YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
1👍1
በደቡብ ኦሞ ዞን የወደቀ ቦንብ አግኝታ ስትጫወት የነበረች ታዳጊ ህይወቷ አለፈ

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ  የወደቀ ቦንብ አግኝታ ስትጫወት የነበረች ታዳጊ ህይወቷ ማለፉን በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ቦንቡን በመቀጥቀጥ ሰትጫወት የነበረችው የሶስት አመት ህፃን በድንገት እጇ ላይ እንዳለ ፈንድቶ  ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት  በህክምና  ስትረዳ ቆይታ ህይወቷ ማለፉ ፖሊስ ገልጿል።

በወረዳዉ ጋዘር ከተማ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ሞ በፍንዳታዉ ጉዳት የደረሰባትን ህፃን በህክምና ስትረዳ ቆይታ በትላንትናዉ እለት ግንቦት 13 ህይወቷ ማለፉ ተገልጿል።

ህፃናት የተለየ ነገር ወድቆ ሲያገኙ ለህይወታቸዉ አደገኛ በመሆኑ ከማንሳት ይልቅ ለቤተሰቦቻቸው በማሳወቅ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲችሉና የሚጫወቱበት ስፍራ ከቤተሰብ እይታ የራቀ መሆን እንደሌለበት ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍1
በኮሎምቢያ የወሊድ መቆጣጠሪያ ህክምናን ብወስድም ልጅ ወልጃለሁ ያለው ግለሰብ በዶክተሩ ላይ ክስ መስርቷል፤ ፍርድ ቤቱ ህፃኑ 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ ዶክተሩ እንዲያሳድግ ውስኗል

አንድ የኮሎምቢያ ዶክተር ለደንበኛው ቋሚ የወሊድ መከላከያ(ቫሴክቶሚ) ህክምና ቢደረግለትም ሰውየው ልጅ በመውለዱ ህፃኑ 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ የገንዘብ እንዲደግፍ ዶክተሩ እንዲያደር በፍርድ ቤት ታዟል።በኮሎምቢያ ሜዴሊን ከተማ የሚኖረው ዶክተር ዲዬጎ ናራንጆ ከዚህ ቀደም ያደረጓቻው የቫሴክቶሚ ህክምና የተሳካለት መሆኑን እና ሌላ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም እንደማያስፈልጋቸው ለቤተሰቡ ተናግረው ነበር።

ይሁን እንጂ ሰውየው ሚስቱን አርግዛ እና ያልታቀደ ልጅ ወልዳለች። ከዚህ በኋላ በተደረገው የወንድ የዘር ፍሬ ምርመራ የቫሴክቶሚው የወሊድ መከላከያ በትክክል አለመሰራቱን አረጋግጠዋል። የሕፃኑ ወላጆች ስህተቱ በገንዘብም ሆነ በስሜታቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ገልፀዋል።

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደሚያሳየው፣ ዶ/ር ናራንጆ ለታካሚው ቤተሰብ 92 ሚሊዮን ፔሶ (20,300 ዶላር) የሞራል ጉዳት፣ 60 ሚሊዮን ፔሶ (13,200 ዶላር) ህጋዊ ክፍያ እና 143 ሚሊዮን ፔሶ (31,500 ዶላር የልጅ ማሳደጊያ እንዲከፍል ወስኗል።

Via ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍1
የሀገሬ ቴሌቭዥን ስራአስኪያጅና ዕውቁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መምህር ብርሃኑ አድማስ ዛሬ በፀጥታ ኀይሎች ከቢሯቸው መወሰዳቸውን ዋዜማ ከአይን እማኞች ሰምቻለሁ ብላለች።። ብርሃኑ የተወሰዱት "ለጥያቄ ትፈለጋለህ" ተብለው መሆኑ ተሰምቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የሙርሌ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ባደረሱት ጥቃት 10 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ መድረሱ ተገለጸ!

በተደጋጋሚ ወቅትና ጊዜ እየጠበቁ ጥቃት የሚሰነዝሩት የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ቅዳሜ ምሽት በከፈቱት ድንገተኛ ተኩስ፤ እስከአሁን 10 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ መድረሱን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ቅዳሜ ምሽት ሦስት ሰዓት አካባቢ የኢትዮጽያን ድንበር ጥሰው በመግባት በጋምቤላ ክልል በማኩዌይ ወረዳ ቢልኬች ቀበሌ እንዲሁም በዋንቱዋ ወረዳ መተሀር ከተማ በመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት፤ እስከአሁን 10 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ መድረሱ ተነግሯል።በጥቃቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ወደ ጋምቤላ ጠቅላላ ሆስፒታል ለሕክምና መላካቸውን የተገለጸ ሲሆን፤ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ደግሞ በኝንኛንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ተመላክቷል።

ጥቃቱን ተከትሎ በጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ቴንኩዌይ ጆክ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኑዌር ዞን በሙርሌ ጥቃት የደረሰባቸውን ዜጎች ምልከታ አድርገዋል።ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በተደጋጋሚ ወቅትና ጊዜ እየጠበቁ ጥቃት የሚሰነዝሩት የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ታጣቂዎች ቅዳሜ ምሽት ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ነው ጥቃቱን ማድረሳቸውን በመግለጽ፤ በደረሰው ጥቃት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ መንግሥት ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለማደን ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለጹም ሲሆን፤ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም የተጠናከረ ጥበቃም እንደሚደረግ አብራርተዋል።አክለውም፤ የክልሉ መንግሥት በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።ከዚህ ቀደም እነዚሁ ታጣቂዎች በኑዌር ዞንና አኙዋ ዞኖች ገብተው የተለያዩ ጥቃቶችን ማድረሳቸው ይታወሳል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ዜጎችን በገዛ ሐገራቸው አማራጭ መፍትሔ ሳይፈለግላቸው ሜዳ ላይ መበተን ከፍተኛ የጭካኔ ተግባር ነው ሲል ጎጎት ፓርቲ ገለጸ፡፡

የጉራጌ ህዝብ እኩልነት እና ፍትህ ፓርቲ በምህጻሩ ጎጎት፣ በሸገር እና አዲስ አበባ ከተሞች እየደረሰ ስላለው ቤት የማፍረስ ዘመቻ እንዲሁም በጉራጌ የመብት ታጋዮች ላይ እየደረሰ ስላለው የመብት ጥሰት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡ፓርቲው በመግለጫው ዜጎችን የማቋቋም እና የመደገፍ ስራ መስራት የሚጠበቅበት መንግስት የዜጎች ከለላ ሳይሆን የስጋት ምንጭ መሆኑን አመላክቷል፡፡

በሸገር ከተማ እየተፈፀመ የሚገኘው ቤት የማፍረስ ዘመቻ በአድማሱ እና ዜጎች ላይ እያደረሰ ባለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት በርካታ ዜጎችን ለከፋ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ ሲል አስታውቋል፡፡በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቤታቸው እና የንግድ ቦታቸው ፈርሶ በከፍተኛ ችግር ላይ ሲገኙ እጅግ በርካታ ዜጎች ደግሞ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ ነው ያለው።ቤታቸው ፈርሶ ለከፋ የጎዳና ህይወት የተጋለጡ በርካታ ዜጎች መኖራቸውም ለመረዳት ችለናል ብሏል ጎጎት።

በዚህ ሂደት እየደረሰ ያለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ከጊዜ ወደ ጊዘ እየተባባሰ መጥቶ ዜጎች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲወድቁ አድርጓል ሲል በመግለጫው አጽዕኖት ሰጥቷል፡፡ዜጎች ቤት እና ንብረታቸው ከመውደሙ በላይ ሰብአዊ ክብራቸው ተዋርዶ፣ የገዛ ቤታቸው ማፍረሻ ሂሳብ እየተጠየቁ፣ እቃቸውን ይዘው እንዳይወጡ እየተከለከሉ መሆኑ፣ ይዘው ከወጡም የኬላ ተብለው ከፍተኛ ገንዘብ እየተጠየቁ እንደሆነ አረጋግጫለሁ ብሏል ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፡፡

ይህ ሁሉ ተግባር ግልፅነት እና ተጠያቂነት በጎደለው መንገድ እየተፈፀመ ይገኛል ሲል አስታውቋል፡፡በሌላ በኩል የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች ጨምሮ በርካታ የጉራጌ ልጆች ከወልቂጤ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከቡታጅራ እና ቡኢ ከተሞች ታፍሰው ቡታጅራ ከተማ በሚገኘው ቡታጅራ ከተማ ፖሊስ ጊዚያዊ ማረፊያ ቤት ታስረው እንደሚገኙ ገልጿል፡፡

የመብት ታጋዮች፣ ፖለቲከኞች፣ ነጋዴዎች፣ አመራሮች፣ ወጣቶች፣ ጋዜጠኞች በህገ ወጥ መንገድ ለወራት በእስር ታግተው ያለ ፍትህ እየተጉላሉ እንደሚገኙ ነው ፓርቲው ያስታወቀው፡፡በመሆኑም የሸገር ከተማ አስተዳደር እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዜጎች ሰብአዊ መብት ላይ እየፈፀሙ ያሉት ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፣ ግልፅ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር እንዲከተሉ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ተገቢው ካሳ እና መቋቋሚያ እንዲሰጣቸው ጎጎት አሳስቧል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የፍትሕ መጽሄት ማነጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል።

ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለDW እንደገለጸው የጸጥታ ሐይሎች በአለፈው ቅዳሜ ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ ከቤቱ ወስደው ካሰሩት ቦኋላ እኩለ ሌሊት ለቀውታል።

ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ፍርድ ቤት የሚቀርበው በአዲስ ክስ ሳይሆን ከዚህ ቀደም "የመከላከያን ስም በማጥፋት" ተብሎ ተከሶበት የነበረና በፍርድ ቤት የተዘጋን ፋይል በማንቀሳቀስ እንደሆነ፤ ሌላ ተጨማሪ ክስ ካለ ግን ዛሬ እንደሚታወቅ ጨምሮ ገልጻል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ጠዋት በጸጥታ ኃይሎች ከቢሯቸው የተወሰዱት ዲ/ን ብርሃኑ አድማሱ ተለቀቁ!

ዛሬ ጥዋት ከሥራ ቦታቸው "ለጥያቄ ትፈለጋለህ" ተብለው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎ የተወሰዱት ዲ/ን ብርሃኑ አድማሱ መለቀቃቸውን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች፡፡

ዲ/ር ብርሃኑ በአሁኑ ሰዓት ወደ ቢሯቸው መመለሳቸውን አዲስ ማለዳ ያረገጋጠች ሲሆን፤ የጸጥታ ኃይሎች የት ወስደዋቸው እንደነበር ማወቅ አልተቻለም፡፡

ዲ/ን ብርሃኑ የሀገሬ ቴሌቭዥን ሥራ አስኪያጅና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ አሉ ከሚባሉ ታዋቂና ተጽዖኖ ፈጣሪ መምህራን መካከል አንዲ ሲሆኑ፤ ከሰሞነኛው የቤተክርስቲያኗ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተገኛኘ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሀሳባቸውን አስፍረው ነበር፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ማኀበረ ቅዱሳን የቴሌቭዥን እገዳውን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ቦርድ የቅሬታ ደብዳቤ ላከ!

ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በግንቦት 13/2015 "ሰበር ዜና" በሚል ባሰራጨው መግለጫ ምክንያት የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት እንዲታገድ መወሰኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ማስታወቁ ይታወቃል።

ይህንንም ተከትሎ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ለባለስልጣኑ በጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ፤ ጣቢያው ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ለማስተማርና ወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችን ለማሳወቅ የተቋቋመ መንፈሳዊ ጣቢያ በመሆኑ የታገደበት የፕሮግራም ይዘት ከመገናኛ ብዙኃን አዋጁ ጋር የማይጋጭ መሆኑን ዝርዝር ምክንያቶችን በማጣቀስ ገልጿል።

👆ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የጻፈው የቅሬታ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ሻሸመኔ እንዲሁም (በቅርቡ ወደ አዳማ) Online የገዙት እቃ፣ ፓስታዎች፣ የባንክ ዶክመንቶች Addis Express (በአዲስ ኤክስፕረስ) በኩል ይላኩ ይቀበሉ።

ለእቃዎች ሙሉ ኃላፊነት እንወስዳለን።

ነጋዴዎች የሞተረኛ እዳታወጡ እኛ ሱቆ ድረስ መተን እንቀበሎታለን።

ስልክ
0980526262
0962627762

https://tttttt.me/deliveryhawassaexpress
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 9 አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ውሳኔ አሳለፈ!

የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ውሎው ችግር ባለባቸውና አስፈላጊ በሆኑባቸው አህጉረ ስብከት ዘጠኝ አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ውሳኔ አሳልፏል።አዳዲሶቹ ኤጲስ ቆጶሳት እነማን እንደሆኑና በየትኞቹ አህጉረ ስብከቶች እንደተሾሙ የተገለጸ ነገር የለም።

[የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ሃይሎችን ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆን ትጥቅ የማስፈታት ስራ መፈፀሙ ተሰማ።

የፕሪቶሪያ ውል አፈጻጸም ለመገምገምና አሁናዊ ሁኔታን ለመመልከት የ43 ሃገራት ወታደራዊ አታሼዎች ከአለፈው አርብ ጀምሮ በትግራይ ጉብኝት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

በአፍሪካ ሕብረት የሰላም ስምምነቱ ተቆጣጣሪ ልኡክ መሪ ሜጀር ጀነራል ስቲፈን ራዲና ዛሬ በመቐለ ከተማ በተሰጠው መግለጫ እንዳሉት የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ነው።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ የኤርትራ መንግስት የዕርዳታ እህል ለሕዝቡ እንዳይዳረስና የአፍሪካ ሕብረት የስምምነቱ ትግበራ ተቆጣጣሪ ስራውን እንዳያከናውን እያደናቀፈ ነው ሲሉ ከሰዋል ሲል DW ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ በሕዳሴ ግድብ ላይ ያሳለፈው የውሳኔ ሃሳብ እንደማትቀበል ገለጸች!

ኢትዮጵያ÷የዓረብ ሊግ በሕዳሴ ግድብ ላይ ያሳለፈው የውሳኔ ሃሳብ እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷በቅርቡ የተካሄደው የዓረብ ሊግ የመሪዎች ጉባኤ ያሳለፈው የውሳኔ ሀሳብ የኢትዮጵያን መንግስት እንዳሳዘነ ገልጿል፡፡

ውሳኔው በተለይም በግድቡ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ድርድር አንዲፈታ እየሰሩ ያሉትን የአፍሪካ ህብረትን እና አባል ሀገራትን ሚና የሚያኮስስ ነው ሲል አብራርቷል፡፡

የውሳኔ ሃሳቡ ታሪክን ከሚጋራው የአፍሪካ እና የዓረብ ሀገራት ግንኙነት በተቃራኒ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑንም አስገንዝቧል፡፡፡በሊጉ የተላለፈው የውሳኔ ሃሳብ የግብጽን የናይል ወንዝ ፍትሃዊ ያልሆነ አጠቃቀም የሚደግፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ስራዎች እየዘመኑና ቴክኖሎጂዎቹ ያለ እረፍት ስራዎችን ማከናወን መቻላቸውን ተከትሎ ብዙ ስራዎች ከሰው ልጆች እጅ እየወጡ ናቸው፡፡

ከሰው ልጅ ተነጥቀው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚተኩ የስራ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው?
በፎቶ እድሜ የሚናገረው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
በዚህም መሰረት በአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ከሚተኩ ስራዎች መካከል ጸሀፊነት፣ መረጃ ትንተና፣ መረጃ ማደራጀት፣ የዲዛይን ስራ (ዲዛይኒንግ) እና የምስል አርትኦት (ቪዲዮ ኢዲቲንግ) ዋነኞቹ ናቸው ተብሏል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ሙያዎች በአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የሚሸፈኑ በመሆናቸው የሰው ልጆች መማር የማይጠበቅባቸው ሙያዎች ናቸው ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡

Via:-አልአይን
@Yenetube @Fikerassefa
የወዳጅ ዘመድዎን ፎቶዎች ከፈለጉት ጽሁፎችና ዲዛይኖች ጋር፣ ሳቢና ማራኪ በሆነ የእንጨት ስራ ቀርፀው ለዘላለም ያስቀምጡ፣ በስጦታ መልክ ያበርክቱ።
ለበለጠ መረጃ @pulsengravings ብለው ያግኙን
ከፈለጉም 0911876009 ላይ ሃሎ ይበሉን
https://tttttt.me/photoengravings ላይ ይቀላቀሉ
👍1
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።

የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

tiktok.com/@u0917040506_0912718883
👍1
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ

ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️

የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ

ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦

🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን  ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።

ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።

በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።

አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj


For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp
👍1
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
👍1