‹‹ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ፒኖ ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት ምክንያት የተገደሉ ሰዎች አስክሬኖች አልተነሱም ›› - ኢሰመጉ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ኢሰመጉ) ይህን ያለው ‹‹ በጋምቤላ ክልል ያለው የጎሳ ግጭት በቂ ትኩረትና ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል! ›› ሲል ሰይሞ ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነው፡፡
‹‹ በጋምቤላ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል ›› ያለው ጉባዔው ‹‹ በክልሉ ኢታንግ ልዩ ወረዳ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ቀበሌዎች ውስጥ ባሉ የአኝዋ እና የንዌር ጎሳዎች መካከል ግጭቱ መጀመሩን ›› አስታውሷል፡፡
ግጭቱ ‹‹ እየተስፋፋ የሄደው በዋናነት ሁለቱ ጎሳዎች በሚገናኙበት ኢታንግ ልዩ ወረዳ ውስጥ ባሉ ቀበሌዎች እና በጋምቤላ ከተማ ነው ›› ብሏል፡፡
‹‹ ኑዌር እና በአኝዋ ጎሳዎች መካከል በተደጋጋሚ ጊዜ የጎሳ ግጭቶች እንደሚነሱ ›› ያስታወሰው መግለጫው ‹‹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተወሰኑ መሻሻሎች ታይተው የነበረ ቢሆንም ይህ ግጭት ዳግም ተቀስቅሷል ›› ሲልም አመልክቷል፡፡
‹‹ ይህ የጎሳ ግጭት በጋምቤላ ክልል በተለይም በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በስፋት የነበረ በመሆኑ ምክንያት በእነዚህ አካባቢዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት ውድመት እና መፈናቀል ደርሷል ›› ብሏል፡፡
‹‹ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ አራት ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን እና በወረዳው ባሉ የተለያዩ ግጭቱ ከፍተኛ በነበረባቸው ቀበሌዎች ላይ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ›› ጉባዔው ከአካባቢዎቹ ካሰባሰባቸው መረጃዎች መረዳት መቻሉን ጠቅሷል፡፡
‹‹ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ፒኖ ቀበሌ ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በጥቃቱ ምክንያት የተገደሉ ሰዎች አስክሬኖች እንዳልተነሱ፣ በእዚህ የጎሳ ግጭት ላይ የተለያዩ መሳሪያዎችን የታጠቁ ሰዎች እየተሳተፉበት በመሆኑ የጉዳቱን መጠን ከፍተኛ እንዳደረገው ›› አመልክቷል፡፡
‹‹ በአኝዋ ዞን ጎግ ወረደ ፑኝዶ ወረዳ አሁን ላይ የተሻለ የጸጥታ ሁኔታ ቢኖርም በአካባቢው በተደጋጋሚ ተመሳሳይ የጎሳ ግጨቶች ስለሚነሱ ስጋቶች መኖራቸውን እንዲሁም ይህንን ግጭት ለመቆጣጠር የክልሉ መንግስት በአጠቃላይ ክልሉ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ሰዓት እላፊ ማወጁንና የክልሉ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት ግጭቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ መሆኑን ›› ካሰባሰብኳቸው መረጃዎች ተርጅቼያለሁ ብሏል፡፡
የጉባዔው መግለጫ ሲቀጥል ‹‹ በተጨማሪም በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በእርስ ግጭት ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በጋምቤላ ክልል በሚገኙ አምስት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ መስፈራቸውን ›› ጠቁሟል፡፡
‹‹ የስደተኞቹ ቁጥር መጠለያ ጣቢያዎቹ ከሚችሉት አቅም በላይ መሆኑንና የሰፈሩባቸው አካባቢዎች ውስጥ ያሉት አንዳንድ የተቀባይ ማህበረሰቦች ከስደተኞቹ ጋር ባለው የጎሳ ልዩነት ምክንያት የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ›› በመግለጫው አትቷል፡፡
‹‹ ይህም ጉዳይ ስደተኞቹን እና ተቀባይ ማህበረሰቦችን ባማከለ ውይይት ላይ በተመሰረተ ዘላቂ መፍትሔ ሊፈታ እንደሚገባውና ይህ ካልሆነ ግን ችግሮች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ›› ኢሰመጉ ከአካባቢዎቹ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ገልፆል፡፡
ጉባዔው በመግለጫው ማጠቃሊያ አምስት ምክረ ሃሳቦችን አስቀምጧል፡፡ በዚህም ‹‹ የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት በክልሉ በተደጋጋሚ በአኝዋ እና በኑዌር ጎሳዎች መካከለ ለሚነሳው ግጭት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ ›› ጠይቋል፡፡
‹‹ በጋምቤላ ክልል በተለይም ውጥረት በተስፋፋባቸው በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ የክልሉ መንግስት ያለውን ስጋትእንዲቆጣጠርና የሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ›› የጠየቀበትም በምክረ ሃሳቡ ውስጥ ተካትቷል፡፡
[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa

የኦሮሞ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ ተወካዮች እና አምባሳደር ማይክ ሐመር ተወያዩ!
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር፣ በዩናይትድ ስቴትስ ከትውልደ ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋራ እንደተወያዩ፣ የኦሮሞ ቅርስ አመራር እና ተሟጋች ማኅበር አስታወቀ።
የኦሮሞ ዳያስፖራ ተወካዮቹ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጥሎት የነበረውን የርዳታ ማዕቀብ መልሶ ማንሣቱ እንዳሳዘናቸው፣ ለአምባሳደር ማይክ እንደተናገሩ፣ መግለጫው አመልክቷል።
ምክንያት ያደረጉትም፣ በኢትዮጵያ፣ አሁንም አለ ያሉትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በመጥቀስ እንደኾነ፣ ማኅበሩ ገልጿል።አምባሳደር ሐመር በበኩላቸው፣ የርዳታ ማዕቀቡን የማንሣት ውሳኔ ላይ የተደረሰው፣ ከሀገር ውስጥም ኾነ ከዓለም አቀፍ አካላት በተገኘው መረጃ መሠረት፣ “በተለይም፣ ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚፈጽመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መቀነስ በማሳየቱ ነው፤” ማለታቸውን መግለጫው አስፍሯል።
በሽግግር ፍትሕ ሒደት ውስጥ፣ “የኦሮሚያ ድርሻ ምን ይኾናል?” የሚለውን ጉዳይ፣ ተወካዮቹ ለአምባሳደር ሐመር እንዳነሡላቸው መግለጫው አመልክቷል።በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር መስተጓጎሉን በተመለከተ፣ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ተወካዮቹ ለአምባሳደር ሐመር እንዳነሡላቸውና በዚኽም የዳያስፖራውን ማኅበረሰብ ለመርዳት ያላቸውን ፍላጎት እንደገለጹላቸው፣ መግለጫው አመልክቷል።
Via VoA

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update: የ "ቴሌግራም" መተግበሪያ ተጠቃሚዎቹ እንደሌሎቹ ማኅበራዊ ትስስር ገጾች "ስቶሪ/Story" መለጠፍ እንዲችሉ የሚያስችል ማዘመኛ ይፋ አድርጓል።
አሁን ላይ ለፕሪሚየም ተጠቃሚዎች ብቻ የተፈቀደው ይህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ፎቶ እንዲሁም ቪዲዮ በስቶሪ እንዲያጋሩ ያስችላል።
ይህ ማዘመኛው ቴሌግራምን ከሌሎቹ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችና የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች ጋር ያመሳስለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

ባህርዳር ዩኒቨርስቲ 7637 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው!
የባህርዳር ዩኒቨርስቲ በ79 የተለያዩ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 7 ሺሕ 637 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።በዘንድሮ አመት በተጀመረው የመውጫ ፈተናም የባህርዳር ዩኒቨርስቲ 85 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎቹ አልፈዋል፡፡
የባህርዳር ዩኒቨርስቲ እያካሄደ በሚገኘው የምረቃ መርሃ ግብሩ ለጋዜጠኛ መአዛ ብሩ እና ጌሪት ሆልትላንድ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ ታውቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር)፣ የዩኒቨርስቲው ሴኔት አባላት፣ ተመራቂዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር "ክልሉን እንታደግ" ሲሉ ጥሪ አቀረቡ!
ባልተለመደ ሁኔታ በላለፉት ሦስት ቀናት በዝግ የተካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት፤ በክልሉ ወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ከአባላቱ ጠንካራ ጥያቄዎችን ማስተናገዱ ተሰምቷል፡፡በምክር ቤቱ ሰብሰባ ላይ ጥያቄ ያነሱት የሕዝብ ተወካዮች፤ "የአማራን ሕዝብ አንገት ለማስደፋት ቀን ከሌሊት የሚሰሩ አካላት አሉ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
አባላቱ ክልሉ አሁን ላይ የገጠመውን አለመረጋጋት ለመፍታት መጀመሪያ የክልሉ አስተዳደር መዋቅር ራሱን መፈተሸና ማስተካከል አለበትም ነው ያሉት።የምክር ቤቱ አባላት አክለውም፤ "ክልሉ ያሉበትን መዋቅራዊ ችግሮች ካላስተካከለና ራሱን አስተካክሎ በግልጽ ካላወጣ፣ የሕዝቡን ጥያቄ መመለስ አይቻልም" ሲሉ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
በየአካባቢው የሚስተዋሉ ውጊያዎች የክልሉን ሕዝብ እያዳከሙ ነው ያሉት አባላቱ፤ የክልሉ መንግሥት መከላከያ ሠራዊት አስገብቶ ውጊያ እንዲደረግ መፍቀድ አልነበረበትም የሚል ትችትም አንስተዋል።ከምክር ቤት በአባላቱ ጠንካራ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡትም ምላሽ፤ “ክልሉን እንታደግ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
“ችግራችንን በራሳችን የመፍታት አቅም እንፍጠር” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በየዞኑ ከምክር ቤት አባላት አምስት አምስት ሰው ተመርጦ የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች የተሳተፉበት ውይይት ያለምንም ገደብ እንዲደረግም ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ ያቀረቡት የውይይት ጥሪ በአስር ቀናት ውስጥ እንዲካሄድም ነው የጠየቁት። በውይይቱ የሚነሱ ጉዳዮች በወረዳ፣ በዞንና በክልል በየደረጃው መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጥረት እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል፡፡አስተዳደራቸው ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ በመሰጠት፤ በሽዋ፣ በወሎ፣ በጎጃምና በጎንደር ውይይት እንዲደረግ ዕድል መፍጠሩን አስታውሰዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ “እንታደገው” ያሉትና የሚመሩት ክልል፤ በተለይ የመከላከያ ሠራዊት በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከተሰማራ ጊዜ ጀምሮ በውጊያ፣ መንገድ በመዝጋት፣ በሕዝብ ተቃውሞና በመሳሰሉት ሁነቶች ውስጥ እያለፈ ነው፡፡
የመከላከያ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከአማራ ክልል የሰላም እጦት ጋር በተያየዘ በቅርቡ በሰጡት አስተያየት፤ “ክልሉ ፓራላይዝድ ሆኗል” ሲሉ መደመጣቸው የሚታወስ ነው፡፡ ፊልድ ማርሻሉ የአማራ ክልል አስተዳደር ሽባ ሆኗል የሚል ይዘት ያለው አስተያየት ከሰጡ በኋላ፤ የመከላከያ ሠራዊት በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ውስጥ ገብቷል፡፡
በመንግሥት እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል ያለው ግጭት፤ ገና ከጅምሩ በውይይትና በድርድር እንዲፈታ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ጥሪ ሲያቀርቡ ቢቆዩም፣ አሁንም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ውጊያዎች እየተካሄዱ ነው፡፡
[Addis Maleda]

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪና ወላጅ አባቷ ከምርቃት ሲመለሱ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ!
በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከሱልልታ ከተማ አቅራቢ በምትገኘው ኮሰ በር አካባቢ ከቀኑ 11:30 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል። ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ፅጌ 16 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሀይሩፍ ተሽከርካሪ 65 መንገደኞችን ካሳፈረ ከህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ጋር ተጋጭቶ አደጋው ደርሷል።
በአደጋው የሀይሩፉ አሽከርካሪን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን በሱልልታ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር ዋና ሳጅን ደፋሩ ምትኩ ተናግረዋል። ከሟቾቹ መካከል የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪና ወላጅ አባቷ ከምርቃት ሲመለሱ በትራፊክ አደጋው ህይወታቸው ሲያልፍ የተመራቂዋ ታናሽ ወንድም የሆነ የ 16 ዓመት ታዳጊ በአደጋው ክፉኛ ቆስሏል።
በአደጋው ህይወታቸውን ካጡ አምስት ሰዎች በተጨማሪ ሶስት ሰዎች ላይ ከባድ ስድስት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ቁጥጥር ዋና ሳጅን ደፋሩ ምትኩ ለብስራት ሬዲዮና ቲቪ ጨምረው ተናግረዋል።
[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬዲዮ]

የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣናቸው ተነሱ።
የኢሚግሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙልጌታን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣን መነሳታቸውን ዋዜማ ዘግባለች።
@YeneTube @FikerAssefa
የኢሚግሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙልጌታን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣን መነሳታቸውን ዋዜማ ዘግባለች።
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
YeneTube
የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣናቸው ተነሱ። የኢሚግሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙልጌታን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣን መነሳታቸውን ዋዜማ ዘግባለች። @YeneTube @FikerAssefa
በተያያዘ ዜና ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።
አዲሷ ተሿሚ ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ከዚህ ቀደም የቱሪዝም ሚንስትር ዲዔታ ፣ በውጪ ጉዳይ ሚር የዲያስፖራ አገልግሎትና በውጪ ሀገር በዲፕሎማቲክ ሚስዮን ውስጥ ይሰሩ እንደነበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
አዲሷ ተሿሚ ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ከዚህ ቀደም የቱሪዝም ሚንስትር ዲዔታ ፣ በውጪ ጉዳይ ሚር የዲያስፖራ አገልግሎትና በውጪ ሀገር በዲፕሎማቲክ ሚስዮን ውስጥ ይሰሩ እንደነበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
371ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ዝግጅት እየተደረገ ነው!
371ሺህ የሚደርሱ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ገለጸ፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሰሜኑ ጦርነት እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች የፖለቲካ ዓላማቸውን በትጥቅ ለማስፈጸም ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና በአሁኑ ጊዜ ወደ ሰላማዊ ትግል ለመግባት የወሰኑ 371 ሺ የሚደርሱ የቀድሞ ተዋጊዎችን በአንድ ቦታ የማሰባሰብ እና መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
(ኢ ፕ ድ)

በ2015 በጀት ዓመት ከቡና የወጪ ንግድ ከአንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳሕለማርያም ገብረመድህን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015 በጀት ዓመት 360 ሺህ 144 ቶን ቡና በላይ በመላክ አንድ ነጥብ 8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 240 ሺህ 369 ቶን በላይ ቡና በመላክ ከአንድ ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ ይህም የዕቅዱን 67 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡
በበጀት ዓመቱ የተላከው ቡና መዳረሻ ሀገራት መካከልም ሳዑዲ ዓረቢያ በመጠን 48 ሺህ 413 ነጥብ 39 ቶን ሲሆን በገቢ 224 ነጥብ 84 ሚሊዮን ዶላር፣ ጀርመን በመጠን 36 ሺህ 065 ነጥብ 71 ቶን ቡና፤ በገቢ ደግሞ 173 ነጥብ 47 ሚሊዮን ዶላር፣ አሜሪካ በመጠን 21ሺህ 020 ነጥብ 86 ቶን፣ በገቢ 150 ነጥብ 47 ሚሊዮን ዶላር ድርሻ ኖሯቸው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን መያዛቸውን ጠቅሰዋል፡፡
አቶ ሳሕለማርያም ወደ ውጪ ከተላከው የቡና ምርት የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር እጅግ መጠነኛ ቅናሽ እንዳለው ገልጸው፤ ከዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ መቀነስ፣ ከነበሩት ሌሎች ፈታኝ ሁኔታዎች አንጻር ሲታይ በእጅጉ የሚበረታታ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተለይ በበጀት ዓመቱ ቡና ላኪዎች በተለያዩ ኤግዚቢሽኖች ላይ በመሳተፍ የሀገሪቱን ቡና የማስተዋወቅ ሥራ ሠርተዋል፡፡ በዚህም 141 ቡና ላኪዎችን እንዲሳተፉ በማመቻቸት 47 ሺህ 424 ቶን ቡና ከገዥዎች ጋር ኮንትራት በመግባት 76 ሚሊዮን 500 ሺህ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
Via EPA

“የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ኹኔታ የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት የሚሻ ነው” ኢሰመኮ
በጋምቤላ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ በነዋሪዎች ላይ ያደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፤ የመንግሥትን ተጨማሪ ትኩረት የሚሻ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።ኮሚሽኑ ከግንቦት ወር 2015 ጀምሮ በተለያዩ የጋምቤላ ክልል አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የትጥቅ ግጭቶችን፣ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃቶችንና አጠቃላይ የጸጥታ ችግሮችን እና በዚህ ሳቢያ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን እየተከታተለ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በተለይም ከግንቦት ወር 2015 ጀምሮ በክልሉ ላለው የጸጥታ ችግር መነሻ፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ በተወሰኑ ነዋሪዎች መካከል የተነሳ አለመግባባት መሆኑ ማረጋገጡን የገለጸ ሲሆን፤ ይሄው አለመግባባት በፍጥነት ወደ ብሔርን መሠረት ያደረገ ውጥረት እንደተሸጋገረ ነዋሪዎች ነግረውኛል ብሏል።ይህንን ተከትሎም የተለያየ ብሔር ታጠቂ ቡድኖች በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ ጎግ ወረዳ፣ በጋምቤላ ከተማ ብሔር ብሔረሰቦች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እና በከተማው በሚገኙ ሌሎች ሰፈሮች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጿል፡፡ በዚህም ምክንያት በርካታ ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉ፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀል እና ንብረት ውድመት መድረሱን አስታውቋል።
በጸጥታው ችግር ምክንያት ገና ወደ አካባቢዎቹ በአካል ደርሶ ምርመራ ለማድረግ አለመቻሉን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ ነገር ግን ነዋሪዎች በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ መንደሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መውደማቸውን ነዋሪዎች ገልጸውልኛል ብሏል።በክልሉ በተደጋጋሚ ከጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳን በሚመጡ ታጣቂ ቡድኖች በሚደርሱ ጥቃቶች እንዲሁም፤ አልፎ አልፎ በክልሉ በሚኖሩ ብሔሮች መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት የሚደርስ መሆኑም በመግለጽ፤ ክልሉ ወደ 350 ሺሕ የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን በስምንት የተለያዩ ካምፖች እንደሚያስተናግድም አስታውሷል።
ከኹለት ወራት በላይ ለዘለቀው የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ችግር እና በክልሉ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በመድረስ ላይ ያሉ ግጭቶች ተሳታፊዎችን በተመለከተ ተጎጂዎችም ሆነ የክልሉ የጸጥታ እና የአስተዳደር ኃላፊዎች፤ የተለያዩ ብሔር ታጣቂ ቡድኖችን በኃላፊነት እንደሚጠቅሱም ኢሰመኮ ገልጿል።በአንዳንድ አካባቢዎች የክልሉ ኑዌር ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ በሌላ አካባቢ የአኝዋ ብሔረሰብ ታጣቂዎች፣ እንዲሁም ከጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች እና በአንዳንድ የስደተኛ ካምፖች ውስጥ እንደሚኖሩ የተገለጸ ሰዎች ጭምር በግጭቶቹ ተሳታፊ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አመላክቷል፡፡
“እነዚህ ጥቃቶች እና ግጭቶች በአብዛኛው ብሔር ናቸው” ያለው ኮሚሽኑ፤ “በሌላ በኩል ግጭት የሚደርስባቸውን አካባቢዎች ያለ የብሔር ልዩነት ኹሉንም ነዋሪዎች አካባቢውን ሸሽቶ ለመፈናቀል፣ ለንብረት ውድመት እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ያጋለጠ” መሆኑን ጠቁሟል።
የክልሉ መንግሥት ከሐምሌ 12/2015 ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ተግባራዊ የሚሆን ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ጠዋት 12፡00 ሰዓት የሚዘልቅ እና በኹሉም የክልሉ አካባቢዎች ተፈጻሚ የሚሆን የሰዓት እላፊ ገደብ፣ እንዲሁም ከተመደቡ የጸጥታ አካላት ውጪ መሣሪያ ይዞ የመንቀሳቀስ ገደብ መጣሉ ይታወሳል።ከዚህ በተጨማሪም የፌዴራል ፖሊስና የአገር መከላከያ ሰራዊት የተውጣጣ ኃይል ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ መሰማራቱን የገለጸው ኢሰመኮ፤ ይህም የክልሉን ጸጥታ ኹኔታ በተወሰነ መልኩ እንዳረጋጋውና በጋምቤላ ከተማ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ማስቻሉን ገልጿል።
ሆኖም በክልሉ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ አፈጻጸም ነዋሪዎችን ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይዳርግ መከላከልን ጨምሮ፣ በክልሉ በተለያየ ወቅት የሚያገረሹ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ነዋሪዎችን ለከፍተኛ ጉዳት የዳረጉ ጥቃቶችን እና ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቆም ተጨማሪ ትኩረት እና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳስቧል።ስለሆነም በክልሉ የተሰማራውን ከፌዴራል እና ከክልሉ የጸጥታ አካላት የተውጣጣ ኃይል ማጠናከር እና አስፈላጊውን ድጋፍ ከመስጠት ተግባር ጎን ለጎን፤ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ በደረሰው ግጭት ሳቢያ አካባቢውን ለቀው ለሸሹ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ሰብአዊ ድጋፍ ማድረስ፣ በግጭቱ የተነሳ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚገባም ገልጿል።
እንዲሁም ለረጅም ዓመታት እና በየጊዜው ወደ ግጭት ለሚያመራው በተቀባይ ማኅበረሰብ እና በስደተኞች መካከል ላለው የላላ ግንኙነት ዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ እንደሚያስፈልግም ኮሚሽኑ አሳስቧል::
@YeneTube@FikerAssefa

ትዊተር አርማውን ከምናውቃት ወፍ ወደ ‘ኤክስ’ ምልክት ሊቀይር መሆኑን ኢላን መስክ ገለጠ!
የትዊተር ባለቤት ኢላን መስክ የትዊተር ‘ሎጎ’ ከተለመደው የወፍ ምልክት ወደ ‘ኤክስ’ [X] ሊቀይር መሆኑን ገልጧል።የቢዝነስ አርማውን ወደ ኤክስ ኮርፕ የቀየረው መስክ “እንደውም ይህን ሊሆን የሚገባው ቀድሞ ነበር” ብሏል።
ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ቢሊየነሩ ልክ እንደ ቻይናው ዊቻት ኤክስ የተባለ “ሁሉን ያካተተ” መተግበሪያ የመሥራት ሐሳብ አለው።የትዊተር አርማ የሆነችው ወፍ እንደምትቀየር እሑድ ዕለት ያሳወቀው መስክ “በቃ ሁላችንም የትዊተር አርማን ቻው የምንልበት ጊዜ ተቃርቧል። ቀስ በቀስ ደግሞ ሁሉንም ወፎች” ብሏል።
የዛኑ ዕለት አዲስ ጊዜያዊ አርማ ይፋ እንደሚደረግም ያሳወቀው መስክ የእንግሊዝኛ ኤክስ ፊደል ምልክት ያለበት አርማ ለጥፏል።የትዊተር ሥራ አስፈፃሚ ሊንዳ ያካሪኖ በትዊተር ገፃቸው አርማ መቀየሩ አስደሳችና አዲስ ጅማሮ ነው ብላለች።በእስያ ሃገራት ለምሳሌ በሕንድ ፔይቲኤም፤ በኢንዶኔዥያ ደግሞ ጎጄክ የሚባሉ መተግበሪያዎች ሁሉን አቀፍና በርካቶች የሚጠቀሙባቸው ናቸው።
Via BBC

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ 17 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጸደቀ!
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለ2016 በጀት ዓመት የሚሆን 17 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካጸደቀው በጀት ውስጥ 74 በመቶው የሚሸፈነው የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል ከሚያስተላልፈው የድጋፍ በጀት ነው።
የትግራይ ክልል የሰሜኑ ጦርነት ከተነሳ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በመደበኛ ሁኔታ በጀት ያጸደቀው፤ ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 14፤ 2015 እንደሆነ የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሀንሳ ተክላይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ለክልሉ መንግስት የሚመደበው በጀት ከዚህ ቀደም ይጸድቅ የነበረው በትግራይ ክልል ምክር ቤት ነበር።
የ2016 በጀት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የጸደቀው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ህግ የማውጣት ስልጣኑን ለክልሉ ስራ አስፈጻሚ አካል በመስጠቱ መሆኑን ኮሚሽነሯ አስረድተዋል። የክልሉ ካቢኔ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባደረገው ስብሰባ፤ ለ2016 በጀት ዓመት 17 ቢሊዮን ብር በጀት ማጽደቁን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባል የሆኑት ወ/ሮ ሀንሳ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ይህ በጀት የሰሜኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ አስቀድሞ ለ2013 በጀት ዓመት ጸድቆ ከነበረው “ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ” ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ ማሳየቱን ጠቁመዋል። የአሁኑ በጀት በ2012 በክልሉ ምክር ቤት ከጸደቀው በጀት ጋር ሲነጻጸር ያለው ልዩነት የ300 ሺህ ብር ገደማ ብቻ ነው።
Via Ethiopia Insider

👎1
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
09 77 64 18 19
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=ያለው
🔹ደሞዝ=6000-10,000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan

በጉራጌ ዞን በታጠቁ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!
በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ፤ ሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እና ዕሁድ ሐምሌ 16/2015 የታጠቁ ኃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።በወረዳው በቼ እና ዲዳ በተባሉ የቀበሌ ከተሞች፤ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ጥቃቱ እንደተሰነዘረ እና ግድያዎች እንደተፈጸሙ ምንጮች ከስፍራው ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል፡፡
ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከአካባቢው መሰወራቸው የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋለ አካል አለመኖሩ ተጠቅሷል።በተጠቀሰው ምሽት ላይ ሦሰት ሰዓት አካባቢ በቼ ቀበሌ ውስጥ በተሰነዘረ ጥቃት ሦስት ሰዎች መገደላቸው የታወቀ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ዕሁድ ሐምሌ 17/2015 ምሽት ኹለት ሰዓት ገደማ አንድ አባውራ ከነባለቤታቸው እና ጎረቤታቸው ከሆኑ ግለሰብ ጋር መገደላቸውን አዲሰ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።
በመስቃንና ማረቆ ብሔረሰብ መካከል ባለው የቆየ አለመግባባት በተደጋጋሚ የሚፈጸም ማንነት ተኮር ጥቃት መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ለአካባቢው ማህበረሰብ በነጻነት መንቀሳቀስ አስቸጋሪ መሆኑ ተመላክቷል።እንደ ነዋሪዎች ገለጻ፤ በአካባቢው ባለው የሰላም እጦት ሳቢያ አብዛኛውየመንግሥት ሠራተኞች ለደኅንነታቸው በመስጋት በሥራ ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ እና ብዙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ዝግ መሆናቸውን ብሎም የተከፈቱትም አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ተነግሯል።
የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ከሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እስከ ሐምሌ 17/2015 ድረስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት እንደደረሳቸው ጠቅሰው፤ “በቂ የጸጥታ አካላት ወደቦታው ልከናል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም፤ ግድያውን በሚመለከት ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው ወይም አይደለም? የሚለውን ጉዳይ በሚመለከት በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በጊዜው ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።
በዞኑ ኹለቱ ወረዳዎች መካከል ዓመታትን ያስቆጠረው ግጭት ዕልባት ሳያገኝ የቀጠለ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ ሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ በርካታ አካላት ለችግሩ ዕልባት ለመስጠት ሙከራ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። በዚህም መሰረት ከአራት ዓመታት በፊት ሰላም ሚኒስቴር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ሰፊ ሥራዎችን ይሰራ እንደነበር ነገር ግን ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ችግሮች ተባብሰው መቀጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
Via Addis Maleda

😭1
በአንዳንድ የአማራ፣ አፋርና ትግራይ አካባቢዎች ያልፈነዳ የጦርነት ቅሪት እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለፀ።
ኮሚቴው ይህን ያለው እ.ኤ.አ ከጥር እስከ ሰኔ 2023 በኢትዮጵያ የነበረው እንቅስቃሴ አስመልክቶ ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም በ8 ገፅ ቀንብቦ ባወጣው ሪፖርት ነው፡፡በሪፖርቱ እንደተመላከተው የጦርነት ቀጣና በነበሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለፈነዱ ፈንጂዎች በአካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይም ለህፃናት አስጊ ሁኖ መቆየቱን ገልጿል፡፡
ምንም እንኳን ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማቅረብ ምቹ ሁኔታዎች በአንፃራዊነት ቢመቻቹም አሁንም ድረስ ግን በመላ አገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊ መብታቸው እየተጣሰ በመሆኑ ከፍተኛ ጥበቃና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመላክቷል።
ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በጋራ በመሆን በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌና ትግራይ በሚገኙና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመድረስ እየሰራ መሆኑን ኮሚቴው ገልፆል፡፡
የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ አስፈላጊ የሚባሉ የሰብዓዊ እርዳታዎችን እንዲሁም የህክምና እርዳታዎች ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀው ሪፖርቱ በተለይ በትግራይ ክልል የነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶችና ህፃናት አመጋገብ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ህይወትን ለመታደግ አፋጣኝ ርምጃ እንድንወስድ አድርጎናል ብሏል፡፡
ባለፉት ጊዜያትም ኮሚቴው 1 ሺህ 156 የተጠፋፉ ሰዎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማገናኘቱን፣ 14 ሺህ 933 ለሚሆኑት ውሃ አቅርቦት ማድረሱን፣ 116 ሺህ 730 ለሚሆኑት አስፈላጊ የቤት ቁሳቁሶች ማቅረቡንና ለ76 የጤና ተቋማት በመደበኛነት መደገፉን አስታውቋል፡፡
[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
ኮሚቴው ይህን ያለው እ.ኤ.አ ከጥር እስከ ሰኔ 2023 በኢትዮጵያ የነበረው እንቅስቃሴ አስመልክቶ ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም በ8 ገፅ ቀንብቦ ባወጣው ሪፖርት ነው፡፡በሪፖርቱ እንደተመላከተው የጦርነት ቀጣና በነበሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለፈነዱ ፈንጂዎች በአካባቢው ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይም ለህፃናት አስጊ ሁኖ መቆየቱን ገልጿል፡፡
ምንም እንኳን ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማቅረብ ምቹ ሁኔታዎች በአንፃራዊነት ቢመቻቹም አሁንም ድረስ ግን በመላ አገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊ መብታቸው እየተጣሰ በመሆኑ ከፍተኛ ጥበቃና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመላክቷል።
ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በጋራ በመሆን በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌና ትግራይ በሚገኙና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመድረስ እየሰራ መሆኑን ኮሚቴው ገልፆል፡፡
የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ አስፈላጊ የሚባሉ የሰብዓዊ እርዳታዎችን እንዲሁም የህክምና እርዳታዎች ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀው ሪፖርቱ በተለይ በትግራይ ክልል የነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶችና ህፃናት አመጋገብ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ህይወትን ለመታደግ አፋጣኝ ርምጃ እንድንወስድ አድርጎናል ብሏል፡፡
ባለፉት ጊዜያትም ኮሚቴው 1 ሺህ 156 የተጠፋፉ ሰዎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማገናኘቱን፣ 14 ሺህ 933 ለሚሆኑት ውሃ አቅርቦት ማድረሱን፣ 116 ሺህ 730 ለሚሆኑት አስፈላጊ የቤት ቁሳቁሶች ማቅረቡንና ለ76 የጤና ተቋማት በመደበኛነት መደገፉን አስታውቋል፡፡
[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
09 77 64 18 19
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=ያለው
🔹ደሞዝ=6000-10,000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
📞 ስልክ:- 09 78 88 18 19
09 77 64 18 19
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
💥 ሼፍ/ዋና እና ረዳት/
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=ያለው
🔹ደሞዝ=6000-10,000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ!
የ2015 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።
በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቃል፡፡

በዐማራ እና አፋር ክልሎች በሳምንት ውስጥ ሦስት የረድኤት ሠራተኞች እንደተገደሉ ተገለጸ!
ባለፈው የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ፣ በአፋር እና ዐማራ ክልሎች፣ ሦስት የረድኤት ሠራተኞች እንደተገደሉ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ገለጸ።
ከሦስቱ ሠራተኞች፣ ሁለቱ በአፋር አንዱ ደግሞ በዐማራ ክልል እንደተገደሉ የተናሩት የምክር ቤቱ ዋና ዲሬክተር ኄኖክ መለሰ፣ ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ፣ በቁጥር 40 የሚደርሱ የሰብአዊ ድጋፍ ሠራተኞች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡
ግድያ የተፈጸመባቸው ሠራተኞች ይሠሩባቸው የነበሩትን ተቋማት ከመግለጽ የተቆጠቡት አቶ ኄኖክ፣ ለረድኤት ሠራተኞች ጥበቃ እና ከለላ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተመልካቾቹን በየወሩ 10 ብር ሊያስከፍል መሆኑ ተሰማ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው አጭር መግለጫ እንዳመለከተው ‹‹ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሰኔ ወር ጀምሮ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ በየወሩ 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌከትሪክ ፍጆታ ቢል ጋር ተዳምሮ እንዲዘጋጅ መደረጉን ›› ይፋ አድርጓል፡፡
መግለጫው ‹‹ ከ50 ኪሎ ዋት ስዓት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ›› የሚጠቀሙ ደንበኞቹን ‹‹ በሙሉ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1278/2015 ዓ.ም በተሰጠው ስልጣን መሰረት አመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ቢል ጋር እንዲሰበስብ መወሰኑን ›› አስታውሷል፡፡
በዚህም ‹‹ የኤሌክትሪክ ፍጆታና የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ ›› በጋራ እንዲሚፈፀም አገልግሎቱ አመልክቷል፡፡