YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያ ብር ከሩብል ጋር ያለውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ሊወስን መሆኑ ታወቀ!

ባንኩ በተጨማሪ የ11 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱ ታውቋል።

እነርሱም የባንግላዴሽ ታካ፣ የባህሬን ዲናር፣ የቦሊቪያ ቦሊቪያኖ፣ የኩባ ፔሶ፣ የአልጄሪያ ዲናር፣የኢራን ሪያል፣ የሚያንማር ኪያት፣ የሞንጎሊያ ቱግሪክ፣ የናይጄሪያ ናይራ፣ የኦማን ሪያል እናየሳዑዲ ሪያል ናቸው።ባንኩ የምንዛሪ ተመኑን ከሀምሌ 3 ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርግ ኢንተርፋክስ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
35😁14🔥2
🚀 ቡስትግራም: ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።

📣🔥👀📹👍


📹የቲክቶክ : ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷የኢንስታግራም: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

📹የዩቲዩብ: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

📹 📷 📹 ✈️

LINK - 🔗 👉 https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram 🕯📈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5
የኬንያዊ ፕረዝዳምት ዊሊያም ሩቶ ፖሊስ የተቃዋሚዎችን እግር ተኩሶ እንዲሰብር ትዕዛዝ ሰጡ።
*
ተቃውሞ የበረታባቸው የኬንያው ፕረዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የንግድ ድርጅቶችን ኢላማ የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን ፖሊስ እግራቸው ላይ ተኩሶ እንዲመታ መመሪያ ሰጥቷል። ፕረዝዳንቱ ተቃዋሚዎች እግራቸው ላይ ተመትተው አቅማቸው እንድዳከም፣ ግን ደግሞ እንዳይገደሉ አዟል።

“የሌላ ሰው ንግድ ወይም ንብረት ሲያቃጥል የተያዘ ማንኛውም ሰው እግሩ ላይ በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል ይግባ፤ ኋላም ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት፤ አትግደሏቸው ነገር ግን እግሮቹ መሰባበራቸውን ያረጋግጡ” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ ለፖሊስ ባስተላለፉት ትዕዛዝ። ዘገባው የቢቢሲ አፍሪካ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
😁2916😭16👍10👀3👎1🔥1
ዩናይትድ ተጨዋቾቹ ማልያ መቀየር ያቆማሉ !

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ በሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች የተለመዱትን ባህላዊ መርሐግብሮች እንደሚሰርዝ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ በወዳጅነት ጨዋታዎች የተለመደውን አርማ እና ስጦታ እንደማይቀያየር ተነግሯል።

በተጨማሪም ተጨዋቾቹ ከወዳጅነት ጨዋታው በፊትም ሆነ በኋላ ማልያቸውን እንዳይቀያየሩ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

ክለቡ ውሳኔውን ያሳለፈው በጀመረው የወጪ ቅነሳ መርሐግብር ምክንያት እንደሆነ ቶክ ስፖርት ዘግቧል።

ይሁን እንጂ ማንችስተር ዩናይትድ ውሳኔው አላስፈላጊ ባህላዊ ስነስርዓቶችን ለማስቀረት በማሰብ መሆኑን መግለፁ ተነግሯል።

Via:- Talk Sport
@Yenetube @Fikerassefa
😁5725
"የኤርትራ ድርጊት በኢትዮጵያ ላይ የጦርነት ስጋት የሚደቅን ነው" -ኢትዮጵያ

በጀኔቫ የተመድ ጽሕፈት ቤት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋአብ ክበበው፣ የኤርትራ ድርጊት በኢትዮጵያ ላይ ቀጥተኛ የጦርነት ስጋት የሚደቅን ነው በማለት ከሰዋል።

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት፣ በኤርትራ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ተቆጣጣሪ ልዩ ራፖርተር የጊዜ ቆይታን ለማራዘም ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ በተሰበሰበበት ወቅት፣ አምባሳደር ጸጋአብ የኤርትራ ወታደሮች በተቆጣጠሯቸው የትግራይ አካባቢዎች የከፉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እየፈጸሙ ይገኛሉ ብለዋል።

አምባሳደሩ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ደቅነዋለች ላሉት ስጋት፣ የኤርትራ ወታደሮች የትግራይ አንዳንድ አካባቢዎችን ተቆጣጥረው እንደሚገኙ የተመድ ልዩ ራፖርተር ለምክር ቤቱ ያቀረቡትን ሪፖርት በአስረጅነት ጠቅሰዋል።

በተመድ የጀኔቫ ቋሚ ጽሕፈት ቤት የኤርትራ ልዑክ አቶ ሃብቶም ዘርዓይ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ውንጀላ ካለፉት ድርጊቶቿና አቋሞቿ ጋር የማቃረንና ወጥነት የሌለው መኾኑን በመጥቀስ፣ በምክር ቤቱ ውስጥ ምላሽ ሠጥተዋል።

የኤርትራ ጦር በዓለማቀፍ ሕግ በሚታወቀው የኤርትራ ግዛት ብቻ እንደሚገኝ የጠቀሱት አቶ ሃብቶም፣ የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ግዛቶችን ይዟል የሚባለው ትርክት "ጦርነት ለመቀስቀስ" እና "ለጦርነት ሽፋን ለመፍጠር ያለመ ሴራ" ነው በማለት ውድቅ አድርገውታል።

ኢትዮጵያ ባኹኑ ወቅት በይፋ ዛቻዎችን መሠንዘር፣ ጦር መሳሪያ ማከማቸትና ቀጠናዊ ሰላምና ጸጥታን የሚያደፈርሱ ድርጊቶችን መፈጸም ቀጥላለች ያሉት አቶ ሃብቶም፤ ኢትዮጵያ ይህን የምታደርገው ውስጣዊ ችግሮቿን ለመሸፋፈን መኾኑን ምክር ቤቱ መረዳት አለበት ብለዋል።

(ዋዜማ)
@YeneTube @FikerAssefa
51🔥5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለንግድ ሱቅ ፈላጊዎች በሙሉ

📍 ፒያሳ ከሚኒልክ አደባባይ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር የሚወስደው መንገድ ላይ የንግድ ሱቆችን መሸጥ ጀምረናል።
👉 2 ቤዝመንት ያለው
👉ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉በ1 ዓመት ተኩል የምትረከቡት

👉ምድር ቤት
20 ካሬ= 7ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2.8ሚሊዮን ብር
👉1ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 5.5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2 ሚሊዮን ብር
👉2ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.8 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.5 ሚሊዮን ብር
👉3ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.2 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.2 ሚሊዮን ብር
👉4ኛ እና 5ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 3.9 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 900 ሺ ብር
👉ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፈል።

ለበለጠ መረጃ
09-76-19-58-35

Telegram username
@Ruthtemersales

Whats app
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835
9
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
1
📌 Minoxidil የወንዶች ፀጉርና ፂም ማሳደግያ

📌 ፀጉሮት እየሳሳ አስቸግሮታል አልያም ፂም ማብቀል ይፈልጋሉ ? መፍትሔውን ይዘንሎት መተናል

ከቆዳችን ስር የሚገኘውን የፀጉር ጉጥ በማንቃት የሳሳን ፀጉር ወደ ቀድሞው የሚመልስ

📌📌 በ"FDA" እውቅናና ማረጋገጫ የተሰጠው ደግሞም በebay ፣ amazon እና በመሳሰሉት የ online መገበያያዎች ላይ "5" ★★★★★ ኮኮብ ያገኘ ነው

በቀን 2 ጊዜ ለሚጠቀሙ ሰዎች በ 1 ወር ውስጥ ውጤት የሚያሳይ

📞 0993944661
Telegram channel link
https://tttttt.me/Ethiopiaminoxidil
7
በአንካራ ስምምነት ከስድስት ወራት በኋላ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል የነበረው የቴክኒክ ድርድር ቆመ!

በአንካራ ስምምነት ከተፈረመ ከስድስት ወራት በኋላ፣ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በባሕር በር ጉዳይ ላይ ሲካሄድ የነበረው የቴክኒክ ድርድር መቋረጡ ታውቋል። ይህ ድርድር የተጀመረው ባለፈው ዓመት ሁለቱ መንግስታት በቱርክ ሽምግልና የውይይት ጠረጴዛ ላይ ከቀረቡ በኋላ ነበር።

የውዝግቡ መንስኤ እና የሽምግልናው ጅማሬ
ባሕር በር የሌላት ኢትዮጵያ በጥር 1፣ 2024 ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈረሟ ውጥረቱ ተባብሶ ነበር።

ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ 20 ኪሎ ሜትር የባሕር ኃይል እና የንግድ መስመር በአደን ባሕረ ሰላጤ እንድትጠቀም የሚያስችል ሲሆን፣ በምላሹም ራሷን የቻለችውን ሶማሌላንድ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እውቅና የማግኘት ዕድል ይሰጣታል። ሶማሊያ ይህንን ስምምነት "ሉዓላዊነቷን የጣሰ ግልጽ ጥሰት" በማለት አውግዛ፣ ስምምነቱ እንዳይጸድቅ ኃይለኛ የዲፕሎማሲ ዘመቻ ጀምራ ነበር። ይህን ውጥረት ለማርገብ ነበር ቱርክ በየካቲት 2024 በአንካራ ሽምግልና የጀመረችው።

በአንካራ በተደረጉ ሦስት ዙር ንግግሮች፣ ታህሳስ 11፣ 2024 ላይ ጊዜያዊ "የአንካራ መግለጫ" ላይ ተደርሷል። በዚህም ሁለቱም ወገኖች በቴክኒካዊ ንግግሮች ለመሳተፍ እና እርስ በእርስ የየብስ ወሰን ክብርን ለመጠበቅ ቃል ገብተው ነበር።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
24😁6
አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን የምትሰጠውን ቪዛ ቆይታ ወደ ሦስት ወር አሳጠረች!

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ቪዛ የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ማጠሩን አስታወቀ።ኤምባሲው ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 3/2017 ዓ.ም. በኤክስ ገፁ ባሰፈረው መረጃ፤ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስደተኛ ባልሆኑ የቪዛ አመልካቾች ላይ ባደረገው የፖሊሲ ለውጥ ምክንያት ውሳኔው መተላለፉን ገልጿል።

በአዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፖሊሲ መሠረት፤ "ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵውያን የሚሰጠው ቪዛ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል እና የሦስት ወር ቆይታ" እንደሚኖረው አስታውቋል።ኤምባሲው በዚሁ የኤክስ ገጽ ልጥፉ ላይ ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. በፊት የተሰጡ ቪዛዎች ባሉበት እንደሚቀጥሉ ገልጿል።

ለንግድ እና ለጉብኝት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ቪዛ "B1" እና "B2" በሚለው ምድብ ውድብ ውስጥ ይካተታል።እስካሁን በነበረው አሰራር በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገቡ ተጓዦች የሚያገኙት ቪዛ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ነበር። በተጨማሪም የቪዛው የቆይታ ጊዜ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ያስችል ነበር።

አሁን ይፋ የተደረገው ፖሊሲ የቪዛውን የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ከማሳጠር በተጨማሪ በአንድ ቪዛ ተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ መግባትን ከልክሏል።በአዲሱ ፖሊሲ ቪዛ የሚያገኙ ተጓዦች የቆይታ ጊዜ ባይጠናቀቅም እንኳ ከአሜሪካ ከወጡ በኋላ በዚያው ቪዛ ተመልሰው መግባት አይችሉም።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተለያዩ አፍሪካ አገራትን ቪዛ የቆይታ ጊዜን ወደ ሦስት ወራት ማሳጠሩን ይፋ ያደረገው በትናንትናው ዕለት ነበር። ይህ ውሳኔ ከተላለፈባቸው ሀገራት መካከል ናይጄርያ እና ጋና ይገኙበታል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
28👎11😁3😭2🔥1
"ኢትዮጵያ በማንኛውም ሁኔታ ከኤርትራ ጋር ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት የላትም" -የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በወቅታዊ የስራ ክንውኖቹ ዙሪያ ለሀገር ውስጥና መቀመጫውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነበያት ጌታቸው የኤርትራና የኢትዮጵያ አሁናዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና ወቅታዊ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

ቃል አቀባዩ ለዚሁ ለቀረበላቸው ጥያቄ <<ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር በማንኛውም ሁኔታ ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የላትም>>ሲሉ አጭር ምላሽ በመስጠት ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት መታቀባቸውን አሻም በታደመችበት ታዝባለች።

በተመሳሳይ ከሰሞኑ በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ የተካሄደውና ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት የብሪክስ ጉባኤ መካሄዱን ያስታወሱት ነብያት ፤ ብሪክስ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ያደረገና ያስተዋወቀ መድረክ ነውም ብለዋል።

በሌላ በኩል በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ከ131ሺህ በላይ የሚሆኑና በተለያዩ ሀገራት በተለይም በመካከለኛው እና ሩቅ ምስራቅ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት መንግስት መመለሱን አምባሳደር ነብያት አስታውቀዋል።

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
😁2214🔥2👍1
የሁቲ አማጽያን በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለተኛውን የቀይ ባህር የጭነት መርከብ አሰጠሙ!

የየመን ሁቲዎች በጉዞ ላይ የነበረ የጭነት መርከብ ላይ ጥቃት ከፈጸሙ እና መርከቡ ቀይ ባህር ውስጥ ከሰጠመ በኋላ ስድስት መርከበኞች መትረፋቸውን እና ቢያንስ ሦስት ሌሎች ሰዎች መሞታቸውን የአውሮፓ የባህር ኃይል ተልዕኮ አስታወቀ።የላይቤሪያን ባንዲራ የሚያውለበልበው እና በግሪክ የሚንቀሳቀሰው 'ኤተርኒቲ ሲ' የተባለው የጭነት መርከብ 25 ሠራተኞችን ይዞ እየተጓዘ ነበር።

መርከቡ ሰኞ ዕለት ከትንሽ ጀልባዎች በተተኮሱ የሮኬት ቦምቦች ከተመታ በኋላ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በዚህም የመንቀሳቀስ አቅሙን እንዳጣ የእንግሊዝ የባሕር ንግድ ሥራዎች ኤጀንሲ (UKMTO) ገልጿል።ጥቃቱ ማክሰኞ ዕለትም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን መርከበኞቹን የማዳን ሥራ የተጀመረው ሌሊት ላይ ነው።

በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎች፤ ኤተርኒቲ ሲ ላይ ጥቃት የፈጸሙት ወደ እስራኤል እየተጓዘ ስለነበረ እንደሆነ አስታውቀዋል።ቁጥራቸው ያልታወቀ ሠራተኞችንም "ደህንነቱ ወደ የተጠበቀ ቦታ" እንደወሰዱ ተናግረዋል።በየመን የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሁቲዎች "በሕይወት የተረፉ የቡድን አባላትን አፍነው መውሰዳቸውን" ገልጾ፤ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርቧል።

የፊሊፒንስ ባለስልጣናት ከቡድኑ አባላት ውስጥ 21 ያህሉ ዜጎቻቸው እንደሆኑ ተናግረዋል።ከቀሪዎቹ መካከል አንዱ የሩስያ ዜግነት ያለው እንደሆነ እና በጥቃቱ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት እግሩን እንዳጣም ተገልጿል።ሁቲዎች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይህንን ዓይነቱን ጥቃት ሲፈጽሙ ይህ ሁለተኛቸው ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
25😭10👍2
1.7 ሚሊዮን ሱዳናውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ተባለ!

የሱዳን ጦር ማዕከላዊ ግዛቶችን ከተቆጣጠረ በወዲህ 1.7 ሚሊዮን ሱዳናውያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት አስታውቋል።ወደ ቀያቸው ከተመለሱት 1.7 ሚሊዮን ሱዳናውያን ውስጥ፤- 1.5 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሲሆኑ፤ 200,000 የሚሆኑት ደግሞ ወደ ሌሎች ሀገራት የተሰደዱ ናቸው።

ስደተኞቹ የተመለሱት የሱዳን ጦር ሴናር ፣ ገዚራ እና ካርቱም ግዛቶችን ከተቆጣጠረ ወዲህ መሆኑን ከፓሪስ ሱዳን ትሪቡን ድረ-ገጽ ትናንት ዘግቧል።"አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) እና UNHCR ትናንት እንዳስታወቁት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሲሆኑ200,000 የሚጠጉ ስደተኞች ደግሞ ከግብፅ እና ደቡብ ሱዳን ወደ ሀገራቸው ሱዳን ተመልሰዋል" ሲል ድረ-ገጹ ዘግቧል።

በሀገሪቱ ያለው የተፈናቃዮች ቁጥር ጦር ሠራዊቱ ሴናር፣ ገዚራ እና ካርቱም ግዛቶችን ከተቆጣጠረ በኋላ በ13 በመቶ ቀንሷል ተብሏል።በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ 2023 ዓ/ም በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ እና በሱዳን ጦር መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ከ12 ሚሊዮን በላይ ሱዳናውያን ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓል።ከነዚህ መካከል ዘጠኝ ሚሊዮን የሚሆኑት በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጠቅሶ ዘገባው አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
24
የትግራይ ኦርቶዶክስ አባቶች የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ንግግር እና በትግራይ ህዝብ ሁኔታ ላይ ያላቸው ግምገማ እንዳሳሰባቸው ገለጹ!

የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በፓርላማ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር እንዳሳሰባቸው ገለጹ። የጠ/ሚኒስትሩ ንግግር በጦርነት በተጎዳው ክልሉ ውስጥ ያለውን የሰላም ሂደት ሊያዳክም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

የሃይማኖት መሪዎቹ፤ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ሁኔታ ግምገማ ከሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር የሚገናኝ አይደለም” ሲሉ ገልጸው፣ እንዲህ ያለው አለመጣጣም ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ሊያባብሰው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

የሃይማኖት መሪዎቹ ረቡዕ ባወጡት መግለጫ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦታው ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እውነታዎች መረዳትን በተመለከተ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ስጋት እየጨመረ መምጣቱንም ገልጸዋል።

ቤተክርስቲያኗ የሽማግሌዎች ልዑክ በቀጥታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዲገናኝ እንደምትልክ አስታውቃለች። መግለጫው እንደገለጸው፤ የስብሰባው ዓላማ የትግራይን ሕዝብ ስጋት ለማሳየት እና ለሰላም ሂደቱ የበለጠ ምላሽ ሰጪ እና ውጤታማ አቀራረብን ለመደገፍ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
29👎21👀2
የጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኤም ፖክስ ተይዘው የነበሩ ስዎች ሙሉ በሙሉ ማገገማቸውን አስታወቀ!

ሚንስቴሩ ግንቦት 16 በበሽታው የተያዘ የመጀመሪያውን ታማሚ መገኘቱን ይፋ ካደረገ በኋላ እስከ ሐምሌ 2 ድረስ ለ520 በበሽታው ለተጠረጠሩ ሰዎች የላብራቶሪ ምርምራ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበሽታው ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በምርመራው 26 ሰዎች በሽታው እንደተያዙ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡በተጨማሪም አንድ ታማሚ በበሽታው ህይወቱ አልፏል፣ ቀሪዎቹ 25 ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ ከበሽታው ማገገማቸውን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ህብረተሰቡ ለበሽታው አጋላጭ ከሆኑ መንገዶች በመጠንቀቅ እና የመከላከያ መንገዶችን ችላ ሳይል በመተግበር የበሽታውን ስርጭት በዘላቂነት እንዲገታ ጥሪ አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
29😁3👍1
የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በሚመለከት የገባችዉን የቃል ማረጋገጫ በጽሑፍ ስምምነት እንድታጠናክር ግብፅ ጠየቀች!

ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ  የሰጠቻቸውን የቃል ማረጋገጫዎች በጽሑፍ ስምምነት እንድትደግፍ ግብፅ ጠየቀች። ይህ ጥያቄ የመጣው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግድቡ በመስከረም ወር እንደሚመረቅ ከገለጹ በኋላ ነው።

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ፣ በቅርቡ ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን ከአብይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውን ጠቁመዋል።

በብሪክስ ስብሰባ ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ግድቡን “ግብፅንና ሱዳንን ሳይጎዳ” የማጠናቀቅ እና ትብብርን የመቀጠል ፍላጎታቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ ማድቡሊ፣ እነዚህ የቃል ማረጋገጫዎች በሁለቱ ሀገራት ወይም በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ያለውን የወደፊት ግንኙነት በሚያደራጅ የጽሑፍ ሰነድ ውስጥ መተርጎም አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “የግብፅ አቋም በፍጹም አልተለወጠም፤ በአባይ ውሃ ድርሻዋ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዲደርስ አትፈቅድም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ግብፅ የልማት ተቃዋሚ ባትሆንም፣ በአባይ ውሃ ላይ ያላትን ህጋዊ መብት እንደምትጠብቅም አስረድተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
33😁18👎11
የኢትዮጵያ ብር በሩሲያ የባንክ ምንዛሬ ውስጥ ተካተተ!

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ሌሊት ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ የኢትዮጵያን ብር በምንዛሬ ዝርዝር ውስጥ አካቷል።ይህም ማለት ብርን ወደ ሩብል እንዲሁም ሩብልን ደግሞ ወደ ብር መመንዘር የሚያስችል ዕድልን ይሰጣል።

በዚህም መሰረት ባንኩ ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57.5872 ሩብል ወይም ለ1 ብር 0.575872 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧል።ባንኩ ለኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ ተመን የኮድ ቁጥር 230 የሰጠ ሲሆን በየዕለቱም የምንዛሬ ተመኑን የሚያሳውቅ ይሆናል።

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ የ12 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱን ከቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
45👍15👀6😭4🔥31
"የትምህርት ቤቶች ግንባታ ምርጫ በዘርና ፖለቲካዊ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የነበረ ቢሆንም ይህንን የሚያስቀር አሰራር ተዘርግቷል" - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ባለፉት ዓመታት በነበረው አሰራር የትምህርት ቤቶች ግንባታ ምርጫ የሚወሰነው በገለልተኝነትና በበቂ መረጃ ሳይሆን በዘር፣ በትውወቅና ፖለቲካዊ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ነበር ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው፣ ይህን ለማስቀረት የትምህርት ቤቶችን ሥርጭት የሚያሳይ የዲጂታል ካርታ አዘጋጅቷል ብለዋል፤ በአገሪቱ ተመጣጣኝና ፍትሃዊ የትምህርት ዘርፍ ልማትን ለማምጣት እየተሰራ ነው ሲሉም አስታወቀዋል።

በሀገሪቱ ተመጣጣኝ የሆነ የትምህርት ዘርፍ ልማትን ለማምጣት ትምህርት ቤቶች ግልጽና ትክክለኛ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ እንዲገነቡ የሚያስችል ዲጅታል የትምህርት ቤቶች ስርጭት የሚያሳይ ካርታ ተዘጋጅቷል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።አክለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የትምህርት እድል ማግኘት እንዳለበት አንስተው ለሁሉም ዜጎች ትምህርትን በፍትሃዊነት ለማድረሰ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የትምህርት ቤቶች ስርጭት ካርታ ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃው የትምህርት ቤቶችን ወቅታዊ ስርጭት፣ የመሰረተ ልማት፣ የህዝብ ብዛት እና ሌሎች መረጃዎችንም አካቶ የያዘ መሆኑን ተጠቁሟል።በመሆኑም ለጋሾችም ሆኑ ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻዎች መረጃውን በመጠቀም ትምህርት ቤቶችን መገንባትና የድርሻቸውን ማበርከት እንደሚችሉ ተገልጿል።በዚህ የትምህርት ስርጭት ካርታ ትምህርት ቤቶቹ የሚገነቡት በተዘጋጀው ስታንዳርድ መሰረት ሲሆን የት ይገነባሉ የሚለውን ምላሽ የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
33👎8😁6👍1🔥1