YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጀንቦሮ ሪል እስቴት በ370 ሚሊዮን ብር ያስገነባቸውን ቤቶች በዛሬው ዕለት አስመረቀ!

ጀንቦሮ ሪል ስቴት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ሁለተኛውን የሪልስቴት ኘሮጀክት ነው ያስመረቀው።በዛሬው ዕለት የተመረቀው ሁለተኛው ኘሮጀክት 72 መኖሪያዎችን የሚይዝ በ1200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው ተብሏል።

ለባለቤቶቹ የተላለፉት እነዚህ ቤቶች 6 መቶ70 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል ነው የተባለው።ለህንፃው አገልግሎት የሚሰጡ የከርሰ ምድር ውሃ፣ሊፍት፣የደህንነት ካሜራዎችና ጀነሬተር እንደተገጠመለትም ተሰምቷል።

በቀጣይ በሳርቤት ሳይት 5ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር እንደሚገነባም ገልጿል።በመጪው አምስት አመታት ውስጥ 5000 አፖርትመንቶችን ፣ ቪላዎችን እና የንግድ ስቆችን ለቤት ገዥዎች በጥራት ሰርቶ ለማጠናቀቅ ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
"በመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ የተደረገ ምንም ዓይነት ጭማሪ የለም"- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

በመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ የተደረገ ምንም ዓይነት ጭማሪ የለም ሲል የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አስታወቀ።በአንዳንድ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች በመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ ጭማሪ ተደርጓል በሚል እየተሠራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ እና ከእውነታ የራቀ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።

ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ የሚገኙ የፌዴራል መንግሥት ይዞታዎችን እና ቤቶችን እያስተዳደረ እንደሚገኝ አስታውቋል።በአሁኑ ሰዓት ኮርፖሬሽኑ 20 ሺህ የሚጠጉ የመኖሪያ እና የንግድ ቤት ደንበኞች እንዳሉት እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባካሄደው የተቋም ግንባታ ለደንበኞቹ ፈጣን እና ዘመናዊ አገልግሎት እያቀረበ እንደሚገኝም አመልክቷል።

ኮርፖሬሽኑ ባቋቋማቸው የነዋሪች ማኅበራት እና በዘረጋው የመረጃ ሥርዓት መሠረት ከተከራይ ደንበኞቹ ጋርም በቅርበት እየሠራ መሆኑን ጠቁሟል።ይሁንና ከሰሞኑ በአንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ መገናኛ አውታሮች የኮርፖሬሽኑን ሎጎ እና ስም በመጠቀም ኮርፖሬሽኑ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ኪራይ ጭማሪ እንዳደረገ ተደርጎ ሐሰተኛ ዜና መውጣቱን ማረጋገጥ መቻሉን ነው ኮርፖሬሽኑ ያስታወቀው።

ኮርፖሬሽኑ የኪራይ ማሻሻያ ማድረግ ሲያስፈልገው ሳይንሳዊ የጥናት ውጤቶችን መሠረት አድርጎ እና ከተከራይ ደንበኞች ጋር አስፈላጊውን ውይይት እና መተማመን ሲፈጠር ብቻ ማሻሻያ ሊያደረግ እንደሚችል እየታወቀ በማኅበራዊ ሚዲያ የኮርፖሬሽኑን ሎጎ እና ስም በመጠቀም የወጣው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን እና በአሁኑ ሰዓት ምንም ዓይነት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ማሻሻያ አለማድረጉን አመልክቷል።

በመኖሪያ ቤቶች ላይ የኪራይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በነዋሪዎች ማኅበራት እና በተዘረጋው የመረጃ ሥርዓት መሠረት ለተከራይ ደንበኞች እንደሚያሳውቅ ገልጿል።ተከራይ ደንበኞች ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በኩል እንደሚያገኙ እና ከሐሰተኛ መረጃ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ኮርፖሬሽኑ ማሳሰቡን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍31
አርባምንጭ አቅራቢያ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች 18 ሰዎች ሳይገድሉ እንዳልቀረ ተገለጸ!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ 18 ሰዎች በፀጥታ አባላት መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ ፡፡ ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የግድያ ድርጊቱ የተፈጸመው በጋሞ ዞን አስተዳደር አርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ ነው ፡፡

የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው የጋሞ ዞን አስተዳደርና የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አባላት ወደ ቀበሌው መግባታቸውን ተከትሎ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡ የግጭቱና የግድያው መንስኤ በአርባ ምንጭ ወረዳ ዙሪያ ሥር ሲተዳደር የቆየውና ሻራ የተባለው ቀበሌ ወደ አርባ ምንጭ ከተማ ይካለል በሚል በተነሳ አለመግባባት መሆኑን ነው የአይን እማኞች የገለጹት፡፡

ዶቼ ቬለ DW በግጭቱ ጉዳት ደርሶባቸው በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ይገኛሉ ሥለተባሉት ተጎጂዎች ሁኔታ ለመጠየቅ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ወንደሰን ወርቁ ጋር ደውሏል ፡፡ ይሁንእንጂ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከደቂቃዎች በኋላ ደውሉልኝ ባሉት መሠረት ቢደወልላቸውም ሥልካቸው በመዘጋቱ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም ፡፡ ያም ሆኖ የሆሰፒታሉ ባልደረባ ነኝ ያሉ አንድ የህክምና ባለሙያ 12 ሰዎች መሞታቸውና ሌሎች በጥይት ተመተው የመጡ 15 ሰዎችን ማየታቸውን ለዶቼ ቬለ አረጋግጠዋል ፡፡

ዶቼ ቬለ DW ለተጨማሪ አስተያየት የጋሞ ዞን ፖሊስንም ሆነ የዞኑ መንግሥት ኮሚኒዩኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ጋር ቢደውልም የሥራ ሃላፊዎቹ ጥሪ ባለመመለሳቸው አስተያየታቸውን ማካተት አልተቻለም ፡፡ ያምሆኖ የዞኑ መንግሥት ኮሚኒዩኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በሻራ ቀበሌ ተከሰተ በተባለው ጉዳይ ዙሪያ በተረጋገጠ የፌስ ቡክ ገጹ መግለጫ አውጥቷል ፡፡ መምሪያው በዚሁ መግለጫው በቀበሌው ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ለማፍረስና የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ለማደፍረስ ታጥቆ ሲንቀሳቀስ ነበር ባለው ኃይል ላይ የተሳካ የኦፕሬሽን ሥራ መከናወኑን ገልጿል፡፡በተካሄደው ኦፕሬሽንም ድምፅ አልባ የሆኑ ስለታማ መሣሪያዎችን ጨምሮ ክላሽ፣ ሽጉጥና በርካታ የግልና የቡድን ጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን መምሪያው አስታውቋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ልዑል ገ/ስላሴ በወንዶች ማራቶን 3ኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳልያን ለሀገራችን ኢትዮጵያ አስገኝቷል!

ውድድሩን ዩጋንዳ በበላይነት ስታጠናቅቅ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለእስራኤል የሚሮጠው ማሩ ተፈሪ ሁለተኛ ሆኗል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።

በማንኛውም Social Media  Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::

ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።

Telegram: @adsommar
📞0929334267
👍3
Forwarded from YeneTube
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
👍1
ከ272 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

የጉምሩክ ኮሚሽን ከነሀሴ 12 ቀን እስከ 18/2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 151 ነጥብ 9 ሚሊዮን የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 120 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 272 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዛቸውን አስታወቀ፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር የላቀ አፈጻጸም የተመዘገበ ሲሆን በዚህም ሞያሌ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርት እና ድሬድዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡በቅደም ተከተላቸውም 55 ሚሊዮን፣ 26 ሚሊዮን እና 22 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ 14 ግለሰቦች እና ስምንት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የኢትዮጵያ መንግሥት የሕዳሴ ግድብን አራተኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጀመሩ ተሰምቷል።

የግድቡ የዘንድሮ ክረምት ውሃ ሙሌት በነሃሴና መስከረም እንደሚካሄድ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ. እንዲኹም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ ቀደም ሲል መናገራቸው ይታወሳል። የውሃ ሙሌቱ በሰከንድ 1 ሺህ 200 ሜትር ኪዩብ መኾኑ ተሰምቷል።መንግሥት ግድቡ በዘንድሮው ክረምት እንዲይዝ ያቀደው የውሃ መጠን፣ ከ10 ነጥብ 8 እስከ 11 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ነው።

Via Wazema
Photo: File
@YeneTube @FikerAssefa
👍2👎1
አንጋፋው ቦክሰኛ በቀለ አለሙ (ጋንች) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ መድረክ በመወከል ቀዳሚ ከሆኑት መከካል አንዱ የሆነው ቦክሰኛ በቀለ አለሙ (ጋንች) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።የ3 ጊዜ የኦሎምፒክ ተሳታፊው በቀለ ዓለሙ በ82 ዓመቱ ነው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

ቦክሰኛ በቀለ በሮም፣ በቶክዮ እና በሜክሲኮ ኦሎምፒክ በቦክስ ዘረፍ ኢትዮጵያን ወክሎ ተሳትፏል።ከሜሲኮው ኦሎምፒክ የተሳትፎ ሜዳሊያም ያገኘ ሲሆን የሌጎስ የአፍሪካ ሻምፒዮን መሆኑም የህይወት ታሪኩ ያስረዳል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በፀጥታ ችግር ምክንያት የአቅርቦት እጥረት እንዳጋጠመዉ አስታወቀ።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ባለዉ የፀጥታ ሁኔታ ሆስፒታሉ ከፍተኛ የሆነ የግብዓት አቅርቦት እጥረት አጋጥሞታል ተብሏል።የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር መርቀኒ አወድ ከኢትዮ ኤፍ እም ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ከክልሉ ባሻገር በአቅራቢያዉ ባሉ የኦሮሚያ ወረዳዎች ጭምር ያለዉ የፀጥታ ስጋት ሳቢያ ሆስፒታሉ ማስተናገድ ከሚችለዉ ታካሚ በላይ በማስተናገድ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም በክልሉ ባለዉ የፀጥታ ሁኔታ የአቅርቧት እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተናቸዉ እንደሆነ ይናገራሉ።ሆስፒታሉ ከፍተኛ የኦክስጅን እጥረት እንዳጋጠመዉና ይህም ለስራቸዉ ፈታኝ እንደሆነባቸዉ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደ ቤንሻንጉል ባሉ ክልሎች ላይ የክልሉ ህዝብ ባለበት ሆኖ አገልግሎት እንዲያገኝ በተይም እንደ ኦክስጅን፣የላብራቶሪ ዕቃዎችን አሟልቱ አገልግሎት እንዲያገኙ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

በክልሉ ከፀጥታ ጋር በተያያዘ በአምቡላንስ ሪፈር ማድረግ ከቆመ ወዲህ ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ ታካሚዎችን እየላክን ነዉ ያሉት ዶክተር መርቀኒ በዚህም ህብረተሰቡ ክፉኛ ተማሯል ብለዋል። በክልሉ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ታካሚዎችን በአሞቡላንስ ሪፈር መላክ ከቆመ አራት አመት እንደሆነዉ ተሰምቷል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍4
አቶ በቀለ ገርባ በአሜሪካ ሀገር ጥገኝነት መጠየቃቸውን አሳወቁ።

ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበሩት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ተቀዳመ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ በቀለ ገርባ በፓርቲያቸው የነበራቸውን ተሳትፎ አብቅተው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናገሩ።

አቶ በቀለ ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ " በሰላማዊ መንገድ ለመታገልም ሆነ በግል በነጻነት መኖር " አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል የሆኑት አቶ በቀለ፣ በውጭ አገር ሆነው ሥልጣኑን ይዘው መቀጠጣለቸው ጠቃሚ ስላልሆነ እራሳቸውን ከፓርቲው ለማግለል መወሰናቸውን ተናግረዋል።

አቶ በቀለ ገርባ ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከት ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ውለው ለ18 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። አሜሪካ ከሄዱ 1 ዓመት ከሶስት ወር ሆኗቸዋል።

አቶ በቀለ ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ዓላማቸው የእርሳቸውን ከእስር መለቀቅ ሲጠይቅ ለነበረው የዳያስፖራ ማኅብረሰብ ምስጋና ለማቅረብ ነበር።

ነገር ግን አሜሪካ በቆዩባቸው ያለፉት 15 ወራት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በመቀየሩ " ወደዚያ አገር መመለሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም " በማለት እዛው ጥገኝነት መጠየቃቸውን እና ከፓርቲው ኃላፊነትም እራሳቸውን ማግለላቸውን ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍71
የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ!

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 22፤ 2015 በነበረው የችሎት ውሎ ከቀድሞው የክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር በአንድ መዝገብ ከተከሰሱ ግለሰቦች መካከል 16 ተከሰሾችን በነጻ ማሰናበቱን የአቶ አብዲ ጠበቃ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

የአቶ አብዲን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት፤ ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ የነበረው ዐቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ ላይ ብይን ለመስጠት ነበር። በዚህም መሰረት ጉዳያቸው በችሎቱ እየታየ ካሉት 42 ተከሳሾች ውስጥ 26 የሚሆኑት በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።

በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ከተባሉት ተከሳሾች መካከል፤ የሶማሌ ክልልን ለስምንት ዓመት ያስተዳደሩት አቶ አብዲ መሐመድ ይገኙበታል። “አብዲ ኢሌ” በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር እንዲከላከሉ የተበየነባቸው፤ “የጦር መሳሪያ ይዞ በማመጽ፣ ወይም የእርስ በርስ ጦርነት በማስነሳት በመንግስት ላይ የሚደረግ ወንጀልን” ፈጽመዋል በሚል በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ዋና ክስ መሆኑን ጠበቃቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👍42
ነገ ለአትሌቶች አቀባበል ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተካፈለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አቀባበል ሲባል ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሠረት ከጠዋቱ 1፡ 00 ጀምሮ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከሚያርፉበት ሒልተን ሆቴል ድረስ ደማቅ የአቀባበል ስነ-ስርዓት እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቅዱስ እስጢፋኖስ ወደ አራት ኪሎ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ በደጎል አደባባይ ወደ ቸርችል ጎዳና፣ ከድላችን ሀውልት በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ከዚያም በሚያርፉበት ሒልተን ሆቴል አካባቢ ለተወሰነ ሰዓት መንገዱ ለትራፊክ ዝግ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

አሽከርካሪዎችም ይህንን በመገንዘብ በቦታው ላይ የሚገኙ የትራፊክ ፖሊስ አባላትን መረጃ በመጠየቅና ተባባሪ በመሆን ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍7
የአፋር ክልል በድንገተኛ ህክምና ከፍተኛ የሞት ምጣኔ የተመዘገበበት ክልል መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአፋር ከልል ከፍተኛ ድንገተኛ ታካሚዎችን በማስተናገድም ግምባር ቀደም መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር ኢሊባቡር ቡኖ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በክልሉ ያለው የድንገተኛ ህክምና ሞት ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ድንገተኛ የጤና እክሎች ከክልል ክልል ከፍያለ መሆኑን የሚገልፁት ዶክተር ኢሊባቡር አንድ አንድ የዪኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ላይ በድንገተኛ ክፍሎች የሚሞቱ ታካሚዎች ከ197 በመቶ በላይ የሚደርስበት ወቅት መኖሩን ያነሳሉ፡፡

የሞት ምጣኔው ከፍ የሚለው በቂ የህክምና ባለሙያ ባለመኖሩ፣በቂ የህክምና ክፍል ያለመኖሩ፣በቶሎ ሪፈር ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ሪፈር ያለማድረግ ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ስራ አስፈፃሚው በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የድንገተኛ ህክምና ውስጥ በርካታ ታካሚዎች ህይወታቸውን እያጡ መሆኑን ለጣብያችን አስረድተዋል፡፡

በዚህም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 37 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ ሆስፒታሎች ከሆስፒታል ጋር ጥምረት በመፍጠር ትልልቅ የሆኑ ሆስፒታሎች አነስተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ህክምና ተቋማት የሚረዱበት ሲስተም መፈጠሩ ተገልፃል፡፡የድገተኛ ክፍል ሞትን ለመቀነስ፣ሰርጀሪ በአግባቡ እንዲሰራና ያለባቸውን የግብዓት እጥረት ለመቅረፍ የሚሰራ ሲስተም መሆኑም ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍18🔥1
ዳሸን ባንክ ከሁለት የአውሮፓ ተቋማት የ40 ሚሊየን ዶላር ብድር ማግኘቱን ተናገረ፡፡

ባንኩ 40 ሚሊየን ዶላር ብድር ያገኘው ከእንግሊዙ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ('ቢ አይ አይ') እና ከኔዘርላንድሱ የስራ ፈጠራና ልማት ባንክ ከሆነው ኤፍ ኤም ኦ መሆኑ በላከው መግለጫ አስረድቷል፡፡ሁለቱ ተቋመት እያንዳንዳቸው 20 ሚሊየን ዶላር በድምሩ 40 ሚሊየን ዶላር ብድር ለዳሸን ባንክ ማቅረባቸውን ተነግሯል፡፡

የብድር ገንዘቡ ኢትዮጵያ ለውጪ ገበያ የምታቀርበውን የግብርና ምርት ለማሳደግ እና በእጅጉ አስፈላጊ የሆነውን የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ለማሻሻል ያስችላል ተብሎለታል፡፡በተለይ በእርሻ ስራ ላይ ለተሰማሩ ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሟላት ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ አስተዋጽኦ ያበረክታል መባሉን ሰምተናል፡፡

ዳሸን ባንክ ብድሩን በማግነቱ ዓይነተ-ብዙ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ ለማቅረብ እንደሚያግዘው ጠቅሷል፡፡ይህም በአመራረት፣ በማጓጓዝ እና በማቀናበር ሂደቶች ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሪ ማቅረብን ይጨምራል ተብሏል፡፡

በዚህ ትብብር 'ቢ አይ አይ' እና 'ኤፍ ኤ ምኦ' የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ በ2021 አዲስ ባወጣው የውጭ ማንዛሪ ማቀላጠፊያ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ለሚገኝ የፋይናንስ ተቋም በውጭ ምንዛሪ የቀረበ የረዥም ጊዜ ብድር ሲሰጡ የመጀመሪያዎቹ ናቸው ሲል ባንኩ አስታውሷል፡፡

በግብርና ለተሰማሩ የንግድ ተቋማት የሚቀርብ ፋይናንስ ከአበባ እስከ ቡና እና የቁም ከብት ድረስ የተሻሻሉ የአመራረት ዘዴዎችን ለማስተዋወቅ፣ ጥራትን ለማሳደግ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ለማሟላት እና እሴት ለመጨመር የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ የ40 ሚሊዮን ዶላሩ ብድር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በእጅጉ እነደሚያስፈልግ አንስተው ለተገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አለን" ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ዳሸን ባንክ ያገኘው የ40 ሚሊዮን ዶላር ብድር በ3 ዓመት ውስጥ የሚመለስ መሆኑን ባንኩ ነግሯል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍3112👎1