YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
Photo
የጤና ችግር ሊያስከትሉ በሚችሉ የውሃ ምርቶች ይዘት ላይ ጥናት ሊደረግ ይገባል ተባለ

👉 በጃር ውሃ ማሸጊያዎች ላይ በተደረገ ምርመራ ከደረጃ በታች ሆነው የተገኙ ስለመኖራቸውም ተነግሯል


በዜጎች ላይ የጤና ችግር ሊያመጡ በሚችሉ የታሸጉ የውሃ መጠጥ ምርቶች ባላቸው ይዘት እና የምርት ጥራት ዙሪያ ጥናት ሊደረግ እንደሚገባ፤ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በዘርፉ አምራቾች ላይ የምርታቸውን ይዘት ጥናት ማከናወን፤ በሌብሊንግ ወይም የምርቱን ገላጭ ጸሁፍ አመሳስሎ የመጠቀም ሁኔታን ለማስቀረት ይረዳል ብሏል፡፡

በንግድ እና በቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፋብሪካ ምርቶች ተቆጣጣሪ አንዷለም ክንዴ ለአሐዱ እንደገለጹት፤ የምርቱ ይዘት በተመለከተ ስለምርቱ መግለጫ ጹሁፍ የሌለው ምርት ገበያ ላይ ማዋል ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም በምርቶች ማሸጊያ ላይ የሚገኙ ስለ ምርቱ የሚገልጹ ዝርዝር መረጃዎች በተመለከተ የቁጥጥር ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አንድን ምርት ለመለየት ብሎም የተመረተበትን ተቋም ምንነት እና አድራሻ ለማወቅ በምርቶች ላይ የሚኖር ገላጭ ጽሁፍ ወይም ሌብሊንግ ማስቀመጥ፤ እራሱን ችሎ የተቀመጠ መስፈርት ስለመሆኑም አስረድተዋል፡፡

"እንደ ሀገር ጥቅም ላይ የሚውለው ውሃ የሚኒራል መጠኑን እንዲሁም የዜጎችን ጤና ከማስጠበቅ አንጻር 'ምርቱን መጠቀም የሚችሉ እና መጠየቀም የማይችሉ' ተብሎ ለመለየት፤ 'በታሸገ ውሃ ውስጥ ያለውን የጨው ይዘት ምን ያህል ነው?' የሚለውን በሌብሊን ወይም በምርቱ ገላጭ ጽሁፍ ላይ መቀመጥ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

"ይህ መገለጫ ፅሁፍ ጠቀሜታው ከጥራት ጋር የተያየዘ ብቻ አይደለም" የሚሉት ተቆጣጣሪው፤ ከጥራት በላይ ስለ አንድ ምርት ለተጠቃሚው መረጃ የሚሰጥ ከዛም ባለፈ ስለአምራቹ ድርጅትም ጭምር መረጃ የሚሰጥ በመሆኑ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሚኒስቴሩ የፋብሪካ ምርቶች ተቆጣጣሪ አንዷለም ክንዴ አክለውም፤ በተከናወነ የፍተሻ ሂደት ላይ ከተወሰዱ ናሙናዎች መካከል የደረጃ ምዘና መስፈርት አሟልተው ያልተገኙ የጃር ውሃ ማሸጊያዎች ስለመኖራቸው ለአሐዱ ተናግረዋል።

በአምራቾች ዘንድ ከደህንነት መስፈርት ጋር በተያያዘ የተለያየ ጉድለቶች እንደሚያስተውሉም ጨምረው ጠቁመዋል።

ግለሰቦች የጃር ውሃ ማሸጊያን ከውሃ በተጨማሪ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚጠቀሙበት ሁኔታ መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህንንም መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚደረግበት አሰራር ላይ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ ገልጸዋል፡፡

በጃር ውሃ ምርት ላይ ምልክት ወይም ስለ ምርቱ የሚገልጽ፤ መለያ በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ እንደ ክፍተት የሚነሳ ጉዳይ ስለመሆኑ ተነግሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍362🔥1
ሶማሊላንድ የባህር ምግብ ኢንዱስትሪዋን በማስፋት ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ፣ ኢትዮጵያም ቁልፍ ገበያዋ ሆናለች ተብሏል!

በሶማሊላንድ በከፍተኛ ሁኔታ የባህር ምግብ ኢንዱስትሪዋን እያስፋፋች እንደምትገኝ ተጠቆመ፤ የኤደን ባሕረ ሰላጤ ዳርቻ ላይ በምትገኘው በርበራ እየተስፋፋ የሚገኘው ኢንደስትሪው በዋናነት ታሳቢ ያደረገው በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የዓሳ ምግብ ፍላጎት ነው ተብሏል።

የዓሣ ፍላጎት እየጨመረ ወደሚገኝባት ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጠናው የዓሳ አቅራቢ በመሆን የባህር ምግብ ኢንዱስትሪዋን በማስፋት ላይ ትገኛለች ተብሏል።

አሁን ላይ የበርበራ ቱና ዓሣ ምርቶች በኢትዮጵያ ሱፐር ማርኬት መደርደሪያዎች ላይ በስፋት መታየት መጀመራቸውን ሆርን ዲፕሎማት ድረገጽ ዘግቧል። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል እየጨመረ የመጣውን የንግድ ትስስር ያንጸባርቃል ሲል ገልጿል።

በከፍተኛ ሁኔታ በኢትዮጵያ ገበያ ከሚታዩ ምርቶች መካከልም የዳህብሺል ግሩፕ አካል የሆነው ሶምቱና ፊሽንግ ኩባንያ የሚያመርተው የቱና ምርትና መሆኑን ጠቁሟል፣ ኩባንያው የወጪ ንግድ ጭማሪ በማሳየት ላይ እንደሚገኝ አመላክቷል።የበርበራ ወደብ ያላት ቅርበት፣ የንግድ አውታር መረቦች እና የሎጂስቲክስ አቅም እየጨመረ የመጣውን የንግድ ትስስር ይደግፋሉ ሲል አስታውቋል።

ከ120 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ በፕሮቲን የበለጸገ አመጋገብ ላይ እያተኮረች መሆኗን የጠቆመው ዘገባው ይህም የባህር ምግቦች ፍጆታ እንዲጨምር አስተዋጽኦ ማድረጉን አመላክቷል።

የሶማሊላንድ የዓሣ ኢንዱስትሪ እድገቱን በማጠናከር በቋሚ ዓሣ ማጥመድ፣ ዘመናዊ ማቀነባበሪያ እና የንግድ አጋርነት ላይ የሚያደርገው ኢንቨስትመንት በርበራን በአከባቢው እና በዓለም አቀፍ የባህር ምርት ገበያ ላይ ያላትን የገበያ ድርሻ የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተጠቁሟል።

@YeneTube
👍24😁32
🇪🇹🐐 በሰሜን ተራሮች የዋልያዎች ቁጥር እያሽቆለቆለ እንደመጣ ተነገረ

በሺዎች ይቆጠር የነበረው የብርቅዬ ዋልያ ቁጥር ወደ 300 ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታውቋል።

በአካባቢው ባለው የፀጥታ ችግር ሳቢያ የቁጥጥር መቀነስ፣ የእሳት አደጋና የሕገ-ወጥ አደኖች መበራከት የዋልያ ቁጥር እንዲመናመን ምክንያት ነው ተብሏል።

ብርቅዬው ዋልያ አይቤክስ ከዚህ በፊት አደጋ ላይ መውደቁን ተከትሎ በተሠራ የእንክብካቤ ሥራ ቁጥሩ አንድ ሺህ መድረስ ችሎ እንደነበር ተገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭20👍15😁3
በሰዎች ዝውውር የተከሰሱ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በእሥራት ተቀጡ!

በህገ ወጥ የሠዎች ዝውውር ተሠማርተዋል የተባሉ አንድ ከፍተኛ የአገር መከላከያ ሠራዊት አዛዥን ጨምሮ ሁለት የሠራዊቱ አባላት በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት ተቀጡ፡፡አባላቱ ቅጣቱ የተላለፈባቸው ትናንት በአርባምንጭ ከተማ በተሰየመው የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባሳለፈው የፍርድ ውሳኔ ነው፡፡

ቅጣቱ የተወሰነው በሠራዊቱ የደቡብ ዕዝ 202ኛ ኮር 1ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻምበል መብራቱ ታዴ እና በሬጅመንቱ የኦራል አሽከርካሪ በሆነው ወታደር ጌታቸው ክብረት በተባሉት  ላይ ነው፡፡አዛዡ እና የሰራዊቱ አባል ቅጣቱ የተወሰነባቸው ህዳር 16 2016 ዓ.ም 52 ኤርትራዊያንን በሠራዊቱ የኦራል ተሽከርካሪ በመጫን ወደ ኬኒያ በማሻገር ላይ እንዳሉ በመያዛቸው መሆኑን የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ  ሽመልስ ጮራ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡

የፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር ዐቃቤ ህግ ክሱ በውክልና በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲታይለት ባቀረበው የክስ መዝገብ መሰረት የተከሳሾቹን ጉዳይ ሲመለከት መቆየቱን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ “ ተከሳሾቹ የሰዎች ዝውውር ወንጀሉን የፈጸሙት ለግዳጅ የተሠጣቸውና የሠሌዳ ቁጥሩ መከ ኮድ  2-2347  የሆነ ኦራል ተሽከርካሪን በመጠቀም ነው ፡፡ ሰዎቹን በመጓጓዝ ላይ እንዳሉ የተያዙትም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሌ ዞን ቀርቀርቴ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡

ተከሳሾቹ  በፎቶ ፣ በሰነድ አና በሰው ምስክር የቀረበባቸውን ክስ ሊያሰተባብሉ አልቻሉም፡፡ ፍርድ ቤቱ እያንዳንዳቸው በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እና እንዲሁም በ10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኗል ፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍345
በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ግሪል ቢዝነስ ውስጥ የገባው፣ የከባድ ሚዛን ቦክስ ሻምፒዮኑ ጆርጅ ፎርማን (Big George) በ76 አመቱ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ቤተሰብ አስታወቀ:: ቤተሰቦቹ በኢንስታግራም አካውንታቸው ሞቱን ይግለፁ እንጂ ምክንያቱን እና የት እንደሞተ አልተናገሩም::
'ቢግ ጆርጅ' የሁለት ጊዜ የለም የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን እና የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ነበር።
ታዋቂው ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን በX ገጹ ላይ በፃፈው የሃዘን መግለጫ "ለጆርጅ ፎርማን ቤተሰብ ሀዘናችንን እንገልፃለን።

ለቦክስ እና ለቦክስ ያበረከተው አስተዋፅኦ መቼም አይረሳም" ብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍28😁3😭3
በዚህ ሳምንት አሊ ዶሮ ላይ የታገቱትን 58 ሰዎች ለመልቀቅ ታጣቂዎች በአንድ ሰው እስከ 1.5 ሚልዮን ብር እየጠየቁ ነው

ከአራት ቀን በፊት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በፍቼ እና ጎሀፂዮን ከተሞች መሀል የታገቱትን 58 ዜጎች ለመልቀቅ ታጣቂዎች ከፍተኛ ገንዘብ እየጠየቁ እንደሆነ ታውቋል።

በአውቶቡስ ሲጓዙ 'አሊ ዶሮ' ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ላይ ከታገቱት ዜጎች መሀል ህፃናት እና እድሜያቸው የገፋ አዛውንት እንደሚገኙበት ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ጠቁመዋል።

መጋቢት 8 ቀን የተፈፀመው ይህ እገታ በመንግስት ሚድያዎችም ሆነ በባለስልጣናት ምንም ቃል ያልተተነፈሰበት መሆኑ እጅጉን እንዳሳዘናቸው የታጋች ቤተሰቦች ገልፀው አሁን ላይ የቻሉትን ለመሰብሰብ የየቤቱ እየዞሩ እየለመኑ እንዲሁም በሶሻል ሚድያ ለህዝብ የእርዳታ ጥሪ እያቀረቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህ መስመር ከዚህ በተደጋጋሚ እገታዎች የሚፈፀሙ ሲሆን በአካባቢው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት በስፋት እንደሚንቀሳቀሱበት ይታወቃል።

"ተስፋችን ገንዘቡን ተበድረንም ሆነ ለምነን መክፈል ነው፣ ልጆቻችንን የሚያድንልን አካል አለ ብለን አናምን" ያሉ አንድ ወላጅ ወጣት ልጃቸው እቃ ለማምጣት አዲስ አበባ ሄዳ ስትመለስ እንደታገተች በእንባ ታጥበው ለሚድያችን አስረድተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭32👍217😁4👎1
ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ!!

( የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ )

የትግራይ ህዝብ ሰላምና ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላማዊ ትግልና ውይይት እንጂ በጦርነት አይደለም የሚል ፅኑ እምነት የትላንት፣ ዛሬና ነገ ኣቋም ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ጠብመንጃ አንስቶ የተቃጣበትን ዘር ማጥፋት ሲጋፈጥ፤የሚያጋጥመውን ሁለገብ ኪሳራ መገመት አቅቶት ሳይሆን እንደ ህዝብ ለመቀጠል ተገዶ የገባበት ብቸኛ ኣማራጭ ስለነበረ ነው።

የትግራይ ህዝብና ሰራዊትም ይህንን ከባድና የተወሳሰበ ትግል ተሸክሞ፣ ለአፍታ እንኳ አጋዥ ሳይጠይቅና ሳይለግም የትግራይ ህዝብ ከገፀ ምድር ለማጥፋት የተወጠነው ኣላማ በማክሸፍ አኩሪ ታሪክ ሰርቷል። የትግራይ ሰራዊትም የዚህ ሂደት ውጤት ነው፡፡

ሰላምን መፈለግ ኣስፈላጊ ቢሆንም፤ የኣንበሳውን ድርሻና ሃላፊነት ያለበት የፌደራል መንግስት የፕሪቶርያው የሠላም ስምምነት ሳይሸራረፍና በኣጭር ግዜ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይጠበቅበታል፡፡

የተፈናቀሉ ወገኖች የሰላምንና ደህንነት ዋስትና ተረጋግጦላቸው ወደቀያቸው እንዲመለሱ፣ የትግራይ ህገ መንግስታዊ ግዛታዊ አንድነት ቅድመ ጦርነት ወደነበረበት እንዲመለስ፣ በትግራይ የሚገኙ የታጠቁ ኃይሎች እንዲወጡ፣ ጦርነቱ ካስከተለው አስከፊ ጉዳት ክልሉ እንዲያገግም የትግራይ መልሶ ግንባታና በጦርነቱ ምክንያት የወደመው ንብረትና መሰረተ ልማት መልሶ የሚተካበትና የሚካካስበት ግልፅ ኣቅጣጫ ተቀምጦ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ኣለበት፡፡

ይህ በሚፈፀምበት ሁኔታ ሰራዊቱና የሰራዊቱ አመራር ለረዥም ጊዜ አይደለም፤ ለአንድ ደቂቃ እንኳን መሳርያ አንግተው ለመንከራተት የሚፈልጉበት ኣንዳችም ምክንያት የላቸውም። ምክንያቱም ጦርነት ምን እንደሆነ በወሬ ሳይሆን በተግባር ስለሚያውቁ። የትግራይ ሰራዊትና ኣመራሩ በትግራይ ህዝብ ላይ ለታወጀው የጅምላ ጭፍጨፋ ጦርነት ለመከላከል የወሰኑት በላያቸው ላይ ይወርድ የነበረው ግፍ እስኪቆም ድረስ ለመታገል እንጂ ጦርነት ምርጫቸው ስለነበረ ኣይደለም ።
በተለያዩ ግዜያት እንደ ታላቅ ገድል በሰበር ዜና በትግራይ ህዝብ፣ በተቋሞቹና መሪዎቹ በዘመን ኣመጣሽ የመገናኛ ኣውታሮች ጥላቻና ፕሮፖጋንዳ ሲሰበክ ከሩዋንዳው እልቂት ቀጥሎ ሊሆን ይችላል። የዚሁ ተቀጥላ በሆነው ድርጊት የተለያዩ ወገኖች ሰራዊታችንና አመራሩን በተደጋጋሚ መሬት ላይ በሌለ የፈጠራ ክስ ሲወነጅሉ እየተመለከትን ነው። ከነዚህ መሰል ክሶች አንዱ በቅርቡ በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በሚተዳደር ማህበራዊ ድህረ ገፅ የተዘረጋው በ ጀነራል ምግበይ ሀይለ ላይ ያነጣጠረ ውንጀላና ስም ማጥፋት ኣንዱ ነው። በተሰራጨው ፅሁፍ ከተካተቱት መልእክቶች መካከል "ምዕራብ ትግራይን አስመልሳለሁ በሚል እሳቤ፤ ሁለት ጊዜ የፌዴራል መንግስት ሠራዊትን ለማጥቃት ሞክሮ በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን ያሥበላ ዉጊያ እምቢ ሲለው የራሱን ታጣቂዎች ረሽኖና ገድሎ ውጊያው ሳይሳካለት አከርካሪው ተመትቶ ሸሽቷል።" የሚል ይገኝበታል። ይህ መግለጫም የሂደቶቹ ተቀጥላና እሳቱ ባለበት ለማርገብ ከመጣር ይልቅ ማርገብገብ፣ ላጋጠመህ የራስ ችግር ለተግባራዊ መፍትሄ ከመጣር ይልቅ የማይመለከተው ኣካል በመፍጠርና ጣት በመቀሰር ሰላምና እድገትን እንዳይፀና የሚያደርግ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

በርግጥ ዜናውን ከውጭ ለሚያይ ወገን ሊያደናግር ይችል ይሆናል፣ እውነቱንና የሰራዊታችንን ፍላጎትና ዓላማ ለሚያውቅ ግን "ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ!!" ከመሆን የዘለለ ፋይዳ ኣይኖረውም። ይህ ግልብና ብስለት የጎደለው ይዘት እንዳለ ሆኖ የትግራይ ህዝብ ግዛታዊ አንድነት ለማስከበር የሚደረግ ተጋድሎ እንዲህ አቃሎና አንኳሶ ማቅረብ ግን የፕሪቶርያውን ስምምነት ወደ መሬት ወርዶ ተግባራዊ እንዲሆን ትልቅ ድርሻ ካለው ተቋም የማይጠበቅና ሀላፊነት የጎደለው ስለሆነ በፍጥነት መስተካከል አለበት።

ጀነራል ምግበይና ጓዶቹ በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት በጥብቅ ዲሲፕሊን ተገዝተው ስራቸውን የሚፈፅሙ እንጂ ከዚህ ተቃራኒ በሆነ ምንም አይነት እንቅቃሴ የሌሉና ያልነበሩ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል። ሰላምን ለማፅናት ከሚያስፈልጉት መሰረታዊ ነገሮች አንዱ እውነት ላይ የተመሰረተ ሀቀኛ መረጃ እንጂ በክፋትና በተንኮል የተጆቦነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሊሆን ኣይችልም፡፡ የሀገርን ሰራዊት ወክሎ መረጃ በሚያሰራጭ የመረጃ ቋት እንዲህ አይነቱ እርባና ቢስ ዜና መዘርጋት የትግራይ ሰራዊት ለሰላም እየከፈለ ያለውን ዋጋና ልፋት የውሃ ሽታ የሚያደርግና በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት ኣይነት መግለጫ መውጣቱ ከልብ ኣሳዛኝ ነው።

በመሆኑም የወጣው መግለጫ የምላስ ወለምታ ሊሆን ስለሚችል መልሶ ቢጠናና ይቅርታ ቢጠየቅበት፤ ሰላምን የሚያፀኑ የፕሪቶርያ ሠላም ስምምነት ሳይሸራረፉና በኣጭር ግዜ ውስጥ ተግባራዊ ሊያደርጉ የሚችሉ ሃቀኛ ተግባሮች እንዲከናወኑ እያሳሰብን፣ በኛ በኩል የፕሪቶርያ ሠላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የሚጠበቅብንን ለመወጣት ቁርጠኝነታችንን መግለፅ እንወዳለን፡፡

የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

13/07/2017 ዓ/ም
@Yenetube @Fikerassefa
👍73😁216😭6
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቅርቡ አሜሪካ "persona non grata" ብላ ያባረረቻቸው በአሜሪካ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ኢብራሂም ራሶል ዛሬ ደብቡ አፍሪካ ሲገቡ የሞቀ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

አምባሳደሩ የትራምፕ አስተዳደር ላይ "የነጭ የበላይነትን ለማምጣት የሚታገል" ሲሉ በሰጡት ትችት ከሀገር እንዲወጡ ቀን እንደተቆረጠላቸው ይታወሳል።
👍69
የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ ከመጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚከተለዉ መሰረት ስራ ላይ እንዲዉል በመንግስት ተወስኗል።

ከመጋቢት 14/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ
ቤንዚን 112.67
ኬሮሲን 107.93
ነጭ ናፍጣ 107.93
ቀላል ጥቁር ናፍጣ 109.22
ከባድ ጥቁር ናፍጣ 106.75 ብር በሊትር የሚሸጥ ይሆናል።
👎47👍21😭13😁119
👍2
YeneTube
Photo
አሜሪካ ከኢራን ጋር በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ መደራደር ትፈልጋለች ተባለ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ ጋር አዲስ የኒውክሌር ስምምነት ሊደረግ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ያደረጉት ንግግር ቀጥተኛ ወታደራዊ እርምጃን ለማስወገድ የሚደረግ ሙከራ ነው ሲሉ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል። "ሁሉንም ነገር በወታደራዊ መንገድ መፍታት አያስፈልገንም" ሲሉ ዊትኮፍ ለፎክስ ኒውስ እሁድ እለት ገልፀዋል። ለኢራን የምንሰጠው ምልክት 'በውይይት፣ በዲፕሎማሲ፣ ወደ ትክክለኛው ቦታ መድረስ ከቻልን ቁጭ ብለን እንይ' ነው። ከቻልን ያንን ለማድረግ ተዘጋጅተናል። ካልቻልን ደግሞ አማራጩ ትልቅ አማራጭ አይደለም ሲሉ አክለዋል።

የዊትኮፍ ይህ አስተያየት የተሰማው ትራምፕ በመጋቢት 7 ቀን በኢራን የኒውክሌር እንቅስቃሴ ላይ ለመነጋገር ቴህራን እምቢ ካለች ወታደራዊ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ለማስጠንቀቅ ደብዳቤ ለኢራን አመራር እንደላኩ ከተናገሩ በኋላ ነው ። ኢራን ከ"ጉልበተኛ" ጋር እንደማትተባበር በመግለጽ አቀራረቡ በካሜኔ ተወግዟል። ትራምፕ እስራኤል በጋዛ ጦርነቷን ከቀጠለች በኋላ በየመን ለሚኖሩት ሁቲዎች ኢራን የምታደርገውን ድጋፍ በመቃወም ቴህራንን አስፈራርተዋል።ባለፈው ሳምንት አሜሪካ በየመን ላይ ያደረገችውን ከፍተኛ የአየር ድብደባ፣ ተከትሎ ቴህራንን የየመን ሁቲዎች ለሚያደርሱት ማንኛውንም ጥቃት ተጠያቂ እንደምትሆን ገልፀዋል።

ኢራን ቡድኑ በገለልተኛነት እንደሚሰራ በመናገር የትራምፕን ዛቻ አጣጥለዋል።ዋሽንግተን የግፊት ፖሊሲዋን እስካልተለወጠች ድረስ ከአሜሪካ ጋር መነጋገር የማይቻል ነው ሲሉ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እሁድ እለት ተናግረዋል ። ሐሙስ ዕለት ደብዳቤው "በእርግጥ የበለጠ ስጋት" እንደሆነ እና ቴህራን በቅርቡ ምላሽ እንደምትሰጥ ገልፀዋል ።ትራምፕ በአንድ ወገን የኢራን ስምምነት አሜሪካን ካስወጡ በኃላ ኢራን የዩራኒየም ማበልጸጓን እስከ 60 በመቶ ከፍ አድርጋለች።


Via:- ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍223
🇪🇹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ከጅቡቲ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን ትላንት ምሽት አከናውኗል።

ብሔራዊ ቡድኑ የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ስድስተኛ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ለሊት 6 ሰዓት በኤል አብዲ ስቴዲየም የሚያደርግ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ወደ አልጀዲዳ ከተማ ተጉዟል።

በላርዪ ዛውሊ የልምምድ ሜዳ በትላንትናው ዕለት ባደረገው የአንድ ሰዓይ የልምምድ መርሃግብርም የቡድኑ አባላት በመልካም ጤንነት ላይ መገኘታቸው ተገልጿል።

በኤል አብዲ ስታዲየም ዛሬ ለሊት የጅቡቲ አቻውን የሚገጥመው ስብስቡ አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ አድርጎ ወደ ሜዳ ይገባል።

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በታሪክ ለ10ኛ ጊዚ ዛሬ ለሊት የሚገናኙ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሀገራቱ በነበራቸው ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ስምንቱን ጨዋታዎች ስታሸንፍ በአንዱ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።

በዘጠኙ ጨዋታዎችም ኢትዮጵያ ጅቡቲ ላይ 33 ግቦች ስታስቆጥር በአንጻሩ ጅቡቲ ኢትዮጵያ ላይ ያገባችው የጎል ብዛት ስምንት ብቻ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
😁44👍23👎1021
ኤርትራ እና ግብጽ የቀይ ባህር ወሰን የሌላቸው ሀገራት ተሳትፎን 'እንደማይቀበሉ' ገለጹ!

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ እና የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ የቀይ ባህር ወሰን የሌላቸው ሀገራት ተሳትፎን 'እንደማይቀበሉ' ገለጹ፤ በተጨማሪም ቀይ ባህርን መጠበቅ እና ማስተዳደር በዋናናት የባህሩ ድንበር ተጋሪ ሀገራት ተግባር እንዲሆን አሳስበዋል።

ሁለቱ ባለስልጣናት ይህንን የገለጹት ትላንት መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም በካይሮ በቀጠናዊ መረጋጋት ጉዳይ፣ ለሶማሊያ ድጋፍ በሚያደርጉበት መንገድ፣ ስለ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እና ስለ ቀይባህር ደህንነት ዙሪያ በመከሩበት ወቅት መሆኑን የግብጽ መገናኛ ብዙሃን በዘገባቸው አስታውቀዋል።

በውይይቱ ወቅት የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ (ዶ/ር) እና የሀገሪቱ የደህንነት የደህንነት ሹም ሜጀር ጄነራል ሀሳን ራሽድ መገኘታቸውን ዘገባዎቹ አመላክተዋል፤ የኦስማን ሳላህ እና አልሲሲ ውይይት በዋናነት ያተኮረው በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ነበር ሲሉ ቃል አቀባያቸው ሞሃመድ ኤልሸናዊ ገልጸዋል፤ ሶማሊያን ለማገዝ ሁለቱ ሀገራት ቁርጠኛ መሆናቸውም በውይይቱ ተገልጿል ብለዋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
😁49👍294👎3
ቱርክ ለ10 ዓመታት አይታ በማታውቀው ተቃውሞ እየተናጠች ነው።

የፕሬዝደንት ጣይብ ረሲፕ ኤርዶዋን ቀንደኛ ተቀናቃኝ በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተከትሎ በመላው ቱርክ ተቃውሞው ተባብሶ ቀጥሏል።ኤክሬም ኢማሞግሉ የኢስታንቡል ከንቲባ ሲሆኑ ባለፈው ከሶስት ዓመታት በኋላ ለሚካሄደው ምርጫ የሪፐብሊካን ፒፕልስ ፓርቲ (ሲኤችፒ) ዕጩ ሆነው እሑድ ዕለት ይመረጣሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።

ኢማሞግሉ እሳቸው ላይ የተከፈቱ ክሶች ፖለቲካዊ እንደሆኑ በመናገር "በፍፁም አላጎበድድም" ሲሉ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት በኤክስ ገፃቸው ፅፈዋል።ኤርዶዋን ሰልፎቹን ወቅሰው ሲኤችፒ "ሰላማችንን ሊበጠብጥ እና ሕዝባችንን ሊከፋፍል የተነሳ" ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

ለአምስተኛ ተከታታይ ምሽት በርካታ ሰዎች በኢስታንቡል ከተማ አዳራሽ አመሻሹን እየተገኙ የቱርክ ባንዲራ እያውለበለቡ ከአድማ በታኝ ፖሊስ ፊት ለፊት ሲዘምሩ እና ሲጮሁ ታይተዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍44👎6😁21👀1
በቴሌግራም እንዳትበሉ ይጠንቀቁ።

የቴሌግራም ፕሪሚየም ለ3 ወራት ብለው Link ከላኩላቹ ሊንኩን አትንኩት ቴሌግራማችሁን ሃክ ሊያደርጉ ይችላሉ።

ነቄ የየኔቲዩብ ቤተሰቦች አደራ 👍
👍58👀2😁1
🇪🇹 ሁለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት የጦር መሳሪያ ማስተኮሻ ሶፍትዌር ማበልፀጋቸው ተነገረ

በአዋሽ አርባ ውጊያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት ለሜካናይዝድ ስልጠና የገቡት ሁለቱ ወጣቶች፤ ከመደበኛ ስልጠናቸው ጎን ለጎን የጦር መሳሪያ ማስተኮሻ ሶፍትዌር አበልፅገው ለተቋማቸው አስረክበዋል።

መሠረታዊ ወታደር ዘላለም ቤዛነህ እና መሠረታዊ ወታደር ዳንኤል ሙልቀን የፈጠሩት ሶፍትዌር ውጤታማነቱ እንደተረጋገጠ መከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡

በፈጠራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የሙሉ አስር አለቅነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍95😁549👎5🔥3
ለሸማቹ ማህበረሰብ እንዲከፋፈል የተላከ የምግብ ዘይት ለቸርቻሪ ነጋዴዎች ሲራገፍ በቁጥጥር  ስር ዋለ

በጅማ ከተማ ወረዳ አንድ ለሸማቹ ማህበረሰብ እንዲከፋፈል የተላከ የምግብ ዘይትን ለቸርቻሪ ነጋዴዎች በድብቅ ሲራገፍ በቁጥጥር  ስር ውላል።

የጅማ ከተማ ፖሊስ ኮሙኒኬሽን  ጽ/ቤት ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን የላከው መረጃ እንደሚያመላክተው  የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 34179 ኦሮ የሆነ ተሽከርካሪ ደርጊቱን ሲፈጽም በቁጥጥር  መዋሉን አስታውቋል። ተሰምቷል። ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ መሰረት ለሊሙ ሰቃ ወረዳ ሸማቾች ማህበር የተላከ አራት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሊትር ዘይት ተይዟል ። 

ዘይቱን ሲያራግፍ የነበረው አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን አቁሞ ቢሰወርም ፖሊስ ግለሰቡን በመከታተል ላይ መሆኑን የዞኑ ጽ/ቤት መግለጫ ያመላክታል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍19😁63
ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የተሰጠ መግለጫ‼️

በ14/7/ 2017 ዓ.ም በEBS ፕሮግራም ላይ በተደረገ ቃለ ምልልስ  ብርቱኳን ተመስገን ከበደ የተባለች  በ2013 የትምህርት ዘመን በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የፋርማሲ ተማሪ ነበርኩ በማለት የሰጠችዉ ሃሳብ ስህተት መሆኑና ዩኒቨርሲቲው የፋርማሲ ትምህርት ሲሰጥ በ2013 የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እንዳልነበረው ይገልጻል።

ስለሆነም ይህ ድርጊት በጣም ሃላፊነት የጎደለው እና ምንም አይነት ማስረጃ የሌለው  ስለሆነ  ግልጽ የሆነ ስም ማጥፋት እና የዩኒቨርሲቲያችንን ስም  የምያጎድል ስለሆነ  ኢቢኤስ ይህን ውንጀላ እስካልቀለበሰ ድረስ ዩኒቨርሲቲው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደምወስድ ይገደዳል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👎287👍45😁15👀7😭64🔥2
ኢትዮጵያ ከ Djibouti 🇩🇯 ጋር ከ1 ሰዓት በኋላ የምታደርገውን ጨዋታ ለማየት ይህን አፕ ዳውን ሎድ አድርጉ። Cricfy TV በነፃ ነው። ለሌላ ጊዜም ይጠቅማችኋል።

Application ለማውርድ በዚህ ገፅ ላይ ካደረግን Copyright ሊዘጋብን ሰለሚችል አዲስ ቻናል ከፍተናል ለቀናል አፕልኬሽኑን

https://tttttt.me/+LMTodBBw8oI4MjY0
👍22😁111
ነዳጅ

የግል ኩባንያዎች ነዳጅ እንዲያስመጡ ተፈቀደ
የግሉ ዘርፍ ከሽያጭ በተጨማሪ ነዳጅ ማስመጣት እንዲችል የሚፈቅደው አዋጅ ስራ ላይ ዋለ፡፡

የነዳጅ ግብይት አዋጅ ቁጥር 1363/2017 ላለፈው 11 አመት በስራ ላይ የነበረውን አዋጅ የቀየረ ሆኖ ባለፈው ጥር ነበር በፓርላማ የፀደቀው፡፡

ይህ አዋጅ በሳለፍነው ሳምንት በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ስራ መግባቱ ነው የታወቀው፡፡

በዚህም እስካሁን በመንግስታዊው የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ብቻ ተይዞ የነበረውን የነዳጅ ከውጭ ገዝቶ የማስገባት ስራ ሌሎች ኩባንዎችም ማከናወን እንዲችሉ በር የሚከፍት ነው፡፡

የነዳጅ ንግድ የመንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ አካል ሆኖ እየተሰራበት የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍29👀7😁211