የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ!
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርአት ዛሬ ተፈጽሟል። የድምጻዊቷ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል።
ድምፃዊቷ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በዓለማዊ ሙዚቃና በመንፈሳዊ መዝሙሮች አገሯንና ህዝቧን ማገልገሏ በህይወት ታሪኳ ላይ ተገልጿል።
ድምጻዊቷ የሰባት ልጆች እናት የአስር ልጆች አያትና የሰባት ልጆች ቅድመ አያት እንደነበረች ኢፕድ ዘግቧል።ድምፃዊቷ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ባሳለፍነው ግንቦት አራት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ አይዘነጋም።
@YeneTube @FikerAssefa

በአገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ ወር ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጂታል ይደረጋል!
በአገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ ወር ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጂታል ሥርዓት የሚደረግ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበባ ከዚህ ወር ጀምሮ የድህረ መብራት ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ይሆናል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ እስካሁን 30 በመቶ ብቻ የሚሆን ተገልጋይ የድህረ ክፍያ በዲጂታል የክፍያ አማራጭ የሚከፍል ሲሆን በአዲስ አበባ ከዚህ ወር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የድህረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በዲጂታል እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡
በቀጣይም በመላ አገሪቱ የሚገኙ አገልግሎት መስጫዎች ከተያዘው ዓመት ሐምሌ አንድ ጀምሮ ድህረ ክፍያ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አማራጭ እንዲያደርጉ ይደረጋል ብለዋል፡፡ እንደ አቶ መላኩ ገለጻ፤ አብዛኞቹ ደንበኞች የድህረ ክፍያ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡
[ኢፕድ]

በቤንች ወረዳ የገዛ ልጇን በገጀራ ቆራሪጣ የገደለች ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች!!
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን በሼይ ቤንች ወረዳ የገዛ ልጇን በገጀራ ቆራሪጣ የገደለች ተጠርጣሪዋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች ።
የልጁ አባት የለም ማን ያሳድጋል በሚል ስሜት ተነሳስታ የገዛ ልጇን ልክ እንደወለደች በገጀራ ቆራሪጣ የገደለችውን ተጠርጣሪዋን እናት በቁጥጥር የሼይ ቤንች ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኢንዶክትሬነሽንና የህዝብ ግንኙነቱ ማስተባበሪያ ኃላፊ ም/ኢ/ር ደሴ ጎንደር አስታውቋል።
በትናንትናው ዕለት በጋያሸማ ቀበሌ ሳዝንስ ተብሎ በሚጠራ መንደር የወለደችውን ልጅ በገጀራ ቆራሪጣ የገደለችውን ተጠርጣሪ ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ በቁጥጥር አወለናታል ነው ያሉት።
የምርመራ ክፍል ጉዳዩን እየመረመረ እንደሚገኝ ተናግረው ሴትዮዋ ባሏ ወደ ስራ ሂደው በመጥፋቱ ልጁን ማን ያሳድጋል በማለት ተነሳስታ እንደገደለች በሰጠችው ቃል መገንዘብ ችለናል ብለዋል።
Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa

በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሙሽራው እና አባትየው ህይወታቸው አለፈ!
በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር ዞን በቋሪት ወረዳ ወይበኝ ቀበሌ ልዩ ቦታው በተለምዶ አነሳት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በባህሉ በወጉ መሰረት ልጃችንን ለልጃችሁ ተባብለው ሙሽሪትና ሙሽራው ሊጣመሩ የሙሽራው ቤተሰብና የሙሽሪት ቤተሰብ በስጋ ዝምድና ሊጣመሩ ቤት ባፈራው እንደአቅም ድግስ በመደገስ የሩቁና የቅርቡ ወዳጅ ዘመድ ልጃችንን ስለምንድር ልጃችንን መርቁልን ማለት የተለመደ ስርዓትና ወግ ነው፡፡
ታዲያ በዕለተ እሁድ ከሩቁ ከቅርብ የተጠራው ቤተዘመዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሙሽራው መምጫ ሰዓት ደረሰ ሙሽራው ከነሚዜወቹ ደረሱ የሙሽሪት ቤተሰቦች በጣም ደስ አላቸው እልልታውን አቀለጡት ሙሽራው ሙሽሪትን በቤተሰብ አስመርቆ ወደቤቱ ሊመለስ ሲል ሞቅ ያለ ጭፈራ ሆታ ተነሳ በጭፈራው መሃል ቅልጥ ያለ የጥይት ተኩስም ተተኮሰ በድንገት ጭፈራ ሲጨፈር የነበረው ሰው ፀጥ አለ በጭፈራው መሃል በተተኮስ ጥይት ሙሽራው እና የሙሽራው አባት ወዲያውኑ ህይታቸው ያልፋል፣ አንድ የሴት ሚዜ አና ሰርጉን ለማድመቅ የተገኙ 4 ሰወች በድምሩ አምስት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን በተደረገላቸው ህክምና ህይወታቸው መትረፉን የወረዳው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረ/ኢ/ር ተመስገን ሙሉነህ ተናግረዋለወ። የወንጀል ድርጊት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያጣሩ መሆኑን ገልፀዋል። መረጃው የምዕ/ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው።

❗️የአፋልጉን ማስታወቂያ❗️
በምስሉ የምትመለከቷት ወጣት እየሩሳሌም ከተማ የምትባል ሲሆን በትላንትናው እለት ግንቦት 06' 2015 ከመኖሪያ ሰፈሯ ቄራ ጎፋ ጀርመን፤በተለምዶ ገና ትምህርት ቤት፤ አካባቢ ጠዋት ላይ ቸርች ለመሄድ እንደወጣች አልተመለሰችም።
ልጃችንን እንድታፋልጉን በእ/ር ርህራሄ እንለምናቹሃለን።
ልዩ ምልክቶች
1_ ቁመት፡ 1:50
2_መልክ፡ ቀይ
3_እድሜ፡ 25
4_ከላይ የለበሰችው፡ ሮዝ ባለ ኮፍያ ጃኬት
5_ከታች፡ ጅንስ ሱሪ
6_ጫማ፡ ጥቁር ሸራ ጫማ
7_ከፊት ጥርሷ አንዱ የወለቀ ነው
8_የአእምሮ እድገት ውስንነት ስላለባት እራሷን በደንብ አትገልፅም
የቤተሰብ ስልክ ቁጥር
1_አቶ ከተማ፡ 0911627318 (አባት)
2_ወ/ሮ አለም፡ 0911059346(ቤተሰብ)
ማንኛዉንም መረጃ በመደወል አሳዉቁን።
በማህበራዊ ድረገፆቻቹህ ሁሉ አጋሩልን።

የእነ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ የርሃብ አድማ
ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸውን ጨምሮ 40 የሚሆኑ እስረኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ
በአማራ ክልል ከልዩ ሃይል መፍረስና ፋኖን ትጥቅ ከማስፈታት ጋር ተያይዞ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነግሯል።
እስረኞቹ የርሃብ አድማውን ማድረግ የጀመሩት በአማራ ክልል የሚካሄደውን እስርና አፈና በመቃወም መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል።
ከዛሬ ሰኞ ግንቦት ሰባት ጀምሮ እስከ ረቡእ ግንቦት 9 የሚቀጥል መሆኑንም ነግረውናል።
በዚህም " ሽብር፣ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራችኃል እየተባለ የአማራ ሙሁራንን፣ ጋዜጠኞችንና ወጣቶችን እንዲሁም የቀን ሠራተኞችን ማሰር ይቁም" በሚል እነ ረ/ፕ ሲሳይን ጨምሮ 40 የሚሆኑ ታስረው የሚገኙ የአማራ ሙሁራንና ሌሎች እስረኞች ናቸው የርሃብ አድማውን የጀመሩት።
አድማውን አስመልክቶ ስለጉዳዩ ያውቁ እንደሆን ያናገርናቸው የእስረኞቹ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝም ጉዳዩን ከእስረኞቹ ቤተሰቦች ከሰሙ በኋላ ወደ እስር ቤት በማምራት አድማ መጀመራቸውን እንዳረጋገጡ ነግረውናል።
Via:- ሮሃ ቲቪ

😁1
ደቡብ አፍሪካ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ገለልተኛ ሆና እንደምትቀጥል ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ተናገሩ!
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሀገሪቱ በዩክሬን ጦርነት ላይ ያላትን አቋም እንድትቀይ "ያልተለመደ ጫና" እየተደረገባት መሆኑን ተናግረዋል።ሳምንታዊው የስራ ማብራሪያቸዉ ላይ ራማፎሳ እንደገለጹት በሩሲያ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ባለዉ የፉክክር ጉዳዮች ላይ ከአንዱ ወግና እንደማትቆም ተናግረዋል ።
ራማፎሳ እንዲህ ሊናገሩ የቻሉት በደቡብ አፍሪካ የአሜሪካ አምባሳደር ሩበን ብሪጌቲ ደቡብ አፍሪካ ገለልተኝነቷን ብታሳውቅም በድብቅ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ ትሰጣለች ሲሉ ከከሰሱ በኋላ ነው። አምባሳደር ብሪጌቲ በታህሳስ ወር ላይ በኬፕ ታውን የባህር ሃይል ጣቢያ ላይ በሩስያ መርከብ ላይ እንደተጫኑ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት እርግጠኛ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ራማፎሳ የቀረበዉን የአሜሪካ ክስ ለመመርመር ተስማምተዋል ነገር ግን ውንጀላውን የሚያረጋግጥ ተጨባጭ ማስረጃ የለም ሲሉ አክለዋል።
[ዳጉ ጆርናል]

በቢሾፍቱ ከተማ ባለ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አራት ፖሊሶች ተገደሉ!
ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ገደማ ላይ በምትገኘው የቢሾፍቱ ከተማ “ማንነታቸው ያልታወቁ” ታጣቂዎች ትላንት እሁድ ግንቦት 6፤ 2015 ሌሊት በፖሊስ ጣቢያ ላይ በከፈቱት ጥቃት፤ አራት የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ተገደሉ። በጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት አንድ የፖሊስ አባል፤ አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፖሊስ ሆስፒታል ተወስዶ በህክምና ላይ መሆኑን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ገልጸዋል።
በቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስር በሚገኘው የክፍለ ከተማ ሶስት ፖሊስ ጽህፈት ቤት ላይ ታጣቂዎች ተኩስ የከፈቱት፤ ሌሊት ስድስት ሰዓት ገደማ ላይ መሆኑን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል። በከተማዋ መግቢያ ላይ “ሰንሻይን” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው በዚሁ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች፤ “ማንነታቸው የማይታወቅ” መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በዚሁ አካባቢ የሚኖሩ አንድ የዓይን እማኝ፤ በትላትናው ዕለት እኩለ ለሊት ገደማ በታጣቂዎቹ እና በፖሊስ አባላቱ መካከል “ከፍተኛ ድምጽ” ያለው የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ገልጸዋል። የተኩስ ልውውጡ ለአንድ ሰዓት ገደማ ያህል የቆየ እንደነበርም ተናግረዋል። ሌላው የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው፤ በፖሊስ ጣቢያው ፊት ለፊት በሚገኘው “ያቱ ሆቴል” ተረኛ የነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ላይ ጭምር ተኩስ ተከፍቶባቸው ነበር ብለዋል።
[Ethiopia Insider]

የመሬት ሊዝ ጨረታ ከአራት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጣ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአራት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ አወጣ ። ለጨረታ የቀረቡት ይዞታዎች መነሻ ዋጋ ከፍተኛው 2,213 ብር መሆኑ ታውቋል።የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓም ይፋ እንዳደረገው፣ በከተማዋ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች 297 ይዞታዎችን ለተጠቃሚዎች በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ ውጥቷል።
በሊዝ ጨረታ እንዲተላለፉ የተዘጋጁት 297 ይዞታዎች አጠቃላይ ካሬ ሜትር 143 ሺህ (14 ነጥብ 3 ሄክታር) ሲሆኑ፣ ይዞታዎቹ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው ብሏል።ለጨረታ ከሚቀርቡ ቦታዎች መካከልም ከዚህ ቀደም በምደባና በጨረታ ወስደው ያላለሙና እርምጃ የተወሰዳባቸው፣ በተለያዩ ጊዜያት በህገ ወጥ መንገድ የተወረሩና ወደ መሬት ባንክ የገቡ መሬቶች እንደሚገኙበት አስታውቋል።
ለጨረታ የቀረቡት ይዞታዎች ዝቅተኛው የጨረታ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር 960.21ብር ሲሆን፣ ከፍተኛ የተባለው መነሻ ዋጋ 2,213. 25 ብር መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ከግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ከግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መሳተፍ እንደሚችሉ ገልጿል።
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ይዞታ የተቀመጠውን መነሻ ዋጋ መሠረት በማድረግ ከአጠቃላይ ዋጋው 20 በመቶውን ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።
በዚህ ጨረታ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ግለሰቦች ፣ የንግድ ማኅበራት ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆኖ መወዳደር እንደሚቻል አመልክቷል።ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክፍለ ከተማ አዳራሽ እንደሚከፈት አስታወቋል።
[Reporter]

Are you the one?
👉 Learning Management System Developers
👉 Tech Startups & Incubators
👉 Digital Solution Providers
👉 Music Streaming Service Providers
👉 Coding Learning Centers
👉 Digital Library Service Providers
👉 Social Media Training Centers
👉 Student Tutorial Service Providers
👉 Professional Toastmaster's Clubs
👉 Student Club Association
👉 Online Education Service Providers
👉 Digital Theology Service Platforms
👉 Distance Education Learning Centers
👉 Short-term Training Service Institutes
When Yes:
Don't miss a chance to exhibit at the
Edition
5th
Event
Back to School Africa
Festival, 2023.
When
May 19 - 21/2023
Dates
Friday, Saturday, & Sunday
Duration
9am - 7pm
Visit event website👇!
www.backtoschoolafrica.com
Follow us on👇
Facebook and LinkedIn
Contact us
☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
With Support of
FDRE Ministry of Education
Sponsors
Oracle Academy
Study in Japan
BUKU Digital Platform
DSTV Ethiopia

መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።
ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ
👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah
👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
tiktok.com/@u0917040506_0912718883

👍1
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️
በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።
ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ
✅ ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️
✅ የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ
✅ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦
🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።
ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።
በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።
✅ አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!
For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj
For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
#Nedaj #nedajapp

ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር ፣
ላንጋኖ ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች
✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን
✔️ ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን
✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር
✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን
✔️ ዘመናዊ ኪችኖች
✔️ የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣
♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣
♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን
♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን
♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣
♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡
🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ
በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511
ይደውሉልን,ይጎበኙን!
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት

ከደቡብ ሱዳን የሚመጡ ታጣቂዎች በጋምቤላ በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ የሚፈፅሙት ዝርፊያ መቀጠሉ ተሰምቷል፡፡
ከሰሞኑን በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የዘረፏቸውን ከ 1 መቶ በላይ ከብቶች ማስመለሱን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡ድንበር ተሸግረው የመጡ የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የዘረፏቸውን ከ 1መቶ በላይ ከብቶች ማስመለስ የተቻለው ከታጣቂዎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ነው፡፡
ከታጣቂዎች ጋር በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከስድስት ያላነሱ ከብቶች ሲገደሉ ሌሎቹን በማስጣል ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ መደረጉን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ም/ ሃላፊ አቶ ኦቶው ኦኮት ለ ኢትዮ ኤፍኤም አስታውቀዋል፡፡ከደብቡ ሱዳን የሚነሱት ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም ወደ ክልሉ የድንበር ወረዳዎች በመግባት ህፃናትን ጨምሮ፤ ከብቶችን በመዝረፍ እና ጥቃት በማድረስ ህገወጥ ድርጊቶችን በተደጋጋሚ ይፈፅማሉ ብለዋል፡፡
በሌላ ዜና በክልሉ ባለፉት ቀናት ከህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከ 30 በላይ ክላሽኮፕ መሳሪያ መያዙንም አቶ ኦኮት ተናግረዋል።
[Ethio FM]

በጦርነት እና ግጭቶች ምክንያት ንብረት የወደመባቸው ተቋማት ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ እና የባንክ ብድር ክፍያ እንዲራዘም ቢወሰንም ተግባራዊ ሊሆን እንዳልቻለ ተገለጸ፡፡
ባለፉት ጥቂት አመታት አገራችን ውስጥ በነበረው ተከታታይ ጦርነት እና ግጭቶች ምክንያት ንብረት የወደመባቸው ተቋማት መልሶ ለመቋቋም የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ በሚንስቴሮች ምክር ቤት ቢወሰንም እስካሁን ተግባራዊ አለመደረጉን የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን ገልጸዋል፡፡
የሚንስቴሮች ምክር ቤት በ89 ኛው ጉባኤው ተቋማቱ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ከመወሰኑ በተጨማሪም ከባንክ የወሰዱትን ገንዘብ የሚከፍሉበት ጊዜ እንዲራዘምላቸው እንዲሁም የግብር ቅነሳ እንዲደረግላቸው ውሳኔ እንዳሳለፈ አስታውሰዉ ዉሳኔዉ አለመተግበሩ ግን ተቋማቱ ዘርፈ ብዙ ለሆኑ ችግሮች ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡
እነዚህ አምራች ተቋማት ከፍተኛ ቁጥር ላላቸው ዜጎች የስራ እድል የፈጠሩ እንደመሆኑ መጠን መሰል በህግ የተፈቀደላቸውን አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸው ከስራው እንዲወጡ ከማድረጉ በተጨማሪም ሌሎች የውጪ ባለሃብቶች ወደ አገር ውስጥ ገብተው የመስራት ፍላጎት እዳይኖራቸው ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡አያይዘውም የሚንስቴሮች ምክር ቤት ውሳኔ ወደ ገንዘብ ሚንስቴር፣ ቀጥሎም ወደ ባንኮች የወረደ ቢሆንም ተግባራዊ ሊያደርጉ አለመቻላቸውን አስታውቀዋል፡፡
[Ahadu]

ሼዶችን እና አረከበ ሱቆችን የመንጠቅ ስራ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለረጅም ዓመታት በግለሰቦች ተይዘው የነበሩ ሼዶች እና በተለምዶ አረከበ ሱቆች የሚባሉትን ተለጣፊ ሱቆች ለ3ተኛ ወገን አሳልፈው የሸጡትን እና ውጤታማ ያለሆኑትን በመንጠቅ ለሌሎች የስራ እድል እየፈጠረበት መሆኑን ተሰምቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ ማስፋፍያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰብሃዲን ሱልጣን ለጣብያው እንደገለፁት ከ2ሺህ በላይ ሼደች መንጠቁን ገልፀው በፍርድ ቤት ያሉ ኬዞችንም በመርታት የማጥራት ስራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
አዲስ መመሪያ ወርዶ ወደ ስራ መገባቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ የመንጠቅና ወደ መንግስት የማስገባት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ለ3ተኛ ወገን የሸጠውን አካል በመንጠቅ ለሚመለከተው አካል የማስተላለፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በመዲናዋ አዲስ አበባ ለስራ አጥ ወጣቶች ተላልፈው ረጅም ግዜ በስራ ላይ ከሚገኙት የመስሪያ ቦታዎች በተለምዶ የአርከበ ሱቆች የሚባሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ተለጣፊ ሱቁ ወይም በተለምዶ አርከበ ሱቅ የሚባለው በ1997 እንዲሁም ከዛ በፊት በሊዝ ለወጣቶች ተላልፎ የተሰጠ ቢሆንም አሁንም ድረስ ሳይሸጋገሩ መቆየታቸው ተነግሯል፡፡

ፍሉሃ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች ከተማ አስተዳደሩ ቃል የገባልንን ምትክ ቤት ሳይሰጠን ከቦታዉ እንድንነሳ በህግ አካላት እየተገደድን ነዉ ሲሉ ቅሬታቸዉን ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የቀበሌ ቤትና ህጋዊ የግል ይዞታ ለነበራቸው በፍልውሃ አካባቢ ለነበሩ የልማት ተነሺዎች በሙሉ ቃል የተገባላቸውን መኖሪያ ቤት አስረክቤያለሁ ሲል አስታውቋል፡፡በፍልውሃ አካባቢ ኑሯቸውን በሸራ መጠለያ ውስጥ ያደረጉ የልማት ተነሺዎች ቃል የተገባልን የመኖሪያ ቤት ድጋፍ አልተፈጸመልንም ብለው ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ለረጅም አመታት በሸራ መጠለያ ውስጥ ኑሯችንን ስንመራ ነበር ነገር ግን ምንም አይነት ምትክ ቦታ ሳይሰጠን በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ከቦታዉ ላይ እንድንነሳ ተገደናል ሲሉ ለአሃዱ እንዲህ ቅሬታቸዉን አሰምተዋል፡፡ አሃዱም በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ፕሬስ ሴክሬተሪ አቶ በረከት ታከለን አነጋግሯል፡፡አቶ በረከት በምላሻቸውም በፍልውሃ አካባቢ የሚገኙ የግል ይዞታ መሬት ለነበራቸው የልማት ተነሺዎች 1.1 ቢሊየን ብር ካሳ መከፈሉንና 5.6 ሄክታር ተለዋጭ መሬት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
በቀበሌ ቤት ይኖሩ ለነበሩ ከ400 በላይ ዜጎች ደግሞ ተለዋጭ የቀበሌ ቤት አስረክበናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የቀበሌ ቤት ወይም የግል ይዞታ ለነበራቸው ዜጎች ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ ምላሽ መሰጠቱን ገልጸው አሁን እየተነሱ ያሉ ቅሬታዎች ግን የቀበሌ ቤት ሳይኖራቸው ሸራ ወጥረው ኑሯቸውን ይመሩ በነበሩ ዜጎች ነው ብለዋል፡፡በመሆኑም ለእነዚህ ዜጎች በከተማ አስተዳደሩ የተዘጋጀ ምንም አይነት ተለዋጭ ቤት እንደሌለም አክለው ተናግረዋል፡፡ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቦታዉ ላይ ተጠልለዉ ሲኖሩ 30 እና 40 አመታት እንዳለፋቸዉ ገልጸዉ ካለባቸዉ የኑሮ ጫና እና የቤተሰብ ቁጥር አኳያ የትኛዉን ቤት ተከራይተዉ ለመኖር አቅም እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
አካባቢዉ ለፈርስ ሲል የከተማ አስተዳደሩ የደሃ ደሃ ቤት ለእናንተም ይሰጣችኃል ብሏቸው እንደነበር ጠቅሰዉ አሁን ይህ ቃል የተገባዉ ነገር ለአንዳንድ ሰዎች ተመርጦ ሲሰጥ ተመልክተናል ሲሉ ጣቢያችን ድረስ በአካል መጥተዉ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ቀበሌ ቤት ወይም የግል ይዞታ ኖሯቸው ምንም አይነት ተለዋጭ ቦታ አላገኘንም ብለው ቅሬታ ለሚያነሱ የልማት ተነሺዎች ግን ቅሬታቸውን ለማስተናገድ ዝግጁ ነዉ ሲሉ አቶ በረከት ተናግረዋል፡፡