YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update: የ "ቴሌግራም" መተግበሪያ ተጠቃሚዎቹ እንደሌሎቹ ማኅበራዊ ትስስር ገጾች "ስቶሪ/Story" መለጠፍ እንዲችሉ የሚያስችል ማዘመኛ ይፋ አድርጓል።

አሁን ላይ ለፕሪሚየም ተጠቃሚዎች ብቻ የተፈቀደው ይህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ፎቶ እንዲሁም ቪዲዮ በስቶሪ እንዲያጋሩ ያስችላል።

ይህ ማዘመኛው ቴሌግራምን ከሌሎቹ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችና የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች ጋር ያመሳስለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
አቶ አህመድ ሽዴ ከአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ጋር ተወያዩ! የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ጋር ተወያይተዋል።በአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል። በዛሬው ዕለትም ከገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ…
#update

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መንግስት መስጠት ያቋረጠውን ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ ለመቀጠል፤ አሁንም መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ አስታወቀ።

ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ወደ ነበረበት ለመመለስ “የደረጃ በደረጃ አካሄድን” እንደሚከተል ገልጿል።ሃያ ሰባት አባል ሀገራትን በስሩ ያቀፈውን የአውሮፓ ህብረትን አቋም ያሳወቁት፤ የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ዩታ ኡርፒላይነን ናቸው። ኮሚሽነሯ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጋር ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 22፤ 2016 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል ውይይት ካደረጉ በኋላ፤ የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን አሁንም እንደ “ስትራቴጂካዊ አጋር” እንደሚመለከታት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት፤ በጥቅምት 2013 በትግራይ ክልል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ወዲህ ተቀዛቅዞ ቆይቷል። ህብረቱ በጦርነቱ ምክንያት ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን 90 ሚሊዮን ዩሮ ከሚጠጋው የበጀት ድጋፍ ማገዱ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ በተመሳሳይ ምክንያት ለኢትዮጵያ ያዘጋጀውን አንድ ቢሊዮን ዩሮ የልማት እርዳታ ሳይያጸድቅ ቀርቷል።

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን ቀጥተኛ በጀት እንደገና ለመልቀቅ አስቦ እንደው ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጥያቄ የቀረበላቸው ኮሚሽነሯ፤ ይህ የገንዘብ ድጋፍ ከመደረጉ በፊት በኢትዮጵያ በኩል መሟላት የሚገባቸው “ፖለቲካዊ ሁኔታዎች” እንዳሉ ተናግረዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
👍174👎3