YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ የመገኛኛ ብዙኃን ነፃነትን ለማሻሻል እና ዓለማቀፍ ደረጃውን ለማስጠበቅ፣ የጋዜጠኞችን በነፃነት የመሥራት መብት ለማስከበር በሚል ከሦስት ዓመታት በፊት ተሻሽሎ የቀረበው አዲሱ የኢትዮጵያ የመገኛኛ ብዙኃን ሕግ በአግባቡ ተግባራዊ አልሆነም ተባለ።

ካርድ የመብቶች እና የዲሞክራሲ ማእከል፣ ከኢንተር ኒውስ ጋር ያዘጋጀውን ጥናታዊ ጽሑፍ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባቀረበበት ወቅት በዚሁ ጉዳይ ላይ ተወያይቷል።በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ መሰረትም፦ የመገናኛ ብዙኃን ሕጉ ተሻሽሎ ከወጣበት ካለፉት 3 ዓመታት ጀመሮ ሞያው በተፈለገው መለኩ አላደገም ተብሏል።

የፖለቲካ ተጽእኖ መኖር እንዲሁም ሕጉ በግጭት ወቅት የወጣ መሆኑ ለዚህ እንደ ምክንያትነት ቀርቧል።ሞያውም የሕግ ከለላ አለማግኘቱ አሳሳቢ ነው ተብሏል።እስካሁንም 39 የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች መታሰራቸው ተገልጿል።የጋዜጠኞች እንግልት እና እስርም በክልል ደረጃ የበለጠ አሰቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ አሳሳቢ ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ በበርካታ ችግሮች መሀል መገናኛ ብዙኃኑ መናገር እንዳቃተዉ በግልፅ የሚታይ ቢሆንም ዛሬ የቀረበው ጥናት ግን ለዚህ ችግሩ ምን እንደሆነ መልስ ለመስጠት አለመሞከሩ የጥናቱ ክፍተት ነው በሚል በታዳሚዎች ተተችቷል። የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች፣ ማኅበራት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት መንግሥት ይጥሰዋል የተባለውን ሕግ መልሶ ለማስተካከል ትልቅ ሥራ ይጠበቅባቸዋል መባሉን DW ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ክፍት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል ያለው
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
1
ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ ተፈናቃዮች በቂ የአፈር ማዳበሪያ እንዳልቀረበላቸው ገለጹ!

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ፣ ለአራት ዓመታት ያህል ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የተሰበሰቡ እና ከማኅበረሰቡ ጋራ ተቀላቅለው የቆዩ አርሶ አደሮች፣ ወደ ቀዬአቸው ተመልሰው የግብርና ሥራቸውን ቢጀምሩም፣ በማዳበሪያ እጥረት እንደተቸገሩ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡

በማንዱራ ወረዳ የዳሲኒ ቀበሌ ነዋሪ እንደኾኑ የተናገሩ አንድ አርሶ አደር፣ ከዘመድ አዝማድ በአገኙት ብድር፣ ትራክተር በሄክታር ስድስት ሺሕ ብር ተከራይተው መሬታቸውን ቢያርሱም፣ ማዳበሪያ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ግብርና ቢሮ በበኩሉ፣ ወደ ክልሉ በቂ ማዳበሪያ እንዳልገባ ገልጿል፡፡የቢሮ ሓላፊው አቶ ባበክር ሀሊፍ እንደሚሉት፣ ከፌዴራል መንግሥቱ ወደ 300 ሺሕ ኩንታል የሚጠጋ የአፈር ማዳበሪያ ተጠይቆ የቀረበው፣ 111 ሺሕ ኩንታል ብቻ ነው፡፡

የቀረበው ማዳበሪያ በቂ ባለመኾኑ፣ አርሶ አደሩ፥ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን በቤቱ እንዲያዘጋጅ ሓላፊው አሳስበዋል፡፡በክልሉ፣ ከ400ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች፣ ቀድሞ ወደነበሩበት አካባቢ እየተመለሱና የእርሻ ሥራቸውን እየጀመሩ እንደኾነ፣ የቢሮ ሓላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በአማራ ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ8.3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች በጦርነትና በጸጥታ ችግር ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ8 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ መደረጉን የተናገሩት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለል አቡሃይ ናቸው፡፡
ይህ ድጋፍም በዋግ ኸምራ ፣ በሰሜን ጎንደር ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ አካባቢ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተሰጠ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት ከሚያደርጉት ድጋፍ ውጭ የአካባቢው ህብረተሰብና ባለሃብቱ በርካታ መጠን ያለው እርዳታ እየሰጠ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው በቂ እርዳታ እየደረሰን አይደለም እየተባለ ያለው ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዓለማቀፍ ህጎችም ሆነ በሃገር ውስጥ ባሉ ህጎች መሰረት ለአንድ ተረጂ ወይም አባወራ እርዳታ የሚቀርበው በየ45 ቀን መሆኑን አንስተው ተፈናቃዮች በአቅርቦትና ግዥ ሂደቶች ላይ የተወሰኑ መዘግየቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው ብለዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ግብይት ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቋ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ በቀጣዩ የ2016 በጀት ዓመት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና፤ በአህጉሪቱ ካሉ ሀገራት ጋር ግብይት እንድትጀምር እቅድ መያዙን እና ዝግጅቶችም እየተጠናቀቁ መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ኢትዮጵያ በአህጉራዊው ነጻ የንግድ ቀጣና የምትገበያያቸውን የምርቶች እና አገልግሎቶች አይነት፤ በቀጣዩ ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ በሚካሄድ የአፍሪካ የንግድ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እንደምታቀርብም ገልጸዋል።

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት፤ በአህጉሩ ስር ባሉ ሀገራት መካከል የሚደረጉ የንግድ ግንኙነቶች ያሉባቸውን ተግዳሮች በመቅረፍ የሀገራቱን የንግድ ልውውጥ ለማሳለጥ ያለመ የአፍሪካ ህብረት ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ 54 የአፍሪካ ሀገራት የፈረሙት ይህ ስምምነት፤ ሀገራቱ እርስ በእርስ በሚገበያዩት ወቅት የሚጣለውን ቀረጥ የማስወገድ እቅድ አለው።

በነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነቱ መሰረት፤ የአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርስ የሚገበያዩዋቸውን 90 በመቶ ምርቶች እና አገልግሎቶች በአስር ዓመት ውስጥ ከቀረጥ ነጻ ያደርጋሉ። በ13 ዓመት ውስጥ ደግሞ ተጨማሪ ሰባት በመቶ ምርቶች እንዲሁ ከቀረጥ ነጻ አድርገው ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዲያስገቡ ይጠበቃል። ሀገራቱ ቀረጥ መጣል የሚችሉት በመረጧቸው ሶስት በመቶ የሚሆኑ ምርቶች ላይ ብቻ ነው።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በኬንያ በደረሰ የከባድ መኪና አደጋ ቢያንስ 48 ሰዎች ሞቱ!

በኬንያ እንቅስቃሴ በሚበዛበት መስቀለኛ መንገድ ላይ በደረሰ በአንድ የትራፊክ አደጋ ቢያንስ 48 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ እና የዐይን እማኞች ገለጹ።አደጋው የተከሰተው ኮንቴኔር የጫነ ከባድ ተሽከርካሪ በምዕራባዊቷ ከተማ ኬሪቾ አቅራቢያ በሚገኝ ሎንዲያኒ መስቀለኛ መንገድ ላይ ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ እንደሆነ የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የፖሊስ አዛዡ ጄፍሪ ማዬክ እንደተናገሩት በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ ሌሎች 30 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።የተጎጂዎች ቁጥርም ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል የፖሊስ አዛዡ ጨምረው ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪም አንድ ወይም ሁለት ሰዎች አሁንም በተገለበጠው ተሽከርካሪ ሥር ሳይሆኑ እንዳልቀሩም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የፈረንሳዩ የዜና ወኪል (ኤኤፍፒ)፣ ቶም ምቦያ ኦደሮ የተባሉ ሌላ የአካባቢው የፖሊስ መኮንን ጠቅሶ እንደዘገበው ወደ ኬሪቾ ሲጓዝ የነበረው ከባድ ተሽከርካሪ ፍጥነቱን መቆጣጠር አቅቶት ስምንት መኪኖችን፣ በርካታ ሞተርሳይክሎችን፣ በመንገድ ዳር የነበሩ ሰዎችን፣ በጎዳና ላይ እቃ ሲሸጡ የነበሩ እንዲሁም በሌላ ሥራ ላይ የነበሩ ሰዎችን ገጭቷል።

የዐይን እማኞችም ተሽከርካሪው በመንገዱ ላይ ተበላሽቶ የቆመውን አውቶብስ ለማለፍ ሲሞክር ከቁጥጥር ውጪ ወጥቶ አደጋው መከሰቱን ለኬንያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልልን ለመመስረት የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ውጤት ሊያጸድቅ ነው!

የፌደሬሽን ምክር ቤት በመጪው ሳምንት ማክሰኞ እና ረቡዕ በሚያደርገው መደበኛ ስብሰባው፤ “ደቡብ ኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ክልል ለመመስረት የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ ውጤት እንደሚያጸድቅ የምክር ቤቱ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የህዝበ ውሳኔውን አጠቃላይ ሪፖርት ከነገ በስቲያ ሰኞ ሰኔ 26፤ 2015 ለፌደሬሽን ምክር ቤት በጹሁፍ ያቀርባል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት፤ ከማንነት እና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር በተያያዙ የሚነሱ ጥያቄዎችን የመመልከት ስልጣን የሰጠው ለፌደሬሽን ምክር ቤት ነው። የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ስልጣን እና ተግባር ለመዘርዘር የወጣው አዋጅ፤ ምክር ቤቱ የህዝብ ፍላጎትን በህዝበ ውሳኔ እንዲረጋገጥ የማድረግ ኃላፊነትንም ሰጥቶታል።

በምርጫ ቦርድ የተከናወነውን ህዝበ ውሳኔ ውጤት የማጽደቅ ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠውም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው። በመጪው ማክሰኞ ሰኔ 27፤ 2015 ከሰዓት በኋላ ተጀምሮ በማግስቱ በሚቀጥለው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ፤ ምርጫ ቦርድ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ህዝበ ውሳኔን ሪፖርት በንባብ እንዲያቀርብ ቀጠሮ መያዙን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ገልጸዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11334/

@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለቻቸውን አንዳንድ የዕርዳታ ገደቦች እንደምታነሳ የዋይት ሃውስ የብሄራዊ ደኅንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ትናንት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ቃል አቀባዩ፣ አሜሪካ አንዳንድ የዕርዳታ ገደቦችን ከኢትዮጵያ ላይ የምታነሳው፣ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሻሻል በማሳየቷ እንደኾነ መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። ኾኖም በተለይ በምዕራብ ትግራይ የአማራ ክልል ታጣቂዎች የሚፈጽሟቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አሜሪካ ማውገዝ እንደምትቀጥል የገለጡት ቃል አቀባዩ፣ አኹን የተነሱት የድጋፍ ገደቦች ሰላምና እርቅን ለማገዝ የሚውሉ መኾናቸውን ገልጸዋል ተብሏል። የአጎዋ እገዳ ግን ለብቻው እንደሚታይ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ባለሥልጣናት መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል ለወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ ምንም ዓይነት ድጋፍ እያደረገ አይደለም ተባለ!

በትግራይ ክልል ለወደሙ ትምህርት ቤቶች በፌዴራል መንግሥትም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ምንም ዓይነት ድጋፍ እየተደረገ አለመሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ በክልሉ ከኹለት ዓመት በላይ ሲካሄደው በነበረው ውጊያ በትምህርት ሴክተሩ ላይ ያደረሰው ውድመት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ፤ የዉድመቱ መጠንም መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ሆኖም የወደሙ ትምህርት ቤቶች በተወሰነ መልኩም ቢሆን ጠግኖ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ከተወሰኑ ተቋማት በስተቀር በፌደራል መንግሥት እስካሁን የተደረገ ድጋፍ እንደሌለ ጠቅሰዋል፡፡ኃላፊው አክለውም በትምህርት ተቋማቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት በቃላት ለመግለጽ እጅግ አዳጋች ነው ካሉ በኋላ፤ ዓለም አቀፍ ተቋማትም ጭምር ካልተረባረቡ አገሪቷ አሁን ካለችበት አቋም አንጻር ትምህርት ቤቶቹን ማደስ የማይታሰብ ነው ብለዋል።

አሁን ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት መጀመሩን ገልጸው፤ ይህም ከሚፈለገው ቁጥር አንጻር ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱ ተማሪዎች 24 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።ይህም ተማሪዎች ቤት ከሚውሉ ይሻላል በሚል ባልተመሟላ የትምህርት ቁሳቁስ እየተማሩ እንደሚገኙ ነው የገለጹት።

እንደ ኃላፊው ገለጻ በጦርነቱ ወቅት የትምህርት ተቋማቱ የወደሙት ኢላማቸውን በሳቱ የጦር መሳሪያዎች ተመተው ሳይሆን፤ ሆነ ተብሎ ትምህርት ቤቶችን ለማውደም ድሮንን ጨምሮ የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም በደረሰባቸው ድብደባ ነው።

በተጨማሪም በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ስር ያሉ ትምህርት ቤቶች አሁንም በኤርትራ እና በአማራ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው፤ "በእነዚህ አካባቢዎች በ100 ሺሕዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች አሁንም ድረስ ከትምህርት ገበታቸው ውጪ ናቸው።" ብለዋል።

አክለውም ከጦርነቱ በፊት በክልሉ ከኹለት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ እንደነበሩ በመግለጽ፤ በዚህ ወቅት ትምህርት እየተማሩ ያሉ ተማሪዎች ቁጥራቸው ክ5መቶ ሺሕ አንደማይበልጥ አብራርተዋል፡፡በጦርነቱ ምክንያት በተማሪዎች፣ በመምህራን እንዲሁም በተማሪ ወላጆች ላይ የደረሰው ስነ ልቦናዊ ጉዳትም እጅግ ከፍተኛ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጉራጌ ዞን በነዋሪዎች ላይ ግድያና እገታ እየፈጸሙ ነው ተባለ!

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በተለይም ሶዶ ወረዳ፤ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውና መንግሥት "ኦነግ ሸኔ" በሚል በአሸባሪነት የፈረጀው ኃይል በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ግድያና እገታ እንደሚፈጽም ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

በተለይ የዱግዳ ጎሮ ቀበሌ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፤ የታጣቂ ቡድኑ አባላት በነዋሪዎች ላይ ተከታታይ ግፍና በደል እየፈጸሙ ነው ብለዋል።

በዚህም የቡድኑ አባላት ነዋሪዎችን አግተው በመውሰድ አርደን የምንበላው ከብት ስጡን፣ የግል የጦር መሳሪያችሁን እንዲሁም ብር አምጡ በማለት በደል እንደሚፈጽሙ ተነግሯል።

ባለፈው ሃሙስ ሰኔ 22/2015 በነዋሪዎቹ ቤት በመግባት "የመንግሥት የጸጥታ አካላትን ትደብቃላችሁ እንዲሁም ያሉበትን ጥቆማ አልሰጣችሁንም" በሚል ነዋሪውን ሲያሰቃዩ እንደነበርና በዚህም ምክንያት አንድ የቀበሌው ነዋሪ የነበሩ አርሶ አደርን መግደላቸው ነው የተገለጸው።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው ከስድስት ወር በፊት ጀምሮ በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ ነበር ያሉት ነዋሪዎቹ፤ ከባለፈው ሰኔ 20/2015 ጀምሮ ግን ግድያ እና እገታ እየፈጸሙ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ነዋሪዎችን አግተው በመውሰድ እስከ 200 ሺሕ ብር እንደሚጠይቁ በመጥቀስም፤ በአካባቢው (በቀበሌው) በቂ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ባለመኖራቸው ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ተናግረዋል።

የታጣቂ ቡድኑ አባላት ወደ ቀበሌው ዘልቀው የሚገቡት ከኦሮሚያ ክልል በመንግሥት የጸጥታ አካላት ሲሳደዱ መሆኑም ተጠቁሟል።

በዚህም ምክንያት በሶዶ ወረዳ ከምሽቱ ኹለት ሰዓት እስከ ጠዋት 12 ሰዓት ድረስ በሰውና በተሽከርካሪዎች ላይ የእንቅሰቃሴ ገደብ መጣሉን ነው የተመላከተው።

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳው በጉዳዩ ላይ መረጃ እየተሰባሰበ መሆኑን ጠቅሰው፤ "ሙሉ መረጃ ሲገኝ የምንገልጽ ይሆናል።" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

እንዲሁም ከጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ ላጫ ጋሩማን እና ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ስልክ ባለማንሳታቸው ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

Via Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል ጠንካራ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በመንግሥት የጸጥታ አካላት እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራውና በመንግሥት "ኦነግ ሸኔ" ተብሎ በአሸባሪነት በተፈረጀው ታጣቂ ቡድን መካከል ከባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ በተለየ መልኩ ጠንካራ ውጊያ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ገልጸዋል፡፡

ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ "በዞኑ በኹለቱ ኃይሎች መካከል ውጊያ መደረግ ከጀመረ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ ካለፈው ሳምንት ሰኔ 17/2015 ጀምሮ እየተደረገ ያለው ውጊያ ግን ጠንካራ ነው።" ብለዋል።

ውጊያው በዞኑ በተለይም ኮምቦሻ እና ጮመን ጉዱሩ ወረዳዎች በስፋት እየተካሄደ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን በእነዚህም አካባቢዎች የንጹሃን ዜጎች ሕይወት መጥፋቱና እና በርካታ የቤት እንስሳት መሞታቸው ተመላክቷል።

በተለይም በኮምቦሻ ወረዳ ቱሉ ሀቢብ ቀበሌ ከአንድ አካባቢ ብቻ ቁጥራቸው ከአስር በላይ የሚሆን ንጹሃን ዜጎች ሕይወታቸው ማለፉን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

ነዋሪዎቹ አክለውም፤ የመንግሥት የጸጥታ አካላት በዋናንተ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአካባቢው እያደረጉት ባለው ኦፕሬሽን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኦነግ ሸኔ አባላት ሳይገደሉ እንዳልቀረ ነው የጠቀሱት።

የአካባቢው ማህበረሰብ በየጊዜው በሚካሄዱ ውጊያዎች ከቀዬው ሲፈናቀል እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም ብዙዎች አካባቢያቸውን ለቀው እየወጡ ነው ተብሏል።

በዚህም ጠንካራ ውጊያ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚፈናቀሉ ሰዎች በብዛት ወደ ሻምቡ ከተማ እንዲሁም ሀባቦ ወረዳና ወደ ሌሎች አንጻራዊ ሰላም ወዳለባቸው የተለያዩ ሥፍራዎች እንደሚሄዱ ተገልጿል።

በአካባቢው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄዱ ተደጋጋሚ ውጊያዎች አርሶ አደሮች ማረስ፣ ተማሪዎችም መማር አለመቻላቸው እንዲሁም የንግድ እንቅስቃሴ ማከናወን አስቸጋሪ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፤ የአካባቢው ሠላም ተመልሶ ማህበረሰቡ የተረጋጋ ሕይወት መምራት ይችል ዘንድ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

Via Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
አንድን ግለሰብ በመግደል አስከሬኑን ቆራርጠው መጸዳጃ ቤት ውስጥ የጣሉት ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ!

678 ሺህ ብር የሚያወጣ በዱቤ የተሸጠን በቆሎ ለግል ጥቅማቸው ለማዋል የንብቱን ባለቤት በመግደል አስከሬኑን በመቆራረጥ መጸዳጃ ቤት ውስጥ የጣሉት ሁለት ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ፡፡ድርጊቱ የተፈጸመው በሀዲያ ዞን ዱና ወረዳ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከተከሳሾቹ አንዱ የንብረቱን ባለቤት በጥይት ከገደለ በኋላ አስከሬኑን ሁለቱም ተከሳሾች ቆራርጠው በማዳበሪያ በመጠቅለል መጸዳጃ ቤት ውስጥ መክተታቸው ተገልጿል፡፡የወረዳው ፖሊስም ለአራት ቀናት ያህል ባደረገው ፍለጋ÷ አገልግሎት መሥጠት ባቆመ አሮጌ መጸዳጃ ቤት ውስጥ የሟችን የተቆራረጠ አስከሬን ማግኘቱን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ!

ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ተጨማሪ ጨዋታ እየቀረው የ2016 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሀድያ ሆሳዕና ያገናኘው የ29ኛ ሳምንት ጨዋታ÷ 9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡

በጨዋታውም÷ ቸርነት ጉግሳ በመጀመሪያው አጋማሽ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን ረትቷል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ክፍት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል ያለው
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ ልማቶች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው ተባለ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በመገባደድ ላይ በሚገኘው የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ጥናት ማድረግ ተጀምሯል።

ግድቡ ሲጠናቀቅ ኃይል ከመስጠቱ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻ ስለሚሆን፣ ባለሃብቶችን በልማት ስራ ላይ ለማሰማራት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት ማስተር ፕለን እየዘጋጀለት መሆኑ ተሰምቷል።የህዳሴ ግድብ ውሃው በተኛበት ቦታ ላይ ደሴቶች መኖራቸው ይታወቃል፤ እነዚህም ለቱሪስት መስህብነት እንደሚሆኑ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።በተጨማሪም ለባህር ትራንስፖርት ምቹ ስለሚሆን የቱሪዝም ዘረፉን ያነቃቃል ነው የተባለው።

ሌላው በአካባቢው ከፍተኛ የአሳ ርባታ ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታ በመኖሩ፣ ግድቡ እንደተጠናቀቀ በእነዚህ ዘርፎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች በጥናት ላይ የተመሠረቱ ለማደሰረግ ጥናቱ ተጀምሯል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።ግድቡን ከዳር ለማድረስ አሁንም ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።አራተኛውን የግድቡን የውሃ ሙሌት ለማከናወን ዝግጅት መጀመሩንም ተሰምቷል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa