የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ያለ ሪፈር እንደሚያስተናግድ ገለጸ።
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ ያለ ሪፈር የጭንቅላት ቀዶ ህክምና እየሰጠ መሆኑን የሆስፒታሉ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ክፍል አስታውቋል።
የክፍሉ ሀላፊ ዶ/ር አብዲ ኤርሜሎ እንደገለጹት የህጻናት ጭንቅላት ቀዶ ህክምና ብቻ ላይ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት የአዋቂዎችንም የህክምና አገልግሎት ጨምሮ እየተሰጠ ይገኛል።
በህጻናት የህክምና አገልግሎት በኩል የሃይድሮሴፋለስ (የጭንቅላት ውሃ መቋጠር) ህመም ህክምና ፣ የኤምኤንሲ ቀዶ ህክምና፣ በአከርካሪ ላይ የሚወጡ ዕጢዎች ህክምና እና ከወሊድ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የተለያዩ የጭንቅላት ችግሮች ህክምና የሚሰጥባቸው ናቸው።
በአዋቂዎች ህክምና ደግሞ የአንጎልና አከርካሪ ዕጢዎች፣ የዲስክ መንሸራተት ከአደጋ ጋር በተገናኘ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ህክምናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ ዶ/ር አብዲ ተናግረዋል።
#ከሁለት_ወር በፊት የኢንዶስኮፒክ ቀዶ ህክምና መጀመሩ በተለይ ለህጻናት የሚደረገውን ህክምና በማሻሻል የጭንቅላት ውሃ መቋጠርን ለማከም ከጭንቅላት ወደ ሆድ የሚሄድ ቱቦ (vp shunt) በመጠቀም ይሰጥ የነበረውን ህክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች በኢንዶስኮፒክ ሰርጀሪ ማስቀረት እንደተቻለም ገልጸዋል።
የህክምና አገልግሎቱ በሳምንት አምስት ቀን እየተሰጠ በወር ከ50 እስከ 60 ቀዶ ህክምናዎች እየተሰሩ የሚገኙ ሲሆን በቀጣይ የሲአር ማሽን ግዢ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ደግሞ የአከርካሪ አጥንት ስብራት ህክምናን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶች በሰፊው እንደሚሰጡ ዶክተሩ ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና በከፍተኛ ደረጃ እንዲሰጥ የሆስፒታሉ የማኔጅመንት አባላት ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ሊመሰገኑ ይገባቸዋል ያሉት ዶክተሩ ህብረተሰቡም የህክምና አገልግሎቶቹን ያለ ሪፈር እንደሚሰጡ አውቆ ህክምና ማግኘት እንደሚችል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።