YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የBETTING ቤት ለመክፈት የሚያስለፈጉ የThermal Printer በUSB እና Ethernet cable የሚሰራውን Xprinter Original Printer እና POZONE BARCODE SCANNER አሰግብተንልዎታል።

ዋጋችን በአስተያየት ነው የትም አወዳድረው ምርጫዎን እኛን ያድርጉ።

Inbox us on Telegram
https://tttttt.me/gamerszone1
#ይደውሉልን - 0911061990
#ይደውሉልን - 0947152583
👍4👎1
የአትክልት ተራ ቤተሰብ/አባል/ ሲሆኑ  የሚያገኙት አገልግሎት 

👉  በገበሬው ዋጋ ወይንም ከገበያው ዋጋ ከ30-50 % በሆነ ቅናሽ

👉እስከ ቤትዎ በራፍ ድረስ ነጻ የዴሊቨሪ አገልግሎት

👉 fresh ወይንም ትኩስ ምርት ብቻ  በንጉስ መስተንግዶ እና የደንበኞች አገልግሎት ጋር

በስልካችን
0965083443
0118536066

በመደወል ወይም በዌብሳይታችን https://atkelttera.com/try/ ላይ ቀጥታ በመመዝገብ የአትክልት ተራ ቤተሰብ መሆን ይችላሉ

እለታዊ የዋጋ ዝርዝር እና ሙሉ መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን @atkelttera1 ላይ ያገኛሉ
👍41
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: ARABIC TRANSLATOR
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC  (WRITING AND SPEAKING)
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 7000
🎯ፆታ: Female (3)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍4
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: DATA ENCODER
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC Or OROMIFA 
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 6000
🎯ፆታ: Female (5)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍2
በዐማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት እንደተቋረጠ ነዋሪዎች ገለፁ!

በዐማራ ክልል፣ በምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች፣ ከትላንት ማክሰኞ ከቀትር በኋላ ጀምሮ፣ የስልክ አገልግሎት በመቋረጡ፣ የዘመዶቻቸውን ደኅንነት ማወቅ እንዳልቻሉ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው፣ የባሕር ዳር እና የዐዲስ አበባ ከተሞች ነዋሪዎች፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም፣ በደንበጫ እና በዙሪያው፣ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ የስልክ አገልግሎት እንደማይሠራ አረጋግጠናል፤ ብለዋል፡፡

ሰሞኑን፣ ዳግም በተቀሰቀሱት ግጭቶች፣ በየዕለቱ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ በስልክ ስለ ደኅንነታቸው እንደሚጠያየቁ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ አሁን ላይ ግንኙነቱ መቋረጡ እንዳስጨነቃቸው ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩን፣ በዋትሳፕ መተግበሪያ መረጃ እንዲሰጡ ተጠይቀው፣ ለቦርድ ስብሰባ ውጭ ሀገር እንደሚገኙና ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች እንደሚመድቡ በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍142
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል ተሽከርካሪው በታጣቂዎች እንደተወሰደበት ገለጸ!

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል ፍኖተ ሰላም ከተማ ከሚገኘው ጽህፈት ቤቱ ለሰብአዊነት ተግባር የሚጠቀመው አምቡላንስ በታጣቂዎች ‘በኃይል’ እንደተወሰደበት አስታውቋል።

ማህበሩ ትናንት መስከረም 9/2016 ምሽት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ ንብረትነቱ የምዕራብ ጎጃም ዞን የቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ የሆነ አምቡላንስ ማክሰኞ መስከረም 8/2016 ዓ.ም “ባልታወቁ የታጠቁ” ኃይሎች እንደተወሰደበት አመላክቷል።

“አምቡላንስ ተሸከርካሪው የተወሰደው በፍኖተ ሰላም ከተማ ከሚገኘው የቅርንጫፉ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን የተወሰደውም በአስገዳጅ ሁኔታ ነው” ሲልም አክሏል።

ይህንን ድርጊት የኮነነው ማህበሩ ተግባሩ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ሥምምነቶች ጋር የሚፃረር እንደሆነም ጠቁሟል።ድርጊቱ “ከማህበሩ ዓላማ ውጪ መሆኑን በመረዳት ድርጊቱን የፈፀሙት አካላት አምቡላንሱን ለማህበሩ በመመለስ ለማኅበረሰቡ የተለመደውን ሰብዓዊ አገልግሎት መስጠት እንድንችል እንድታደርጉ እንጠይቃለን” ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

ማህበሩ አክሎም በመላው ኢትዮጵያ ለሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የማህበሩ ሠራተኞች፣ በጎፈቃደኞችና አምቡላንስን ጨምሮ ተሽከርካሪዎች “በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ታጣቂ ኃይሎች ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡና ማኅበረሰቡም መሰል ድርጊቶችን እንዲያወግዝ እንጠይቃለን” ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍22👎81
መንግሥት ከመጠባበቂያ መጋዘኑ የሁለተኛ ዙር ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነው ተባለ!

መንግሥት ከመጠባበቂያ መጋዘኑ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች አፋጣኝ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አራት ሚሊዮን ዜጎች የሁለተኛ ዙር ሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አታለለ አቡሀይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅትና አጋር አካላት በኢትዮጵያ ለተወሰኑ ወራት ምግብ ነክና ሌሎችንም ሰብዓዊ ድጋፎች ማቋረጣቸውን ተከትሎ መንግሥት ክፍተቶችን ለመሙላት ከራሱ መጠባበቂያ የምግብ ክምችት መጋዘኖች ወጪ አድርጎ በመጀመሪያው ዙር ለአራት ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ አድርጓል።

በተመሳሳይ መልኩ በሁለተኛ ዙር ለአራት ሚሊዮን ዜጎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ድጋፉን ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል።ኮሚሽኑ ድጋፎችን የሚያደርገው በየ45ቀኑ እንደሆነ የገለጹት አቶ አታለል፤ አጋር አካላት እርዳታ ማድረግ ካቆሙበት ጊዜ ጀምሮ መንግሥት ክፍተቱን ለመሙላት እየሠራ እንዳለ ጠቁመዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
👎15👍113
በአፋር ክልል ተርበናል ብሎ መጠየቅ ለእስር እየዳረገ ይገኛል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።

በአፍዴራ እና በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች በርሀብ ምክንያት ዜጎች አየሞቱ ይገኛሉ ነው ያሉት።ከጦርነት ማብቃት በኋላ መንግስት የአፋር ክልል ህዝብን ዞር ብሎ አላየም ይህ በመሆኑም ህዝቡ ለዘርፈ ብዙ ችግር መጋለጡን ነው የተነገረው።

የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል መንግስት የክልሉን ህዝብ እረስተውታል ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።በክልሉ ያሉ አመራሮች በህገወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ በመሰማራታቸው ህጋዊ ሆኖ መስራት ወንጀል እየሆነ ነው ብለዋል።

በተለይም የክልሉ ሀላፊዎች የጨው ምርት ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ዜጎች ክንዳቸው እያሳረፉ እንደሚገኙ ነው ዜጎች የተናገሩት።አሁን ላይ በክልሉ በጨው ምርት መሰማራት ከባድ መሆኑን የሚናገሩት ዜጎች ሁሉም ነገር በሙስና ሆኗል ብለዋል።

በክልሉ በጨው ምርት ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው የዶቢ የጨው አምራቾች ማህበር በክልሉ መንግስት ቅሬታውን አሰምቷል።ማህበሩ ባልታወቀ ምክንያት ስራው እንዲያቆም ከክልሉ የማእድን ቢሮ ተነግሮታል።

ማህበሩ ይህ ውሳኔ ድንጋጤ እንደፈጠረበት አስታውቆ የክልሉ ማእድን ልማት ቢሮ ሀላፊዎች አምራቾችን በራሳቸው ሰዎች ለመተካት የወጠኑት ሴራ ነው ሲሉ የማህበሩ አባላት ተናግረዋል።በክልሉ ጨው አምራቾች ምርታቸው የሸጡበት የ6ወር ክፍያም እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል።

በክልሉ የጨው አምራች ማህበራት በግለሰቦች እና በመንግስት ሀላፊዎች እየተዘወረ ይገኛል ብለዋል። የጨው ምርት እና ጅምላ አከፋፋዮችም የባለስልጣን ቤተቦች ሠሆናቸውን የተናገሩት የዶቢ ጨው አምራች ማህበር አሁን ላይ ችግር ላይ መውደቁን ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት በጨው ጉዳይ ቅሬታ የሚያነሱ ዜጎችን ለእንግልት እየዳረገ እና እያሰረ እንደሚገኝ ነው ማህበራቱ የተናገሩት።በመሆኑም የፌደራል መንግስት የችግሩን ግዝፈት ተረድቶ መፍትሔ እንዲሰጣቸው የማህበሩ አባላት ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍17👎3🔥1
ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም. ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር እንደሚቀጥል ተገለፀ!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ የአስራር ለውጦች እያደረገ ቢሆንም በተያዘው ዓመት የተማሪዎች ቅበላ በምደባ እንደሚሆን አስታወቀ።

የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ የተቋሙን ሽግግር በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሲሰጡ፤ በ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ አንድ ዓመት ተኩል ይፈጃል ተብሎ በሚጠበቅ የሽግግር ሂደት ላይ እንዳለ የተናገሩት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ሳሙኤል ሙሉ በሙሉ ራስ ገዝ መሆን ሲችል አዳዲስ ተማሪዎችን በዩኒቨርስቲው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ እንደሚቀበልም ጠቁመዋል።

የተቋሙ ራስ ገዝ መሆን ከፍለው መማር የማይችሉ ተማሪዎችን አይቀበልም ማለት አይደለም ያሉት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ፤ የዩኒቨርስቲውን መግቢያ የሚያሟሉ ብቁ ተማሪዎች በመንግስት ድጋፍ ዩኒቨርስቲውን መቀላቀል እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር ለማገዝ ቻንስለር ጨምሮ የቦርድ አመራሮችና ፕሬዝዳንቶች መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በዓለም አቀፍ መስፈርቶች ተወዳድረው እንደሚቀጠሩ ተጠቁሟል።ተቋሙ ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ተማሪዎችን በምደባ እንደማይቀበል አስታውቆ ነበር።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
👍37🔥42
የBETTING ቤት ለመክፈት የሚያስለፈጉ የThermal Printer በUSB እና Ethernet cable የሚሰራውን Xprinter Original Printer እና POZONE BARCODE SCANNER አሰግብተንልዎታል።

ዋጋችን በአስተያየት ነው የትም አወዳድረው ምርጫዎን እኛን ያድርጉ።

Inbox us on Telegram
https://tttttt.me/gamerszone1
#ይደውሉልን - 0911061990
#ይደውሉልን - 0947152583
👍7
የአትክልት ተራ ቤተሰብ/አባል/ ሲሆኑ  የሚያገኙት አገልግሎት 

👉  በገበሬው ዋጋ ወይንም ከገበያው ዋጋ ከ30-50 % በሆነ ቅናሽ

👉እስከ ቤትዎ በራፍ ድረስ ነጻ የዴሊቨሪ አገልግሎት

👉 fresh ወይንም ትኩስ ምርት ብቻ  በንጉስ መስተንግዶ እና የደንበኞች አገልግሎት ጋር

በስልካችን
0965083443
0118536066

በመደወል ወይም በዌብሳይታችን https://atkelttera.com/try/ ላይ ቀጥታ በመመዝገብ የአትክልት ተራ ቤተሰብ መሆን ይችላሉ

እለታዊ የዋጋ ዝርዝር እና ሙሉ መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን @atkelttera1 ላይ ያገኛሉ
👍31
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: ARABIC TRANSLATOR
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC  (WRITING AND SPEAKING)
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 7000
🎯ፆታ: Female (3)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👎3
አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

የድርጅት ስም :SAFRON FORIGEN EMPLOYMENT AGENCY

🎯የ ስራ መደብ: DATA ENCODER
🎯የ ስራው መስፈርት: FLUENT IN ARABIC Or OROMIFA 
🎯BASIC skill in computer
🎯የትምህርት  ደረጃ...Degree
🎯ደሞዝ : Net 6000
🎯ፆታ: Female (5)
🎯የስራ  ቦታ: Enqulal Fabrika Tadese Chekol Building 3th floor
🎯መመዝገብ የምትፈልጉ በ ስልክ በመደወል ያናግሩን
+251911272714/+251911002525
👍4👎2
ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሜሪካንን በመሰለል ክስ ተመሠረተበት!

ለመንግስት በኮንትራትነት ይሠራ የነበረ አብረሃም ተክሉ ለማ የተባለ ትውልደ ኢትዮጵያ የአሜሪካንን መንግስት በመሰለል ባለፈው ነሐሴ 18 ቀን 2015 በቁጥጥር ሥር መዋሉን ዛሬ ይፋ የሆነው የክስ ሰንድ አመልክቷል።

የኢንፍሮሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆነው፣ የሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ ነዋሪው የ50 ዓመቱ አብረሃም ተክሉ ለማ፣ ሌላ ሀገርን ለመደገፍ የብሄራዊ መከላከያ መረጃን በማስተላለፍ፣ የብሄራዊ መከላከያ መረጃን ሌላ ሀገርን ለመደገፍ ለማስተላለፍ በማሴር እንዲሁም ሆን ብሎ የብሄራዊ መከላከያ መረጃን በግል መያዝ የሚሉ ክሶች ተመሥርተውበታል።

በቀረበው ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ ከታህሳስ 2014 እስከ ነሐሴ 2015 ባለው ግዜ ውስጥ ግለሠቡ የስለላ ሪፖርቶችን ኮፒ በማድረግ፣ ሚስጥራዊ መሆናቸውን የሚያሳዩ ምልክቶችን ሠርዟል ተብሏል። “ሚስጥር” እና “ከፍተኛ ሚስጥር” የሚሉ ምልክቶችን ጥበቃ ከሚደረግበት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ ሆኖ መሠረዙን ክሱ አመልክቷል።

ሰንዶቹ አንድ ሀገርን ወይም አንድን አካባቢ የሚመለከቱ እንደሆኑ እና ተከሳሹ ካለ ፈቃድ ኮፒ ማድረጉ፣ ማስወገዱ እና በግል መያዙ ተመልክቷል።

አብረሃም ተክሉ ለማ ሚስጥራዊ የመከላከያ ሰነዶቹን የሌላ ሀገር መንግስት የስለላ ተቋም ጋር ግንኙነት ላለው ባለሥልጣን አሳልፎ መሥጠቱን ክሱ በተጨማሪ አመልክቷል። በመልዕክት ልውውጣቸውም ወቅት፣ አብረሃም ተክሉ ለማ ለባለሥልጣኑ መረጃን በማስተላለፍ መርዳት እንዳሚሻ ገልጿል ብሏል ክሱ።

አብረሃም ተክሉ ለማ ለውጪ ሀገር ባለሥልጣኑ አስተላልፎታል የተባለው መረጃ፣ በስም ባልተጠቀሰው ሀገር እና በቀጠናው የሚገኝን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ የሳተላይት ምስል እና ሌሎች ሌሎች ወታደራዊ መረጃዎችን ይጨምራል ተብሏል።

ሁለቱ የስለላ ክሶች እስከ ሞት ቅጣት ወይም እስከ ዕድሜ ልክ እስራት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ እና ሰነዶችን ለግል መያዝ የሚለው ክስ ደግሞ እስከ 10 ዓመት የእስር ቅጣት ሊያስከትል እንደሚችል ተመልክቷል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍23👎76
የሱዳኑ መሪ ጦርነቱ ወደ ጎረቤት አገራት ሊስፋፋ ይችላል ሲሉ በተመድ ስብሰባ ላይ ተናገሩ!

የሱዳኑ መሪ በሃገራቸው የተከሰተው ጦርነት ወደ ጎረቤት አገራት ሊስፋፋ ይችላል ሲሉ በተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናገሩ።የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብድል ፋታህ አል-ቡርሃን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በጀነራል ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራውን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሽብርተኛ ቡድን ብሎ እንዲፈርጀውም ጥያቄ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል የፈጥኖ ደራሹ ኃይል መሪ ጀነራል ሃምዳን ደጋሎ የተኩስ አቁም ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።ሱዳን ከባለፈው ሚያዚያ ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት የተዘፈቀች ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ አገር ጥለው ተሰደዋል።

በአውሮፓውያኑ 2021 ሁለቱ መሪዎች ተባብረው መፈንቅለ መንግሥት ማወጃቸው ይታወሳል።ነገር ግን በሁለቱ መካከል ያለው የሥልጣን ሽኩቻ ጦር እንዲማዘዙ አድርጓቸዋል።ሐሙስ ዕለት ለተባበሩት መንግሥታት ንግግር ያደረጉት ጀነራል አል ቡርሃን የሳቸው ፓርቲ የሰላም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጠዋል።

“ጦርነቱን ለማቆምና እና የሕዝባችንን ስቃይ ለመግታት ዝግጁ ነን” ነገር ግን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ፈቃደኛ አይደለም ብለዋል።ነገር ግን በቅፅል ስማቸው ሄሜቲ ተብለው የሚታወቁት ተቀናቃኛቸው ጀነራል ደጋሎ ለተመድ በላኩት ተንቀሳቃሽ ምስል ግጭቱን በንግግር ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።ሁለቱ የጦር ጀነራሎችን ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ አሜሪካ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ግብጽ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍17🔥21
"የተባበሩት መንግሥታት ፀጥታ ምክር ቤት ረብ የለሽና ኢ-ዲሞክራሲያዊ ነው" የኬንያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ

የኬንያ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ መድረክ ላይ ተገኝተው የተመድ ፀጥታ ምክር ቤትን ረብ የለሽና ኢ-ዲሞክራሲያዊ ሲሉ ተናገሩ።

አቶ ሩቶ በንግግራቸው ወቅት የሄይቲን ጉዳይ ነቅሰው በማንሳት፤ የተባበሩት መንግሥታት ሄይቲን ገጥመዋት ላሉት ተግዳሮቶች ትድግና አስቸኳይ ፍኖተ ካርታ ዘርግቶ ሕብረ ብሔራዊ ፀጥታ አስከባሪ ኃይል ድጋፍ እንዲልክም አሳስበዋል።

የኬንያው ፕሬዚደንት የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ተቋማትን አስመልክተው የተናገሩ ሲሆን፤ አክለውም፤

"የተባበሩት መንግሥታት ፀጥታው ምክር ቤት ረብ የለሽ፣ ኢ-ዲሞክራሲያዊ፣ አካታች ያልሆነ፣ ሁሉን አቀፍ ውክልና የለሽ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የሚሻ ካለ፤ በእዚያ ሳቢያ በዓለማችን ላይ በአሁኑ ወቅት ተንሰራፍቶ ያለው የተወሰኑ ተዋንያን ተጠያቂነት ሳያገኛቸው የሉላዊ ጉዳዮች መከወን ነው" ብለዋል።

[SBS]
@YeneTube @FikerAssefa
👍529🔥4
በነሐሴ ወር የሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት 28.2 በመቶ ሆኖ ተመዘገበ!

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በነሐሴ ወር የሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽብት 28.2 በመቶ መመዝገብን አሳዉቋል።

አገልግሎቱ በወሩ ዉስጥ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት የምግብ ዕቃዎች ዋጋዉ 26.5 በመቶ ድርሻ መያዙን ገልፆ ምግብ ነክ ያልሆኑ ደግሞ 30.7 በመቶ ድርሻ መያዛቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስፍሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍14👎7🔥32
በአዲስ አበባ ከተማ ሽንኩርት በኪሎ ከ95 ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑ ሸማቾች ተናገሩ

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ አንድ ኪሎ  ሽንኩር ከ95 ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑን ነዋሪዎች ለብስራት ተናግረዋል።

እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ በየጊዜው በአትክልት ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ ከገቢያቸው ጋር ሊመጣጠን እንዳልቻለ እና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ተናግረዋል።ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ የከተማ አስተዳደሩ ከአምራች አርሷ አደር ማህበራ እና ከክልሎች ጋር በመቀናጀት ለነዋሪው ሽንኩርት እያቀረበ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በዋነኛነት 72 የሚደርሱ የእሁድ ገበያ ቦታዎች እንዳሉ እና በከተማ ውስጥ የተገነቡ ወደ አገልግሎት እየገቡ ያሉ የአትክልትና የፍራፍሬ ማቅረቢያ ማዕከላት ውስጥም የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ባማከለ ሁኔታ እንዲሸጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።በዚህ ገበያ ላይ  እንደየ ጥራቱ ደረጃው ሽንኩርት ከ47 ብር እስከ 62 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ሰውነት ከበአሉ ወዲህ ጭማሪ መኖሩን እኛም ታዝበናል ያሉ ሲሆን በመደበኛ ገበያ ውስጥ  አላስፈላጊ እና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪዎች መታየታቸውን ገልፀዋል።ለዚህም የደላሎች ጣልቃ ገብነት ተገቢ ላልሆነው እና ምክንያታዊ አይደለም ለተባለው የዋጋ ጭማሪ ሚና አላቸው።

እንደ አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ይህ የዋጋ ጭማሪ ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንደማያውቅ እና እንደ ቢሮም የገበያ ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ምንም እንኳን አቶ ሰውነት በእሁድ ገበያዎች ላይ ሽንኩርት ከ47 እስከ 62 ብር እየተሸጠ ነው ቢሉም ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ገበያዎች ላይ ባደረገው ምልከታ ከተገለፀው ዋጋ በላይ እንደሚሸጥ ከሸማቾች ሰምቷል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
👍298👎8🔥3
የዐማራ ክልል ግጭት መቀጠሉን ተከትሎ በመጪው ወር ሊደረግ የነበረው የጣና ፎረም ስብሰባ ተላለፈ!

በኢትዮጵያ ዐማራ ክልል የሰው ህይወት የቀጠፈው ግጭት መቀጠሉን ተከትሎ፣ በአፍሪካ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር የተቋቋማው ጣና ሮረም በመጪው ጥቅምት ሊያደርገው የነበረውን ስብሰባ ወደ ሚያዚያ አስተላልፏል።

መድረኩ ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ ስብሰባው የተላለፈው “ባልተጠበቁ ሁኔታዎች” ምክንያት ነው ብሏል። ጣና ፎረም በየዓመቱ በዐማራ ክልል ይደረግ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን የፌዴራል መንግሥት በክልሉ ያሉ ኃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት በሚያደርገው ጥረት አካባቢው የግጭት አውድማ ሆኗል ሲል አሶስዬትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል።

ጣና ፎረም የተባለው ስብስብ “ለአህጉሪቱ አሳሳቢ ችግሮች አፍሪካ-መር መፍትሄ” ለመሻት እንደሚጥር ይናገራል። “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በማዕከል ሥልጣንን ለመቆጣጠር የሚያደርጉትን ጥረት የሚገዳደሩ አንዳንድ ብሔሮች በመኖራቸው፣ አሳሳቢ የተባሉት አንዳንዶቹ ችግሮች በፎረሙ ጓሮ እየተከሰቱ ናቸው” ሲል ዘገባው አክሏል።

ላሊበላን ጨምሮ በክልሉ ባሉ ከተሞች ሕይወት የቀጠፉ የድሮን ጥቃቶች እና የከባድ መሣሪያ ድብደባዎች መካሄዳቸውን፣ ፎረሙ በሚካሄድባት ባህር ዳር ከተማም ጦርነት መካሄዱን፣ ከሰማይ ወታደራዊ አውሮፕላኖችን እንዲሁም በጎዳናዎች ላይ ተኩስ እንደሚሰሙ ነዋሪዎች መናገራቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጣና ፎረም አጋሮች መሆናቸውን ያመለከተው ሪፖርቱ፣ ከፎረሙ አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ ጠቁሟል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍26👎43
የBETTING ቤት ለመክፈት የሚያስለፈጉ የThermal Printer በUSB እና Ethernet cable የሚሰራውን Xprinter Original Printer እና POZONE BARCODE SCANNER አሰግብተንልዎታል።

ዋጋችን በአስተያየት ነው የትም አወዳድረው ምርጫዎን እኛን ያድርጉ።

Inbox us on Telegram
https://tttttt.me/gamerszone1
#ይደውሉልን - 0911061990
#ይደውሉልን - 0947152583
👍31