YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አሜሪካ የሩሲያን ድንበር ተሻግሮ ከተፈጸመው ጥቃት ራሷን አራቀች።

ሩሲያንና ዩክሬን ከሚያዋስናቸው አንዱ በሆነው የቤልጎሮድ ግዛት በኩል ሰኞ እለት ታጣቂዎች ገብተው ጥቃት ፈጽመዋል ተብሏል።ሩሲያ በዩክሬን ወረራ ከፈጸመች በኋላም የሩሲያን ድንበር የተሻገረ ወረራ ሲፈጸም የመጀመሪያው ነው።ሩሲያ በቤልጎሮድ ግዛት አሜሪካ ሰራሽ ሃምቪስን ጨምሮ በርካታ ከጥቅም ውጭ የሆኑ የምዕራባውያን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ምስሎችን አውጥታለች።

አሜሪካ በበኩሏ “ በሩሲያ ውስጥ ጥቃቶችን አላበረታታንም” ስትል ተናግራለች።በዚህ ጥቃት ላይ አሜሪካ ያቀረበችው የጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋላቸውን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎችም መድረኮች ላይ እየተሰራጩ ያሉ ዘገባዎችን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምነዋል።

ነገር ግን አገራቸው “የእነዚህ ዘገባዎች ትክክለኛነትን በተመለከተ በዚህ ጊዜ ትጠራጠራለች” ብለዋል።ማቲው ሚለር ማክሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ይህንን ጦርነት እንዴት መምራት እንዳለባት የመወሰን የዩክሬን ጉዳይ ነው” ሲሉ አክለዋል።በድንበር አቅራቢያ የሚገኙ የቤልጎሮድ መንደሮች ነዋሪዎች በደረሰው ከባድ መሳሪያ ጥቃት ተፈናቅለዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቤጂንግ ገባ!

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቻይና ቤጂንግ ገባ።ልዑኩ ቤጂንግ ሲደርስ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች፣ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች እና በቻይና የዳይስፖራ ማህበረሰብ ተወካዮች አቀባበል ተደርጎለታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል ‹ በአዲስ አበባ ቤተ መንግስት እንዲገነባ ክልላዊ ህገ መንግስቱ ይፈቅድለታል › አለ፡፡

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ሐይሉ አዱኛ ከአሻም ወቅታዊ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት ‹ ክልሉ በአዲስ አበባ ቤተ መንግስት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተቋማትን የመገንባት መብት እንዳለው ይደነግጋል› ብለዋል፡፡

አክለውም ‹ ይህ እንደ አዲስ ጥያቄ የሚያሰነሳ ጉዳይ አይደለም › ብለዋል፡፡ሃላፊው ‹‹ ፊንፊኔ ›› እያሉ የሚጠሯት አዲስ አበባ የክልሉ መቀመጫ ከሆነች 30 ዓመታት ማስቆጠሩንም ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን እርሳቸው ይህን ቢሉም የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ የተቀየረው በ1997 ዓ.ም መሆኑን አሻም ብትጠይቃቸው እርሳቸው ግን 30 ዓመታትን አስቆጥሯል ባይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በማያወላዳ መልኩ አዲስ አበባ የፌደራሉ መንግስት መቀመጫና የሀገሪቱ መዲና መሆኗን ቢደነግግም የቢሮው ሃላፊ ግን ‹ የክልሉ ህገ መንግስት አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ መሆኗን ደንግጓል › ሲሉ ሞግተዋል፡፡

እርሳቸው ይህን ቢሉም አሻም ‹ የህግጋት ሁሉ የበላይ የሀገሪቱ ህገ መንግስት መሆኑን › አስታውሳ ብተጠይቃቸውም ‹ የክልሉ ህገ መንግስት አዲስ አበባ የኦሮሚያ መቀመጫ መሆኗን ይደነግጋል › ሲሉ መልሰዋል፡፡

Via Asham TV
@YeneTube @FikerAssefa
1
ጋምቤላ-በሁለት ጎሳ አባላት ግጭት 7 ተገሉ!

በጋምቤላ ክልል በሚኖሩ በሁለቱ ነባር ብሄረሰብ አባላት መካከል ካለፈዉ እሁድ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 7 ሰዎች ተገደሉ።የክልሉ ነዋሪዎች እንዳሉት በግጭቱ ምክንያት የጋምቤላና የኢታንግ ከተሞች የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና የተለያዩ መደብሮች ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ተዘግተዋል።

በጋምቤላ ክልል በርካታ ቁጥር ባላቸዉ በኑዌርና በአኙዋክ ቤሔረሰብ አባላት መካከል ግጭቱ የተቀሰቀሰበት ምክንያት እስካሁን በዉል አልታወቀም።የኑዌር ብሔረሰብ ተወላጅ የሆኑት የኢታንግ ከተማ ነዋሪ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ እንደተናገሩት ኢታንግ ዉስጥ በተደረገዉ ግጭት ከሁለቱም ወገን 4 ሲገደሉ ሌሎች 5 ቆስለዋል፡፡

የአኙዋክ ብሔር ተወላጅ የሆኑት የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው ሰዎች መገደላቸውን አስታውሰው፣ የመንግስት ስራ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እንደሌለና የአገልግሎት መስጫ ተቋማትም ዝግ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ቤተክርስትያኗ የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤን መጠናቀቅ አስመልክቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፋለች!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ከግንቦት 1 ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ድረስ ሲደረግ የነበረው የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤን መጠናቀቅ አስመልክቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፋለች።በዚህም በሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፈን በሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰይሟል።

እንዲሁም በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ግንኙነትን በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ ተሰይሞ በስራ ላይ ያለው ልዑክ የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ምላዕተ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፏል።በተጨማሪም ጉባኤው በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት የትግራይ ወገኖች ያሉበትን ከፍተኛ ችግር ታሳቢ በማድረግ 20 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶሱ ወስኗል።

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በአህጉረ ስብከትና በአብያተ ክርስትያናት የተቋረጠው አገልግሎት እንዲቀጥል፤ ችግሮችም በዘላቂነት እንዲቀረፉ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳት ከፌደራልና ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በመወያየት ችግሮቹ እንዲፈቱ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።

ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ ክፍት በሆኑና በተደራቢነት በተያዙ ጉልህና አንገብጋቢ ችግሮች ባሉባቸው ኦሮሚያና ደቡብ ክልል ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስመራጭ ኮሚቴ እንደሚሰየም ቅዱስ ሲኖዶስ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ ሊሰጥ ነው!

ጉዳዩን አስመልክቶ የስፑትኒክ አለም አቀፍ የዜና አገልግሎት ድርጅት እና ሬዲዮ÷ በሩሲያ - አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተስፋዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱ በአሌክሳንደር ጎርቻኮቭ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፈንድ እና በሰብአዊ እርዳታ ማእከል ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን÷ በሩሲያ እና በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር አድማስ” ለመፍጠር ያለመ የባለሙያዎች እና ትምህርታዊ ዝግጅት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።በውይይቱ ላይ ከሩሲያ እና አፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራንና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ከፈረንጆቹ መስከረም 2023 ጀምሮ ቢያንስ አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት የአማርኛ እና የስዋሂሊ ቋንቋ ማስተማር እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል።ማስሎቭ አክለውም በአዲሱ ልዩ መርሐ-ግብር በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ዮሩባ ቋንቋን የሚያስተምሩበትን ዕድልም እየተመቻቸ መሆኑን ነው የገለፁት።

ወደ አፍሪካ በፍጥነት ፊትን ለማዞር ከኢኮኖሚው ጋር በቀጥታ ሊሰሩ የሚችሉ ፍጹም የተለዩ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ሲሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡አፍሪካ አንድ ትልቅ አህጉር ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖት እና ህብረ ብሔራዊ ማንነቶች ያሉባት አህጉር መሆኗን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ሰላም አዲስ አበባ ላይ ያላችሁ ነጋዴዎች እንዴት ናችሁ?

ሱቆን በነፃ በየኔቲዩብ ላይ ልናስተዋውቅ በአዲስ ሀሳብ መተናል።


ያናግሩን @Fikerassefa
👍1
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል። 

🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥NGO በማንኛውም

     🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
     🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
     🔹ደሞዝ: 18,500+

💥ሹፌር በሁሉም

     🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:13,500+

💥ስልክ ኦፕሬተር

     🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 6500

💥ጉዳይ አስፈፃሚ

     🔹የት/ደረጃ:10
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:7000

💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ

    🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ፡4500

💥አካውንታንት

🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500

💥ካሸር አሰልጥኖ

🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500

💥ባርማን/ባሬስታ

🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት

💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት

     🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 3500


💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች

     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,000

💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)

🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።

የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

tiktok.com/@u0917040506_0912718883
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት የአፍሪካ ሀገራት ገለልተኛ አቋም መያዝ እንደሌለባቸው ገለጸች

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በጦርነቱ ዙሪያ ዝምታን መርጠዋል ያሏቸው የተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት ለኬቭ ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ኩሌባ በዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜለንስኪ የቀረበውን ባለ 10 ነጥብ የሰላም እቅድም የአፍሪካ ሀገራት እንዲደግፉት ነው ጥሪ ያቀረቡት።

ከሩሲያ እና ዩክሬን የግብርና ምርቶችን በስፋት የሚያስገቡት የአፍሪካ ሀገራት የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ "የሩሲያን ወረራ" ለማውገዝ በጠራው ስብሰባ ድምጽ ከመስጠት መቆጠባቸው ይታወሳል።

የዩክሬኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ይህ ገለልተኛ ከዩክሬን በተቃርኖ እንደመቆም የሚታይ መሆኑን በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ በአፍሪካ ህብረት ተገኝተው ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር እንደሚመክሩ በአፍሪካ ህብረት የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ብሪጌት ማርኩሰን በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያገናኘው የአሰብ ኮሪደር የመንገድ ግንባታ በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ!

ኢትዮጵያን በአሰብ በኩል ከኤርትራ ጋር የሚያገናኘው የሜሎዶኒ መገንጠያ-ማንዳ-ቡሬ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሆነ ተገለጸ፡፡የመንገድ ግንባታው 71 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በመንግስት በተመደበ ሁለት ቢሊዮን ብር በጀት በአስፋልት ኮንክሪት እና በሲሚንቶ ኮንክሪት ንጣፍ ደረጃ እየተገነባ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

መንገዱ በገጠር 10 ሜትር እና በቀበሌ ከተሞች ደግሞ 21.5 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡የግብዓት እጥረት፣ በአካባቢው በነበረ የጸጥታ ችግር እና በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ተቀብረው ያልመከኑ ፈንጂዎች መኖር በግንባታ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድሩም ችግሮችን በመቋቋም ግንባታው በተፋጠነ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የሀገራዊ እና ቀጣናዊ ትስስሩ ጥረቱን ከማፋጠን ባሻገር የአካባቢው ነዋሪዎች የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም መሰል ግልጋሎቶችን መዳረስ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ የአሰብ ኮሪደር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የሚካሄደው ሻንዶንግ ሉሽያዎ ግሩፕ ካምፓኒ ሊሚትድ በተባለ የውጭ ሀገር የሥራ ተቋራጭ ሲሆን ግንባታው በመጪው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት መንግስታት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 2.4 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ቃል እንደተገባላት አስታወቀ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ በአሜሪካ፣ ኒውዮርክ ረቡዕ ግንቦት 16 2015 ዓ.ም በተካሄደ ጉባዔ እንደተናገሩት፣ ድርጅታቸው ያስፈልገኛል ካለው 7 በሊዮን ዶላር ውስጥ 2.4 ቢሊዮን ዶላር ቃል እንደተገባለት አረጋግጠዋል፡፡

ከረቡዕ ጉባዔ አስቀድሞ ሦስቱ ሀገራት ከሚያስፈልጋቸው ውስጥ ያገኙት አነስተኛ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ 22 በመቶ፣ ሶማሊያ 25 በመቶ እንዲሁም ኬንያ 21 በመቶ ብቻ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ድርጅቱ ቃል ተገብቶልኛል ካለው የ2.4 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የምትወስደው አሜሪካ ናት፡፡ ዩናይተድ ስቴትስ እ.አ.አ. በ2023 በጀት ዓመት በዚህ ዙር ቃል የገባችውን 524 ሚሊዮን ዶላር ጨምሮ አጠቃላይ ልገሳዋን 1.4 ቢሊዮን አድርሳዋለች፡፡

የአውሮፓ ኮሚሽን 185 ሚሊዮን፣ ጀርመን 163 ሚሊዮን፣ ብሪታኒያ 120 ሚሊዮን፣ ኔዘርላንድስ 92 ሚሊዮን ዶላር ለመለገስ ቃል ገብተዋል፡፡በመንግስታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪን ፊልድ ‹ ይህ የሁላችንም(ጥረት) ዓለም አቀፋዊ ችግር ነው › ብለዋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
የባህርዳር ከተማ ደጋፊዎች ላይ የቦንብ ጥቃት ደረሰ!

በእግርኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የቅዱስ ጊዮርጊስና የባህርዳር ከተማ ሊካሄድ 36 ሰዓት በቀረበት ወቅት የባህርዳር ደጋፊዎች ላይ የደረሰው የቦንብ ጥቃት አነጋጋሪ ሆኗል።

ደጋፊዎቹ ቡድናቸውን ለመደገፍ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የተፈቀደላቸውን አውቶቢስና ሌላ በተከራዩት ተጨማሪ አውቶቢስ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ለሊት 10 ሰዓት ላይ በሙላለም የባህል ማዕከል አየተሰባሰቡ ባሉበት አደጋው መድረሱ ታውቋል በጉዳቱ እስካሁን የሞተ ሰው የሌለ ሲሆን ከ20 የሚበልጡ ደጋፊዎች ግን ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን ምስክሮች ተናግረዋል።

ቦንቡ ተወርውሮ ይሁን ተጠምዶ በሚለውና አጠቃላይ ጉዳት ዙሪያ የክልሉ መንግስትና ፖሊስ የሚሰጠው መግለጫ ይጠበቃል።

Via Hatrick Sport
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ የቤት መፍረስ ቅሬታ ለፌደራሉ እንባ ጠባቂ ተቋም ስለመግባቱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ መናገሩን ቪኦኤ ዘግቧል።

አስተዳደሩ የተጠቀሰውን ያህል ቅሬታ እንዳልቀረበለት መግለጡን ዘገባው አመልክቷል። የአስተዳደሩ ሃላፊዎች፣ ለተቋሙ ቀረበ የተባለው ቅሬታ ውይይት ያልተደረገበት፣ ባግባቡ ያልተጣራና ከአንድ ወገን ብቻ የተገኘ መረጃ ነው ያሉ ሲኾን፣ እንባ ጠባቂ ተቋም ግን በቅሬታው ዙሪያ ከአስተዳደሩ ጋር መወያየቱን እንደተናገረ ዘገባው ጠቅሷል። አስተዳደሩ "ሕገወጥ" ብሎ ካፈረሳቸው ቤቶች ጋር በተያያዘ፣ እንባ ጠባቂ ተቋም 100 ሺህ ቅሬታዎች እንደተቀበለ ከቀናት በፊት መግለጡ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ አዋጅን አጸደቀ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1294/2015 በአብላጫ ደምፅ አጸደቀ።ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስበሰባ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ በሚመለከት ሰፊ ውይይት አድርጓል።

የሰው ሀብት ልማት የሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አዋጁን ለማፅደቅ የቀረቡ የውሳኔ ሀሳቦችን አቅርበዋል።

ረቂቅ አዋጁ ለሀገር ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራና በምርምር የላቀ እውቀት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት የሚሰሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሰላም አዲስ አበባ ላይ ያላችሁ ነጋዴዎች እንዴት ናችሁ?

ሱቆን በነፃ በየኔቲዩብ ላይ ልናስተዋውቅ በአዲስ ሀሳብ መተናል።

ወደ ክፍለኃገር ብዙ ደምበኛ ላያችሁ ብታናግሩን ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ያናግሩን @Fikerassefa
የባህር ዳር ከተማ ከንቲባና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በትላንትናው ለሊት ስለተፈፀመው የቦንብ ጥቃት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከንቲባው ፤ " ክለባችን ባህር ዳር ከነማ በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ዋንጫ ለማንሳት እየተፎካከረ ይገኛል " ብለዋል።

ይህንን መሠረት በማድረግ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ከሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው በአካል ተገኝተው ለመደገፍ ጉዞ ወደ ሀዋሳ ለማድረግ ዝግጅት ጨርሠው ወደ ተዘጋጀላቸው አውቶብስ እየገቡ ባሉበት ሁኔታ በተወረወረባቸው ቦንብ 23 የክለቡ ደጋፊዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል።

ከንቲባው ቦንቡን የወረወሩት " ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት " ናቸው ብለዋል።ቀላልና ከባድ ጉዳት ያደረሰባቸው የክለቡ ደጋፊዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከንቲባው ገልጸዋል።

Via Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa