YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቅዱስ ሲኖዶስ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል እየተደረጉ ባሉ ግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖቻችን ካለፈው የጦርነት ውጤት በመማር የተፈጠረውን ችግር በጥበብና በማስተዋል እንዲሁም በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ወቅታዊ ሀገራዊ ሰላምን በተመለከተ አጀንዳ በመቅረጽ በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ  መግለጫ ሰጥቷል ፤ በመግለጫውም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም መደፍረስና የእርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት የበርካታ ወገኖቻችን ውድ ሕይወት እያለፈ እና በርካታ የሀገርና የሕዝብ ሀብትና ንብረት እየወደመ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ትገልጻለች ብሏል።

ሰላም ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ፍጡራን መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ሰላም ከሌለ ቀድሶ ማቁረብ፣ ነግዶ ማትረፍ፣ አርሶ ማምረት፣ ተምሮ ማስተማር  ወልዶ ማሳደግ፣ ወጥቶ መግባት፣ አገር መምራትና ማስተዳደር አይቻልም ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅሉ ሰላም ሲጠፋ አብረው የሚጠፉ መልካም እሴቶቻችን ብዙ ናቸው፡፡ በቅርብ ጊዜ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ጦርነት የበርካታ ወገኖቻችንን ሕይወት የቀጠፈ ከመሆኑም በላይ ከሞት የተረፉት ወገኖቻችንም ለስደትና ለረሀብ የዳረገ፣ ለአካልና ለእእምሮ ስብራት ያጋለጠ ከመሆኑም በተጨማሪ በርካታ አድባራትና ገዳማትን እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትን ያፈረሰ እና መተኪያ የሌላቸውን ውድ ቅርሶቻችንን ያወደመ እጅግ በጣም አስከፊ ተግባር መሆኑ ይታወሳል።

በመሆኑም፡-
በሀገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነትና ግጭት ተወግዶ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ልንማጸን ይገባል ሲል የገለጸ ሲሆን በሀገራችን በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሰላም እጦትና የእርስ በርስ ግጭት ወደፊት ሊያስከትል የሚችለው ችግር ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለአገራዊ ሰላም የበኩላቸውን ጥረት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ መልእክቱን አስተላልፏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመጨረሻም በየትኛውም የሀገራችን ክፍል እየተደረጉ ባሉ ግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖቻችን ካለፈው የጦርነት ውጤት በመማር የተፈጠረውን ችግር በጥበብና በማስተዋል እንዲሁም በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ  ተወያይተው እንዲፈቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ከአደራ ጋር ታስተላልፋለች ሲል መልዕክቱን ማስተላለፉ ተገልጿል።

ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በቅዱስ ሲኖዶሱ የተወገዙ የትግራይ ክልል አባቶች ውሳኔውን እንደሚቃወሙና ዳግም እንዲያጤነው ጠየቁ!

በትግራይ ክልል የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ሓላፊዎች፣ በአክሱም ከተፈጸመው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እና ሹመት እንዲሁም፣ ‘መንበረ ሰላማ ከፍተኛ ቤተ ክህነት’ በሚል ከሚያደርጉት ክልላዊ እንቅስቃሴ ጋራ በተያያዘ፣ ትላንት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈባቸውን ውግዘት፣ “ከንቱ ውግዘት ነው” ሲሉ እንደማይቀበሉት ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በአክሱም የተፈጸመውን ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት የሰጡ እና የተቀበሉ፣ እንዲሁም ‘መንበረ ሰላማ’ በሚል በክርስቲያናዊ ትውፊት የማይታወቅ እንቅስቃሴ ያመነጩ እና ያስተባበሩ፥ አራት ሿሚ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ዘጠኝ ተሿሚ መነኰሳትንና ሁለት ሌሎች ግለሰቦችን፥ ከማዕርገ ክህነታቸው በመሻር፣ ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እና አባልነት በመለየት ማውገዙን፣ በትላንትናው መግለጫው አስታውቋል፡፡

ለቅዱስ ሲኖዶሱ የውግዘት መግለጫ መልስ የሰጡት፣ በክልሉ የሚገኙ አባቶች፣ ውግዘቱ፥ የትግራይን ሕዝብ ያለአባት ለማስቀረት የተላለፈ እና በጦርነት ጊዜ የተፈጸመው በደል ቅጥያ ነው፤ ብለዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
   "Do or Die..!" 

የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!

ቤት ...
መሬት...
መካዝን...
ኢንዳስትሪ...
ኢንቨስትመንት...
ሪል ስቴት ..
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..

አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው

..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..

መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!

   +251937736408
https://tttttt.me/shger21
  Inbox @FikreabAmanu

ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን  ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
    🌹 የኔክሰስ ሆቴል
    🌹 የግራንድ ሆቴል
    🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
    🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
        ✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
        ✍️50/50  ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
                 09 77 64 18 19

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=ያለው
     🔹ደሞዝ=6000-10,000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
👍1
በአማራ ክልል ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ተወሰነ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በአማራ ክልል ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወሰነ።

የክልሉ መንግስትም በአማራ ክልል ያጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ፣ በክልሉ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ፣ ሁኔታውን በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ፣ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት እንዲደነግግ እና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ ማቅረቡን አስታውሷል፡፡

በመሆኑም መደበኛ የህግ ስርዓትን መሰረት አድርጎ ይህን ፈር የለቀቀ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በህገመንግስቱ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ስላለበት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆነ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው  ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ወስኗል።

ውሳኔው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ መፈጸም እንደሚያስችላቸው የታመነበት በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ሆኖ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ነፃነቱ ተጠብቆ መንቀሳቅስ እንዲችል፣ በትምህርት ዘርፍ ለተጀመረው የሪፎርም እንቅስቃሴ ፈር ቀዳጅ ሆኖ እንዲወጣ እድል ይፈጥርለታል ተብሏል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ስርዓትን በቀዳሚነት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተምሳሌት እንደሚሆን ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የኮርፓሬት ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ ዓባይነህ ሙሉጌታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የኮርፓሬት ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ ዓባይነህ ሙሉጌታ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት (ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም) በ37 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍1
ሀዋሳ ናችሁ?

የዴሊቨሪ ሀዋሳን መተግበሪያ ያውርዱ በመጀመሪያ ኦርደሮ ቦነሶችን ያግኙ።

ሲመዘገብ 50 ብር ይሰጦታል

👌 shorturl.at/bKVZ3
#ሰበር_ዜና

የተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ

የአብን ፓርቲ አባልና ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ሃምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ አማካይነት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች በማህበራዊ ትስስር ገፆች በስፋት እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

የፓርቲው አባል እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ለእስራቸው ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል።

አባሉ ምንም እንኳን ያለ መከሰስ መብት ቢኖራቸውም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አማካይነት በቁጥጥር ስር ሳይውሉ እንዳልቀረ ተጠቁሟል።

ያም ሆኖ ግን አቶ ክርስቲያን ታደለ ታስረዋል መባሉን ተከትሎ ከፓርቲያቸው አብን ሆነ እስሩን ፈፅሟል ከተባለው የመንግስት አካል በኩል የተሰጠ ምላሽ እና ማብራሪያ በይፋ አልወጣም።

Via ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍3
Forwarded from YeneTube
   "Do or Die..!" 

የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!

ቤት ...
መሬት...
መካዝን...
ኢንዳስትሪ...
ኢንቨስትመንት...
ሪል ስቴት ..
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..

አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው

..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..

መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!

   +251937736408
https://tttttt.me/shger21
  Inbox @FikreabAmanu

ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን  ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0
1👍1
Forwarded from YeneTube
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
    🌹 የኔክሰስ ሆቴል
    🌹 የግራንድ ሆቴል
    🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
    🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
        ✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
        ✍️50/50  ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
1