YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በዎላይታ ዞን ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሽራተት አደጋ የ7 ወገኖች ሕይወት አለፈ!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በላሾ እና 01 ቀበሌዎች የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሽራተት አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ እንዳስታወቀው በወረዳው በሁለቱም ቀበሌ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ 2 ወንድ 5 ሴት በድምሩ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ከሟቾች በተጨማሪ አንድ ወንድና አንድ ሴት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በንብረት ላይም ጉዳት መደረሱ ተገልጿል።ከዚህ ቀደም በዞኑ ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወቃል።

በተመሳሳይ መልኩ በክልሉ ሀምሌ 15፣ 2016 #ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት መለፉም አይዘነጋም።

@YeneTube @FikerAssefa
😭22👍113👀1