በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤4
የትራምፕ አስተዳደር ከ1,000 በላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞችን ከስራ አሰናበተ
የትራምፕ አስተዳደር የፌደራል የመንግስት ሰራተኞችን ቁጥር ለመቀነስ በሚያደርገው ጥረት፣ ከ1,000 በላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞችን ከስራ እንዳሰናበተ የሲቢኤስ ኒውስ ዘገባ አመልክቷል።
ዘገባው እንደሚያመለክተው፣ ባለፈው አርብ ለውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በተላከ እና በቢቢሲ የአሜሪካ ዜና አጋር በተገኘ ማስታወቂያ መሰረት፣ በግዳጅ ከስራ ከተሰናበቱት ውስጥ 1,107 የሲቪል ሰርቪስ እና 246 የውጭ አገልግሎት ሰራተኞች ይገኙበታል ተብሏል።
ከዚህ ቀደምም፣ የፌደራል መንግስትን በስፋት የማደራጀት ጥረት አካል በመሆን፣ ከ1,500 በላይ የሚሆኑ ሌሎች የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በፈቃደኝነት ስራቸውን ለቀው እንደነበር ተገልጿል።
ይህን የጅምላ ሰራተኛ ቅነሳ የሚተቹ ወገኖች፣ ቅነሳው የመስሪያ ቤቱን ስራ በእጅጉ እንደሚጎዳ ሲከራከሩ ቆይተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

❤19😭5
ግብጽ የከረሙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ወደ ቱርክ በማቅናት በአንካራ ከኤርዶጋን ጋር መምከራቸው ተገለጸ!
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ መሃሙድ ትላንት ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ አንካራ በማቅናት ከፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶሃን ጋር መምከራቸው ተገለጸ፤ በግብጽ ካይሮ የከረሙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ከቱርኩ አቻቸው ጋር በዝግ መምከራቸውን የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በአንካራው ስብሰባ የሁለቱ መሪዎች በቀጠናው ስላሉ ውጥረቶች መወያየታቸውን የጠቆሙት የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ኤርዶጋን በቀጠናው እየተስተዋሉ ያሉ ውጥረቶች የአፍሪካ ቀንድን መረጋጋት የበለጠ ሊያናጉ የሚችሉ መሆናቸውን በመግለጽ ሰጋታቸውን መግለጻቸውን አስታውቀዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት የወጡ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈረመው የአንካራው ስምምነት እክል እንዳጋጠመው እና መቆሙን አመላክተዋል፤ ከሚያዚያ ወር ወዲህ ምንም አይነት የውይይት መርሃግብረ አልተያዘም ብለዋል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa

❤25😁10
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት 350.13 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት 350.13 ቢሊዮን ብር ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ፀደቀ።ይህ በጀት ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ108 ቢሊዮን ብር ወይም የ45 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱል ቃድር ሬድዋን አስታውቀዋል።
አቶ አብዱል ቃድር ሬድዋን የበጀት ረቂቅ አዋጁን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት፣ በጀቱ የሚሸፈንባቸውን ዋና ዋና የፋይናንስ ምንጮች ዘርዝረዋል።
በዚህም መሰረት፡-
- ከታክስ ከ238 ቢሊዮን ብር በላይ ወይም 68 በመቶ
- ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ከ56 ቢሊዮን ብር በላይ
- ታክስ ካልሆነ ገቢ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ
- ከመንገድ ፈንድ 1.8 ቢሊዮን ብር
- ከውጭ ብድርና እርዳታ ደግሞ 6.98 ቢሊዮን ብር እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከፀደቀው አጠቃላይ በጀት ውስጥ፣ 70.35 በመቶ ለካፒታል በጀት፣ 26.22 በመቶ ለመደበኛ በጀት እንዲሁም 3.43 በመቶ ለመጠባበቂያነት መያዙ ታውቋል።

❤22👎8
Forwarded from HuluGames Community
100 አሸናፊዎች የሚያገኙ 100 ብር!
በዚህ ሻሞ ለመሳተፍ:
1. @hulujackpot
2. @HuluPayGiveaways
የማሸነፍ እድልዎን ያሳድጉ:🚀
▫️ የግል ሊንክዎን ያጋሩ = እድልዎ ይጨምራል
▫️ የበለጠ ያጋሩ = የበለጠ የማሸነፍ እድል
▫️ ለእያንዳንዱ ሰው በሊንክዎ የተሳተፈ = ተጨማሪ ነጥብ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤9👍2
YeneTube
Photo
የቤት ሰራተኛዋን ገድለው ሁለት ህፃናትን አግተው አስር ሚሊዮን ብር የጠየቁ አጋቾችን በቁጥጥር ስር አውሎ ህፃናቱን ለቤተሰቦቻቸው ማስረከቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ!
ደርጊቱ የተፈጸመዉ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አለም ባንክ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ከቀኑ 11፡45 ላይ ነዉ፡፡
የቤት ሰራተኛ የሆነችው ሀብታሟ ወርቁ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በስለት ተወግታ መሞቷን እና እህትማማች የሆኑ የአስርና የሰባት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃን እምነት አሽናፊ እና ጄሪ አሽናፊ መጥፋታቸው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ሪፖርት ይደሰርሰዋል፡፡
ጠቅላይ መምሪያው የፎረንሲክ ፣ የምርመራ እና የክትትል ቡድን አባላትን በማደራጀት ወንጀል ወደተፈፀመበት ስፍራ ከሄዱ በኃላ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ሥራው መጀመሩን የጠቅላይ መምሪያው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ገልፀዋል፡፡
የሟች ማንነት እንጂ የገዳይ ማንነት አለመታወቁ ፣ ሀብታሟን ማን ገደላት ? ህፃናቱስ የት ተሰውሩ ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እና ወንጀል ፈፃሚውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንዲሁም የጠፉትን ህፃናት ለማግኘት ክትትሉ በቀጠለበት ሒደት መንግስቱ ደላሳ የተባለ ግለሰብ ለህፃናቱን ወላጅ እናት ለወ/ሮ ሃዊ ዮሴፍ ስልክ በመደወል ህፃናቱን ማገቱን 10 ሚሊዮን ብር ካልተሰጠው ልጆቹን እንደሚገድላቸው እንዲሁም ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቀች በህፃናቱ ላይ የከፋ እርምጃ እንደሚወስድ የሚገልፅ መልእክት ያስተላልፋል፡፡
ህፃናቱ ከዚህ ቀደም አጋቹን ስለሚያውቁትና የደገሰላቸውን የሞት ድግስ ባለማወቃቸው ያለጭንቀት ሲጫወቱ እና ልጆቹ እርሱ ጋር መሆናቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ ለወ/ሮ ሃዊ ይልካል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር ባደረጉት የክትትል ሥራ የፖሊስ አባላት ቀንና ሌሊት ባደረጉት ያላሰለሰ ክትትል አጋቹን እና ሌሎች ተባባሪዎቹን ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ/ም በቁጥጥር ስር በማዋል ሁለቱንም ህፃናት በአዳማ ከተማ ልዩ ቦታው ቦሌ ሰፈር እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ታግተው ከተቀመጡበት ቤት በሰላም ማስለቀቁን ኮማንደር ማርቆስ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣዎችን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
የህፃናቱ ወላጅ እናት ወ/ሮ ሃዊ ዮሴፍ እና አባታቸው አቶ አሸናፊ ጫኔ እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በተፈፀመው የወንጀል ድርጊት በእጅጉ ተጨንቀው እንደነበር ተናግረው አዲስ አበባ ፖሊስ እና ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ጥረት ልጆቻቸውን በሰላም በማግኘታቸው በፀጥታ አካላት ተግባር ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው እንቅስቃሴ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከታቸውን ለዚህም በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ስም ኮማንደር ማርቆስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
መሰል ችግር ሲያጋጥም ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ፖሊስ አስታውቆ ነገር ግን ልዩ ልዩ ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ስለ ወንጀሉ መረጃ ማሰራጨት ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ምቹ ሆኔታን እንደሚፈጥር ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢው ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
Via AMN

❤79😭21👍4
መንግሥት ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ በመሳተፍ የ173 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉደለቱን እንደሚሸፍን አስታወቀ!
መንግሥት ለ2018 ካፀደቀው በጀት ውስጥ 173 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን የተጣራ የበጀት ጉደለት፣ በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አማካይነት የዕዳ ሰነዶችን በመሸጥ ጉደለቱን እንደሚሸፍን አስታወቀ።
መንግሥት ይህንን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነዶች ምዝገባና የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግብይትን ባለፈው ዓርብ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋ በተጀመረበት ዕለት ነው።
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የሚሰጠውን የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት ባለፈው ዓርብ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋ ባስጀመረበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ግበያ ሥራ መጀመር የበርካታ ዓመታት የሪፎርም ሥራዎች፣ የፖሊሲ ቅንጅትና የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ቁርጠኝነት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143326/

❤30😁6🔥5👎2
Forwarded from YeneTube
ፒያሳ የመጨረሻው ሱቅ እና ቤት ሽያጭ ❗️
ፒያሳ ሀገር ፍቅር ቲያትር እና ሚኒሊክ አደባባይ መሀል የንግድ ሱቆች
* የግል የሚያደርጉት የንግድ ሱቆች ፒያሳ ላይ ብቸኛው እየሸጠ ያለው ቴምር ሪልስቴት ነው
* ሚኒሊክ አደባባይ ጋር በመንግስት የሚሰራው የ አውቶብስ እና የታክሲ ተርሚናል አጠገብ
* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት
* 4700 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል
* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም
* በወር ከ80,000 ብር በላይ የኪራይ ገቢ የሚኖራቸው
* ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
ቴምር ሪልስቴት.......
ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ወገኖቻችን በሙሉ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ፕሮሰስ ማድረግ የምትችሉበትን እና መግዛት መዋዋል የምትችሉበትን መንገዶች አመቻችተናል!
ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ
☎️ +251976195835
በዋትሳፕ ያገኙናል -
https://wa.me/251976195835
Telegram username
@Ruthtemersales
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴
https://www.facebook.com/share/1ABkH3oH9x/

❤6
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለፀጥታ ሥጋት የሆኑ የውጭ አገር ስደተኞች መኖራቸውን አስታወቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምን በተመለከተ የተለየ አቋም ይዘው ለፀጥታ ሥጋት በመሆን የሚንቀሳቀሱ የውጭ አገር ስደተኞች በከተማዋ እንዳሉ አስታወቀ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለፀጥታ ሥጋት የሆኑ ዜጎች መኖራቸውን ያስታወቀው 4ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በዓድዋ ሙዚየም ሲያካሂድ ነው፡፡
በጉባዔው የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በሰጡት አስተያየት፣ ከአንዳንድ ጎረቤት አገሮች አዲስ አበባ መጥተው በሐሰተኛ የገንዘብ ኅትመትና የገንዘብ ዝውውር የማታለልና የማጭበርበር ወንጀል የሚሳተፉ የውጭ ዜጎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
ወንጀለኞቹ ሐሰተኛ ዶላር በማተም ድርጊት እንደሚሳተፉ፣ መኖሪያቸውን በከተማዋ ካደረጉ በርካታ ስድተኞች ውስጥ በግድያና በዝርፊያ የሚሳተፉ እንዳሉም አስረድተዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143314/

❤20😁10🔥1
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባቱን ቢሮው አስታወቀ!
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት 1ሺህ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት አቅዶ 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማስገባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አድማሱ ሞርካ፤ ከዕቅዱ በላይ የተከናወነበት ምክንያት መንግስት ለወርቅ አቅራቢዎች ያደረገው “ማበረታቻ እና ህገ-ወጥ ግብይት መቀነስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራቸው" ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዘርፉ እንዲነቃቃና አምራቹ ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቅሰዋል።በክልሉ የተመረተው ወርቅ በአነስተኛና ባህላዊ ወርቅ አምራቾች መሆኑን ገልጸው፤ ይህም የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አሳድጓል ነው ያሉት።
ከወርቅ በተጨማሪ የድንጋይ ከሰልና እምነበረድ በስፋት እየተመረተ መሆኑን ጠቅሰው በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።
አቶ አድማሱ ከማዕድን ምርቱ 49 ሚሊዮን ብር መሰበሰቡንም ጠቅሰው፤ በቀጣይ ትላልቅ ካምፓኒዎችን በመጋበዝ በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ለማሰማራት ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።

❤20👎6🔥1👀1
በጅቡቲ የሚገኘው የሆራይዘን ነዳጅ ማጠራቀሚያ ተርሚናል ጥገና አለመከናወኑ የነዳጅ ጭነቱ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል ተባለ!
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው ነዳጅ ጅቡቲ በሚገኘው የሆራይዘን ነዳጅ ማጠራቀሚያ ተርሚናል በኩል መሆኑን ተከትሎ፤ የማጠራቀሚያ ተርሚናሉ ጥገና ባለመከናወኑ የነዳጅ ጭነቱ እንዲቀንስ ማድረጉን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታውቋል፡፡የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እስመላለም ምህረቱ ለአሐዱ እንደገለጹት ከሆነ፤ ችግሩን ለመፍታት ተጨማሪ 2 የነዳጅ ተርሚናሎችን እንዲኖሩ ከጅቡቲ መንግሥት ጋር ውይይት እንደተደረገ ይገኛል።
በጅቡቲ ከውጭ የሚገባው ነዳጅ በሆራይዘን ተርሚናል በኩል ከመርከብ ወርዶ ወደ ተሽከርካሪዎች እንደሚጫን ያስረዱት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖው በምስረታው ጊዜ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን እንደነበርና አሁን ያለው ፍላጎት 4 ነጥብ 2 እንደደረሰ ተናግረዋል።ነዳጅ ማጠራቀሚያው ከ20 ዓመት በፊት የተቋቋመ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን፤ ረዘም ላለ ጊዜ የነዳጅ ማውረድ እና ጭነት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ተርሚናል በመሆኑ በፖምፕ እና የሲስተም ክፍተቶች በመኖራቸው በነዳጅ የጭነት አገልግሎቱ ላይ አልፎ አልፎ ጭነቱ እንዲቀንስ ምክንያት ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓጓዝበት መንገድ ለተሽከርካሪዎች ምቹ አለመሆኑን በማንሳት፤ በአሽከርካሪዎች ዘንድ ቅሬታ እንደሚነሳም ለአሐዱ ተናግረዋል።አክለውም ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ከተደረገ በኃላ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚደረግ የነዳጅ ዝውውር እና የነዳጅ ሽያጭ ለነዳጅ አቅርቦቱ ላይ እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
Via Ahadu

❤26😭1
ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶች ምልክት እንዲለጠፍባቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ።
ቢው ከአገራዊ ጠቅላላ ምርት 1.4 በመቶ እንዲሸፍን መታቀዱ ተሰምቷል።የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈልባቸው በገንዘብ ሚኒስቴር የተመረጡ ምርቶች፣ ምልክት እንዲለጠፍባቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ፡፡
በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 (በተሻሻለው) አንቀጽ 29 እና 42 (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ‹‹የኤክሳይዝ ምልክቶች አስተዳደር ሥርዓትን ለመወሰን የወጣው መመርያ ቁጥር 1072/2017››፣ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው በተለይ በአልኮልና በትምባሆ ምርቶች ላይ የሚደረገውን ክትትልና ቁጥጥር የሚያጠናክር የኤክሳይዝ ምልክት እንዲለጠፍባቸው አስገዳጅ ሆኗል።
የአልኮል መጠጦች፣ አልኮል አልባ ቢራ፣ የወይን ጠጅ ወይም የተጣራ አልኮል የታከለበት ወይን ጠጅ፣ የአልኮል መጠናቸው ከ0.5 በመቶ በላይ የሆነ ተመሳሳይ ምርቶች የኤክሳይዝ ምልክት ሊደረግባቸው እንደሚገባ በመመርያው ተደንግጓል።
Via Ethio FM

❤10👍7👎1
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ዶላር ውጪ በሌሎች ምንዛሬዎች ለመገበያየት እየሰራች መሆኑን ገለጸች!
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ዶላር ውጪ በሌሎች ምንዛሬዎች ለመገበያየት በሚያስችሏት እርምጃዎች ላይ እየሰራች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ።በዚህም በተለያዩ ጊዜያት ከሀገራት ጋር የተደረሱ ስምምነቶች መኖራቸውም ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፤ ውሳኔው ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር፣ የንግድ ሚዛንን ለመጠበቅ እና በአንድ ምንዛሪ ላይ የመመካትን አሉታዊ ተፅእኖ ለመከላከል ያለመ ነው።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ባሳለፍነው አርብ ዕለት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ እንደ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ካሉ ሀገሮች ጋር በምንዛሬያቸው እንዲገበያዩ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሷን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው፤ መንግስት የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብርን ለማመቻቸት ከአሜሪካን ዶላር ውጪ በሌሎች ምንዛሬዎች ለመገበያየት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ እየሰራ ነው ብለዋል።
ይህ እርምጃ የሀገሪቱን የውጭ ገበያዎች መዳረሻ ለማስፋት ያለመ ነው ብለዋል። አክለውም ከአሜሪካ ዶላር ውጪ ተጨማሪ ምንዛሬዎች መኖራቸው አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ሲሉ ተናግረዋል።
Via AS/EBC

❤29👍16😁9🔥1