YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
ምርጫ ቦርድ የሕወሓትን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ይነሣልኝ ጥያቄ ውድቅ አደረገ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው ይነሣልኝ ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ውድቅ ያደረገበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
1
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር የኢትዮጵያው "ቦርከና" ጋዜጣ "በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ውጥረት እየተፈጠረ ይኾን?" በማለት ያተመውን ሃተታ "በሐሰትና ግምታዊ ድምዳሜ የተሞላ" በማለት ተችቷል።

ሚንስቴሩ በመግለጫው፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በቅርቡ ስለ ሱዳኑ ግጭት በሰጡት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያን ጎሸም ያደረጉ አስመስሎ አቅርቧል በማለት ወቅሷል። ጋዜጣው "ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሥመራ መሄድ ፈልገው፣ የኤርትራ መንግሥት ሁለት ጊዜ ፍቃድ ነፍጓቸዋል" እንዲኹም "ኤርትራ ለአማራ ፋኖዎች ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠቷ የዐቢይ ካድሬዎች ኢሳያስን እየተቹ ነው" በማለት የጻፋቸው ነገሮች "ሐሰት" መኾናቸውንም ሚንስቴሩ ገልጧል። ሚንስቴሩ፣ ኤርትራ አዲስ ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገች እንደኾነ ጋዜጣው ያሰራጨውን ወሬም "የተሳሳተ" በማለት አስተባብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአደጋ ስራ ላይ ህይወታቸዉን ላጡ ሰራተኞቹ እዉቅና ሰጠ!

የአዲስአበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአደጋ መከላከል ወቅት አደጋ አጋጥሟቸዉ ህይወታቸዉን ላጡ የቀድሞ ሰራተኞቹ እዉቅና ሰጥቷል።

በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ስነስርዓት ከ 1981 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰቱ አደጋዎች ህይወታቸዉን ላጡ የቀድሞ ሰራተኞች ቤተሰቦች የሜዳሊያ ፣ የእዉቅና ሰርተፍኬት እና የ 20 ሺህ ብር ቦንድ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

ኮሚሽኑ ለቀድሞ 8 ሰራተኞቹ ነዉ እዉቅናዉን በዛሬው እለት የሰጠዉ። ሰራተኞቹ በእሳት አደጋ ፣ ከወንዝ ሰዎችን ለማዉጣት ባደረጉት ጥረት በተበከለ ዉሃ በመመረዛቸዉ ፣ በመኪና አደጋ እና በአደጋ መከላከል ወቅት በተለያዩ ጉዳቶች ህይወታቸዉን ያጡ ናቸዉ። ኮሚሽኑ ለሰራተኞች ቤተሰቦች እዉቅናዉን ሰጥቷል።

በነገዉ እለትም በአለማቀፍ ደረጃ ለ 24ኛ በአዲስአበባ ደረጃ ለ 2ኛ ግዚ በሚያከብረዉ የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ቀንን "የሚጠብቁንን እናክብር በሚል ቃል" ነዉ።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
1
የአርቲስት ሒሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ሰኞ ይፈጸማል!

የአርቲስት ሒሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር ከነገ በስቲያ ጉለሌ በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር እንደሚፈጸም የቀብር ስነ ስርዓት አስፈጻሚ ኮሚቴው ገለጸ።

ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ፣ የሒሩት በቀለ አስከሬን የፊታችን ሰኞ ሻላ መናፈሻ ጀርባ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ሽኝት ከተደረገለት በኋላ ወደ ወዳጅነት አደባባይ እንደሚያመራ ገልጿል።

በወዳጅነት አደባባይ በሚኖረው መርሐ-ግብር በመሰረተ ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን አማካኝነት የፀሎት ስነ ስርዓት፣የአበባ ማስቀመጥና የታዋቂ ሰዎች ንግግር እንደሚደረግ ኢዜአ ዘግቧል።

በመጨረሻም፣ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጉለሌ በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸም ኮሚቴው አስታውቋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የመንግስት መ/ቤቶች የስራ ሰዓትን ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም እየተሰራ ነው ተባለ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግስት የስራ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበትን ሰዓት ከ8 ሰዓት ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡መ/ቤቶቹ አገልግሎታቸውን እስከ ምሽት ድረስ እንዲሰጡ የማድረጉ ተግባር የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴም ያነቃቃል ተብሏል፡፡የከተማ አስተዳደሩ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ባካሄዱት የጋራ ውይይት ላይ ይፋ የተደረገው እቅድ እንደሚያመለክተው፤ በከተማዋ የሚታየውን የተገልጋዮችን ችግርና መጉላላት ለመቅረፍ የሚቻልበት መንገድ እየተፈለገ ነው፡፡

የመንግስት መ/ቤቶች ለተገልጋዮች በሚሰጡት አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እየቀረቡ መሆኑን የሚጠቁመው ዕቅዱ፤ ይህን ቅሬታና ችግር ለመፍታት የአገልግሎት ሰዓቱን ወደ 16 ሰዓት ማራዘም እንደ አንድ መፍትሄ መወሰዱንና ይህም ለመተግበር እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።በዚሁ የመንግስት ስራን ወደ 16 ሰዓት ለማራዘም በተያዘው እቅድ ሰራተኞች በፈረቃ የሚሰሩበት ሁኔታ ሊመቻች እንደሚችልና አሰራሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞችን አዋጅ የማይጥስ እንደሚሆንም ተነግሯል፡፡ የከተማው አስተዳደር የመ/ቤቶቹን የአገልግሎት ሰዓት የማራዘም ፈቃዱን ተግባራዊ ለማድረግ ጥናት እያካሄደ መሆኑንና በመጪው በጀት ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

Via Addis Admass
@YeneTube @FikerAssefa
የሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ!

የሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሙዚቀኛው አድናቂዎች እና ዘመድ ወዳጆቹ ተገኝተዋል።

ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው ኃይሉ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ትምህርቱን 'ሜጀር ክላርኔት' በማድረግ የተመረቀ ሲሆን የአልቶ ሳክስፎን እና ክራር ተጨዋችም ነበር።በአስደናቂ ክላርኔት ጨዋታው የሚታወቀው ዳዊት ፍሬው በሙዚቃ ትምህርት ቤት ቆይታው፣ የታላላቅ ሙዚቃ አቀናባሪዎች /ኮምፖዘሮችን/ የክላርኔት ሥራዎች ተጫውቷል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
Are you the one?

👉  Learning Management System Developers
👉  Tech Startups & Incubators
👉  Digital Solution Providers
👉  Music Streaming Service Providers
👉  Coding Learning Centers
👉  Digital Library Service Providers
👉  Social Media Training Centers
👉  Student Tutorial Service Providers
👉  Professional Toastmaster's Clubs
👉  Student Club Association
👉  Online Education Service Providers
👉  Digital Theology Service Platforms
👉  Distance Education Learning Centers
👉  Short-term Training Service Institutes

When Yes:
Don't miss a chance to exhibit at the

Edition
5th

Event
Back to School Africa
Festival, 2023.

When
May 19 - 21/2023

Dates
Friday, Saturday, & Sunday

Duration
9am - 7pm

Visit event website👇!  
www.backtoschoolafrica.com 

Follow us on👇
Facebook and LinkedIn

Contact us
 
    ☎️ :   +251 974 08 2036
              +251 974 08 2037

With Support of
FDRE Ministry of Education

     Sponsors
Oracle Academy
Study in Japan
BUKU Digital Platform
DSTV Ethiopia
👍1
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።

የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

tiktok.com/@u0917040506_0912718883
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ

ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️

የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ

ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦

🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን  ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።

ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።

በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።

አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj


For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp
😁1
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊውን ለመለየት ሁለተኛ ዙር ድምጽ ሊሰጥ ይችላል!

በተጠባቂው የቱርክ ምርጫ ሁለቱም ዕጩዎች አሸናፊ የሚያደርጋቸውን የመራጮች ድምጽ እንዳገኙ እየገለጹ ቢሆንም፣ አሸናፊውን ለመለየት ወደ ሁለተኛ ዙር ድምጽ መስጠት ሊያመሩ ይችላሉ።ለ20 ዓመታት በሥልጣን የቆዩት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን በፓርቲያቸው ዋና ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ተጨማሪ አምስት ዓመት ለመምራት የሚያስችላቸው ድምጽ እንዳገኙ እርግጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።ተቀናቃኛቸው ከማል ኪሊዳሮግሉ ምርጫውን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ምልክቶችም ታይተው ነበር።

ሆኖም ግን የመጀመሪያው ዙር ሲጠናቀቅ ያልተቆጠሩ ድምጾች በመገኘታቸው ከኤርዶዋን በታች ሆነዋል።የኤርዶዋን ጥምረት በምክር ቤት ከፍተኛውን መቀመጫ ሊያገኝም ይችላል።የቱርክ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለወራት ያህል ባደረጉት ንቅናቄ የኤርዶዋን የሥልጣን ዘመን እንዲያከትም ሲጥሩ ቆይተዋል።እአአ በ2016 የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከተካሄደ በኋላ ኤርዶዋን ሥልጣናቸውን እያራዘሙ እዚህ ደርሰዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ቲማቲም በ2 ሳምንት ውስጥ የ40 ብር የዋጋ ጭማሪ አሳየ!

በአዲስ አበባ ከተማ በአትክልትና ፍራፍሬ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እየታየ ስለመሆኑ ቅሬታቸዉን ለብስራት ሬዲዮ ያቀረቡ ሸማቾች ገልጸዋል፡፡

ሽንኩርት በኪሎ 50 ብር ቲማቲም ከ 80 እስከ 90 ብር እየተሸጠ መሆኑን የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በተለይ ቲማቲም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ  የ40 ብር ጭማሪ ማሳየቱን  እንዳስደነገጣቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።በአሁኑ ሰአት ገቢያቸው እና ኑሮው እየተመጣጠነ አለመሆኑ እና የሚፈልጉትን ሸምተው መኖር አለመቻላቸው ኑሮአቸውን እንዳከበደውም አክለዋል።

ሬዲዮ ጣቢያው በተለያዩ የገበያ ስፍራዎች ተዘዋውሮ ለማየት እንደሞከረው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ከመኖሩ ባሻገር የቲማቲም አቅርቦቱ ከእለት እለት እየቀነሰ መሆኑን ሃሳባቸውን ከሰጡ ነጋዴዎች ለመገንዘብ ተችሏል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
አሁን ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ስጋት ምክንያት ለቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ለወራት ያልተከፈለ ደሞዝ በወቅቱ መክፈል እንዳልተቻለ ተገለጸ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ ለሚገኙ የቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል የጦር ቁስለኞች ለወራት ያልተከፈላቸውን ደሞዝ ማድረስ እንዳልተቻለ የገለጹት በቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል የጤና መምሪያ ሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሽታውዓለም አሰጋ ናቸው፡፡

ከባህር ዳር እስከ አዲስ አበባ የትራንስፖርት በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የፋይናንስ ባለሙያዎችን ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ በመላክ ለአባላቱ ደሞዝ መክፈል አልተቻለም ብለዋል፡፡
ለአንዳንድ አባላት በመተማመኛ እና በሂሳብ ቁጥራቸው ለወራት ያልገባላቸውን ደሞዝ መክፈል መቻሉን ገልጸው ተንቀሳቅሰው የሂሳብ ደብተር መክፈት ላልቻሉ ቁስለኞች ግን የፋይናንስ አባላትን በአየር ትራንስፖርት ወደ አዲስ አበባ በመላክ ገንዘባቸውን ለማድረስ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ቁስለኞቹ በአዲስ አበባ የተለያዩ ካምፖች በቂ የህክምና አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውንም ጠቅሰው ነገር ግን ለቀላል የህክምና አገልግሎቶች ተደጋጋሚ ቀጠሮ የመስጠት ሁኔታ እንደሚስተዋልም ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩ እየተቀረፈ እንዳለም አንስተዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
ቻይና ሲሰልለኝ ያዝኩት ያለችውን አሜሪካዊ በእድሜ ልክ እስራት ቀጣች!

ቻይና ሲሰልለኝ አግኝቸዋለሁ ያለችውን የ78 ዓመት አሜሪካዊ በእድሜ ልክ እስራት ቀጣች፡፡ቻይና ኑሮውን በቋሚነት በሆንግ ኮንግ ያደረገውን ጆን ሺንግ ዋን ልዩንግ እድሜ ይፍታህ የፈረደችበት በስለላ ወንጀል ክስ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሰውዬው ከሁለት ዓመት በፊት በቻይና የጸረ-ስለላ ተቋም በቁጥጥር ስር አውሎት እንደነበር እና ፍርድ ቤቱ በስለላ ክስ ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው እድሜ ልክ እስራት እንደፈረደበት አስታውቋል፡፡

የሰውዬው እስር በሁለቱ ኃያላን አገራት መካከል የተጀመረውን የንግድ ጦርነት እና ፍጥጫ የበለጠ ሊያሻክረው ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩም ተመላክቷል፡፡

ሁለቱ አገራት በታይዋን ጉዳይ በደቡብ ቻይና ባህር፣ በኮሮና ወረርሽኝ መነሻ እንዲሁም አሜሪካ በአየር ክልሏ አግኝታ ባፈነዳቻቸው የቻይና ሰው አልባ ፊኛዎች ምክንያት ከፍተኛ መካረር ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ!

የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርአት ዛሬ ተፈጽሟል። የድምጻዊቷ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል።

ድምፃዊቷ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በዓለማዊ ሙዚቃና በመንፈሳዊ መዝሙሮች አገሯንና ህዝቧን ማገልገሏ በህይወት ታሪኳ ላይ ተገልጿል።

ድምጻዊቷ የሰባት ልጆች እናት የአስር ልጆች አያትና የሰባት ልጆች ቅድመ አያት እንደነበረች ኢፕድ ዘግቧል።ድምፃዊቷ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ባሳለፍነው ግንቦት አራት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ አይዘነጋም።

@YeneTube @FikerAssefa