በኢትዮጵያ ለወራት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረዉ ክልከላ ተነሳ!
በኢትዮጽያ ለወራት ያህል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱን ለማወቅ ተችሏል።በኢትዮጵያ ከየካቲት ወር መጀመሪያ አንስቶ በኢንተርኔት አገልግሎቶች ማለትም በፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ቴሌግራም እና ቲክቶክ ላይ ገደብ መጣሉ የሚታወስ ነው።
ይህም የቪፒኤን መጠቀሚያ ፍላጎትን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሻቅብ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ነገር ግን በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ፤ ከዛሬ ሐምሌ 10/2015 ማምሻውን ጀምሮ መነሳቱን ማረጋገጥ ተችሏል።
@YeneTube @FikerAssefa

💥💥💥አስቸኳይ የስራ ቅጥር💥💥💥
✅ድርጅታችን በተዘረዘሩት የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል።
═••════••• •••••• •••••• •
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ባንክ ተላላኪና ፅዳት
☆የት/ደረጃ:- ማንበብ እና መፃፍ የምትችል
☆የስራ ልምድ:- ያላት
☆ፆታ:- ሴት
☆ደሞዝ:4,500
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ:- መምህር በሉም ረዳትናዋና
☆የት/ደረጃ:- 10/ዲግሪ/ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:- ዐ አመት እና ከዛ በላይ
☆ፆታ:- ወንድ/ሴት
☆ብዛት:- 20
☆ደሞዝ:-8,700
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኮንስትራክሽን/ፎርማል
☆የት/ደረጃ:# ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:# 0-2 ዓመት
☆ፆታ:# ወንድ
☆ብዛት:# 7
☆ደሞዝ:-በስምምነት
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኦፌስ እንጅነሪግ
☆የት/ደረጃ:# ዲግሪ
☆የስራ ልምድ:# 2አመት
☆ፆታ:# ሴት/ወንድ
☆ብዛት:# 7
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ተጫራች/የጨረታ ባለሙያ/
☆የት/ት ደረጃ: መፃፍ እና ማንበብ
☆የስራ ልምድ: ጨረታ ሰርቶ የሚያውቅ
☆ፆታ: ወንድ
አድራሻችን:-አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደቦሌ በሚውደው መንገድ ወረድ ብለው አዋሽ ባንክ ፊትለፊት ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ/ቁ 006
ስልክ : 0991333943/0991334043
https://tttttt.me/JobsAtHewan

በጎንደር ከተማ ታግቷል የተባለዉ እስራኤላዊ አዛዉንት ቤተሰቦቹን ገንዘብ ለመቀበል አልሞ መሆኑን የእስራኤል መንግስት አሳወቀ!
በጎንደር ከተማ ታግቷል በተባለዉ የ 79 አመት አዛዉንት እስራኤላዊ ጉዳይ ዉዝግብ አስነስቶ እንደነበር ይታወሳል። የእስራኤል ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢንተርፖልን አጋር በማድረግ ግለሰቡን በእገታ ለማስለቀቅ ጥረት እያደረኩ ነዉም ብሎ ነበር።
ለህክምና እና ለቤተዘመድ ጥየቃ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል የተባለዉ አዛዉንቱ ግለሰብ ሳይታገት ታግቻለሁ ማለቱን የእስራኤል መንግስት አረጋግጫለሁ በማለቱ ጥረቱን እንዳቋረጠዉ ገልጿል። በሀገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲመራ የነበረዉም ግለሰቡን የማስለቀቅ ጥረት እንዳቆመዉ አሳዉቋል።
ግለሰቡ በእስራኤል የሚኖሩ ቤተሰቦቹን እስከ 2.5 ሚሊዮን ብር ድረስ ታግቻለሁ በሚል ሰበብ ሲጠይቅ እንደነበር የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኀን መዘገባቸዉን ብስራት ራዲዮ ተመልክቷል። ግለሰቡ ታግቷል በተባለበት ወቅትም የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምንም የቀረበለት አቤቱታ አለመኖሩን አሳዉቆ ነበር። አቪ የተሰኘዉ የግለሰቡ ወንድ ልጅ እገታዉ የዉሸት እንነበር እና ገንዘብ ፍለጋ መሆኑን አረጋግጧል።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሳይታገቱ ታግቻለሁ በማለት ከቅርብ ቤተሰብ ፣ ከፍቅረኛ እና ከዘመድ አዝማድ ገንዘብ ለማግኘት የመሞከር ጥረት አሁን ድንበር ተሻጋሪ ሆኗል። በትናንትናው እለትም በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ወረዳ የሚኖር ወጣት ቤተሰቦቹን ሳይታገት ታገቻለሁ በሚል 500 ሺህ ብር የጠየቀ ቢሆንም በደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
@Yenetube @Fikerassefa

ኢትዮ ቴሌኮም 75 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ!
ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት 75 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ የኢትዮ ቴሌኮምን የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን በሚመለከት በዛሬው ዕለት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም በበጀት ዓመቱ ኢትዮ ቴሌኮም 75 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የገለጹ ሲሆን፤ ገቢው የተገኘው ተቋሙ ከሚሰጣቸው 203 ምርትና አገልግሎቶች መሆኑን አስታውቀዋል።
ይህም ገቢ የዕቅዱን 101 በመቶ መሆኑን በመግለጽ፤ ከባለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ23.5 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስረድተዋል።
እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ገቢዎች 164 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ጨምረው ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ የኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 72 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ከዕቅድ አንፃርም 98 በመቶ አፈጻጸም መመዝገቡን ተነግሯል።
ከመደበኛ አገልግሎት በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ 203 ምርትና አገልግሎት ለደንበኞች የቀረበ ሲሆን ከዚህም መካከል 116ቱ አዲስ ምርትና አገልግሎቶች መሆናቸውም ተመላክቷል።

Forwarded from YeneTube
💥💥💥አስቸኳይ የስራ ቅጥር💥💥💥
✅ድርጅታችን በተዘረዘሩት የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል።
═••════••• •••••• •••••• •
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ባንክ ተላላኪና ፅዳት
☆የት/ደረጃ:- ማንበብ እና መፃፍ የምትችል
☆የስራ ልምድ:- ያላት
☆ፆታ:- ሴት
☆ደሞዝ:4,500
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ:- መምህር በሉም ረዳትናዋና
☆የት/ደረጃ:- 10/ዲግሪ/ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:- ዐ አመት እና ከዛ በላይ
☆ፆታ:- ወንድ/ሴት
☆ብዛት:- 20
☆ደሞዝ:-8,700
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኮንስትራክሽን/ፎርማል
☆የት/ደረጃ:# ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:# 0-2 ዓመት
☆ፆታ:# ወንድ
☆ብዛት:# 7
☆ደሞዝ:-በስምምነት
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኦፌስ እንጅነሪግ
☆የት/ደረጃ:# ዲግሪ
☆የስራ ልምድ:# 2አመት
☆ፆታ:# ሴት/ወንድ
☆ብዛት:# 7
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ተጫራች/የጨረታ ባለሙያ/
☆የት/ት ደረጃ: መፃፍ እና ማንበብ
☆የስራ ልምድ: ጨረታ ሰርቶ የሚያውቅ
☆ፆታ: ወንድ
አድራሻችን:-አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደቦሌ በሚውደው መንገድ ወረድ ብለው አዋሽ ባንክ ፊትለፊት ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ/ቁ 006
ስልክ : 0991333943/0991334043
https://tttttt.me/JobsAtHewan
✅ድርጅታችን በተዘረዘሩት የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል።
═••════••• •••••• •••••• •
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ባንክ ተላላኪና ፅዳት
☆የት/ደረጃ:- ማንበብ እና መፃፍ የምትችል
☆የስራ ልምድ:- ያላት
☆ፆታ:- ሴት
☆ደሞዝ:4,500
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ:- መምህር በሉም ረዳትናዋና
☆የት/ደረጃ:- 10/ዲግሪ/ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:- ዐ አመት እና ከዛ በላይ
☆ፆታ:- ወንድ/ሴት
☆ብዛት:- 20
☆ደሞዝ:-8,700
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኮንስትራክሽን/ፎርማል
☆የት/ደረጃ:# ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:# 0-2 ዓመት
☆ፆታ:# ወንድ
☆ብዛት:# 7
☆ደሞዝ:-በስምምነት
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኦፌስ እንጅነሪግ
☆የት/ደረጃ:# ዲግሪ
☆የስራ ልምድ:# 2አመት
☆ፆታ:# ሴት/ወንድ
☆ብዛት:# 7
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ተጫራች/የጨረታ ባለሙያ/
☆የት/ት ደረጃ: መፃፍ እና ማንበብ
☆የስራ ልምድ: ጨረታ ሰርቶ የሚያውቅ
☆ፆታ: ወንድ
አድራሻችን:-አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደቦሌ በሚውደው መንገድ ወረድ ብለው አዋሽ ባንክ ፊትለፊት ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ/ቁ 006
ስልክ : 0991333943/0991334043
https://tttttt.me/JobsAtHewan
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፌደራሉ ጤና ሚንስቴር አንድ የትግራይ ክልል ወረዳን በድረገጹ ላይ ባወጣው መረጃ ወደ አማራ ክልል በማካለል "ሕገመንግሥታዊ ጥሰት ፈጽሟል" ሲል ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ከሷል።
አስተዳደሩ፣ የጤና ሚንስቴር ድርጊት ትምህርት ሚንስቴር ባለፈው ወር የፈጸመውን ስህተት የደገመ ነው ብሏል።ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ሚንስቴሩ "ሃላፊነት የጎደለውን ድርጊቱን እንዲያርም" እና "የትግራይን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ" ጠይቋል። ፌደራል መንግሥቱ በሚንስቴሩ አመራር ላይ ርምጃ እንዲወስድና ጤናና ትምህርት ሚንስቴሮች የሠሩትን ወንጀል እንዲያስተካክልም አስተዳደሩ ጥሪ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ የፌደራሉ መንግሰትና የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከትግራይ አባቶች ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ሚናቸውን እንዲወጡ ›› ለሁለተኛ ጊዜ ጠየቀች፡፡
በሌላ በኩል ‹‹ የትግራይ ክልል አባቶች የፈፀሙትን የቀኖና ጥሰት መላው ምዕመን እንዲቃወም ›› ጥሪ ቀርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባዔ ‹‹ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወቅታዊ የቀኖና ጥሰት አስመልክቶ ›› ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ ነው ጥሪውን ያቀረበው፡፡
ጉባዔው ‹‹ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሚመሩት ሰላም ልዑክ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ጳጳሳትና ምእመናን ጋር ሊካሄድ ሞክሮ ባልተሳካው የሰላም ጥረትና ያን ተከትሎ በዚያ የሚገኙ አባቶች ከሕገ ቤተክርስቲያንና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ በሆነ መንገድ 10 ኤጰስ ቆጶሳትን እንሾማን የሚል ይፋዊ መግለጫ መስጠታቸውን ›› አስመልክቶ ውይይት አካሂዷል፡፡
የቤተ ክርስሪያኗ የሰላምና የዕርቅ ልዑካን ‹‹ ተደጋጋሚ የሰላም ስራ አለመሳካቱን ›› ያስታወሰው ጉባዔው ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫውን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም ‹‹ በየደረጃው ያሉ የቤተክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተርክስቲያን እና ምዕመናንና ምዕመናት እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በአንድነትና በኅብረት በመቆም ድርጊቱን እንዲቃወሙና በማዕከል ደረጃ የሚተላለፉትን ውሳኔዎች ተግባራዊ በማድረግ ለቤተክርስቲያኒቱ አንድነትና ሉዓላዊነት የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ ›› ጥሪ አስተላልፏል፡፡
መግለጫው ‹‹ ቤተክርስቲያን ላይ እየተከሰቱ ያሉ የሕገ ቤተክርስቲያንና የቀኖና ጥሰቶች ከቤተክርስቲያኒቱም አልፎ ሀገራዊ አንድነትና ሉዓላዊነትን የሚያናጋ ብሎም ሀገራዊ ቀውስ የሚያስከትል እንደመሆኑ መጠን የፌዴራል መንግሥቱና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ለችግሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት የውይይት መድረክ በማዘጋጅት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ›› ለሁለተኛ ጊዜ ጠይቋል፡፡
ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ‹‹ እንዲያሸማግሉ ጥሪ መቅረቡ ›› አይዘነጋም፡፡
[Asham]

"ፑቲንን በቁጥጥር ስር ማዋል ከሩሲያ ጋር ጦርነት ማወጅ ነው" - ራማፎሳ
ደቡብ አፍሪካ የሩሲያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጆሃንስበርግ በቁጥጥር ስር ማዋል ከሞስኮ ጋር ጦርነት እንደማወጅ ይቆጠራል አሉ።
ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሩሲያም በስልጣን ላይ ያሉትን ፕሬዝዳንቷን መያዝ እንደ ጦር አዋጅ እወስደዋለሁ ማለቷን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የአለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ያወጣባቸው መሆኑና ደቡብ አፍሪካም ፈራሚ ሀገር እንደመሆኗ ፑቲንን በቁጥጥር ስር አውላ አሳልፋ እንድትሰጥ ትገደዳለች።የፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አስተዳደር ፑቲንን በቁጥጥር ስር አውሎ ችግር ውስጥ መግባት እንደማይፈልግ የትናንቱ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ ያመላክታል።
የሀገሪቱ ዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ “ዲሞክራቲክ አሊያንስ” ግን የራማፎሳ አስተዳደር ፑቲንን እንዲይዝ ጉዳዩን በፕሪቶሪያ ወደሚገኝ ፍርድ ቤት በመውሰድ ጫና እያደረገ ይገኛል።ራማፎሳ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት የጽሁፍ ምላሽ ፕሬዝዳንት ፑቲንን መያዝ የዩክሬን ጦርነትን ለማርገብ ሀገራቸው እያደረገች የምትገኘውን ጥረት እንደሚያሰናክል ነው ያብራሩት።
ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ስድስት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የሩሲያ እና የዩክሬን ፕሬዝዳንቶች ያነጋገሩ ሲሆን፥ ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረውን ጦርነት ለማስቆም ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።
[Alain]

በድረ ገጾቻቸው ላይ የጫኑትን ዘገባ እንዲያወርዱ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጠ።
የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የክስ መዝገብ በፌደራል ዐቃቤ ሕግ በሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ - መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ውድቅ ሆነ።
በዛሬው የችሎት ውሎ የዋስትና ጥያቄ የቀረበው በሽብር ጉዳይ ከተከሰሱ ሰዎች በመሆኑ እና የሽብር ክስ የሚቀርብባቸው ሰዎች ጥፋተኛ ሆነው ሲገኙ እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ በመሆኑ የዋስትና መብት የሚያሰጥ አይደለም በሚል የቀረበው የዋስትና ክርክር የሕግ ክልከላ ያለበት በመሆኑ ነው ተብሏል።
በመሆኑም ችሎት የቀረቡ ተከሳሾች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ችሎቱ በሙሉ ድምጽ መወሰኑንና ጠበቆች የክስ መቃወሚያ ለሀምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲያቀርቡ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ሲሉ ከተከሳሽ ጠበቆች አንደኛው ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።ችሎቱ ይህንን ውሳኔ ማሰማቱን ተከትሎ ተከሳሾች በጋራ ጭበጨባ እና መፈክር አሰምተዋል።
ተከሳሾች ለችሎቱ ጥያቄ አቅርበውባቸው ከነበሩ ገዳዮች መካከል በተለይ መንግሥት በሚያስተዳድራቸው መገናኛ ብዙኃን በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ወቅት የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያወጣው እና ያሰራጨው መግለጫ ተከሳሾቹ ተጠርጣሪ ሆነን ሳለ እንደ ጥፋተኛ አድርጎ ያቀረበብን በመሆኑና ይህም መልካም ስማችን የሚያጎድፍ በመሆኑ የመገናኛ ብዙኃኑ የሥራ ኃላፊዎች ስለ ጉዳዩ ችሎት ቀርበው እንዲያስረዱና እንዲጠየቁ የሚል ነበር።
ዛሬ የዋለው ችሎት ይህንን መግለጫ እንዳለ ያቀረቡት መገናኛ ብዙኃን በድረ ገጾቻቸው ላይ የጫኑትን ዘገባ እንዲያወርዱ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ሲል DW ዘግቧል።

የመጀመሪያው ዙር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች የመበተን ስራ በመጪው መስከረም ሊጀመር ነው!
ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የመጀመሪያውን ዙር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን የመበተን (demobilization) ስራ በመስከረም ወር እንደሚጀምር አስታወቀ። በተሃድሶ ፕሮግራም ውስጥ እንዲያልፉ እቅድ ተይዞላቸው የነበሩ የቀድሞ ተዋጊዎች ብዛትም በ122 ሺህ ገደማ መጨመሩን ገልጿል።
ትጥቃቸውን የሚፈቱ ኃይሎች “ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ ለማድረግ” የተቋቋመው የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን፤ 250 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን በክህሎት ስልጠና እና በስራ ፈጠራ ወደ ማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዲቀላቀሉ ለማድረግ አቅዶ ነበር። ከተቋቋመ ስምንት ወራት ያስቆጠረው ኮሚሽኑ፤ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የቀድሞ ተዋጊዎች ከሚገኙባቸው ክልሎች እና የተሃድሶ ፕሮግራሙን በገንዘብ ከሚደግፉ አካላት ጋር ውይይት ሲያደርግ ቆይቷል።
በፕሮግራሙ ውስጥ ያልፋሉ ተብሎ የሚጠበቁ የቀድሞ ተዋጊዎች ብዛት 371,971 እንደሆነ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽኑ ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 12፤ 2015 ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር በአዲስ አበባ ባደረገው ውይይት ላይ አስታውቋል። ኮሚሽኑን የሚመሩት የቀድሞው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተሾመ ቶጋ፤ “ከሚመለከታቸው የክልል፣ የመከላከያ እና የእኛ ተቋም ጋር ሆነን በመነጋገር የደረስንበት ዳታ [ነው]” ሲሉ የቀድሞ ተዋጊዎች ብዛት ቀደም ሲል በእቅድ ከነበረው የጨመረበትን ምክንያት አስረድተዋል።
Via Ethiopia Insider

በጋምቤላ ክልል ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ!
በክልሉ ሰሞኑን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉ ተሰምቷል።
ከዛሬ ጀምሮ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ተሽከርካሪም ሆነ ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን የክልሉ ካቢኔ አስታውቋል።
ከተመደቡ የፀጥታ አካላት ውጪ የትኛውንም ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻልም ተገልጿል።
በሌላ በኩል ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ሆነ አገልግሎት ሰጪ የንግድ ተቋማት ከነገ ጀምሮ መደበኛ ስራውቸዉን እንዲያከናዉኑ ካቢኔዉ አሳስቧል።
በክልሉ ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ እጃቸው ያለበት አመራርም ሆነ ሌላ አካላትን ተጣርቶ ተጠያቂ እንደሚደረግም ካቢኔዉ አሳዉቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
በክልሉ ሰሞኑን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉ ተሰምቷል።
ከዛሬ ጀምሮ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ተሽከርካሪም ሆነ ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን የክልሉ ካቢኔ አስታውቋል።
ከተመደቡ የፀጥታ አካላት ውጪ የትኛውንም ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻልም ተገልጿል።
በሌላ በኩል ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ሆነ አገልግሎት ሰጪ የንግድ ተቋማት ከነገ ጀምሮ መደበኛ ስራውቸዉን እንዲያከናዉኑ ካቢኔዉ አሳስቧል።
በክልሉ ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ እጃቸው ያለበት አመራርም ሆነ ሌላ አካላትን ተጣርቶ ተጠያቂ እንደሚደረግም ካቢኔዉ አሳዉቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
💥💥💥አስቸኳይ የስራ ቅጥር💥💥💥
✅ድርጅታችን በተዘረዘሩት የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል።
═••════••• •••••• •••••• •
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ባንክ ተላላኪና ፅዳት
☆የት/ደረጃ:- ማንበብ እና መፃፍ የምትችል
☆የስራ ልምድ:- ያላት
☆ፆታ:- ሴት
☆ደሞዝ:4,500
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ:- መምህር በሉም ረዳትናዋና
☆የት/ደረጃ:- 10/ዲግሪ/ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:- ዐ አመት እና ከዛ በላይ
☆ፆታ:- ወንድ/ሴት
☆ብዛት:- 20
☆ደሞዝ:-8,700
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኮንስትራክሽን/ፎርማል
☆የት/ደረጃ:# ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:# 0-2 ዓመት
☆ፆታ:# ወንድ
☆ብዛት:# 7
☆ደሞዝ:-በስምምነት
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኦፌስ እንጅነሪግ
☆የት/ደረጃ:# ዲግሪ
☆የስራ ልምድ:# 2አመት
☆ፆታ:# ሴት/ወንድ
☆ብዛት:# 7
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ተጫራች/የጨረታ ባለሙያ/
☆የት/ት ደረጃ: መፃፍ እና ማንበብ
☆የስራ ልምድ: ጨረታ ሰርቶ የሚያውቅ
☆ፆታ: ወንድ
አድራሻችን:-አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደቦሌ በሚውደው መንገድ ወረድ ብለው አዋሽ ባንክ ፊትለፊት ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ/ቁ 006
ስልክ : 0991333943/0991334043
https://tttttt.me/JobsAtHewan
✅ድርጅታችን በተዘረዘሩት የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል።
═••════••• •••••• •••••• •
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ባንክ ተላላኪና ፅዳት
☆የት/ደረጃ:- ማንበብ እና መፃፍ የምትችል
☆የስራ ልምድ:- ያላት
☆ፆታ:- ሴት
☆ደሞዝ:4,500
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ:- መምህር በሉም ረዳትናዋና
☆የት/ደረጃ:- 10/ዲግሪ/ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:- ዐ አመት እና ከዛ በላይ
☆ፆታ:- ወንድ/ሴት
☆ብዛት:- 20
☆ደሞዝ:-8,700
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኮንስትራክሽን/ፎርማል
☆የት/ደረጃ:# ዲፕሎማ
☆የስራ ልምድ:# 0-2 ዓመት
☆ፆታ:# ወንድ
☆ብዛት:# 7
☆ደሞዝ:-በስምምነት
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ኦፌስ እንጅነሪግ
☆የት/ደረጃ:# ዲግሪ
☆የስራ ልምድ:# 2አመት
☆ፆታ:# ሴት/ወንድ
☆ብዛት:# 7
═••════••• •••••• •••••• •••════•
🔊 የስራ መደብ: ተጫራች/የጨረታ ባለሙያ/
☆የት/ት ደረጃ: መፃፍ እና ማንበብ
☆የስራ ልምድ: ጨረታ ሰርቶ የሚያውቅ
☆ፆታ: ወንድ
አድራሻችን:-አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደቦሌ በሚውደው መንገድ ወረድ ብለው አዋሽ ባንክ ፊትለፊት ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ/ቁ 006
ስልክ : 0991333943/0991334043
https://tttttt.me/JobsAtHewan
ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው የአርት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ በዛሬው ዕለት ይከናወናል!
ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው የአርት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ በዛሬው ዕለት ይከናወናል፡፡የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በሴኔት ሌጅስሌሽን አንቀጽ ቁጥር 9/2010 መሰረት የአርት የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰጣት በሙሉ ድምጽ ማፅደቁ ይታወቃል።
በዚህም የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው የክብር ዶክትሬት በዛሬው ዕለት ይሰጣል።አርቲስት ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት እጅጋየሁ ሽባባው "ጂጂ" የሀገር ፍቅርን የተላበሱ የኪነ ጥበብ ሥራዎቿን ለአድማጭ አበርክታለች።
በተለይ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ረገድ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፋለች፡፡በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር በስድስት ኮሌጆች በ27 ትምህርት ፕሮግራሞች እና በድኅረምረቃ ትምህርት ሦስት ፕሮግራሞች ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ተማሪዎችን ያስመርቃል።
በዩኒቨርሲቲው ለተከታታይ አራት ዓመታት እና በመደበኛው መርሐ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከነበሩ ተማሪዎች ወንድ 381 እና ሴት 259 በድምሩ 640 እንዲሁም የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም ስልጠና የወሰዱ 110 መምህራንን ጨምሮ በአጠቃላይ 750 ተማሪዎች ናቸው የሚመረቁት።እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 67.5 በመቶ 50% እና ከዚያ በላይ በማምጣት ማለፍ ችለዋል።
[Walta]

❤1
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየ የትምህርት መሰክ ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ይገኛሉ!
በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ከሚያሰመርቁ ዩኒቨርስቲዎች የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ደብረብርሃን፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ብርሃን፣ ወለጋ፣ አርባምንጭ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋና ሰመራ ዩኒቨርስቲዎች ይገኙበታል።
በተመሳሳይ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው የአርት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ በዛሬው ዕለት ይከናወናል። የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰጣት በሙሉ ድምጽ ማፅደቁ ይታወቃል።
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በመደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር በስድስት ኮሌጆች በ27 ትምህርት ፕሮግራሞችና በድኅረምረቃ ትምህርት ሦስት ፕሮግራሞች ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ተማሪዎችን ያስመርቃል።
በሌላ በኩል የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለ15 ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 90 ተማሪዎችን አሰመርቋል። ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 268 ሴት ተማሪዎች ይገኙበታል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቢኒያም በለጠ የክብር ዶክትሬት ሰጠ!
የመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ሕሙማን ማዕከል መሥራች ቢኒያም በለጠ ለባረከተው በጎ ስራ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የክብር ዶክተሬት ዛሬ ተሰጥቶታል።
ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ 642 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በሚሊኒየም አዳራሽ እያስመረቀ ነው።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ሌሎችም ተገኝተዋል።
Via Ethio FM

"የወረታ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ተገደሉ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ሃሰተኛ መረጃ ነው"- የወረታ ከተማ አስተዳደር
በትናንትናው እለት ማለትም ሃምሌ 12/2015 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ የቀድሞ ፖሊስ አባል የነበሩና ጡረታ የወጡና በንግድ ስራ የተሰማሩት አቶ መልኬ ጤናው የተባሉ ግለሰብ ድንገተኛ ግድያን ተከትሎ የተሳሳተና ከእውነት የራቀ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቶ ነበር።
በዚህም መሰረት የወረታ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ተገደሉ ተብሎ የተለቀቀው መረጃ ከእውነት የራቀና የተሳሳተ መረጃ መሆኑንና የወረታ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊም በአሁኑ ሰዓት በስራ ላይ ያሉና ስራቸውን እያከናወኑ ያሉ መሆኑን የወረታ ከተማ አስተዳደር በፌስቡክ ገፁ ገልጿል።አስተዳደሩ ህብረተሰቡ በሃሰተኛ መረጃ ከመደናገር እራሱን እይዲጠብቅ አሳስቧል።

👍2
የቀድሞው የብአዴን ከፍተኛ አመራር አቶ ታደሰ ካሳ ከእስር ተለቀቁ!
ለአራት ዓመት ተኩል በእስር ላይ የቆዩት የቀድሞው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ከፍተኛ አመራር አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ ሐሙስ ከእስር መለቀቃቸውን ጠበቃቸው ህይወት ሊላይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። አቶ ታደሰ ከእስር የተለቀቁት፤ የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት በነጻ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ካስተላለፈ አንድ ሳምንት በኋላ ነው።
ከጥረት ኮርፖሬት ጋር በተያያዘ በከባድ የሙስና ወንጀል ተከስሰው የተፈረደባቸው አቶ ታደሰን በተመለከተ፤ የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት በዋለው ችሎቱ ነበር። ችሎቱ ጉዳዩን የተመለከተው የአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2012 ዓ.ም “ጥፋተኛ ናቸው” በማለት አቶ ታደሰ ላይ ያስተላለፈውን ቅጣት በተመለከተ በቀረበለት አቤቱታ መሰረት ነው።
ደንበኛቸው እስከ ዛሬ ድረስ ሳይፈቱ የቆዩት፤ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወራት የታሰሩበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት “በራሱ መልቀቅ ስለማይችል” እንደሆነ ጠበቃ ህይወት አስረድተዋል። ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ አብዛኛውን የእስር ጊዜያቸውን በባህር ዳር ማረሚያ ቤት ያሳለፉት አቶ ታደሰ፤ በህክምና ምክንያት በተዛወሩበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የቆዩት “በአደራ” ነበር።

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷ ከተናጋ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ተወቃሽ ይሆናሉ" ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግር ዙሪያ ዛሬ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በትግራይ ክልል ተካሄደ የተባለው ሕገወጥ "የኤጲስ ቆጶሳት" ምርጫ ወደ ሹመት እንዳያመራ የፌደራል እና የክልል መንግስታት እንዲያስቆሙ ጠይቀዋል።
በትግራይ የሚገኙ አህጉረ ስብከትን የሚመሩ ሊቃነ ጳጳሳት ሕገወጥ "የኤጲስ ቆጶሳት" ምርጫ ማካሄዳቸውን እና ይህ ምርጫ ወደ ሹመት እንዳያመራ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ኃላፊነት እንዳለባቸው ነው ብፁዕነታቸው ያስታወቁት።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት መናጋት የሀገርም አንድነት መናጋት ነውና ይህ ሹመት እንዳይፈጸም ኃላፊነታቸውን ካልተወጡ በታሪክ ተወቃሽም ተከሳሽም የፌደራል እና የክልል መንግስታት መሆናቸው አይቀርም ብለዋል ብፁዕ አቡነ አብርሃም።
በትግራይ ክልል ተፈጥሮ የነበረው ችግር ሁሉንም ያሳዘነ እንደነበር እና የተፈጠረው ችግር እንዳይፈጠር ቅዱስ ሲኖዶስ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም አለመሳካቱን በተጨማሪም ችግሩ የሚፈታው በክልሉ ያሉ የተራቡትን ፣ የፈረሱትን እና የደከሙትን በማበርታት በመስራት መሆኑን ፤ ይህን ለማድረግም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዝግጁ መሆኗም ነው የተገለጸው።
መረጃው የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ነው!