YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአሜሪካ ኢንባሲ ማስጠንቀቂያ ለኢትዮጵያውያን።

በቪዛዎ ከተፈቀደሎት ጊዜ በላይ ከቆዩ ወደፊት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ ቋሚ እገዳ ሊጣልቦትና በህግ ሊያስጠይቅ ይችላል።
የቆንስላ ኦፊሰሮች የኢሚግሬሽን ሙሉ ታሪክዎን ማግኘት ይችላሉ።  በተጨማሪም ከዚህ በፊት የተላለፉት የኢሚግሬሽን ሕግ ጥሰቶች ካሉም የቆንስላ ኦፊሰሮች ያውቃሉ።
ቪዛዎን በትክክል መጠቀም የእርስዎ ኃላፊነት ነው"ብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍29😭10👎3😁32
በምሥራቅ ጎጃም በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ታወቀ


(T.me/Yenetube) - ፈጣን የዜና ምንጭ

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሐሙስ ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም. በትምህርት ቤት ዙሪያ በደረሰ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።

በዞኑ እናርጅ እናውጋ ወረዳ ገደብ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ የትምህርት ቤት አጥር ለማጠር እና ቤት ለመሥራት 'ለልማት ሥራ' የወጡ "ሰላማዊ ሰዎች" በጥቃቱ መገደላቸውን ገልፀዋል።

የአካባቢው አስተዳደር ግን ጥቃቱ በአካባቢው ተሰብስበው በነበሩ የፋኖ ታጣቂዎች ላይ እንጂ በንፁሃን ነዋሪዎች ላይ አለመፈጸሙን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈጸመ ስለተባለው ጥቃት ክትትል እያደረገ መሆኑን አመልክቷል። ነዋሪዎች እንደተናገሩት "ተሰብስበው" በከተማዋ ያለው ገደብ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አጥርን እያጠሩ በነበሩ የሰዎች ላይ ነው ጥቃቱ የተፈፀመው።
ጥቃቱ በተፈፀመበት አካባቢ በቅርብ ርቀት ላይ እንደነበሩ የተናገሩ ሌላ የዓይን እማኝ ወዲያው ጩኸት፣ ግርግር እና ድንጋጤ መፈጠሩን ጠቁመው "የሆነውን አናውቀውም" ሲሉ በቅፅበቱ የነበረውን ሁኔታ ገልፀዋል። እሳቸውን ጨምሮ ሥራ ላይ የነበሩ ሰዎች ጥቃቱ ወደተፈፀመበት አካባቢ ሲጠጉ "ሰው የሚባል አይለይም" ሲሉ ስለ ጉዳቱ ተናግረዋል።

"እንዳለ በሙሉ ጥቁር ነገር ነው የሆነው። አካባቢው በሙሉ ሰው የሚባል ነገር የለም። ከወደቀው ውስጥ የሚጮህ አለ፤ የሚንከባለል አለ። የተፈጠረው ነገር ይዘገንናል። ሰው ለሆነ እጅግ የሚዘገንን ድርጊት ነው" ብለዋል።

የፈረሰውን የትምህርት ቤቱን አጥር እያጠሩ እያለ ቀኝ እጃቸውን ተመትተው መቁሰላቸውን የተናገሩ ሌላ ነዋሪ "ከባድ ፍንዳታ" መከሰቱን ጠቅሰው "ብዙ ሰው ነው የተጎዳው" ብለዋል።

"ባሕር ዛፍ የሚቆርጥ፤ ሚስማር የሚመታ አለ፤ ማገር የሚቆርጥ አለ፤ የሚይዝ አለ" ሲሉ ማኅበረሰቡ መሰባሰቡን የገለፁ ሌላ የዓይን እማኝ የሟቾቹን ቁጥር "ብዛት ይኖረዋል" በማለት ገልፀዋል። አስከሬን ስለማንሳታቸው የተናገሩ ሌላ እማኝ ደግሞ አብዛኛው የጥቃቱ ተጎጂዎች ወዲያው ሕይወታቸው ማለፉን ገልፀው፤ ሟቾቹ በአብዛኛው ወጣቶች ናቸው ብለዋል።

ከ24 በላይ ቁስለኞችንም ወደ ሕክምና መወሰዳቸውን የገለፁት እማኞች፤ አብዛኞቹ በከተማዋ ወደሚገኘው ገደብ ጤና ጣቢያ ከደረሱ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ከ70 በላይ አስከሬን አንስተው በባጃጅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ማመላለሳቸውን የተናገሩ አንድ የዓይን እማኝ፤ ታዳጊዎችን እና ሽማግሌዎችን ጨምሮ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 120 እንደሚደርስ ገልፀዋል። "ከ115 እስከ 120 የሚሆን አስከሬን ነው የተቀበረው። ያልታወቀም ይኖራል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ድንጋጤ ውስጥ ስለነበርን" ብለዋል።

ሌላ የዓይን እማኝ በበኩላቸው 57 አስከሬን እስከሚነሳ ድረስ እንደነበሩ ጠቁመው የሟቾቹ ቁጥር ከ100 በላይ እንደሚሆን ገምተዋል። አስከሬኖቹ ላይ ከባድ ጉዳት በመድረሱ ሟቾችን መለየት ከባድ እንደነበር የተናገሩት እማኞች በዚህ ምክንያት እና በስጋት እስከ ቀትር 08፡00 ድረስ ገደብ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በጅምላ እንደተቀበሩ ገልፀዋል።

"አሞራ እንዳይበላቸው ቅበሩ ሲባል ማኅበረሰቡ በፍጥነት አምስት የሚሆን መቃብር ውስጥ ነው የቀበራቸው" ሲሉ አንድ ነዋሪ ተናግረዋል።

የመንግሥት ኃይሎች ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ተከትሎ ስጋት ያደረባቸው አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች መሸሸታቸውን የተናገሩ አንድ ነዋሪ፤ ተጨማሪ ጥቃቶች መፈፀማቸውንም ጠቁመዋል።

ማኅበረሰቡ ከተረጋጋ በኋላ ለሟቾቹ ድንኳን እንደተጣለ እና ከቀናት በኋላ በአካባቢው "ፍራጅ" የሚባለው ማስተዛዘኛ መርሃ ግብር እንደተደረገም ነዋሪዎች ተናግረዋል። "ሰሞኑን ሲሸበር ነበር። ሕዝቡ በሙሉ ሽብር ላይ ነው ያለው" ሲሉ ዳግም የድሮን ጥቃት ይደርሳል በሚል የፋሲካ በዓልን በስጋት ማሳለፋቸውን "በዓል የሚባል ነገር የለም" ብለዋል።

"ከባድ ሐዘን ውስጥ ነው ያለው። በዓል ምንም አይመስልም ነበር። ለበዓል ከከተማ የሚመጡ ልጆች አልመጡም" ሲሉ አካባቢው በሐዘን ድባብ ውስጥ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ግጭት በ2015 ዓ.ም. መጨረሻ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከተማዋ በፋኖ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር እንደሆነች ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ ሲፈፀም ግን የፋኖ ታጣቂዎች ከተማዋ ውስጥ እንዳልነበሩ እና በአካባቢው ግጭት እንዳልነበረ ጠቁመዋል።

ታጣቂዎቹ "አንዳንድ ሥራ ለመሥራት ካልመጡ በቀር ከተማው ውስጥ አይታዩም" ሲሉ አንድ ነዋሪ ተናግረዋል።
ነጋዴ እንደሆኑ የተናገሩ አንድ የዓይን እማኝ ሟቾቹ ንፁሃን ስለመሆናቸው ሲናገሩ "በርካቶቹን በንግድ ሥራቸው" የሚያውቋቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

"የፋኖ አባላት ቢሆኑ [አስከሬን ሲነሳ] ታጣቂ እናገኝ ነበር። ፋኖዎችን እና ማኅበረሰቡን [ለይተን] እናውቃቸዋለን። [ፋኖዎች] በአንድ ላይ ነው የሚንቀሳቀሱት" ሲሉ ሌላ ነዋሪ ተናግረዋል።

ሌላ ነዋሪ በበኩላቸው "የተሰበሰው አጥር የሚያጥረው እና ቤት የሚሠራው ሰው በቀረፃው [የድሮን ቅኝት] የፋኖ ስብስብ ነው ተብሎ ታስቦ ይሁን ያወቅነው ነገር የለም። ምንአልባት ሲሰበሰብ ፋኖ ነው ተብሎ ታስቦ [ይሆናል] እንደዚያ ነው እኛ የተረዳነው" ሲሉ ጥቃት ሊፈጸም የቻለበትን ምክንያት ግምታቸውን ገልፀዋል።

የእናርጅ እናውጋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሙሉ ጌቴ ንፁሃን ሰዎች ተገደሉ መባሉን "የጠላት ወሬ" ያሉ ሲሆን፤ እርምጃው "ፅንፈኛ" ያሏቸው የፋኖ ታጣቂዎች ላይ መወሰዱን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"እዚህ አካባቢ ቁጥሩ በርከት ያለ የኃይል ስብስብ አለ። ሰብስበው ሥልጠና ጭምር [እንደሚሰጡ] መረጃው አለኝ። የትምህርት ቤት አጥር፤ ቤት ሥራ የሚባለው ነገር ማሳመሪያ ነው . . ." በማለት ንፁሃን በፍንጣሪም ቢሆን አልተገደሉም ሲሉ አስተባብለዋል።

የፋኖ ታጣቂዎች በበኩላቸው በወረዳው በስፋት እንደሚንቀሳቀሱ ጠቁመው ገደብ ከተማ አካባቢ ላይ ግን በወቅቱ "ምንም ዓይነት የታጠቀ ኃይል" አልነበረም በማለት በጥቃቱ የተገደለ አባል እንደሌላቸው ተናግረዋል።

አካባቢውን ለሥልጠና እንደማይጠቀሙት የተናገሩት የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢ አቶ አስረስ ማረ ዳምጤ "ሁሉም ግድያው የተፈፀመባቸው ሲቪሊያን ናቸው። አንድም የታጠቀ ኃይል በቦታው ላይ አልነበረም" በማለት ግድያውን ማኅበረሰቡን ከማሸበር ጋር አያይዘውታል።

ምንጭ: ቢቢሲ አማርኛ

@Yenetube @Fikerassefa
😭66👍508👀3
ራሺያ ለቡርኪናፋሶ

የቡርኪናፋሶ መሪ በሆነው ኢብራሂም ትራኣሬ ላይ ከቀናት በፊት ለ19ኛ ጊዜ የተቀነባበረ የግድያ ሙከራ መደረጉን ተከትሎ ትራኦሬ ለራሺያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስቸኳይ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲደረግለት መጠየቁን እና ራሺያም የጦር መሳሪያ በአስቸኳይ ወደ ቡርኪናፋሶ ለመላክ ቁርጠኛ መሆኗን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

(T.me/Yenetube) ፈጣን የዜና ምንጭ

የግድያ ሙከራው በፈረንሳይ የሚደገፍ በመሆኑ እና በሀገሪቱ የታጠቁ ቡድኖች ከፍተኛ ስጋት መፍጠራቸውን ተከትሎ ራሺያ ለቡርኪናፋሶ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ ይጠበቃል።
ራሺያ እና ቡርኪናፋሶ በባለፈው ጥቅምት ወር በወታደራዊ ጉዳዮች በትብብር ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ነው።
ትራኦሬ "ሀገሬ እና ህዝቤ ነፃ እስከሚወጣ ድረስ እዋጋቸዋለሁ" ብለዋል።


@Yenetube @Fikerassefa
👍12115🔥9
በትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት አለፈ!

በምዕራብ አርሲ ዞን ኔጌሌ አርሲ ወረዳ ራፉ ሃርጊሳ ቀበሌ በደረሳ የትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት ሲያልፍ በ22 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አካል ጉዳት ደረሰ፡፡

አደጋው የደረሰው፤ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ተሳቢ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በማጋጨቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አደጋውን ተከትሎም ከሟቾች በተጫመሪ በ16 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ6 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኔጌሌ አርሲ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
😭56👍171
Forwarded from HuluPay Community
🔥 በTelegram ላይ የተረጋገጠ ምልክት (Verified Checkmark) ለማግኘት የእርስዎን አካውንት አሁን Premium ያድርጉት

Telegram Premium በመግዛት የተረጋገጠ ምልክት ያግኙ!

አስደናቂ ፊቸሮችን ያግኙ!
- 4GB እስከሆኑ ፋይሎችን ይጫኑ
- በፍጥነት ያውርዱ
- የእርስዎን online status ከሌሎች ይደብቁ
- እስከ 4 accounts ድረስ ይጠቀሙ
- ልዩ ስቲከሮች እና ኢሞጂዎች 🎭
- የድምፅ መልእክቶችን ጽሁፍ ያድርጉ
- ልዩ badges ያግኙ
- ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ
አሁኑኑ ይቀላቀሉ እና የእርስዎን Telegram ተሞክሮ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩ! 🚀

📲 ሁሉፔይን ለመጠቀም ሁሉፔይ ሚኒ አፕን
https://tttttt.me/HuluPayOfficialBot/start?startapp እዚህ ሊንክ ጋር ያገኛሉ 🔗

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍122
Forwarded from In Africa Together
🌏IAT & IAIC INTERNATIONAL STUDENT FAIR🌎

Ready to study abroad and change your life?

🎓This is your chance to meet top university representatives from:

USA 🇺🇸 Canada 🇨🇦 Sweden 🇸🇪
Germany 🇩🇪 France 🇫🇷 Finland 🇫🇮 Denmark 🇩🇰 and more!

📆 May 3 & 4
🕐 3:00 - 10:00 (LT)
📍Ghion Hotel

Don’t forget to bring:
🪪Passport or Birth certificate
📚Transcripts or Student copy

Entrance Fee: FREE!!

💡Opportunities:
- Study loan options
- Learn about the scholarships offered

🏆Don’t miss this golden opportunity to take your future global!

🆓No entrance fee — just register now!

Click the link below to book your spot: 🔗
https://forms.gle/81ZueGK5d9R9Cg9P6
👍2
Forwarded from YeneTube
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍4
‹‹አሥር ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ረሃብ ተጋርጦባቸዋል››  የዓለም የምግብ ፕሮግራም

አሥር ሚሊዮን ኢትዮጵያን ረሃብ እንደተጋረጠባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

በመላው ኢትዮጵያ ለከፋ ረሃብ ከተጋለጡት ውስጥ ሦስት ሚሊዮን ያህሉ በግጭትና በአየር ፀባይ መለዋወጥ (Extreme Weather) ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በየመጠለያው ሲረዱ የነበሩ ናቸው ብሏል፡፡

የድርጅቱ ነፍስ የማዳን ተግባራት አቅም በመዋዕለ ንዋይ እጥረት የተነሳ እጅግ መዳከሙን ያወሳው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ከአሥር ሚሊዮን ረሃብተኞች 3.5 ሚሊዮን ያህሉ እጅግ ተጠቂ ተብለው የተያዙና ዕርዳታ ከእነ አካቴው ሊቋረጥባቸው እንደሚችል አስታውቋል፡፡

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ ከፈረሰ በኋላ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታ የማድረስ አቅሙ በእጅጉ እንደተጎዳ በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
😭30👍8😁21
በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት ጌሾ ወንዝ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ዛሬ ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም 18 ሰው የጫነ ሚኒባስ ታክሲ ዋናውን መንገድ ስቶ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ በተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ 18 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እንዳስታወቀው ከሆነ፤ ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች በኮሚሽኑ አምቡላንስ እና በፖሊስ አምቡላንስ ወደ አቤት ሆስፒታልና አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ተወስደው ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋ ጥሪዉ ለኮሚሽን መ/ቤቱ እንደደረሰ የአምቡላንስ አገልግሎት ቡድኑ በስፍራዉ ፈጥኖ በመድረስ በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች የከፋ ጉዳት ሳይደርስባቸዉ በሕይወት በማውጣትና የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና በመስጠት ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ማድረጉም ነው የተገለጸው።

ጉዳት ከደረሰባቸው ተጎጂዎች መካከል አንድ ነፍሰ ጡር ሴትና ወደትምህርት ቤት እየሄዱ ያሉ ተማሪዎች እንደሚገኙበት ያስታወቀው ኮሚሽኑ፤ የአደጋውን መንስዔ እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ፖሊስ እያጠራ እንደሚገኝ ገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍46😭265
የሪፖርተር ጋዜጠኛ ታሰረ!

የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር ታሰረ፡፡ጋዜጠኛ አበበ የታሰረው ትናንት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት አካባቢ ነው፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው ከልደታ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎች መረጃ በማሰባሰብ ላይ እያለ ሲሆን፣ የታሰረበት ምክንያት እስካሁን ግልጽ አልሆነም፡፡ ጋዜጠኛ አበበ በዕለቱ በፖሊሶች ተይዞ ከመወሰዱ በስተቀር በወቅቱ ወዴት እንደተወሰደና እንደታሰረ ባለመታወቁ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት በማድረግ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባደረገው ትብብር ጋዜጠኛው በልደታ ክፍል ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጌጃ ሰፈር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ታውቋል፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው እየሠራው ለነበረው ዘገባ ሚዛኑን ለመጠበቅ፣ የክፍለ ከተማውን ኃላፊዎች ለማነጋገር በሥፍራው በተገኘበት ወቅት ነበር፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👎21👍15😭9
በአዲስ አበባ የመሬት ሊዝ 5ኛ ዙር ጨረታ ከፍተኛው ዋጋ በካሬ 265 ሺህ ብር ተመዘገበ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ባካሄደው 5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል።

በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች ለ427 ፕሎቶች ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ጨረታ በአንድ ካሬ ሜትር ከፍተኛው ዋጋ 265 ሺህ ብር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተመዝግቧል።

የጨረታ ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ እንደገለጹት፣ በዚህ ዙር ጨረታ ከፍተኛ ተወዳዳሪነት የታየ ሲሆን፣ በተለይም ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎች ከፍተኛ ዋጋ ተሰጥቷቸዋል

ይህ ውጤት ከዚህ ቀደም ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በአስር ክፍለ ከተሞች በተካሄደው በ4ተኛዉ ዙር የሊዝ ጨረታ ከነበረው ከፍተኛ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው።  በወቅቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አንድ ካሬ ሜትር መሬት በ306 ሺህ 600 ብር ከፍተኛ ዋጋ ተመዝግቦ እንደነበር ካፒታል መዘገብ ይታወሳል። በንፅፅሩ ዝቅተኛው ዋጋ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 12 ሺህ 320 ብር ነበር።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍40👎83🔥2👀1
Forwarded from HuluPay ️⭐️
🔥 10% (እስከ 500 ብር) ኮሚሽን ወዲያውኑ አግኙ! 🔥

ጓደኞቻችሁ ቴሌግራም ፕሪሚየም መግዛት ይፈልጋሉ! አሁኑኑ ጋብዟቸው እና በእያንዳንዱ ግዢ ላይ 10% ኮሚሽን አግኙ። 💰🚀 ለመላክ ይጫኑ!
👍32🔥1
🌏IAT & IAIC INTERNATIONAL STUDENT FAIR🌎

Ready to study abroad and change your life?

🎓This is your chance to meet top university representatives from:

USA 🇺🇸 Canada 🇨🇦 Sweden 🇸🇪
Germany 🇩🇪 France 🇫🇷 Finland 🇫🇮 Denmark 🇩🇰 and more!

📆 May 3 & 4
🕐 3:00 - 10:00 (LT)
📍Ghion Hotel

Don’t forget to bring:
🪪Passport or Birth certificate
📚Transcripts or Student copy

Entrance Fee: FREE!!

💡Opportunities:
- Study loan options
- Learn about the scholarships offered

🏆Don’t miss this golden opportunity to take your future global!

🆓No entrance fee — just register now!

Click the link below to book your spot: 🔗
https://forms.gle/81ZueGK5d9R9Cg9P6
2👍2
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍7
በአውሮፓ ውስጥ በቱጃሩ ሰው የፖለቲካ አመለካከት የተነሳ የቴስላ ተሽከርካሪ ሽያጭ 28.2 በመቶ ቀንሷል ተባለ

በአውሮፓ ውስጥ አዲስ የመኪና ሽያጭ ከአንድ አመት በፊት በመጋቢት ወር ከነበረው 28.2 በመቶ ቀንሷል ፣ ምንም እንኳን አጠቃላይ የባትሪ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሽያጭ በወር ውስጥ 23.6 በመቶ እንደጨመረ የአውሮፓ አውቶሞቢል አምራቾች ማህበር (ኤሲኤኤ) መረጃ አሳይቷል። በአውሮፓ ውስጥ አጠቃላይ አዲስ የመኪና ሽያጭ በወር ውስጥ 2.8% ከፍ ብሏል ፣ በብሪታንያ እና በስፔን ባለሁለት አሃዝ ዝላይ ጭማሪ አሳይቷል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ትርፍ መጨመር የነዳጅ እና የናፍታ መኪናዎች ውድቀትን እንደሚያካክስ መረጃው አመላክቷል።

በአውሮፓ የቴስላ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የሽያጭ ማሽቆልቆል ከቻይና ጋር ያለው ፉክክር እየበረታ እና አንዳንዶች በፖለቲካዊ አመለካከቱ ላይ ተቃውሞ በማሳየታቸው አሽከርካሪዎች የኤሎን ማስክን የኤሌክትሪክ መኪና ከመግዛት እየተቆጠቡ ይገኛል። አውሮፓውያን መኪና ሰሪዎችም ከቻይና ጋር ያለውም ፉክክር እየታገሉ ሲሆን በሀገር ውስጥ ገበያ ከፍተኛ ወጪን ቢኖርም ዋሃውን ለማውረድ እየተዋጉ ይገኜል። አሁን ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በአውቶሞቢሎች ላይ የጣሉት የ25 በመቶ ታሪፍ ጋር በመታገል ለኢንዱስትሪው ያለውን ፈተና ይበልጥ አስከፊ አድርጎታል።

በአውሮፓ ህብረት ፣ በብሪታንያ እና በአውሮፓ ነፃ ንግድ ማህበር የመጋቢት ወር ሽያጮች ለሁለት ወራት ከነበረበት መቀዛቀዝ በኋላ ወደ 1.42 ሚሊዮን መኪናዎች ከፍ ብሏል ሲል የአውሮፓ አውቶሞቢል አምራቾች ማህበር (ኤሲኤኤ) መረጃ አሳይቷል በቮልስዋገን እና ሬኖ የተመዘገቡት የተሽከርካሪ ሽያጭ በ10.3 በመቶ እና 13 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በአውሮፓ የቴስላ ሽያጭ ለሶስት ተከታታይ ወር ቀንሷል። ከዓመት በፊት ከነበረበት 28.2 በመቶ ሲቀንስ የጠቅላላ ገበያ ድርሻው ከአንድ አመት በፊት ከነበረበት 2.9 በመቶ ወደ 2 በመቶ ቀንሷል።

ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍257
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ “ከቀያቸው ተፈናቅለው በአስከፊ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን መመለስ ነው” - ፕሬዚደንት ታደሰ ወረደ

በትግራይ ክልል ከቀያቸው ተፈናቅለው በከፋ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የመመለስ ጉዳይ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ ነው ሲሉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያስታወቁት የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት መከታተል፣ ማረጋገጥና ማክበር ተልእኮ ከፍተኛ ሀላፊ ሆኖው የተመደቡትን ሜጀር ጀነራል ሳማድ አክሶዴ ትላንት ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዚደንቱ አክለውም ተፈናቃዮችን ለመመለስ፣ የትግራይ ሰራዊት ወደ ህብረተሰቡ የማቀላቀልና መልሶ የማቋቋም በአጠቃላይ በፕሪቶርያው ስምምነት አፈፃፀም ዙርያ ከፌደራል መንግስት ጋር በመቀራረብ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ሜጀር ጀነራል ሳማድ አክሶዴ በበኩላቸው በፕሪቶርያው ስምምነት አፈፃፀም፣ ተፈናቃዮች መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በዲዲአር አፈፃፀም ሂደት ለመወያየት መምጣታቸውን በመጠቆም ለፕሪቶርያው ስምምነት የተሟላ ትግበራ የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚሰሩ መግለፃቸውን የፕሬዝዳንቱ የጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍44😁52
አሜሪካ " ነገር አለ ! " ብላለች !

ባልታሰበ ሰዓት የሚከሰት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ስላለ። አሜሪካ U.S. Embassy Addis Ababa በአዲስ አበባ ችግሮች ስለሚከሰቱ ራሳችሁን ጠብቁ ብላ ዜጎቿን አስጠንቅቃለች። ወንጀል በየትኛውም ቦታ እና በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት ይችላል; ንቃት ተጋላጭነትን ለመቀነስ ቁልፍ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያ ያላችሁ ዜጎቼ ተጠንቀቁ ፤ ነገር አለ ብላለች። ሰልፎችን፣ ስብሰባዎችን እና ሌሎች ትላልቅ የህዝብ ስብስቦች ባሉበት ቦታ እንዳትገኙ ስትል ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለዜጎቿ ሰታለች። ፖሊሶች እና ሁከትን አጣምራ ችግሮች ቅርብ ናቸው ያለችው አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣይነት ምን ሊከሰት እንደሚችል የፖለቲካ መልዕክት ያለው እድምታዋን ተንፍሳለች። ሁሉም ሰው እንዲነቃ እናበረታታለን ብላለች።
👍141👎55😁226🔥1😭1