ሳውዲ አረቢያ በጦርነት ውስጥ ላለችው ሱዳን የሰብአዊ እርዳታ ማቀላጠፊያ 100 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባች፡፡
የሳውዲው ንጉስ ሳልማን እና አልጋ ወራሻቸው ሞሐመድ ቢን ሳማን ለሱዳን የ100 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንዲሰጥ ማዘዛቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡የአገሪቱ ሕዝብም የበኩሉን እንዲለግስ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ማዕከላት እንደሚከፈቱ ታውቋል፡፡
ሳውዲ አረቢያ ለሱዳን ሰብአዊ እርዳታዎች እና መድሐኒቶችን እንደምታቀርብ ተጠቅሷል፡፡እርዳታውን በአፋጣኝ ለማቅረብ መታቀዱ ተሰምቷል፡፡ከ3 ሳምንታት በላይ ያስቆጠረው የሱዳኑ የእርስ በርስ ጦርነት ከእለት ወደ እለት ሰብአዊ ቀውሱን እያከፋው መምጣቱ ይነገራል፡፡
✍Sheger
@YeneTube @FikerAssefa

በክልሎች ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ በኤሌክትሮኒክ ግብይት እንደሚፈፀም የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ገለፀ!
በክልሎች ከዛሬ ግንቦት አንድ ጀምሮ ነዳጅ በኤሌክትሮኒክ ግብይት እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ጀምሮ ነዳጅ በኤሌክትሮኒክ ግብይት እንዲፈፀም በማድረግ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች በሌሎች ክልሎች እንዳይከሰቱ የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅት እንዲያደርጉ መደረጉን በባለስልጣኑ የነዳጅ ስርጭት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ዴሬሳ ኮቱ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ነዳጅን በኤሌክትሮኒክ መገበያየት ሲጀመር የነበረው ሰልፍ አሁን መስተካከሉንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የነዳጅ እጥረት ማጋጠም፣ የመተግበሪያ አጠቃቀም እውቀት ማነስ ፣ ነዳጅን በኤሌክትሮኒክ የግብይት ስርዓት የመግዛት ፍላጎት ማጣት አሁንም ያልተቀረፉ ችግሮች እንደሆኑም አቶ ዴሬሳ ጠቁመዋል። ነዳጅ በሁሉም ማደያዎች እንዲኖር የነዳጅ አቅራቢ ድርጅትም ከክልሎች ጋር ተቀናጅቶ ያለውን ችግር ለመፍታት እንደተዘጋጁም ተጠቁሟል። በአዲስ አበባ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት መነሻ በማድረግ የነዳጅ ግብይቱ በኤሌክትሮኒክ ግብይት የተለያዩ አማራጮች እና በኩፖን ጭምር እንደሚከናወን አቶ ዴሬሳ ገልጸዋል።
በክልሎች ግን በኩፖን እና በካርድ የነዳጅ ግብይት እንደማይከናወን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ከኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይቱ ጋር በተያያዘ በክልሎች ከኔትወርክ ጋር ለሚስተዋሉ ችግሮች ከወዲሁ ጊዜያዊ መፍትሄ እንዲሰጥ ለኢትዮ-ቴሌኮም ጥያቄ ማቅረቡን የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን አስታውቋል።
[EBC]

በቤንዚንና ናፍጣ የሚሠሩ የውሃ ፓምፖች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተወስኗል!
በናፍጣ እና ቤንዚን የሚሠሩ የውሃ ፓምፖች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መወሰኑን እና ይልቁንም ሶላር ኢነርጂ እና ሌሎች ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አማራጮች ላይ ትኩረት መደረጉን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ።የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ሚኒስቴሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑንና በዚህም ውጤታማ የሚባሉ ክንውኖች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
[EPA]

ሩሲያ የድል ቀኗን እያከበረች ነው!
ሩሲያ የቀድሞ ሶቪየት ህብረት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ናዚ ጀርመንን ያሸነፈችበትን 78ኛ ዓመት የድል ቀን በሞስኮ እያከበረች ነው።ፕሬዝዳንት ቭላዲሜር ፑቲን በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ዓለም በወሳኝ የለውጥ ጊዜ ላይ መሆኗን ጠቅሰው ምዕራባዊያን በሩሲያ ላይ በይፋ ጦርነት እንደከፈቱባት ገልጸዋል።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ያለችው ጦርነት የጸረ ናዚዝም እሳቤ እና ሉዓላዊነትን የማስከበር ትግል መሆኑንም በንግግራቸው አመልክተዋል።በሥነ ሥርዓቱ ላይ በእግረኛ ወታደሮች፣ ታንኮች እና ሚሳኤሎች የታጀበ የወታደራዊ ሰልፍ ትርዒት ተካሂዷል፡፡
በምዕራብ ግንባር የናዚ ጦር ሶቪየት ህብረትን በወረረበት ወቅት ከየሶቭየቱ ቀዩ ጦር ከባድ ምት ደርሶበት የተፍረከረከው እና ከ91 ሺሕ በላይ ተዋጊ የተማረከበት ስታንግራድ በተባለ ቦታ ነበር፡፡የናዚ ሽንፈት የመጀመሪያው መጨረሻ የተባለለት ይህ ጦርነት ለሶቭየቶች ጣፋጭ ድል በመሆኑ ሩሲያ በየዓመቱ በድምቀት ትዘክረዋለች፡፡

የሱዳን ተፈናቃዮች ቁጥር ከ700 000 በለጠ!
የሱዳን መከላከያ ሠራዊትና የሐገሪቱ ፈጥኖ ደራሽ ጦር የገጠሙት ዉጊያ ከቤት ንብረቱ ያፈናቀለዉ ሕዝብ ቁጥር ከ700 ሺሕ በለጠ።የተፋላሚ ኃይላት መሪዎች ካለፈዉ ሳምንት ወዲሕ ዉጊያዉን ጋብ በማድረጋቸዉ ከቤት ንብረቱ የሚፈናቀለዉ ህዝብ ቁጥር ባንድ ሳምንት ዉስጥ በእጥፍ ጨምሯል።
የተባበሩት መንግስታት የፍልሰት ጉዳይ ድርጅት (IOM) እንዳስታወቀዉ እስካለፈዉ ሳምንት ማክሰኞ ድረስ የተፈናቃዩ ቁጥር 340 ሺሕ ነበር።ዉጊያ በተባባሰበት ወቅት መዉጪያ አጥቶ የነበረዉ ሕዝብ ካለፈዉ ሳምንት ወዲሕ በብዛት ከያለበት ሸሽቷል።ዉጊያዉ ዛሬም አልቆመም።ተፋላሚ ኃይላት በዘላቂነት ተኩስ እንዲያቆሙ ለማግባባት በሳዑዲ አረቢያና በዩናይትድ ስቴትስ ሸምጋይነት የተደረገዉ ድርድር እስካሁን ያመጣዉ ዉጤት የለም።ጂዳ-ሳዑዲ አረቢያ ላይ በተያዘዉ ድርድር የሱዳን መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል ቡርሐንና የፈጥኖ ደራሹ ጦር አዛዥ ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ ተወካዮቻቸዉን ልከዋል።
የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የጠቀሳቸዉ አንድ የሳዑዲ አረቢያ ዲፕሎማት እንዳሉት ግን ሁለቱም ወገኖች በጦርነቱ እናሽንፋለን ከሚል ስሜትና ዕምነት ገና አልተላቀቁም።ሱዳናዊዉ የፖለቲካ ተንታኝ ኹሉድ ኸይር በበኩላቸዉ ሁለቱ ጄኔራሎች ተወካዮቻቸዉን ወደ ጂዳ የላኩት ለየወገናቸዉ ድጋፍ ለማግኘት እንጂ ተኩስ ለማቆም አልመዉ አይደለም።የጄኔራል አል ቡርሐን ልዩ መልዕክተኛ ዳፋላሕ አል ሐጂ ዓሊ በበኩላቸዉ ድጋፍ ለማሰባሰብ የተለያዩ ሐገራትን እየጎበኙ ነዉ።ዓሊ ሰሞኑን ከአፍሪቃ ሕብረት፣ ከኢትዮጵያና ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረዋል።
[DW]

ተያዘች
2 ህፃናት በመግደል የተጠረጠረችው ነጋሴ ከበደ ጫካ ውስጥ ተያዘች
የ2 ህጻናት ልጆችን በቢላዋ አርዳ በማቃጠል ገላ የተሰወረችው ተጠርጣሪ ነጋሴ ቡራዬ ሳንሱሲ ጫካ ውሰጥ አሁን ተይዛለች።
@Yenetube @Fikerassefa

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ቀናት ይፋ አደረገ
*****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ 8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ 6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
አያይዘውም ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩ ሲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ አሳስበዋል።
በ2015 ዓ.ም 75ሺህ 100 የ8ኛ እንዲሁም 75ሺህ 78 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን እንደሚወስዱ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፑቲን፡ “የትኛውም የበላይነት አስተሳሰብ አስጸያፊ፣ ወንጀለኛ እና ገዳይ ነው ብለን እናምናለን። ነገር ግን የምዕራባውያን ልሂቃን አሁንም ልዩ ነን የሚለውን ሀሳብ አጥብቀው ቀጥለውበታል።"
"ምዕራባውያን ግጭቶችን እና መፈንቅለ መንግስትን ያስነሳሉ። የራሳቸውን አገዛዝ ለማስቀጠል ባህላዊ እሴቶችን ያጠፋሉ"።

የታንዛኒያው ድርድር እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ!
በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል በታንዛኒያ የተጀመረው የሰላም ድርድር እንደሚቀጥል፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አስታወቀ።የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ሓላፊ ኃይሉ አዱኛ፣ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋራ ያላቸውን ልዩነቶች በንግግር ለመፍታትና ድርድሩ ፍሬያማ እንዲኾን፣ መንግሥታቸው ቁርጥ አቋም እንዳለው ተናግረዋል።
የክልሉን የሰላም ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና ኅብረተሰቡ ተረጋግቶ ወደ መደበኛ ኑሮው እንዲመለስ፣ የሰላም ድርድሩ አስፈላጊ መኾኑን ገልጸዋል። ድርድሩ እንዲሳካም የተለያዩ አካላትን ትብብር ጠይቀዋል።ባለፈው ሳምንት፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል በታንዛኒያ የተካሔደው የመጀመሪያ ዙር የሰላም ድርድር፣ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ላይ ሳይደረስ መጠናቀቁ በመንግሥት በኩል ተገልጿል። ከስምምነት ላይ ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች ምን እንደኾኑና ቀጣይ ዙር ውይይትም መቼ እንደሚካሔድ፣ በሁለቱም አካላት የተገለጸ ዝርዝር የለም።
Via VoA

የማላዊ ፍርድ ቤት ተማሪዎች ጸጉራቸዉን ድሬድ ማድረግ እንዲችሉ ፈቀደ
በማላዊ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የትምህርት ባለስልጣናት በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ጸጉራቸዉን ድሬድ ያደረጉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ በ2016 እና 2010 ዓመት ወደ ህዝብ ትምህርት ቤት ለመግባት የተከለከሉ ሁለት የራስተፈሪያን ልጆች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ በዞምባ ከተማ ባስቻለዉ ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የሁለቱ ተማሪዎች ጉዳይ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካገኙ በኋላ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።በማላዊ የሚገኘው የራስተፈሪያን ማህበረሰብ እና የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጉዳዩን ለመፍታት የተካሄደው ውይይት ባለመሳካቱ የተራዘመ የህግ ክስ ቀርቦ ውሳኔው ሰኞ እለት ተላልፏል።
ዳኛ ንታባ ድሬድ ያደረጉ ህጻናት ትምህርት ቤት እንዳይማሩ መከልከል የመማር መብታቸውን መጣስ ነው ሲሉ ውሳኔ አስተላልፈዋል።"የትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የራስተፋሪያን ማህበረሰብ ልጆች ድሬድ አድርገዉ በክፍል ውስጥ እንዲገቡ ለመፍቀድ መግለጫ ማውጣት አለበት ይህንኑ የሚገልጽ መመሪያ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ማሳወቅ እንደሚኖርበት" ዳኛ ንታባ አዘዋል፡፡
ይህዉ ጉዳይ በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ የራስተፈሪያን ማህበረሰብ ስም በሶስት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አማካይነት ወደ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ችሏል፡፡
Via ዳጉ ጆርናል

ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልልን ጨምሮ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች እና አካባቢያዊ ምርጫን በ2016 ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱን ገለጸ !
የትግራይ ክልልን ጨምሮ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች እና አካባቢያዊ ምርጫን በ2016 ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።ቦርዱ የ2015 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተወሰኑ ክልሎች በሚገኙ አካባቢዎች 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አለመካሄዱን ገልጸዋል። ይህንኑ ምርጫ ለማካሄድ በ2015 ዝግጅት ለማድረግ ታቅዶ እንደነበርም ተናግረዋል።በሌላ በኩል የአካባቢ ምርጫ ለማካሄድ ቢታቀድም አለመሳካቱን ገልጸው እነዚህን ምርጫዎች በ2016 ለማካሄድ ቦርዱ ዕቅዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን ተናግረዋል።
ባለፉት ወራት ከፖለቲካ ፓርቲዎች አሠራር ጋር በተያያዘ አንዳንድ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያካሂዱ በተለያዩ አካላት መከልከላቸውን ቦርዱ ማረጋገጡን እና አንዳንድ የፓርቲ አመራሮች ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።ቦርዱ ለዚህ ችግር መፍትሔ ለመስጠት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢው መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ትዊተር የድምጽ እና ቪድዮ ጥሪ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ!
ትዊተር ኩባንያ ከጽሑፍ እና ፎቶ በተጨማሪ የድምፅ እና ቪድዮ ጥሪ ማድረግ የሚያስችል አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡የትዊተር ባለቤት ኤለን መስክ በትዊተር ገጹ እንዳስታወቀው “በቅርቡ ከማንኛውም ሰው ጋር በትዊተር አድራሻ የድምጽ እና ቪዲዮ መልዕክት መለዋወጥ የሚያስችል አገልግሎት በዚህ መድረክ ላይ እየመጣ ነው” ብሏል፡፡
አገልግሎቱ ሲጀመር ማንኛውም ሰው በየትኛውም ዓለም ከሚኖር ሰው ጋር ስልክ ቁጥሩን መስጠት ሳይጠበቅበት መነጋገር ይችላልም ነው የተባለው፡፡
በዚህም ትዊተር በሜታ ኩባንያ ባለቤትነት እንደተያዙት ዋትስአፕ፣ ሜሴንጀር እና ኢኒስታግራም የድምፅ፣ ጽሑፍ፣ ፎቶ እና ቪዲዮ መልዕክቶችን መለዋወጥ የሚያስችል አገልግሎት መስጠት ያስችለዋል፤ ልምድ ካካበቱት ከሜታ መተግበሪያዎች ጋርም ለመወዳደር ያስችለዋል ተብሏል፡፡ከዚህ በተጨማሪም መልዕክቶች እንዳይጠለፉ ከላኪ እስከ ተቀባይ የማመስጠር (end-to-end encryption) አገልግሎትም መስጠት እንደሚጀምር ባለቤቱ ኤለን መስክ በመልዕክቱ አስታውቋል፡፡

ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር ስምምነት ሳይደረስ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ተገለጸ!
ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ላይ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ባለሥልጣኑ ዛሬ ለግልና መንግስተዊ ላልሆኑ ትምህርት ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ደብዳቤ ከወላጆች ጋር ስምምነት ላይ ሳይደረስ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምንም ዓይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ የግል ትምህርት ተቋማት የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከወላጆች ጋር በነበረ ውይይት ስምምነት ላይ መድረስ ያልተቻሉባቸው መድረኮችን በአካል ተገኝቶ ማረጋገጡን አመልክቷል፡፡
የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከተማሪ ወላጅ ተወካዮች እና ከባለሥልጣኑ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጥ አቅጣጫ ብቻ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር ፣
ላንጋኖ ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች
✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን
✔️ ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን
✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር
✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን
✔️ ዘመናዊ ኪችኖች
✔️ የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣
♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣
♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን
♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን
♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣
♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡
🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ
በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511
ይደውሉልን,ይጎበኙን!
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት

👍1
Meri Geta Tibebu
👉አስደሳች ዜና ማየት ማመን ነው
መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሔ ስራይ
👉ለአስም (ለሳይነስ)
👉 ለአይነጥላ ለሰው እጅ ለገርጋሪ👇
እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች መቶ ተመርምሮ የለብወትን ችግር አውቆ መታከም ይችላሉ
እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል
👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።
ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ
👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah
👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️
በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።
ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ
✅ ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️
✅ የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ
✅ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦
🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።
ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።
በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።
✅ አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!
For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj
For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
#Nedaj #nedajapp

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል መኒ (MPESA) ፈቃድ አገኘ!
በኢትዮ ጵያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ዛሬ አንድ ዓመት የሞላው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል መኒ (MPESA) ፈቃድ ማግኘቱን አስታወቀ።
የሳፋሪኮም ኬንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ፒተር ንዴግዋ ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ ም ንጋት ላይ የተቋማቸውን ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ሪፖርት ሲያቀርቡ እንዳስታወቁት፣ በኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አንድ ዓመት የሞላው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የድጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ሞባይል መኒ ፈቃድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማግኘቱን አስታውቀወል። ወደሚቀጥሉት ሳምንታት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ጠቁመዋል።
Via Reporter