መንግስት በኢንተርኔት ሚዲያዎች እየመጣበት ያለዉን ተቃዉሞ ለመመከት በሚመስል መልኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ እና ለዋልታ ዳጎስ ያለ የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ ነው ተባለ!
በፓርቲ ንብረትነት ለሚታወቁት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና ለዋልታ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ባልተለመደ መልኩ የፌደራሉ መንግስት በርካታ መጠን ያለው ገንዘብ ድጎማ እያደረገላቸው መሆኑን ዋዜማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።
የሚድያ ተቋማቱ ገንዘቡን ስራቸውን ለማስፋፊያ እንዲሁም ለሰራኞቻቸው ደሞዝ ጭማሪ እና ማሻሻያዎችን ለመተግበር ይጠሙበታል ተብሏል። ሁለቱ ሚድያዎች በኢህአዴግ ጊዜ ከአራቱ እህት ድርጅቶች የቦርድ አባላት የሚሾሙላቸው ፣ እንዲሁም አመታዊ ትርፋቸውን በኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ከሚተዳደሩ ኩባንያዎች ጋር የሚከፋፈሉት ነው። ገንዘብ ሲያስፈልጋቸውም ከባንኮች ይበደሩ ይሆናል እንጂ በቀጥታ በፌደራሉ መንግስት በኩል አይሰጣቸውም ነበር።
ዋዜማ ከምንጮቿ እንደሰማችው ዋልታ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት እስከ ሁለት ቢሊየን ብር ከመንግስት እንደሚያገኝ እንደሚያገኝ ታሳቢ አድርጎ ዕቅድ አውጥቷል። የገንዘቡን መጠን ፣ እንዲሁም ገንዘቡ የሚሰጠው በብድር ይሁን በልግስና ከተቋሙ አመራሮች ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ይሁንና የሚዲያ ተቋሙ አመራሮች ገንዘቡን ለማግኘት ከገንዘብ ሚኒስቴር ሰዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን ሲያደርጉ እንደነበር ተረድተናል።
ዋልታ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የቅርብ ሰው እንደሆኑ በሚነገርላቸው እና “ሰውዬው” የሚለውን መጽሀፍ በጻፉት መሀመድ ሀሰን በዋና ስራ አስፈፃሚነት እየመሩት ይገኛሉ።
ተቋሙን ሰፋፊ የፕሮግራም ማሻሻያዎችን ለማድረግ ፣ የህንፃና እና ስቱዲዮ ግንባታዎችን ለማከናወን እየተዘጋጀ መሆኑን ሰምተናል። እንዲሁም ለሰራተኞች የደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ማስተካከያ ባለፉት ቀናት አድርጓል።ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በበኩሉ ድጎማን ለመቀበል ሰሞኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ምላሽ እየተጠባበቀ ይገኛል።
እነዚህ መገናኛ ብዙሀን ከመንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ ድጎማ ያገኙት በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በሰላም ሚኒስቴር በኩል ገንዘብ ፈሰስ በተደረገላቸው ወቅት ነበር። በውጪ ሀገራትና በሀገር ቤት በመንግስት ላይ ተቃውሞና ትችት የሚያቀርቡ የኢንተርኔት ሚዲያዎች መበራከታቸው እንዲሁም በመንግስት ላይ የተደራጀ የተቃውሞ ዘመቻዎች መጀመራቸው መንግስት በሙሉ አቅሙ ተቃውሞውን ለመመከት አስቦ ሚዲያዎች ላይ ትኩረት አድርጓል ብለው እንደሚገምቱ አንድ የፋና ብሮድካስት የስራ ሀላፊ ነግረውናል።
ዋልታም ሆነ ፋና የኢህአዴግ መክሰምን ተከትሎ ብልፅግና ሲመሰረት በየኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል በነበረው አለመግባባት እንድም እንዲፈርሱ አልያም ባለቤትነቱ ለሌላ አካል እንዲተላለፍ የሚሉ አማራጮች ቀርበው ነበር። በወቅቱ የብልፅግና ሊቀመንበር በሚዲያ ተቋማቱ ዕጣ ፈንታ ላይ ጥናት እንዲደረግና እንዲቀርብ አዘዙ።
ጥናቱ የሚዲያ ተቋማቱ ወደ ሕዝብ ንብረትነት ቢዛወሩ የተሻለ መሆኑን አልያ ግን ከመዘጋት ውጪ አማራጭ እንደሌላቸው ምክረ ሀሳብ አቀረበ። ይሁንና “የፖለቲካ ፍላጎት” እንዳለው የሚነገርለት “ቡድን” አጀንዳውን አደፋፍኖ ተቋማቱን በበላይነት መቆጣጠር ችሏል ይላሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁና በሂደቱ የተሳተፉ ምንጮች።
[ዋዜማ]
@YeneTube @FikerAssefa

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ከ2 ሺሕ 100 በላይ መምህራን እና 1 ሺሕ 700 ተማሪዎች መሞታቸው ተገለጸ!
በሰሜን ኢትዮጵያ ለኹለት ዓመት በቆየው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ብቻ፤ 2 ሺሕ 146 መምህራን እና 1 ሺሕ 700 ተማሪዎች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታውቋል፡፡ተቋሙ በክልሉ በርካታ ትምህርት ቤቶች ላይ መጠነ ሰፊ ውድመት መድረሱን ገልጾ፤ በጦርነቱ በትምህርት ዘርፉ ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን በገንዘብ ተመን በተመለከተ የሚካሄደው ጥናት አለመጠናቀቁን ጠቅሷል፡፡
የተማሪዎችና የመማሪያ ክፍል ጥምርታን በተመለከተም፤ ከጦርነቱ በፊት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአንድ መማሪያ ክፍል ውስጥ በአማካኝ 39 ተማሪዎች ይማሩ የነበረ ሲሆን፣ ከጦርነቱ በኋላ አንድ መማሪያ ክፍል ለ434 ተማሪዎች ሆኗል ነው የተባለው፡፡በኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁ ከጦርነቱ በፊት ለ43 ተማሪዎች መማሪያ የነበረ አንድ ክፍል ከጦርነቱ በኋላ ለ365 ተማሪዎች መማሪያ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ሆኖም ጉዳት የደረሰባቸው የትምህርት ተቋማቱን መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን በመለየት፣ ጥገና ለማድረግ የአጭር እና የረዥም ጊዜ እቅድ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡በሌላ በኩል በአጠቃላይ በክልሉ የጤና ሴክተር ላይ ከ65 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚተመን ጉዳት መድረሱን ነው ተቋሙ ያስገነዘበው፡፡
በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው የጤና ተቋማት ተለይተው ለጤና ሚኒስቴር እና ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ቢቀርብም በጀት ተፈቅዶ እስካሁን የተሰራው ስራ የሚፈለገውን ያህል አይደለም ተብሏል፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጉዳት የደረሰባቸው አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም እና ተፈናቃዮች ያሉባቸውን የመጠለያና የምግብ ችግሮች ለማቃለል የብዙ ባለድርሻ አካላትን አስተዋጾ የሚጠይቅ ስለሆነ ሁሉም ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡

👍1
የዳያስፖራ አባላት የገንዘብ፣ ጉዞ እና መዋእለ ንዋይ እቀባ ዘመቻ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጀምረዋል።
ውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሲቪል ማኅበራት «ግፈኛ አገዛዝ» ያሉት መንግሥት ላይ የገንዘብ ተጽእኖ ለማሳደር ዘመቻ ጀምረዋል። ማኅበራቱ ዘመቻቸው፦ ኢትዮጵያ ውስጥ በገዢው ብልጽግና መንግሥት ይፈጸማል ያሉትን ኢ-ፍትኃዊነትና ዘረኝነት በመቃወም፤ ትኩረቱ ፍትሕ ላይ ያተኮረ መሆኑንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራው ማኅበረሰብም ወደ ሀገር ቤት የሚልከውን ገንዘብ በባንኮች እንዳይጠቀም ጥሪ አስተላልፈዋል። ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ የሚያደረጓቸውን ጎዞዎች እንዲያቋርጡ እና መዋእለ ንዋይ ፍሰት (ኢንቨስትመንት) ለማደርግ የሚደረጉ ሂደቶች በአጠቃላይም መቋረጥ አለበት ብለዋል።
ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚንሥትር አህመድ ሽዴ ባቀረቡት ዘገባ፦ የፌድራል መንግሥት የበጀት ጉድለት እንደገጠመው ይፋ አድርገዋል።የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሀገሪቱ ኤኮኖሚ ላይ 28 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኪሳራ ማድረሱን ዐሳውቀዋል ። ሚንስትሩ ጉድለት ያሉትን ለመሸፈንም ከአገር ውስጥ 194.6 ቢሊዮን ብር በብድር መንግስት መውሰዱን ገልጸዋል። «ብድሩም የተገኘው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀጥታ ብድር፣ ከትሬዠሪ ቦንድ እንዲሁም ከትሬዠሪ ቢል ነው።ካሉት የፋይናንስ ተቋማት 194.6 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን ሬይዝ ተደርጓል»ም ብለዋል ። መንግስት ከፍተኛ የገንዘብ ችግር እንደገጠመው፤ የኑሮ ውድነቱም በከፍተኛ ደረጃ ማኅበረሰቡን እንዳማረረው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
Via DW

የአፍሪካ ኅብረት በትግራይ ክልል ተዋጊዎችን ማሰናበት እና መልሶ ማዋሐድ በአፋጣኝ እንዲተገበር አሳሰበ!
በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሠረት፣ “የትግራይ ተዋጊዎች ኃይል” የተባለውን ታጣቂ አደረጃጀት የማፍረስ ሒደት እና ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ኑሮ መልሶ የማዋሐድ፣ እንዲሁም ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ሥራዎች፣ በአስቸኳይ ሊተገበሩ እንደሚገባ፣ የአፍሪካ ኅብረት አሳሰበ፡፡አህጉራዊ ኅብረቱ፣ በፌዴራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል፣ ባለፈው ጥቅምት ወር በፕሪቶርያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ትግበራ ሒደት መገምገሙን፣ በአወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡በጉዳዩ ላይ፣ የትግራይ ክልል የኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤትንና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርን አስተያየት ጠይቀናል፡፡
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት በእና በህወሓት መካከል፣ ባለፈው ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ-ፕሪቶርያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ትግበራ ሒደት የሚከታተለው እና የሚቆጣጠረው የአፍሪካ ኅብረት ቡድን፣ ትላንት ረቡዕ፣ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም.፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከህወሓት እንዲሁም ከኢጋድ ተወካዮች ጋራ በመኾን፣ አፈጻጸሙን መገምገሙን፣ የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል::በዘላቂነት ተኩስ የማቆም ስምምነቱ መሠረት፣ የትግራይ ተዋጊዎች ከባድ ትጥቆችን እንደፈቱ፣ ቀላል እና መካከለኛ ትጥቆችን ደግሞ በማስረከብ ሒደት ላይ እንዳሉ መግለጫው አመልክቷል፡፡
በትግራይ ክልል፥ ያልተገደበ ሰብአዊ ርዳታ እንዲገባ ማመቻቸት፣ መሠረታዊ አገልግሎቶች ማለትም የጤና፣ የትራንስፖርት፣ የንግድ እንቅስቃሴ መጀመር እና የትምህርት ቤቶች በአብዛኛው የክልሉ አከባቢዎች ዳግም መከፈት የሚሉት፣ በጋራ ግምገማው በአዎንታዊነት መጠቀሳቸውን መግለጫው ጠቅሷል፡፡በሌላ በኩል፣ በጦርነቱ ወቅት፣ በትግራይ ክልል የነበረውን የተዋጊዎች አደረጃጀት ማፍረስ እና ወደ ሰላማዊ ኑሮ መልሶ የማደራጀት ሥራው፣ በአፋጣኝ መተግበር እንዳለበት የጋራ ግምገማው ማሳሰቡን መግለጫው አመልክቷል፡፡
ነገ ዐርብ፣ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም.፣ የሰላም ስምምነቱ ፈራሚ የኾነው ህወሓት፥ የተዋጊዎቹን፣ የመካከለኛ እና ቀላል የጦር መሣርያዎች፣ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንደሚያስረክብና ተዋጊዎቹን የማሰናበት ሥራ ደግሞ በይፋ እንደሚጀመር ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት በመጠበቅ ረገድ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው የመመለሱ ሥራም እንዲተገበር፣ የአፍሪካ ኅብረት በመግለጫው አሳስቧል፡፡
የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም፣ በሰላም ስምምነቱ መሠረት፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው ከመመለሳቸው አስቀድሞ፣ የውጭ ወታደሮች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ያልኾኑ ኃይሎች፣ ከክልሉ መውጣት ይገባቸዋል፤ ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት ያወጣውን መግለጫ አስመልክቶ ማብራርያ የሰጡን፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አቶ ገብረ መድኅን ገብረ ሚካኤል፣ የትጥቅ መፍታቱ እና ተዋጊዎችን በትኖ ወደ ቀድሞ ሕይወት የመመለሱ ሥራ፣ ከሌሎች አገሮች ተሞክሮ አኳያ፣ ጊዜ የሚወስድ ተግባር እንደኾነ ጠቅሰው፣ በፕሪቶርያው ስምምነት አተገባበር ግን፣ “ሒደቱ እየተቀላጠፈ ነው፤” በማለት ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ፣ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች፣ መሠረታዊ ሕዝባዊ አገልግሎቶች ተጀምሯል፤ የተባለው፣ “የተጋነነ አገላለጽ ነው፤ ገና ብዙ መሥራት ያስፈልገዋል፤” ብለዋል፣ አቶ ገብረ መድኅን፡፡የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ፣ የሰላም ስምምነት ሂደቱ እንዳይደናቀፍ ፣ በትኩረት ሊሠሩ ይገባል ያሏቸውንም ጉዳዮች አንሥተዋል፡
የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት ትግበራ የሚከታተለውና የሚቆጣጠረው ቡድን፣ ሥራው፥ እስከ ታኅሣሥ 2023 እንዲቀጥልም፣ በትላንትናው ዕለት መወሰኑን፣ የኅብረቱ መግለጫ አስታውቋል፡፡በመጨረሻም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት፣ “ለኣፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” በሚለው አህጉራዊ መርሕ መሠረት፣ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ እያሳዩ ለሚገኙት ተነሣሽነት እና ትብብር፣ ኅብረቱ በመግለጫው አመስግኗል፡፡
Via VoA

የሙስሊሙ ማኀበረሰብ በሸገር ከተማ እየተፈፀመ ያለውን መስጂድ የማፍረስ ሒደት በመቃወም በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ አካኼደ።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
የሸገር ከተማን መስጂድ ፈረሳ በመቃወም በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ!
በአዲሱ የሸገር ከተማ አስተዳደር እየተፈጸመ የሚገኘውን መስጂድ የማፍረስ ተግባር በመቃወም ሙስሊሙ ማኀበረሰብ በአዲስ አበባ አንዋር መስጂድ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂዷል።የሰልፉ ዋነኛ ዓላማም በአዲሱ የሸገር ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የመስጂድ ፈረሳዎች በአስቸኳይ እንዲቆም ማሳሰብ መሆኑ ታውቋል።ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንዋር መስጂድ ላይ የተቃውሞ እያደረገ ያለውን ህዝበ ሙስሊም እንዲበተን ማድረጉም ተነግሯል።
የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ግንቦት 15/2015 በሰጠው መግለጫ፤ በከተማ አስተዳደሩ እየተካሄደ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ ያወገዘ ሲሆን፤ ዛሬ ግንቦት 18/2015 በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ኹሉም መስጂዶች የጁምዓ ኹጥባ መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ የሚገኘውን የመስጂድ ፈረሳው የተመለከተ እንዲሆን ማሳሰቡን መዘገባችን ይታወሳል።
ምክር ቤቱ በአዲሱ የሸገር ሲቲ ከተማ አስተዳደር ከረመዳን 1 ጀምሮ የፈረሱ መስጂዶች ቁጥር 19 መድረሳቸውን ያስታወቀ ሲሆን፤ እነዚህ የፈረሱት መስጂዶች በከተማ አስተዳደሩ ሥር በሚገኙት በቡራዩ መልካ ኖኖ፣ በኮዬ ፈጬ፣ በሰበታ፣ በፉሪ፣ በአጃምባና ሌሎችም አካባቢዎች እንደሆነ ገልጾ ነበር፡፡በተመሳሳይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጻፈው ደብዳቤ፤ በሸገር ከተማ እያፈረሱ ስላሉ መስጂዶች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ መጠየቁም ይታወሳል።
[Addis Maleda]

የህወሓት ታጣቂ ሃይሎች የመጀመሪያው ዙር የተሃድሶና መልሶ የማቋቋም መርሐ ግብር ተጀመረ!
የህወሓት ታጣቂ ሃይሎች የመጀመሪያው ዙር የተሃድሶና መልሶ የማቋቋም መርሐ ግብር ዛሬ ከመቀሌ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ኩሐ በይፋ ተጀምሯል።በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተወካይ ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያ እንደገለጹት÷ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት በኢትዮጵያ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል።
“ታጣቂዎች በዚህ ሰላም ተጠቅማችሁ የራሳችሁን ህይወት መቀየርና፥ በክልሉ ብሎም በኢትዮጵያ ልማት መሳተፍ፤ የተፈጠረውን ሰላምም ዘላቂ ለማድረግ መስራት ይኖርባችኋል” ብለዋል።
መንግስት ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ወደ መደበኛ ህይወታችሁ እስክትመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፥ ለተሀድሶ የገቡት እስከሚቋቋሙ ድረስ ተገቢው ዕገዛ የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል።የህወሓት ታጣቂ ሀይሎች ተወካይ ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሀይለ በበኩላቸው፥ “እናንተ የተሀድሶ መርሐ ግብርን አጠናቃችሁ ወደ ህብረተሰቡ ስትመለሱ የልማትና የሰላም ሀይል መሆን አለባችሁ” ብለዋል።

ከጁምዓ ሶላት በኋላ በመርካቶ አካባቢ በተፈጠረ ረብሻና ግርግር የሰው ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ!
ዛሬ ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ በሌሎች አካባቢዎች መስጂዶች ፈርሰዋል በሚል ምክንያት በመርካቶ ዙሪያ በተፈጠረ ረብሻና ግርግር የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።ፖሊስ ባወጣው መግለጫ በተፈጠረው ረብሻና ግርግር ህግ በማስከበር መደበኛ ሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱንም አስታውቋል።
በተለይም በተለምዶ ጋዝ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተፈጥሮ በነበረ ግርግር ሁለት ግለሰቦች ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ሆስፒታል ከተላኩ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉንም ነው የገለጸው።በተጨማሪም አራት ግለሰቦች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ህግን ለማስከበር በተሰማሩ 37 የፖሊስ አመራርና አባላት እንዲሁም 15 የሚሆኑ የተለያዩ የፖሊስ አጋዥ ሀይሎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና መላካቸውንም ገልጿል።
ረብሻውን ባስነሱት አካላት በተጨማሪ ንብረትነታቸው የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሆኑ ሁለት አውቶቡሶች ላይ ጉዳት መድረሱንም በመግለጫው አመላክቷል።መነሻውን አንዋር መስጂድ ያደረገው ረብሻ በጋዝ ተራ፣ ቆርቆሮ ተራ፣ ሰባተኛ አካባቢ፣ አመዴ እና በተለያዩ አካባቢ ለማዛመት የተሞከረ ቢሆንም በፀጥታ አካሉ ጥረት ረብሻው ሳይስፋፋ መቆጣጠር ተችሏልም ነው ያለው።
[FBC]

ከሀዋሳ ፣ ከአዳማ ፣ ከሻሸመኔ አስቸኳይ ፖስታ ወደ አዲስ አበባ ያሉበት ድረስ በ 300 ብር ብቻ።
እንዲሁም
Online የገዙትን ልብስ፣ጫማ የተለያዩ እቃዎችን ከአዲስ አበባ እቃው ያለበት ድረስ በመምጣት እንቀበሎታለን። እንዲሁም ሀዋሳ ፣ አዳማ ፣ ሻሸመኔ ፣ያሉበት ድረስ እናደርሳለን።
የየኔቲዩብ እህት ድርጅት አዲስ ኤክሰረስ
T.me/Addisexpressdelivery

መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።
ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ
👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah
👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
tiktok.com/@u0917040506_0912718883