ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ስራ ካቆመ ሶስት ወራት ማስቆጠሩ ተገለጸ
በአዲስአበባ የሚገኘዉ ከቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጨው ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ስራ ካቆመ ሶስት ወራት ማስቆጠሩን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 26ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ሪፖርት ያቀረቡት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ። ለዚህም ተቋሙ ከኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የሚደረግለት ክትትልና ድጋፍ የሌለ መሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።
የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫዉ በሰዓት 50 ሜጋ ዋት ለማመንጨት የተቋቋመ የነበረ ቢሆንም ከሶስት ወራት በፊት መስሪያቤቱ ባደረገዉ ክትትል 13 ሜጋ ዋት ብቻ እያመነጨ የነበረ መሆኑን ጨምረዉ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።
ባለስልጣኑ ዉፍረታቸዉ 0.03 ሚሊ ሜትር እና ከዚያ በታች የሆኑና ከአፈር ጋር በቀላሉ የማይቀላቀሉና የማይበሰብሱ ምርቶችን ተለይቶ ከተቀመጠው አገልግሎት በቀር ወደ ሀገር እንዳይገቡ ወይም እንዳይመረቱ ተከታታይነት ባለዉ መልኩ ክትትል ማድረግ ሲገባዉ ይህን ያለከናወነ መሆኑ ፤ ከህግ ዉጪ የሰሩ ተቋማትንም እርምጃ እንዲወሰድባቸው ያላደረገ እንዲሁም በርካታ ሀላፊነቶቹን ያልተወጣ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ፊት ተናግረዋል።
Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተገለጸ!
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከሰኔ 23/2015 እስከ ሐምሌ 30/2015 ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሁሉም ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በሰኔ ወር በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
በዚሁ መሠረት፦
1. ቤንዚን ……………………………………… ብር 69.52 በሊትር
2. ነጭ ናፍጣ…………………………………… ብር 71.15 በሊትር
3. ኬሮሲን ……………………………………... ብር 71.15 በሊትር
4. የአውሮፕላን ነዳጅ …………………………. ብር 65.35 በሊትር
5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ………………………….. ብር 57.97 በሊትር
6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ………………………….. ብር 56.63 በሊትር የሚሸጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

ፍትህ ሚንስቴር በሕክምና ሙያ ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የተመለከተ የምርመራና ክስ የተግባር መመሪያ አዘጋጅቶ ለባለድርሻ አካላት ለውይይት ማቅረቡን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል።
የተግባር መመሪያው የተዘጋጀው፣ በሕክምና አገልግሎት ወቅት በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ የሚካሄዱ ምርመራዎችና የሚመሠረቱ ክሶች የሚመሩባቸውን መርኾዎች ለመቅረጽ፣ የምርመራና ክስ ሂደቶች የሕክምና ሙያን ልዩ ባሕሪያት እንዲያገናዘቡ ለማድረግና የተጎጂዎችን ጥቅም ለማስከበር እንደኾነ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።በሕክምና ወቅት በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ ምርመራ ለማድረግና ክስ ለመመስረት እንዲኹም ፍርድ ቤቶች ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት ሲቸገሩ ይስተዋላል።

Forwarded from YeneTube
ክፍት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል ያለው
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan

የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ
መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች
የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar
Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር
Contact Us:
@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58
☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇
🤳ስልክ ቁጥራችን 9445
Website
www.sabinaadvisors.com
👇👇 ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602
ከታላቅ አክብሮት ጋር !!!
https://tttttt.me/sabinaadvisor
https://www.facebook.com/sabinaadvisor
መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች
የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar
Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር
Contact Us:
@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58
☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇
🤳ስልክ ቁጥራችን 9445
Website
www.sabinaadvisors.com
👇👇 ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602
ከታላቅ አክብሮት ጋር !!!
https://tttttt.me/sabinaadvisor
https://www.facebook.com/sabinaadvisor
👍1
Forwarded from YeneTube
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው
Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy
Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL
Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥስት ክስ በማንሳት ምንም የፋይናንስ ድጋፍ ክልከላ እንደማይደረግባት አስታወቀች!
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥስት ክስ በማንሳት አገሪቱ ከዚህ በኋላ ምንም አይነት የፋይናንስ ድጋፍና አቅርቦት ክልከላ እንደማይደረግባት አስታወቀች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰነድን ዋቢ አድርጎ ፎሬይን ፖሊሲ መፅሄት እንደፃፈው፤ ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ላይ የምታነሳውን የሰብዓዊ መብት ጥስት ክስን ጥላለች።
ለአገሪቱ ኮንግረስ የተላከው ይህ የውስጥ ማስታወሻ አሜሪካ ይህንን ክስ በማንሳቷ ከዚህ በኋላ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ኢትዮጵያ ከዋሽንግተንም ሆነ ከሌሎች ዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ገንዘብ እንዳታገኝ ሲያደርግ የነበረውን መከላከል ያቆማል ይላል።
የአሜሪካ ውሳኔ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) እና ከዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍና ብድር እንድታገኝ የሚያስችል ነው።
ውሳኔው ዋሽንግተን በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የሻከረውን የኹለቱን አገራት ግንኙነት ለማደስ ፍላጎት እንዳላት ያሳያል መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በተፈናቃዮች በተጨናነቁት የደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፖች የኩፍኝ ወረርሽኝ ተከሠተ!
በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖች ውስጥ የኩፍኝ ወረርሽኝ እንደተከሠተ፣ የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡የኩፍኙ ወረርሽኝ ከተከሠተ፣ ሁለት ሣምንት መቆጠሩን የገለፁት የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሓላፊ አቶ በቀለ ገብሬ፣ እስከ አሁን 80 ሰዎች በኩፍኝ መያዛቸውን ገልፀዋል።
በበሽታው የተያዙት ሰዎች ቁጥር፣ የመምሪያ ሓላፊው ከተናገሩት እንደሚበልጥ፣ በልዩ ልዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ይናገራሉ፡፡
በበሽታው እስከ አሁን የሞት አደጋ አለመድረሱንና እንዳይስፋፋ ግን፣ 10ሺሕ ለሚደርሱ ተፈናቃዮች ክትባት ሲሰጥ እንደቆየ፣ ሓላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡20ሺሕ ተፈናቃዮች ይኖሩበታል በሚባለው ቻይና ካምፕ፣ የተፈናቃዮቹ አስተባባሪ የሆኑት ቤትዬ ደርቤ፣ የኩፍኙ ክሥተት አሳሳቢ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡
ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና በጤናው ዘርፍ እንደሚሠሩ የተናገሩ አንድ የከተማዋ ነዋሪ በበኩላቸው፣ “በሽታው ከመጠለያ ጣቢያዎቹ ውጭ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት አድሮብናል፤” ብለዋል፡፡ከዚህ ቀደም የመጠለያ ካምፖች አቅንቶ በነበረበት ወቅት ያናገራቸው ተፈናቃዮች፥ በቂ የመጸዳጃ፣ የውኃ፣ የምግብ እና የመጠለያ አቅርቦት በሌለበት በማንኛውም ሰዓት ወረርሽኝ ሊከሠት ይችላል፤ የሚል ስጋት እንዳለባቸው፣ ተፈናቃዮቹ መናገራቸው
ተዘግቦ ነበር፡፡
ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ልየ ዞኖች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ ስድስት መጠለያ ጣቢያዎች የሚኖሩ ተፈናቃዮች ቁጥር 30ሺሕ እንደሚደርስ፣ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
Via VoA

ጀሞ መስታወት ፋብሪካ ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ ስድስት የንግድ ሱቆች ተቃጠሉ!
በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት ምሽት 1:44 ሰዓት ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ አንድ ጀሞ መስታወት ፋብሪካ ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ ስድስት የንግድ ሱቆች መቃጠላቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አራት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና 28 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የተሰማሩ ሲሆን፤ የእሳት አደጋዉ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርሰ መቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል። በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል፤ ምሽት 3:43 ሰዓት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጣፎ 2 ኛ በር አካባቢ መንገድ ሲጠቀም የነበረ የ44 ዓመት እግረኛ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-53457 በሆነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገጭቶ ሕይወቱ ማለፉ ተነግሯል።የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሽከርካሪዉ ተጭኖት የነበረዉን አስከሬን በማሽነሪ ተጠቅመዉ ማውጣታቸውም ተገልጿል።

ሰሜን ሆቴል አካባቢ በሲኖትራክ የተገጨው ግለሰብ ህይወቱ አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት ሰኔ 23 ከቀኑ 6 ገደማ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታዉ ሰሜን ሆቴል ፊት ፊት በሲኖትራክ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3_ኢት A04091 የሆነ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ መንገድ በመሻገር ላይ ያለ ዕድሜዉ 50 ዓመት የተገመተ ሰዉ ገጭቶ ህይወቱ አልፏል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በተሽከርካሪዉ ተገጭተው ህይወቱ ያለፈዉን ግለሰብ አስከሬን ከተሽከርካሪዉ ስር በማሸነሪ ታግዘዉ አዉጥተዉታል።

የፈረንሳይ አመጽ ተጠናክሮ ሲቀጥል ለአመጹ ምክንያት የሆነው ፖሊስ ተከሰሰ!
ባለፈው ማክሰኞ ፓሪስ አቅራቢያ አንድ ታዳጊ የገደለው የፖሊስ መኮንን ክስ ቢመሰረትም አመጹ በአገሪቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።የ17 ዓመቱ ናሄል ኤም ከቅርብ ርቀት በጥይት ተመትቶ ነው የተገደለው።
ይህን ተከትሎ የተነሳው አመፅ በመላው ፈረንሳይ እየተቀጣጠለ ይገኛል። የሟች እናት ሐሙስ ዕለት የጠሩት ሰልፍ በርካታ ግጭቶችን አስከትሏል።በሊል እና ማርሴ ከተሞች በርካታ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ለእሥር በቅተዋል።
ናንቴር በተሰኘችው ታዳጊው በሚኖርባት ከተማ አንድ ባንክ ያለበት ሕንፃ በእሳት ተቃጥሏል።ማሕበራዊ ሚድያ ላይ የሚለጠፉ ምስሎች እንደሚያሳዩት በርካታ ሥፍራዎች በእሣት እየጋዩ ነው።በፓሪስና በሌሎች ከተማዎች የአውቶቡስና ባቡር ትራንስፖርት በሃገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 3 ሰዓት ጀምሮ ተቋርጧል።
አንዳንድ ከተሞች ሰዎች በምሽት እንዳንይንቀሳቀሱ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥለዋል።የፈረንሳይ መንግሥት አመፁን ለመግታት 40 ሺህ የፖሊስ ሠራዊት በሃገሪቱ አሰማርቷል።ማክሰኞ እና ረቡዕ ምሽት በነበሩ ተቃውሞዎች በርካታ ተሽከርካሪዎችና ሕንፃዎች የእሣት ሲሳይ ሆነዋል።
[BBC]

የመውጫ ፈተና ሙከራ (Mock exam) በዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ ነው።
በአገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና በሙከራ ደረጃ እየተሰጠ ነው።ከዋና ፈተና አስቀድሞ ከሰኔ 26 - 29 ሞዴል ፈተና እንደሚሰጥም ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር የአካዴሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር ) እንደገለጹት ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እየተሰጠ ያለው ከ168 ሺ ለሚበልጡ እጩ ምሩቃን ነው።
የሙከራ ፈተናው ተማሪዎች የራሳቸውን መለያ ቁጥር እና የይለፍ ቃል ተጠቅመው በቀላሉ መፈተን እንዲችሉና ከፈተና ስርዓቱ ጋር እንዲተዋወቁ እንደሚያስችል ዶ/ር ኤባ ተናግረዋል።
የሙከራ ፈተናው በፈተና ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ለመፍታት ታስቦ የተዘጋጀና ተማሪዎች የሚገመገሙበትና ውጤቱም የሚያዝ አለመሆኑን መሪ ስራ አስፈጻሚው አመላክተዋል።
ከሰኞ ሰኔ 26 - ሐሙስ ሰኔ 29 ለሁሉም የግልና የመንግስት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በጥያቄ ክብደቱም ሆነ ብዛቱ ከመውጫ ፈተና ጋር ተመሣሣይ የሆነ ሞዴል ፈተና በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚሰጥ ዶ/ር ኤባ ጠቁመዋል።
እየተሰጠ ባለው የሙከራ መውጫ ፈተና ከኔትዎርክና ከኃይል መቆራረጥ ፣ ከመለያ ቁጥርና ይለፍ ቃል መለዋወጥ ከመሳሰሉ ያለፈ የጎላ ችግር አለማጋጠሙንም ተናግረዋል ።
ተማሪዎች ከፈተና ስርዓቱ ጋር በመለማመድና ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለመውጫ ፈተናው ማዘጋጀት እንዳለባቸው ዶ/ር ኤባ አሳስበዋል።
የ2015 ዓም የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 6 2015 ዓ.ም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።
@YeneTube@FikerAssefa

ከ500 ሺህ እስከ 1ሚሊዮን ብር ከፍለዉ የተለቀቁ ሹፌሮች ‹ያገቱን ታጣቂዎች የመንግስት ፀጥታ ሐይሎችን የደንብ ልብስ የለበሱ ናቸው› አሉ፡፡
ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም መንግስት ሸኔ በሚለው ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባላት ከ30 በላይ የከባድ መኪና አሽከርካሪና ረዳቶች መታገታቸውን አሻም ከሰለባዎቹ መረዳት ችላለች፡፡
ለአጋቾቹ የተጠየቁትን ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁት ሰለባዎቹ እንደሚሉት ‹እገታውን የፈፀሙት ታጣቂዎች የመንግስት የፀጥታ ሀይሎችን የደንብ ልብስ የለበሱ ናቸው › ስሜና ድምፄ ለደህንነቴ ሲባል ይቆየኝ ያለና ታግቶ 500 ሺህ ብር ከፍሎ የተለቀቀ ረዳት በበኩሉ ‹ ሸኔ ከተባለዉ ታጣቂ ቡድን አምልጠን 7 ሰአት የፈጀ ጉዞ ካደረግን በኋላ በክልሉ ሚሊሻ ተይዘን ከ100 እስከ 150 ሺህ ብር ለእኛ ካልከፈላችሁን ለሸኔ አሳልፈን እንሰጣችኋለን በሚል አግተዉ ቤተሰብ ጋር እያሥደወሉን ገንዘብ ተቀብለዉ ለቅቀዉናል › ሲል ተናግሯል፡፡
ሌላኛው ሰለባ ደግሞ ‹መንግስት ሸኔ ሲል የሚጠራቸዉ ቡድን አባላት ናቸዉ ያገቱን ያሉ ሹፌርና ረዳቶች አጋቹ ቡድን ወስዶ በአርሶ አደር ቤት አስቀምጦ እየመገበ ገንዘብ ቤተሰቦቻችን እንዲያመጡ በየደቂቃዉ ያስደዉላል› ሲሉ ይናገራሉ፡፡
አሻም ያነጋገረቻቸው ወላጅ ልጃቸውን ከአጋቾቹ ገንዘብ በመክፈል ያስለቀቁ አንድ ወላጅ ደግሞ ያለፉበትን ውጣ ውረድ ለአሻም አሰረድተዋታል፡፡ለልጃቸው ሲሉ ‹ቤታቸውን ሽጠዋል፤ በእምነት ተቋማት፣ ነጠላ ዘርግተው› ለምነዋል፡፡
አሻም የሰላበዎቹን ቅሬታ መነሻ በማድረግ የመከለከያ ሰራዊትን፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስንና የኦሮሚያ ክልልን ለማነጋገር ሞክራለች፡፡ ለአሻም ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጄላን አብዲ መረጃውን ሀሰት ነው ሲል አጣጥለውታል፡፡
‹በሠራዊቱ ውሰጥ ይህንን የወረደ ተግባር የሚፈፅም አመራርም ሆነ አባል የለም።› ሲሉም አስተባብለዋል፡፡
‹ነገር ግን ኅብረተሰቡን ለማሳሳት በተለያዩ ጊዜ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የሌሎች ፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ለብሰው ሲዘርፋ የነበሩ የተደራጁ የዝርፊያ ቡድኖች በተለያዩ ጊዜ በቁጥጥር ሥር ውለው ለፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደረገው ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው ያሉ አሉ።› ሲሉ ለአሻም ነግረዋታል፡፡
[Asham]

"ታግቻለሁ በማለት የፍቅር ጓደኛዋን 500 ሺህ ብር የጠየቀችው ግለሰብ በመኖሪያ ቤቷ በቁጥጥር ስር ዋለች" - ፖሊስ
ሳትታገት ታግቻለሁ በማት የፍቅር ጋደኛዋን 500 ሺህ ብር የጠየቀችው ተከሳሽ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ተጠርጣሪዋ ግለሰብ የማታለል ወንጀሉን የፈፀመችው በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ አይ ሲ ቲ አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ የመገኛኛ ብዙኃን ነፃነትን ለማሻሻል እና ዓለማቀፍ ደረጃውን ለማስጠበቅ፣ የጋዜጠኞችን በነፃነት የመሥራት መብት ለማስከበር በሚል ከሦስት ዓመታት በፊት ተሻሽሎ የቀረበው አዲሱ የኢትዮጵያ የመገኛኛ ብዙኃን ሕግ በአግባቡ ተግባራዊ አልሆነም ተባለ።
ካርድ የመብቶች እና የዲሞክራሲ ማእከል፣ ከኢንተር ኒውስ ጋር ያዘጋጀውን ጥናታዊ ጽሑፍ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባቀረበበት ወቅት በዚሁ ጉዳይ ላይ ተወያይቷል።በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ መሰረትም፦ የመገናኛ ብዙኃን ሕጉ ተሻሽሎ ከወጣበት ካለፉት 3 ዓመታት ጀመሮ ሞያው በተፈለገው መለኩ አላደገም ተብሏል።
የፖለቲካ ተጽእኖ መኖር እንዲሁም ሕጉ በግጭት ወቅት የወጣ መሆኑ ለዚህ እንደ ምክንያትነት ቀርቧል።ሞያውም የሕግ ከለላ አለማግኘቱ አሳሳቢ ነው ተብሏል።እስካሁንም 39 የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች መታሰራቸው ተገልጿል።የጋዜጠኞች እንግልት እና እስርም በክልል ደረጃ የበለጠ አሰቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ አሳሳቢ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ በበርካታ ችግሮች መሀል መገናኛ ብዙኃኑ መናገር እንዳቃተዉ በግልፅ የሚታይ ቢሆንም ዛሬ የቀረበው ጥናት ግን ለዚህ ችግሩ ምን እንደሆነ መልስ ለመስጠት አለመሞከሩ የጥናቱ ክፍተት ነው በሚል በታዳሚዎች ተተችቷል። የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች፣ ማኅበራት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት መንግሥት ይጥሰዋል የተባለውን ሕግ መልሶ ለማስተካከል ትልቅ ሥራ ይጠበቅባቸዋል መባሉን DW ዘግቧል።