ የሚሉ አስተያየቶች ቀርበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
47👍9😭3👎1
Forwarded from YeneTube
ፒያሳ የመጨረሻው ሱቅ እና ቤት ሽያጭ ❗️

ፒያሳ ሀገር ፍቅር ቲያትር እና ሚኒሊክ አደባባይ መሀል የንግድ ሱቆች

* የግል የሚያደርጉት የንግድ ሱቆች ፒያሳ ላይ ብቸኛው እየሸጠ ያለው ቴምር ሪልስቴት ነው

* ሚኒሊክ አደባባይ ጋር በመንግስት የሚሰራው የ አውቶብስ እና የታክሲ ተርሚናል አጠገብ

* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት

* 4700 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል

* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም

* በወር ከ80,000 ብር በላይ የኪራይ ገቢ የሚኖራቸው

* ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

ቴምር ሪልስቴት.......
  
ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ወገኖቻችን በሙሉ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ፕሮሰስ ማድረግ የምትችሉበትን እና መግዛት መዋዋል የምትችሉበትን መንገዶች አመቻችተናል!

ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ

☎️ +251976195835

በዋትሳፕ ያገኙናል -

https://wa.me/251976195835

Telegram username
@Ruthtemersales

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

https://www.facebook.com/share/1ABkH3oH9x/
7
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
2
የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ የሆነው የቀይ ባህር አፋር በሰመራ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የታደሙበት ህዝባዊ ጉባኤ ማካሄዱ ተገለጸ!

- “በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ውጥረት መንገሱን ጠቁሞ የአፋር ህዝብ የጦርነት ሜዳ እንዳይሆን አስግቶናል” ብሏል

በኤርትራ በተቀዋሚነት የሚንቀሳቀሰው የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (RSADO) በአፋር ክልል ሰመራ-ሎጊያ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ በታደሙበት ሕዝባዊ ጉባኤ ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ-ሎጊያ ከተማ ማካሄዱ ተገለጸ።

ድርጅቱ በኤርትራ የሚያደርገውን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፤ጉባኤው የተዘጋጀው በቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና በሌሎች የሲቪክ ማህበራት መሆኑም ተጠቁሟል።

“በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለስልጣናት መካከል የቃላት ጦርነትን ተከትሎ ባሁኑ ወቅት በድንበር አከባቢዎች ላይ ውጥረት መንገሱን ያመለከተው ድርጅቱ (RSADO) የቀይ ባሕር አፋር ህዝብ የጦርነት ሜዳ እንዳይሆን አስግቶናል” ሲል ገልጿል፡፡

አሁን ላይ በኤርትራ ያለው መንግስት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ወደብ እንድትጠቀም ፍላጎት የለውም በማለት ስርዓቱን በመታገል የህዝባቸውንም ሆነ የኢትዮጵያን ፍላጎት ማስከበር ለነሱ በጎ አጋጣሚ መሆኑን የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ሀሩን አመላክተዋል፡፡

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
25👎4🔥3😁1
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ሠራተኞቹ በኢትዮጵያ መከላከያ መገደላቸውን አስታወቀ!

ከአራት ዓመታት በፊት በትግራይ ጦርነት ወቅት በክልሉ የሰብዓዊ ተልእኮ ላይ የነበሩ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) ሶስት ሰራተኞች "ሆን ተብሎ እና በግልጽ ተለይተው" በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት "ያነጣጠረ ግድያ" እንደተፈጸመባቸው ድርጅቱ አስታወቀ።

የረድዔት ድርጅቱ ሰራተኞቹ በተገደሉበት መንገድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት 'ኮንቮይ' [ተሽከርካሪዎች] እንደነበር ማረጋገጡን እንዲሁም አንድ የጦሩ አዛዥ "ተኩስ" እና "አስወግዳቸው" የሚል ትዕዛዝ መስጠታቸውን ጠቁሟል።

አንድ የኤም.ኤስ.ኤፍ ከፍተኛ ኃላፊ ራኬል አዮራ "ሆን ተብሎ ነው የተገደሉት፤ ከአጥቂዎቻቸው ጋር ፊት ለፊት እየተያዩ ነበር እና በጣም በቅርብ ርቀት ብዙ ጊዜ በጥይት ተመተው ነበር" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ድርጅቱ ይህን ያስታወቀው ከአራት ዓመታት በፊት፣ ሰኔ 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሶስት ሰራተኞቹ ላይ "ሆን ተብሎ ያነጣጠረ" ግድያ መፈጸሙን አስመልክቶ በውስጣዊ ምርመራ የደረሰባቸውን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

ሙሉ ዘገባው:
https://www.bbc.com/amharic/articles/cvg9zqgng55o

@YeneTube @FikerAssefa
😭2925👎4😁1
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ሸገር ዳቦ ከ260 ሚሊየን በላይ ዳቦ እንዳመረተ ተነገረ!

ሸገር ዳቦን ጨምሮ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚገኙ በመንግስት እና በግል ባለሀብቶች ከተገነቡ 30 የሚሆኑ የዳቦ ፋብሪካዎች 26ቱ በስራ ላይ እንደሚገኙ በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ብርሀኑ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሸገር ዳቦ የሽያጭ ቦታዎች እንዳሉ የሚገልፁት አቶ አሸናፊ ከዚህ በተጨማሪ በትምህርት ቤቶች ላይ ለሚከናወነው የተማሪዎች ምገባ ስነስርዓት ዳቦ እንደሚቀርብ ገልፀዋል። ለትምህርት ቤቶች ብቻ በቀን ከ800 ሺህ በላይ ዳቦ ለተማሪዎች እንደሚቀርብ በማንሳት ከዚህ ባሻገር ዳቦው ለሜቅዶንያ እና በየወረዳው ላሉ የምገባ ማዕከሎች እና ሱቆች ተደራሽነት እንደሆነ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በአመት በመዲናዋ ከ360 ሚሊየን በላይ ዳቦ እየተመረተ ሲሆን ከ260 ሚሊየን በላይ የሚሆነው ሸገር ዳቦ እንደሆነ የገለፁት አቶ አሸናፊ የከተማ አስተዳደሩ ከ 36 ቢሊየን ብር በላይ በየወሩ ድጎማ በማድረግ ለህብረተስቡ ዳቦ በዝቅተኛ ዋጋ እየተከፋፈለ እንዳለ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ ሶስት የዳቦ ፋብሪካዎች ስራ እንደሚጀምሩም አክለዋል።

በተያያዛ ጉዳይ ብስራት "በዳቦ መጠን ማነስ ይታያል" በሚል ከከተማይቱ ነዋሪዎች የደረሰውን ቅሬታ ለአቶ አሸናፊ ብርሃኑ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ግራም በሚሰርቁ የዳቦ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ገልፀው ነዋሪው እንደዚህ አይነት አጠራጣሪ ነገሮችን ሲያጋጥመውና የግራም ስርቆቶችን ሲመለከት በቢሮው ነፃ የስልክ መስመር 8588 ላይ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
😁3928
ቪዛ እና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላደሱ የውጭ ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ ተደረገⵑ

-የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከ34 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡንም አስታውቋል

አገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት እንደገለጹት በ2017 በጀት ዓመት አንድ ሚሊዮን 465 ሺህ 989 ፓስፖርት ሊሰጥ ችሏል፡፡በሰጠው አገልግሎቶች 34 ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ገቢ እንደሰበሰበም አስታውቀዋል፡፡

አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር የሚፈጥሩ የማጭበርበርና የማታለል ተግባር፣ በሕገ-ወጥ መንገድ በኦንላይን አስቸኳይ ፓስፖርት የሚሞሉ 231 ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።በተመሳሳይ ሦስት ሺህ 868 ግለሰቦች የተጭበርበረ ሰነድ በመጠቀም ፓስፓርት ሊያወጡ ሲሞክሩ በሕግ እንዲጠየቁ መደረጉን ያስረዱት ወይዘሩ ሰላማዊት፤ 12 ሺህ 127 የውጭ ዜጎች ሃሰተኛ ሰነዶችን በመያዝ በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው ርምጃ ሊወሰድባቸው ችሏል።

ሦስት ሺህ 263 የቪዛ እና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳያድሱ የቀሩ ሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የውጭ ዜጎችን በመያዝ የክፍያ መመሪያው በሚያዘው መሠረት አስፈላጊውን ውዝፍ ከፍለው ከሀገር እንዲወጡ መደረጉንም የኢፕድ ዘገባ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
😁2216🔥1
“በአፋር ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል ወይንም የአፋር ክልል መንግስት ትንኮሳ አድርገን ነው የምንወስደው” - ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ

በአፋር ክልል የሚገኙ የትግራይ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል መንግስት ወይንም የአፋር ክልል መንግስት ትነኮሳ አደርገን ነው የምንወስደው ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ ገለጹ።

የክልሉ የሰማዕታት ኮሚሽን ባዘጋጀው መድረክ ላይ ትላንት ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ “በዚያ በኩል የሚኖር ምንም አይነት ተነሳሽነት/እንቅስቃሴ እንደ ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ እዚያ ያሉ ሀይሎች ብቻ አድርጎ አይወስደውም፣ ወይ የፌደራል መንግስት ነው ካልሆነም የአፋር መንግስት ነው ብሎ ነው የሚወስደው” ብለዋል።

“እዛ ካሉት (ነጻ መሬት) ሀይሎች ጋር ያለው ልዩነት መቶ በመቶ መፈታት ያለበት በሰላማዊ መንገድ ነው፤ ነገር ግን ማንኛውም ትንኮሳ ከአፋር ክልል በኩል ከመጣ ወይ የአፋር መንገስት ነው አልያም የፌደራል መንግስቱ ነው ተብሎ የሚወሰድ እንጂ የትግራይ ተወላጆች/ተጋሩ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም” ሲሉም አስታውቀዋል፤ ታጣቂዎች “የውክልና (Proxy) ሀይሎች ሁነው እንዳያገለግሉ የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ ተደምጠዋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
43👍6👎6😁4
በደቡብ ጎንደር ዞን በድርቅ ምክንያት ከ175ሺህ በላይ ሠዎች እርዳታ ይፈልጋሉ!

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ከመቀጠዋ፣ ከጋይንትና ከእብናት ወረዳዎች አስተያየታቸውን የሰጡን አረሶ አደሮች እንዳሉት በአካባቢዎቹ በተደጋጋሚ የተከሰተው ድርቅ ነዋሪዎቹ አካባቢያቸውን እንዲልቁ እያደረጋቸው ነው፡፡

ከላይ ጋይንት ወረዳ አስተያየታቸውን የሰጡን ነዋሪ  የአካባቢው ነዋሪዎች የሚቀምሱት ነገር የለም፣ እርዳታ መጣ ቢባልም በቂ ባለመሆኑ ነዋሪው ስደቱን መርጧል ሲሉ ነው ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩት፣ በተለይ ምጥራባ፣ ዳባ ወቶክሶስ፣ ላይ ነጋላና ታች ነጋላ በተባሉ ቀበሌዎች ጉዳቱ የከፋ መሆኑን ማየታቸውን አስረድተውናል፡፡

ሌላው አረሶ አደር በበኩላቸው ቁመና (እንስሳት ማለታቸው ነው) ያላቸው ሠዎች እየሸጡ ለጊዜው ከሩቅ ቦታ እህል በውድ ዋጋ እየሸመቱ ለመመገብ ቢሞክሩም ዘላቂ ሊሆን እንዳልቻለ አመልክተዋል፣ የሚሽጥ እንስሳት የሌላቸው ወገኖች ግን በርህብ እየተሰቃዩ እንደሆነ ነው የገለጡት፡፡ወጣቶች የቀን ሥራ ሰርተው ለማደር ቢሞክሩም የሚሰራ ሥራ ባለመኖሩ ምርጫቸው ወደ ሌላ አካባቢ መሄድና ስደት ሆኗል ሲሉ ነው ያስረዱት፡፡

በስልክ ያገኝናቸው አንዲት እናት እንዳስረዱን “እንኳን ሠው እንስሳቱ በድርቁ ምክንያት እየተጎዱ ነው” ብለዋል፡፡ የሚሰጠው እርዳታም ከጥራትም ከመጠንም እጅግ ያነስ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የበላሳ ወረዳ ነዋሪ በሰጡን አስተያየት ሳሚ፣ ላቫ፣ ሳውጋሪ፣ አጃንዳብ፣ ላየና ሴራ በተባሉ ቀበለኤዎች የሚኖሩ በሺህ የሚጠሩ ነዋሪዎች በድርቅ ተጠቅተዋል ብለዋል፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን  አደጋ መከላክልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ ተጨማሪ አስተያየት እንዲሰጡን በስልክ ብንጠይቅም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ነዋሪዎቹ መንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት፣ በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ለችግራቸው እንዲደርሱላቸው ጠይቀዋል፡፡

በአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ አበባው አየነው በጉዳዩ ዙሪያ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ በዞኑ በሚገኙ 7 ወረዳዎች በሚገኙ 57 ቀበሌዎች በተከሰተው ድርቅ 175ሺ 915 ሠዎች መጠቃታቸውን ጠቅሰው በምንግሥት ለእብናት፣ ለስማዳ፣ለሰዴ ሙጃና መቀጠዋ ተረጂዎች 12ሺ 419  ኩንታል የምግብ እህል ተከፋፍሏል ነው ያሉት፣ የኢተዮጵያ ቀይ መስቀልም 1ሺህ 500 ለሚሆኑ የእብናትና መቀተዋ ተርጂዎች ይፊኖ ዱቄት እርዳታ ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

በድርቁ ምክንያት ቤቱን ዘግቶ የተፈናቀለ ሠው የለም ሲሉ የተናገሩት አቶ አበባው፣ ሆኖም ሥራ ለመፈለግ ወደሌሎች ቦታዎች የተንቀሳቀሱ ሠዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አመልክተዋል፡ለድርቁ መባባስና ለምርት መቀነስ ከዝናብ እጥረቱ በተጨማሪ በክልሉ ያለው ወቅታዊ የሠላም እጦት ሌላው ምክንያት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጠዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
13😭7👎1
ሞስኮን ከምድረ ገጽ የሚያጠፋ መሳሪያ ልንልክ ነዉ ! /ትራምፕ /

የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፑቲን ከዩክሬን ጋር ካልተደራደሩ ሩሲያ በታሪኳ አይታዉ የማታዉቀዉ መአት እንደሚወርድባትና ከባድ መዘዞችን እንደሚገጥማት ማስጠንቀቃቸው ተነገረ ።

ዶናልድ ትራምፕ ቭላድሚር ፑቲንን የሰላም ስምምነቱን ካልተቀበሉ ለዩክሬን ሞስኮን ማጥፋት የሚችሉ ኃይለኛ የመርከብ ሚሳኤሎችን እንደሚያስታጥቋት ዝተዋል።

ፑቲን በወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ድብደባ ማድረጋቸውን በመቀጠላቸዉ የተናደዱት ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ የሚጠቀሙባቸውን “የላይኛው መስመር ጦር” ወደ ኪየቭ ለማሰማራት ለመላክ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።

ለሳምንታት በዩክሬን ላይ የቦምብ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ፑቲንን ወደ ድርድር ለመመለስ ትራምፕ በጦር መሣሪያ ቤታቸው ውስጥ ያለውን “ሁሉንም ነገር” የሚያበላሽ የጦር መሣሪያ ለመላክ ቃል ገብተዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዩክሬንን ለመርዳት እምብዛም ጥቅም ላይ ያልዋሉትን ሎክሂድ ማርቲን መሳሪያዎችን ለማቅረብ እያሰቡ ነው ተብሏል።

ወደ ዩክሬን ለመላክ ከታቀዱት የጦር መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ የአሜሪካ የጋራ ከአየር ወደ ላይ የሚቆም ክሩዝ ሚሳኤሎች መታጠቅ የሚችለዉ ከ155 ማይል - 75 ማይል ርዝመት ያለው (JASSM) የዉጊያ ጀት ሲሆን ይህ አሜሪካ በተለያዩ አዉደ ዉጊያዎች በማሰማራት ከምትታወቅበት ጀቶች መካከል ቀዳሚዉ መመኪያዋ የሆነ ጀት እስከ 230 ማይል የሚደርስ ክልል የማጥፋት አቅም ያለው እና 450 ኪሎ ግራም የጦር ጭንቅላት የታጠቀ ነው።

ጀምስ ጀቶች በዝቅተኛ ከፍታ ላይ መብረር ስለሚችሉ እጅግ በጣም ጥሩ ራዳር-ማምለጥ ችሎታቸውም የተመሰከረላቸው ናቸዉ ።

በጥቅሉ አሜሪካ ለዩክሬን ለማድረግ ያሰበችዉ $74 billion ወታደራዊ ድጋፍ መካከል ከዩክሬን ድንበር ቢወንጨፉ ቢያንስ 30 የሩሲያ አየር ማረፊያዎችን የማጥፋት አቅም እንዳላቸዉ የሚነገርላቸዉ ከአየር ላይ ወደ አየር የሚተላለፉ የአርበኞች ሚሳኤል ሲስተሞች እና ባትሪዎች ጀቶችንና ሌሎች መሳሪያዎች ይገኙበታል ተብሏል።

ዩክሬንን እያሳየችዉ ያለዉን 'ታላቅ ድፍረት' ያወደሱት
ትራምፕ ቮልዲሚር ዜለንስኪ ኪየቭ የሩስያን ሁለቱን ታላላቅ ከተሞች በአሜሪካ ፋየር ልትመታ ትችል እንደሆነ ጠይቀው እንደነበርም ተነግሯል። ሲል የዘገበው ሲቢሲ የዜና ወኪል ነዉ ።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ
@Yenetube @Fikerassefa
53😁35👎9👀2👍1
Forwarded from YeneTube
በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት እሽቅድድም የማይደረግባቸው ዘርፎች አልነበረም ማለት ይቻላል። ከፉክክሮቹ አንዱ የሆነው ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። የጠፈር እሽቅድድም ደግሞ ከነዚህ ሁሉ ታዋቂው ነው። ይሁን እንጂ ብዙ የማትሰሙትና ከጠፈር በተቃራኒ የተጀመረ ፕሮጀክት ነበረ። አላማው በተቻለ መጠን በጥልቀት መቆፈር። ይህ ፕሮጀክት ሁለት አስርት አመታትን የፈጀ ሲሆን ምን ምን ተገኙበት? ምን ያህል መቆፈር ተቻለ እና ለምን ቁፋሮው ቆመ የሚለውን እናያለን።

ፕሮግራሙን ከመጀመሮ በፊት ቪዲዮውን ላይክ እና ሼር ቻናሉንም ሰብስክራይብ ያድርጉ

https://youtu.be/4N3QkwkO7Ms
23👎2
Forwarded from YeneTube
ፒያሳ የመጨረሻው ሱቅ እና ቤት ሽያጭ ❗️

ፒያሳ ሀገር ፍቅር ቲያትር እና ሚኒሊክ አደባባይ መሀል የንግድ ሱቆች

* የግል የሚያደርጉት የንግድ ሱቆች ፒያሳ ላይ ብቸኛው እየሸጠ ያለው ቴምር ሪልስቴት ነው

* ሚኒሊክ አደባባይ ጋር በመንግስት የሚሰራው የ አውቶብስ እና የታክሲ ተርሚናል አጠገብ

* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት

* 4700 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል

* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም

* በወር ከ80,000 ብር በላይ የኪራይ ገቢ የሚኖራቸው

* ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

ቴምር ሪልስቴት.......
  
ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ወገኖቻችን በሙሉ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ፕሮሰስ ማድረግ የምትችሉበትን እና መግዛት መዋዋል የምትችሉበትን መንገዶች አመቻችተናል!

ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ

☎️ +251976195835

በዋትሳፕ ያገኙናል -

https://wa.me/251976195835

Telegram username
@Ruthtemersales

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

https://www.facebook.com/share/1ABkH3oH9x/
7
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
1