የ51 የሽብር ወንጀል ተከሳሾችን ጉዳይ የሚመለከቱ ዳኛ በሌላ መተካት፤ በችሎት ቅሬታ አስነሳ!
አምስት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ጨምሮ የ51 የሽብር ወንጀል ተከሳሾችን ጉዳይ ከሚመለከቱት ዳኞች መካከል አንዱ መቀየራቸው በተከሳሾች እና ጠበቆቻቸው በኩል ቅሬታን አስነሳ። ጉዳዩን በተለመከተ በጽህፈት ቤት ቅሬታ የቀረበላቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፤ “ዳኞችን መቀየር የፍርድ ቤቱ አስተዳደር ስልጣን ነው” ሲሉ ለጠበቆች ምላሽ ሰጥተዋል ተብሏል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሶስተኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት ለዛሬ ሰኞ ሐምሌ 3፤ 2015 ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፤ ተከሳሾች ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ነበር። ሆኖም በመቅረጸ ድምጽ የተቀዳው የባለፈው የችሎት ውሎ ሂደት ዘግይቶ በመገልበጡ እና አንዱ የችሎት ዳኛ በመቀየራቸው ትዕዛዙ አለመድረሱን ተናግረዋል።
በሃምሳ አንዱ ግለሰቦች ላይ በይፋ ክስ ከተመሰረተበት ከሰኔ 1፤ 2015 ጀምሮ መዝገቡን ሲመለከቱ የቆዩት ሶስት ዳኞች ሲሆኑ፤ ከእነርሱ መካከል የግራ ዳኛው በዛሬው ችሎት በሌላ ዳኛ ተተክተው ታይተዋል። ዛሬ በአካል ችሎት ፊት ከቀረቡት 23 ተከሳሾች መካከል የመናገር ዕድል የተሰጣቸው አምስት ተከሳሾች፤ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ትዕዛዝ ሊሰጥ አለመቻሉ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa

የትግራይ ቤተ ክርስቲያን አባቶች በመቀለ በተካሄዱ ሥነ ሥርዓቶች ላይ አለመገኘታቸው ተነገረ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያትክ የተመራው ቡድን መቀለ ውስጥ ባካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የትግራይ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች ሳይገኙ መቅረታቸው ተነገረ።ለሁለት ዓመት በተካሄደው ጦርነት ምክንያት በቤተክርስቲያኑ አባቶች መካከል ሻክሮ የቆየውን ግንኙነት ለማሻሻል በፓትሪያርኩ የሚመሩ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች ሰኞ ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም. ወደ መቀለ ማቅናታቸው ይታወቃል።
አባቶቹ ረፋድ ላይ መቀለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ከጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ጋርም ተገናኝተዋል።ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጦርነቱ ወቅት የሚጠበቅበትን አላደረገም በሚል በተደጋጋሚ ወቀሳ ሲሰነዝሩ የነበሩት የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች በስፍራው እንዳልተገኙ ተገልጿል።
የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጦርነቱን በማውገዝ እና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ከጎናችን አልቆሙም ያሉት የትግራይ ቤተክርስቲያን አባቶች ከማዕከላዊው ሲኖዶስ በመነጠል የራሳቸውን ቤተክህነት ማቋቋማቸው ይታወቃል።ዛሬ ወደ መቀለ ያመራው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ በቤተክርስቲያኗ አባቶች መካከል የተፈጠረውን ቅሬታ ለማሻር ንግግር መጀመር እና በችግር ላይ ላሉ የክልሉ ነዋሪዎች ድጋፍ ማድረግ አላማው እንደሆነ በስፋት ሲነገር ቆይቷል።
በጦርነቱ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ ምዕመናን እና የቤተክርስቲያኗ አባቶች የሚጠብቁባትን ባለማድረጓ ቅዱስ ሲኖዶስ ባለፈው ሳምንት ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ ያሉ ሁኔታዎችን በተመለከተም ለመነጋገር ወደ ትግራይ አባቶች እንደሚጓዙ መገለጹ ይታወሳል።ከዚህ በፊት በነበረው ልምድ እና በተያዘው መረሃ ግብር መሠረት የቤተክርስቲያኗ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች በክልሉ ባለሥልጣናት እና በሃይማኖት አባቶች አቀባበል እንደሚደረግላቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ የትግራይ ሃይማኖት አባቶች እንዳልነበሩ ተዘግቧል።
ከዚያም በኋላ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት አቡነ ማቲያስ የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ በጦርነት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲደርስ የሰጠውን የሃያ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ለአቶ ጌታቸው ረዳ አስረክበዋል።
በሥነ ሥርዓቱ አቡነ ማቲያስ “በሕዝቡ ላይ የደረሰው መከራ ከባድ እና ታይቶ የማይታወቅ ነው” በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ መጠየቁን አስታውሰው፣ ድጋፉም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ “ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ተቀራርቦ መወያየት እና መነጋገር ይኖርብናል” ብለዋል።በዚህ ወቅትም አቶ ጌታቸው ረዳ ድጋፉ ዘግይቶ የተሰጠ ቢሆንም ጥረቱን በአዎንታዊ መልኩ እንደሚመለከቱት ገልጸው፣ አስተዳደራቸው በሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ የማይገባ መሆኑን በመጥቀስ “በሕዝቦች መካከል ያለ ቅራኔ እና አለመግባባት በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶሱ የጀመረው ጥረት ተገቢ” መሆኑን መናገራቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
አቶ ጌታቸው በተጨማሪም በተፈጠረው ጦርነት ወቅት ቤተክርስቲያን ከአፈናቃዮች ጋር ቁማለች የሚል ቅሬታ እንዳለ በመግለጽ “ቅሬታው የሕዝብ በመሆኑ በችግሮቹ ዙሪያ መተማመን እና መግባባት እንደሚያስፈልግ” ተናግረዋል።በፓትርያርኩ በኩል ከቤተክርስቲያኗ የተሰጠው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለአቶ ጌታቸው በተሰጠበት ሥነ ሥርዓት ላይም የክልሉ የሃይማኖት አባቶች ያልተገኙ ሲሆን፣ የልዑካን ቡድኑ በመቀለ ከተማ የሚገኙ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎችን ጎብኝቷል።
ለሁለት ዓመታት የተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት በአገሪቱ በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ ከባድ ውድመት ያስከተለ ሲሆን፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት እንደጠፋበት ይነገራል።ጦርነቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከልም ቅሬታን በመፍጠር የክፍፍል በርን ከፍቷል።
ባለፈው ሳምንት የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተክርስቲያኗ ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ ጥሪ ባለማቅረቧ፣ በጦርነቱ ወቅት በክልሉ የሚገኙ የቤተክርስቲያኗ አባቶችን እና የትግራይን ሕዝብ በአካል ባለመጠየቋ እንዲሁም ባለማጽናናቷ ይቅርታ ጠይቃለች።
የሽረ እንደ ሥላሴ አገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ እና የመንበረ ሰላማ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑትን ንቡረእድ ተስፋይ ተወልደ “ይቅርታ ጥሩ ጅምር ቢሆነም፣ በቂ ግን አይደለም” በማለት ተናግረዋል።ነገር ግን እስካሁን የክልሉ ቤተክህነት አባላት በተናጠል በይቅርታው ዙሪያ ከሰጡት አስተያየት ውጪ፣ በይፋ ከአባቶቹ የተሰጠ ምላሽ የለም።
Via ቢቢሲ አማርኛ

👍1
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተናን ይዘጋጁ፡፡ አፕሊኬሽኑ
✅ ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
✅ የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
✅ ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡
ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric

የሱዳን ጦር በአዲስ አበባው የኢጋድ ስብሰባ አልተሳተፈም!
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ትናንት በአዲስ አበባ ምክክር አድርጓል።ተፋላሚ ሃይሎቹ በስብሰባው ላይ እንደሚሳተፉ አረጋግጠው የነበረ ቢሆንም፥ ተወካዩን የላከው የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ብቻ ነው።የሱዳን ጦር ተወካይ አዲስ አበባ ቢገቡም በምክክሩ ላይ አልሳተፍም ማለታቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ የአራትዮሽ (ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ጂቡቲ) ስብሰባውን የሚመሩት የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያን ሩቶ በሌላ ካልተተኩ ጦሩ በስብስባው ላይ እንደማይሳተፍ ነው ያስታወቀው።ፕሬዝዳንቱ ለፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ያደላሉ የሚል ወቀሳ ከሱዳን ጦር ተደጋግሞ ተሰምቷል።
ኢጋድ በበኩሉ የሱዳን ጦር በስብሰባው ላይ እንደሚሳተፍ አረጋግጦ ሳይሳተፍ በመቅረቱ እንዳዘነ ገልጿል።የፖለቲካ አማካሪያቸውን ወደ አዲስ አበባ የላኩት ጀነራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ጦሩ በስብሰባው ላይ አለመሳተፉን “ሃላፊነት የጎደለው ባህሪ” ብለውታል።የአራቱ ሀገራት መሪዎች በቀጣይ ተፋላሚ ጀነራሎቹን ፊት ለፊት ለማገናኘት ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠቁመዋል።
ተፋላሚዎቹ በአፋጣኝ ግጭት አቁመው ዘላቂ የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ እንዲደርሱም ነው የጠየቁት።ኢጋድም የአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይልን ወደ ሱዳን እንዲያሰማራ ሊጠይቅ እንደሚችል ነው ይፋ ያደረገው።ተጠባባቂ ሃይሉ በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ ንጹሃንን ለመጠበቅ እና የሰብአዊ ድጋፎች ያለገደብ እንዲንቀሳቀሱ ያግዛል ተብሎም ታምኖበታል።
Via Alain

በክልሎች ይሰጥ የነበረው የአስመጪና ላኪዎች የንግድ አገልግሎት ወደ ፌዴራል መዞሩ ተገለጸ!
በክልሎች ይሰጥ የነበረው የአስመጪዎችና ላኪዎች ንግድ አገልግሎት ከሐምሌ 1/2015 ጀምሮ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኩል እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በክልሎችና በኹለቱ ከተማ አስተዳደሮች በኩል ይሰጥ የነበረው የአስመጪና ላኪ የንግድ አገልግሎት፤ አስተዳዳራዊ ክፍተቶች የታዩበት፣ የኮንትሮባንድ ንግድ የተበራከተበት በመሆኑና በወቅቱ አገልግሎቱ ያልወረደላቸው ክልሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በማንሳታቸው፤ ይህን ችግር ለመፍታት የአስመጪና ላኪዎች ንግድ አገልግሎት ከሐምሌ 1/2015 ጀምሮ በፌዴራል ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑን ሚኒስትር መስራ ቤቱ ገልጿል፡፡
ከሐምሌ 1/2013 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት ማንኛውም አስመጪና ላኪ ነጋዴ ሲስተሙን በመጠቀም ባለበት ቦታ ሆኖ አገልግሎት ማግኘት የሚችልበት ሲሆን፤ በአገልግሎቱ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጥያቄዎች ካሉ በ 965 የጥሪ መዕከል ደውሎ መረጃ ማግኘት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩና የሰላም ልዑኩ አባላት አዲስ አበባ ገቡ!
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሳላም ልዑክ
ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቀባበል የተደረገላቸው ቅዱስ ፓትርያርኩና የሰላም ልኡኩ አባላት ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት በጦርነት ምክንያት ለተፈናቃሉ ወገኖች የሚሆን የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።
የቤተክርስቲያኒቱ ርእሰ አበው የሆኑት ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ክልሉ ሲደርሱ በትግራይ ክልል በሚገኙ ብፁዓን አባቶች፣ ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ምንም ዓይነት መንፈሳዊ የአቀባበልም ይሁን የሽኝት ሥነ ሥርዓት ያልተደረገላቸው ሲሆን፤ ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ጭምር የኪዳን ጸሎትን በተዘጋ የቤተክርስቲያኒቱ ደጅ ላይ ለማድረግ ተገደዋል።
የሰላም ልኡኩ በክልል ትግራይ ያሉ ብፁዓን አባቶችን ለማግኘትና ከእነርሱም ጋር ለመወያየት ከወራት በፊት ጀምሮ ጥረት ቢያደርግም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ እንደቀረ ልዑኩ ገልጿል ።
Via EOTC TV
@Yenetube @Fikerassefa

"የሸኔ ጥያቄ ምን እንደሆነ አይታወቅም" ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
ለኦሮሞ ሕዝብ ቆሜያለሁ የሚለው “ሸኔ” ጥያቄው ምን እንደሆነ እንኳን ካለመታወቁም በላይ፤ ኦሮሞን እየገደለ ይገኛል ሲሉ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናገሩ፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ይህን ያሉት በማዕከላዊ ዕዝ በተልዕኮ አፈጻጸም የላቀ አስተዋፅኦ ላስመዘገቡ የዕዙ ኮሮችና ክፍለ ጦሮች የዕውቅና አሰጣጥ መድረክ ላይ ሲሆን፤ በመድረኩም “የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ለመጣል ባንዳዎች እየሰሩ ነው” ብለዋል፡፡ አክለውም፤ ለኦሮሞ ሕዝብ ቆሜያለሁ የሚለው ሸኔ ጥያቄው ምን እንደሆነ እንኳን ካለመታወቁም በላይ ኦሮሞን እየገደለ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
“እኛ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊ አይደለንም ስንል ፖለቲካ አይገባንም ማለት አይደለም” ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ “እንደ ወታደር ኢትዮጵያን የመውደድና የመጠበቅ ጽኑ ዓላማችን የሚመነጨው ከአገራችን ታሪክና ኹለንተናዊ ገጽታ ነው፡፡” ብለዋል።
“ሸኔን ጨምሮ የአገራችንን ሰላም አደፈርሳለሁ የሚልን ማንኛውንም ሃይል በሃይል እስከመጣ ድረስ እንዋጋዋለን” ያሉት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ፤ አሁን ላይ በባንዳዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ሴራዎች በታሪክ እየተመዘገበ ስለመሆኑ መዘንጋት እንደሌለበት ማመላከታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የእውቅና ሥነሥርዓት "ምንጊዜም ለመዘመን እና ለድል አድራጊነት እንዘጋጅ" በሚል መሪ ሐሳብ በጅማ ከተማ ጊቤ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በበዓሉ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮችና መኮንኖች ተገኝተውበታል።
Via Addis Maleda

❤1
በደቡብ ክልል አሌ ልዩ ወረዳ ሦስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ!
በደቡብ ክልል በኮንሶ እና አሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ፣ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት፣ ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ፣ የወረዳው መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ተወካይ፣ አቶ ምንጩ እሸቴ ተናግረዋል።የጥቃቱ ሰለባዎች፣ ወደ ገበያ በማቅናት ላይ የነበሩ ሰዎች እንደኾኑ የገለጹት አቶ ምንጩ፣ አሁንም በአካባቢው የጸጥታ ስጋት ስለመኖሩ ጠቁመዋል።
Via VoA

YeneTube
በደቡብ ክልል አሌ ልዩ ወረዳ ሦስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ! በደቡብ ክልል በኮንሶ እና አሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ፣ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት፣ ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ፣ የወረዳው መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ተወካይ፣ አቶ ምንጩ እሸቴ ተናግረዋል።የጥቃቱ ሰለባዎች፣ ወደ ገበያ በማቅናት ላይ የነበሩ ሰዎች እንደኾኑ የገለጹት አቶ ምንጩ፣ አሁንም በአካባቢው የጸጥታ ስጋት ስለመኖሩ…
በተያያዘ ዜና
በመተማ ወረዳ አንድ ሰው በታጣቂዎች ሲገደል ዘጠኝ እንደታገቱ ተገለጸ!
በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀሊት በተባለ ቀበሌ፣ ታጣቂዎች፥ አንድ ሰው እንደገደሉና ዘጠኝ ሰዎችን አግተው እንደወሰዱ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ነዋሪዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በወረዳው፣ ከሽንፋ ተነሥቶ ወደ ገንዳዋ ቀበሌ እየተጓዘ የነበረን አንድ አይሱዚ ተሽከርካሪ፣ ጉባይ ጀጀሊት በምትባል ቀበሌ፣ በተለምዶ የልዩ ኀይል ካምፕ እየተባለ በሚጠራው ቦታ አስቁመው ተሳፋሪዎችን ከአስወረዱ በኋላ፣ አንድን ወጣት ሲገድሉ ዘጠኝ ሰዎችን ደግሞ አግተው ወደ ጫካ ይዘዋቸው ሔደዋል፡፡
ለታጋች ቤተሰቦችም ስልክ ደውለው፣ መጠኑ የተለያየ ብዙ መቶ ሺሕ የማስለለቂያ ቤዛ (ገንዘብ) እየጠየቁ እንደኾነ፣ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ነዋሪዎቹ፣ ለግድያው እና ለእገታው ተጠያቂ ያደረጉት፣ በጫካ የነበሩና በእርቀ ሰላም ስም ተመልሰው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉ ‘ጽንፈኛ’ ሲሉ የጠሯቸው፣ የቅማንት ታጣቂዎች እንደኾኑ አመልክተዋል፡፡
በወረዳው፣ ተደጋጋሚ የግድያ እና የእገታ ድርጊት እንደሚፈጸም የገለጹልን ሲሳይ የተባሉ ሌላ አስተያየት ሰጪ፣ በአካባቢው ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ፣ ከዐማራም ከቅማንትም ወገን የኾኑና “ሽፍታ” ሲሉ የጠሯቸው ኀይሎች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ “ጥቃቱን ማስቆም አልቻሉም” ያሏቸውን የአካባቢውን የጸጥታ አካላት እና ባለሥልጣናት፣ ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ፣ በተጠቀሱት የወረዳው አካባቢዎች፣ ግድያ እና እገታው መኖሩን አምነው፣ በሥፍራው ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ኀይሎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው፤ ብለዋል ሲል የዘገበው የአሜሪካ ድምፅ ነው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
በመተማ ወረዳ አንድ ሰው በታጣቂዎች ሲገደል ዘጠኝ እንደታገቱ ተገለጸ!
በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀሊት በተባለ ቀበሌ፣ ታጣቂዎች፥ አንድ ሰው እንደገደሉና ዘጠኝ ሰዎችን አግተው እንደወሰዱ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ነዋሪዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በወረዳው፣ ከሽንፋ ተነሥቶ ወደ ገንዳዋ ቀበሌ እየተጓዘ የነበረን አንድ አይሱዚ ተሽከርካሪ፣ ጉባይ ጀጀሊት በምትባል ቀበሌ፣ በተለምዶ የልዩ ኀይል ካምፕ እየተባለ በሚጠራው ቦታ አስቁመው ተሳፋሪዎችን ከአስወረዱ በኋላ፣ አንድን ወጣት ሲገድሉ ዘጠኝ ሰዎችን ደግሞ አግተው ወደ ጫካ ይዘዋቸው ሔደዋል፡፡
ለታጋች ቤተሰቦችም ስልክ ደውለው፣ መጠኑ የተለያየ ብዙ መቶ ሺሕ የማስለለቂያ ቤዛ (ገንዘብ) እየጠየቁ እንደኾነ፣ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ነዋሪዎቹ፣ ለግድያው እና ለእገታው ተጠያቂ ያደረጉት፣ በጫካ የነበሩና በእርቀ ሰላም ስም ተመልሰው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉ ‘ጽንፈኛ’ ሲሉ የጠሯቸው፣ የቅማንት ታጣቂዎች እንደኾኑ አመልክተዋል፡፡
በወረዳው፣ ተደጋጋሚ የግድያ እና የእገታ ድርጊት እንደሚፈጸም የገለጹልን ሲሳይ የተባሉ ሌላ አስተያየት ሰጪ፣ በአካባቢው ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ፣ ከዐማራም ከቅማንትም ወገን የኾኑና “ሽፍታ” ሲሉ የጠሯቸው ኀይሎች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ “ጥቃቱን ማስቆም አልቻሉም” ያሏቸውን የአካባቢውን የጸጥታ አካላት እና ባለሥልጣናት፣ ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ፣ በተጠቀሱት የወረዳው አካባቢዎች፣ ግድያ እና እገታው መኖሩን አምነው፣ በሥፍራው ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ኀይሎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው፤ ብለዋል ሲል የዘገበው የአሜሪካ ድምፅ ነው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
❤1
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተናን ይዘጋጁ፡፡ አፕሊኬሽኑ
✅ ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
✅ የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
✅ ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡
ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
✅ ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
✅ የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
✅ ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡
ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
የጨፌ ኦሮሚያ በግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አነሳ!
ጨፌ ኦሮሚያ ላለፉት ሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔውችን በማሳለፍ ትናንት አጠናቋል።ጨፌው አባሉ የነበሩትን የነቀምቴ ከተማ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ የአቶ ቶሌራ ረጋሳ ጨዋቃን ያለመከሰስ መብ አንስቷል።
የአቶ ቶሌራ ረጋሳ ጨዋቃ ያለመከሰስ መብት የተነሳው የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ በነበሩበት ወቅት የከተማዋ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በነበሩት በአቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ ግድያ እንሆነ ተነግሯል።
የነቀምቴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ ከወራት በፊት በመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።

በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የተጀመረው ውይይት እንዲቀጠል የጨፌው አባላት ጠየቁ!
በኦሮሚያ ክልል ለቀጠለው አለመረጋጋት እልባት ለመስጠት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል ተጀምሮ የተቋረጠው የሰላም ድርድር፣ እንዲቀጥል መደረግ አለበት፤ ሲሉ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባላት ጠየቁ፡፡
በክልሉ ምክር ቤት ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የተናገሩት፣ የኦሮምያ ክልል የብልጽግና ቢሮ ሓላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ፣ አምስት ዓመት ያስቆጠረው የሰላም ዕጦት፣ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ፣ የተጀመረው ውይይት እንዲቀጥል መንግሥት ቁርጠኛ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡
በታንዛንያ ዛንዚባር፣ መንግሥትን ወክለው በቅድመ ድርድር ንግግሩ የተሳተፉት የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊ ኮሚሽነር ከፍ ያለው ተፈራ በበኩላቸው፣ ውይይቱ እንዳልተቋረጠ ገልጸዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ሰለሞን ተፈራ፣ ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር በአፋጣኝ ቀጥሎ ችግሩ እልባት ካላገኘ፣ “መዘዙ ብዙ ነው፤” ሲሉ አመልክተዋል፡፡
በቅድመ ድርድር ንግግር የተጀመረው ውይይት ቀጣይነት ቅድመ ኹኔታዎችን እንዳስቀመጠ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

አምስት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ‹ በኢትዮጵያ አስቸኳይ የሃገር አድን ውይይት እንዲካሄድ › ጠየቁ።
‹ ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው ወደ ማታውቅ ጥፋት በመሄድ ላይ መሆኗን › የገለፁት አምስቱ ፓርቲዎቹ ‹ በመንግስት አና በታጠቁ ሃይሎች መካከል አስቸኳይ የሃገር አድን ውይይት ማድረግ ይግባል › ሲሉ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠይቀዋል።
አምስቱ የፖለቲካ ድርጅቶች እናት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ፓርቲ(አኢዴፓ)፣ የአማራ ግዮናዊ ንቅናቄ(አግን)ና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ናቸው፡፡
ፓርቲዎቹ በጋራ በሰጡት መግለጫቸው ‹ በዚች አገር የሚታየው ችግር ምንጩ መንግስት እና የታጠቁ ሃይሎች ናቸው › ብለዋል። አክለውም ‹ በመንግስት እና በታጠቁ ሃይሎች መካከል የሚደረግ አስቸኳይ ውይይት ለኢትዮጵያ ብቸኛ መፍትሄ መሆኑን › አመላክተዋል።
ይህ በአስቸኳይ እንዲደረግ የጠየቁት አገርን የማዳን ውይይት ላይ የሀገር ህልውና ያገባናል የሚሉ ወገኖች ሁሉ እንደሚሳተፉበት ተናግረዋል፡፡
በትብብር የሚሰሩት ፓርቲዎቹ በአስቸኳይ እንዲካሄድ የጠየቁት ውይይት መንግስት በአዋጅ ካቋቋመው ‹ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በምንም ዓይነት መንገድ የሚገናኝ እንዳልሆነ › አመላክተው ‹ በመንግስት እና በተቃናቃኝ ወገኖች መካከል የሚደረግ ስለመሆኑ › አመላክተዋል።
‹ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በራሱ መንገድ የሚሰራውን ስራ እየሰራ ቢሆንም አገር ግን በመሃል አደጋ ላይ ስለወደቀች አገርን ለምክክር ኮሚሽኑ ከነ ህልውናዋ ለማድረስም ቢሆን አስቸኳይ ውይይት ማደረግ ይገባል › ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ‹ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ በግራም በቀኝም የሚታዩ ችግሮች ሁሉ የምክክር ኮሚሽኑ የመወያያ አጀንዳዎችን ለይቶ ከጨረሰ በኋላ የተፈጠሩ በመሆናቸው ኢትዮጵያ አይናችን እያየ ልትፈራርስ የምትችልበት ደረጃ ላይ ትገኛለች › ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡
‹ መንግስት ከህወሓት ጋር የገባበትን ችግር በፕሪቶርያ በሰላም ድርድር ፈትቶ ሲያበቃ ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሲል ከሚጥራው ታጣቂ ጋር በዛዚንባር የሰላም ንግግር እያደረገ ባለበት አግባብ፣ ከአማራ ሃይሎች ጋር አዲስ ግንባር መፍጠሩ ለሃገር ይዞት የሚመጣን ቀውስ ፈጣን በሆነ ውይይት መፍታት ይገባል › ሲሉም አክለዋል።
በመሆኑም ‹ የሃገሪቱ መንግስት ጥሪውን ተቀብሎ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ውይይቱን ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ማደረግ እንዲጀምር › ጥሪ አቅርበዋል።
ፓርቲዎቹ አክለውም ‹ የውይይት ጥያቄያቸውን ለሶስቱም የመንግስት አካላት ማለትም ለህግ አውጭው፣ ህግ አስፈፃሚው እና ህግ ተርጓሚው አካል መላካቸውን › ይፋ አድርገዋል።
መንግስት የተጠየቀውን ፈጣን የውይይት ጥያቄ ተቀብሎ እንዲካሄድ ማድረግ ካልቻለ ‹ መንግስትን በማስገደድ ውይይቱ እንዲካሄድ ማድረግ እንችላለን › ሲሉም ገልፀዋል።
‹ በመላ ሃገሪቱ የተጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ በመምራት እና ትግሉን በማቀጣጠል መንግስት ላይ በሰላማዊ የትግል ጫና በማሳደር አስገድደን ወደ ውይይት እንዲመጣ እናደርጋለን › ሲሉም የወጠኑት አስረድተዋል።
Via Asham

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጥሰት አሳሳቢነቱ መቀጠሉን ገለጸ፡፡
ከሰኔ 2014-ሰኔ 2015 ድረስ ያለዉን ዓመታዊ ሪፖርቱን ይፋ ያደረገዉ ኮሚሽኑ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጥሰት አሳሳቢነቱ መቀጠሉን አስታዉቋል፡፡ዓመታዊ ሪፖርቱ ካለፈው ዓመት አንጻር ግጭቶችን በሰላም በመፍታት ረገድ አበረታች ጅማሮዎች ቢስተዋሉም፣ በሪፖርት ዘመኑ ተለዋዋጭ እና ዘርፈ ብዙ የመብቶች ጥሰቶች በተለያዩ የመንግሥት መዋቅሮች እና መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላት መፈጸማቸውን አብራርቷል።
የዘፈቀደ እስርና ተገቢ ያልሆነ አያያዝ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል አጠቃቀም፣ በሚዲያና ተቃዋሚዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፣ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀሰ መብት ላይ የተጣለ የዘፈቀደ ገደብ፣ ሕጋዊ ሂደትን ያልተከተለ የቤቶች ፈረሳ፣ በግዳጅ ማስነሳትና በኑሮ ውድነት የተነሳ የደረሰው እንግልትና የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲሁም በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋም አሳሳቢነታቸው ከቀጠሉ ጉዳዮች ውስጥ እንደሚገኙ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በየካቲት ወር 2015 ዓ.ም. የተጀመረው የክልሎችን ልዩ ኃይሎች መልሶ የማደራጀት እንቅስቅሴ ተከትሎ፣ በተለይም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶች እና የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር፣ በኦሮሚያ ክልል በግጭት ውስጥ የሚገኙ አካባቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣት፣ እንዲሁም በሁሉም ክልሎች ዘላቂ መፍትሔ ባለማግኘታቸው በተደጋጋሚ በሚያገረሹ ግጭቶች ሳቢያ የሚደርሰው ሞት፣ አካል ጉዳት፣ መፈናቀል እና የመሠረተ ልማቶች እና የንብረት ውድመቶች አሁንም አሳሳቢነቱ መቀጠሉን በሪፖርቱ አስታዉቋል፡፡
የዘፈቀደ እና ሕገ ወጥ እስሮች፣ አስገድዶ መሰወር፣ የዋስ መብትን አለማክበር፣ ድብደባና የማሰቃየት ድርጊቶች መፈጻመቸው ተጠቁሟል፡፡
በጦርነት እና በትጥቅ ግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም፣ እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔ ከመስጠት አስፈላጊነት በተጨማሪ፣ የጸጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣት በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ላይም ከፍተኛ ጫና እና ጥሰት ማስከተሉን አንስቷል፡፡
እነዚህ ችግሮች እንዳሉ ሆነው፣ መሠረታዊ በሆኑ የምግብ እና ምግብ ነክ ምርቶች ላይ የሚታየው ዋጋ መናር እና በአሁኑ ወቅት ያለው አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ሰዎችን ለከፍተኛ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየዳረጉ መሆኑ ኮሚሽኑ አሳሳቢ ጉዳዮች ብሎ ካመላከታቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው።
በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው ጦርነት በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. በተደረገው ዘላቂ ተኩስ ማቆም እና የሰላም ስምምነት መሠረት ማብቃቱና፤ ኮሚሽኑና የተ.መ.ድ. ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት በጣምራ ባካሄዱት ምርመራ ከሰጧቸው ምክረ ሐሳቦች መካከል አንዱ የሆነውን የሽግግር ፍትሕ የሰላም ስምምነቱ አካል እንዲሆን መደረጉ፣ ይህንንም ተከትሎ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ የፖሊሲ አማራጮች (Green Paper) ማዘጋጀቱ እና ማኅበረሰብ አቀፍ ውይይቶች ማካሄድ መጀመሩ በመልካም ከተጠቀሱ እመርታዎች መካከል ናቸዉ፡፡
በስተመጨረሻም የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በ2015 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት “ሰዎች በሰላም ወጥቶ የመግባት፣ ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስ እና የመሥራት መብቶቻቸው ባልተከበረበት ሁኔታ የተመዘገቡ መልካም ለውጦች ዘላቂነት አይኖራቸውም” ያሉ ሲሆን፤ የትጥቅ ግጭቶችን ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ ለማስቆም እና የሰዎችን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ መከናወን ካለባቸው ተግባራት በተጨማሪ የፍትሕ እና የአስፈጻሚ አካላት ተቋማት በቁርጠኝነት የሕግ የበላይነትን ሊያስከብሩ” እንደሚገባ አሳስበዋል።

👍2
በጎንደር ከተማ እስራኤላዊ ዜጋ ታገተ በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ ገለጸ!
በጎንደር ከተማ አንድ እስራኤላዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ታገተ በሚል በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለጸ፡፡የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮምሽነር አየልኝ ታክሎ፤ ሰሞኑን በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች አንድ እስራኤላዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ በጎንደር ከተማ ታገተ በሚል በሀሰት የተለቀቀው መረጃ ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
በከተማዋ እገታ ተፈጽሞብናል የሚል አቤቱታ ያቀረበ አካል እንደሌለም ተናግረዋል።ረዳት ኮምሽነሩ አክለውም፤ ተጨባጭ እና ባልተረጋገጠ መረጃ እገታ ተፈፅሟል የሚሉ አካላት የኅብረተሰቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚያውክ በመሆኑ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ይህን ይበል እንጂ፤ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ፤ በዜግነት እስራኤላዊ የሆነ አንድ ግለሰብ በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ታግቶብኛል ሲል አስታውቋል፡፡የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው፤ ግለሰቡ ጎንደር አቅራቢያ መታፈኑን ሰኞ ዕለት ሪፖርት እንደተደረገለት የገለጸ ሲሆን፤ አፋኞቹ ወንጀል ለመፈጸም ተነሳስተው ያደረጉት ነው ሲልም ገልጿል። ዲፕሎማቶች ከአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች እና ከኢንተርፖል ጋር በመቀናጀት ታጋቹን ለማስለቀቅ እየሰሩ እንደሚገኙም አስታውቋል፡፡
የእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን በበኩላቸው፤ እስራኤላዊው ታጋች እድሜው በ70ዎቹ የሚገመት መሆኑን ጠቅሰው፤ ከቀናት በፊት ወደ ጎንደር ከተማ ያቀናው ሕክምና ለማግኘት እንደነበር ገልጸዋል፡፡ከአጋቾቹ ጋር ኢንተርፖል እና የአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች ግንኙነት ለማድረግ መሞከራቸውን ዘገባዎቹ ያመላከቱ ሲሆን፤ በወቅቱም ማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቃቸው ጠቁመዋል።
አጋቾቹ ግለሰቡን ለመልቀቅ በመጀመሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ጠይቀው እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ ካጋቾቹ ጋር በተደረገ ውይይት ገንዘቡ ወደ ሺዎች መውረዱም ነው የተጠቀሰው፡፡ታጋቹ እስራኤላዊ በድምጽ ለቤተሰቦቹ በላከው መልዕክት “እርዱኝ፣ በጫካ መሃል ላይ እገኛለሁ” ማለቱን ዘገባዎቹ ያስነበቡም ሲሆን፤ “ዝናብ እየዘነበብኝ ነው እርዱኝ፤ እሁድ ዕለት መምጣት ነበረብኝ ግን መቆየቴ አይቀርም፤ ልጆቼ እርዱኝ፣ አሁን ያለሁበት ሁኔታን ለጠላቶቼም አልመኘውም" ሲል መደመጡንም ገልጸዋል፡፡
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር ከተማ አንድ እስራኤላዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ታገተ በሚል በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለጸ፡፡የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮምሽነር አየልኝ ታክሎ፤ ሰሞኑን በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች አንድ እስራኤላዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ በጎንደር ከተማ ታገተ በሚል በሀሰት የተለቀቀው መረጃ ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡
በከተማዋ እገታ ተፈጽሞብናል የሚል አቤቱታ ያቀረበ አካል እንደሌለም ተናግረዋል።ረዳት ኮምሽነሩ አክለውም፤ ተጨባጭ እና ባልተረጋገጠ መረጃ እገታ ተፈፅሟል የሚሉ አካላት የኅብረተሰቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚያውክ በመሆኑ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ይህን ይበል እንጂ፤ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ፤ በዜግነት እስራኤላዊ የሆነ አንድ ግለሰብ በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ታግቶብኛል ሲል አስታውቋል፡፡የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው፤ ግለሰቡ ጎንደር አቅራቢያ መታፈኑን ሰኞ ዕለት ሪፖርት እንደተደረገለት የገለጸ ሲሆን፤ አፋኞቹ ወንጀል ለመፈጸም ተነሳስተው ያደረጉት ነው ሲልም ገልጿል። ዲፕሎማቶች ከአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች እና ከኢንተርፖል ጋር በመቀናጀት ታጋቹን ለማስለቀቅ እየሰሩ እንደሚገኙም አስታውቋል፡፡
የእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን በበኩላቸው፤ እስራኤላዊው ታጋች እድሜው በ70ዎቹ የሚገመት መሆኑን ጠቅሰው፤ ከቀናት በፊት ወደ ጎንደር ከተማ ያቀናው ሕክምና ለማግኘት እንደነበር ገልጸዋል፡፡ከአጋቾቹ ጋር ኢንተርፖል እና የአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች ግንኙነት ለማድረግ መሞከራቸውን ዘገባዎቹ ያመላከቱ ሲሆን፤ በወቅቱም ማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቃቸው ጠቁመዋል።
አጋቾቹ ግለሰቡን ለመልቀቅ በመጀመሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ጠይቀው እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ ካጋቾቹ ጋር በተደረገ ውይይት ገንዘቡ ወደ ሺዎች መውረዱም ነው የተጠቀሰው፡፡ታጋቹ እስራኤላዊ በድምጽ ለቤተሰቦቹ በላከው መልዕክት “እርዱኝ፣ በጫካ መሃል ላይ እገኛለሁ” ማለቱን ዘገባዎቹ ያስነበቡም ሲሆን፤ “ዝናብ እየዘነበብኝ ነው እርዱኝ፤ እሁድ ዕለት መምጣት ነበረብኝ ግን መቆየቴ አይቀርም፤ ልጆቼ እርዱኝ፣ አሁን ያለሁበት ሁኔታን ለጠላቶቼም አልመኘውም" ሲል መደመጡንም ገልጸዋል፡፡
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
👍2
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተናን ይዘጋጁ፡፡ አፕሊኬሽኑ
✅ ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
✅ የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
✅ ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡
ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
✅ ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
✅ የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
✅ ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡
ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
ከአዲስ አበባ የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ውል ባለመፈጸማቸው፤ ሁለተኛ ለወጡ ተጫራቾች ጥሪ ቀረበ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአንድ ወር በፊት የመሬት ሊዝ ጨረታ ባካሄደባቸው ቦታዎች ላይ ተጫርተው አንደኛ ከወጡ አሸናፊዎች ውስጥ፤ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ ውል አለመፈጸማቸውን የከተማዋ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ውል ካልፈጸሙት አሸናፊዎች ውስጥ “የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የተጫረቱ” ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ግምት እንዳለው ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከአራት ዓመት በኋላ የተደረገውን የመሬት ሊዝ ጨረታ ያወጣው በግንቦት 2015 መጀመሪያ ላይ ነበር። በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ 297 ቦታዎች በቀረቡበት በዚህ ጨረታ፤ ተወዳዳሪዎች ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት እስከ 700 ሺህ ብር በሚጠጋ የመወዳደሪያ ዋጋ ተጫርተዋል። የከተማይቱ ቢሮ በግንቦት ወር መጨረሻ የ287 ቦታዎች አሸናፊዎች በለየበት ወቅት፤ ለአንድ ካሬ ሜትር 414 ሺህ ብር ካቀረቡ ተጫራች ከፍተኛው የማሸነፊያ ዋጋ መመዝገቡ ይፋ ተደርጓል።
የጨረታ አሸናፊዎቹን ዝርዝር ሰኔ 11፤ 2015 ያሳወቀው የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፤ ተጫራቾች በአስር የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዳቸው ላይ ያቀረቡትን ቅድመ ክፍያ ፈጽመው ውል እንዲያስሩ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ሆኖም በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ውስጥ ውል የፈጸሙት የጨረታ አሸናፊዎች 131 ያህሉ ብቻ መሆናቸውን የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍ ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ማዕድን በምቹ የግብይ ሥርዓት እንዲከናወን የሚያግዝ ዲጂታል መገበያያ ማዕከል ተከፈተ፡፡
የማዕድን ዲጂታል መገበያያ ማዕከልን ያስተዋወቀው በቀድሞ አጠራሩ “የኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን በአሁኑ መጠሪያው ደግሞ የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ነው፡፡ኮርፖሬሽን በማዕድን ዘርፍ ልማት ላለፉት 60 ዓመታት በውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ በሰፊ ዕድል በፈጠራና በማህበረሰብ ልማት በርካታ ውጤቶችን ያስመዘገበ ተቋም መሆኑን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ራሄል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከማዕድን ፍለጋና ልማት ሥራዎች በተጨማሪ የማዕድን ምርመራ ቁፋሮ (ድሪሊንግ)ና የማዕድን ላቦራቶሪ ፣ የማዕድን ጥናት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ኮርፖሬሽናችን በትላንትናው ዕለት በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነውን የጌጣጌጥ ማዕድናት የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት ይፋ አድርጓል፡፡
ዲጂታል የግብይት ሥርዓት በመጠቀም ለጊዜው በጌጣጌጥ ማዕድናት ወደፊት ደግሞ ሌሎችንም ማዕድናት ለማስተዋወቅ ፣ ለመሸጥና ለመግዛት የሚያስችል መሆኑ ተነግሮለታል፡፡ይህ አዲስ ዲጂታል የግብይት ሥርዓት ለማዕድን ላኪዎች የንግድ መዳረሻዎችን ለማስፋት የሚያግዝ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ማዕድናት ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው ሲሉ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊት በነበረው የጌጣጌጥ ማዕድናት የግብይት ሥርዓት ገዢና ሻጭን በተግቢው ደረጃ ለማገናኘት ከፍተኛ ችግር ያለበት፣ ግልጽኝነት የሌለውና ለኢ-መደበኛ የንግድ ሁኔታዎች የተጋለጠ መሆኑ ተነስቷል፡፡የዲጂታል ማዕድን የግብይት ሥርዓቱ በዓለም ላይ የሚገኙ እንደ ኦፓል፣ ሩቢ፣ ኤመራልድ፣ ሳፋየር፣ እና ሌሎች በርካታ የጌጣጌጥ ማዕድን ዓይነቶችን ከሸማቾች ጋር እንዲያገናኝ ተደርጎ መሰራቱ ተጠቅሷል፡፡
በዚህም የእያንዳንዱን የጌጣጌጥ ማዕድን ባህሪያት፣ የጥራት ደረጃ ከየት አገርና ቦታ እንደተመረቱ መግለጫ አለው ተብሏል፡፡የኢትዮጵያ ማዕድናት ዲጂታል የግብይት ሥርዓት በኢግል ላየን ቴክኖሎጂ ሲስተም ሶፍትዌሩ የተዘጋጀ ሲሆን ወጪው ደግሞ በዳሽን ባንክ እንደተሸፈነ ሰምተናል::
Via Sheger

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ በፈቃዳቸው ከኃፊነታቸው ለቀቁ!
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።ዳይሬክተሩ ከአራት ዓመታ በላይ ከመሩት ተቋም ስራቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን ተናግረዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኃላፊ ስራቸውን ለምን እንደለቀቁ ያሉት ነገር የለም።
ጂማ ዲልቦ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ዘርፉ ከነበረበት ድባቴ ወጥቶ ለሀገር ልማትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አስተዋጽኦ ማበርከት መጀመሩ በቀጣይ ዓመታት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።ዋና ዳይሬክተሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ተሻሽሎ ተቋሙ ዳግም ሲደራጅ ጀምሮ ነበር በኃላፊነት ላይ የነበሩት።

በትግራይ 1 ሺህ 3 መቶ ገደማ ሰዎች በረሃብ ህይወታቸው ማለፉን የክልሉ ጊዜያዊ መስተዳድር አስታወቀ!
በትግራይ ክልል በዓለም አቀፍ ተቋማት ሲቀርብ የነበረዉ የሰብዓዊ ድጋፍ በክልሉ ተፈጽሟል ከተባለዉ ስርቆት ጋር በተያያዘ ከተቋረጠ ወራት አስቆጥሯል። የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር የሆኑት ዶ/ር ገብረህይወት ገብረእግዚአብሔር ለብስራት ራዲዮ እንደተናገሩት ፤ በክልሉ በድምሩ 1 ሺህ 2 መቶ 98 ሰዎች በረሃብ ህይወታቸውን እንዳጡ ተናግረዋል።
በምዕራብ ትግራይ ዞኖች ከሚገኙ ተፈናቃዮች 5 መቶ 70 ሰዎች በምግብ እጥረት ህይወታቸው ማለፉን ኮሚሽነር ዶ/ር ገብረህይወት ገልጸዋል። በሌላ በኩል በሽሬ ፣ አዲግራት እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይና በመቀሌ ዙሪያ ባሉ ዞኖች እና ወረዳዎች 7 መቶ 28 ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸዉን ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
እንደ ዶ/ር ገብረህይወት ገለጻ ፤ በክልሉ ያለዉ የረሃብና ቸነፈር ከፍተኛ በመሆኑ እንደ አክሱም እና ሌሎች መረጃ ባልተሰበሰባቸዉ አካባቢዎች ቀሪ ሶስት ዞኖች ያለዉ ወቅታዊ መረጃ ሲገኝ ደግሞ ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁመዋል። ከሟቾቹ ዉስጥ ነፍሰጡሮች ፣ ህጻናት እና እድሜያቸዉ የገፋ ሰዎች ከፍተኛዉን ድርሻ ይይዛሉ ብለዋል።
የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በክልሉ ከ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጦርነቱ ምክንያት እርዳታ ጠባቂ እንዲሆኑ ተገድደዋል ብለዋል። ዶ/ር ገብረህይወት ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና ለአለማቀፍ ተራድዖ ድርጅቶች ችግሩ ከአቅም በላይ ደረጃ ላይ መድረሱን ብናሳዉቅም ድጋፍ እየቀረበልን አይደለም ብለዋል።
ብስራት ራዲዮ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለል አቦሀይን የሟቾች ቁጥርን በሚመለከት የጠየቀ ቢሆንም ቁጥሩ የተጋነነ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ለክልሉ እስከ ቅርብ ሳምንታት ድረስ ድጋፍ ማቅረቡንም ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይም ጣቢያችን በተጨማሪ መረጃ ይመለሳል።
[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]