YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአማራ ክልል መንግስት “ጥቂት ሃይሎች” በመንግሥት የፀጥታ አካላት ላይ ትንኮሳ እየፈፀሙ ነው አለ!

የአማራ ክልል መንግስት ዛሪ ባወጣው መግለጫ በክልል “ጥቂት ኃይሎች” የክልሉ ህዝብ ፍላጎት ባልሆነበት ሁኔታ በመንግሥት የፀጥታ አካላት ላይ ትንኮሳ እያደረጉ ነው አለ።“የአማራ ክልልን እና ኢትዮጵያን ትርምስ ውስጥ ሊከቱ” ነው የተባሉት ኃይሎች እና የቀረበውን የሰላም አማራጭ ገፍተው መንግሥትን ደካማ ለማድረግና ለመገዳደር የሞከሩ ቡድኖች ላይ መንግስት “በተመረጠ ሁኔታ ሕግ የማስከበር ሥራ ላይ ይገኛል” ብሏል።

የህግ ማስከበር ዘመቻው “ችግር ባለባቸው ውስን አካባቢዎች” እንጂ በሙሉ ክልሉ የሚደረግ አይደለም ያለው የክልሉ መንግስት፣ “ጽንፈኛ የሆነው የማኅበራዊ ሚዲያ "አንቂ" ነኝ ባይ እንደሚለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ውስጥም አለመሆናችን መታወቅ አለበት” ሲል አፅንዖት ሰጥቷል።

በሌላ መልኩ እየተከናወነ የሚገኘው የሕግ ማስከበር ሥራ የአማራን ሕዝብ ትጥቅ ማስፈታት አይደለም ሲል በድጋሜ የገለፀው የአማራ ክልል አስተዳደር፣ የህግ ማስከበር ዘመቻው የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ነው ብሏል።በአማራ ክልል የፌደራል መንግስት መደበኛ ታጣቂ ያልሆኑ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት እንቅስቃሴ ከተጀመረ በኋላ የተከሰተው አለመረጋጋት፣ በቅርቡ ከደረሰው የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ በኋላ መባባሱን ነዋሪዎች እየገለፁ ይገኛሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
ምክር ቤቱ በሸገር ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ የሚገኘው የመሰጂዶች ፈረሳ በአሰቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ!

የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል "በሸገር ሲቲ" እየፈረሱ ያሉት መሰጂዶች በአሰቸኳይ እንዲያስቆም ለኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ መጻፉን አስታውቋል።በጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤ፤ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እየፈረሱ ያሉ መስጂዶች በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ ጠይቋል።

የፈረሱ መስጂዶች በሸገር ከተማ አስተዳደር በፍጥነት እንዲሰሩና ሕዝበ ሙስሊሙን አስተዳደሩ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በተፃፈው ደብዳቤ መሠረት:-

1.በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ዉንዴሳ ወረዳ ልዩ ሥፍራ ቀርሳ በቀን 14/07/15

2. በሸገር ከተማ ሰበታ ክፍለ ከተማ መጉላ ቶውፊቅ መስጂድ 19/08/15

3. በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አን ኢ ሳይት ሰላም መስጂድ በቀን 24/08/25

4. በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ በቀን 25/08/15 መፍረሳቸውና ጉዳዩ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ደብዳቤ መጻፉም ተገልጿል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ

ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️

የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ

ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦

🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን  ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።

ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።

በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።

አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj


For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
Meri Geta Tibebu
👉አስደሳች ዜና ማየት ማመን ነው

መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
   መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሔ ስራይ
👉ለአስም (ለሳይነስ)

👉 ለአይነጥላ ለሰው እጅ ለገርጋሪ👇

       እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች መቶ ተመርምሮ የለብወትን ችግር አውቆ መታከም ይችላሉ

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን  ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
    መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
👍21
ኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ስጋትነቱ ቢያበቃም አሁንም ጥንቃቄ ያሻል ሲል ጤና ሚኒስቴር አሳሰበ!

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆኑ ቢነሳም አሁንም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በሳርስ እና በኮቪድ-2 እንደሚያዙ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ በዚህ ሳቢያ በርካቶች ለህልፈት እንደሚዳረጉ ጠቅሶ፥ አዲስ የበሽታው ዝርያ ሊከሰት የሚችልበት ስጋት እንዳለም አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት በፈረንረጆቹ ጥር 30 ቀን 2020 ኮቪድ 19ኝን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት እንደሆነ መፈረጁን ተከትሎ ባለፉት ሶስት ዓመታት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት እንደሀገር የመንግስት፣ የአጋር፣ ባለድርሻ አካላትና የማህበረሰቡን አቅም በማስተባበር እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሶሪያ ወደ አረብ ሊግ አባልነቷ እንድትመለስ ተፈቀደላት!

ሶሪያ ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪው የአረብ አጋር የጋራ ማኅበር ወደ ሆነው አረብ ሊግ መልሳ እንድትቀላቀል ተፈቀደ።ተቃዋሚዎች ላይ በደረሰው ጭቆና ምክንያት ከአሥር ዓመት በፊት ነበር ከሊጉ የተባረረችው።ከተቃውሞው በኋላ አገሪቱ ወደለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ገብታ ቆየረታለች።ወደ ሊጉ መመለሷ ሶሪያ ከአረብ አገራት ጋር ያላት ግንኙነት እየተሻሻለ መሆኑ ማሳያ ነው ተብሏል።

ሊጉ በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ ጉባዔ የሚያካሂድ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንት ባሻር አል-አሳድ በጉባዔው ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ሶሪያ ወደ አረብ ሊግ መመለሷን ተችተዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ እንዳሉት፣ ሶሪያ ወደ ሊጉ ለመመለስ ብቁ ባትሆንም፣ አረብ ሊግ የሶሪያን ቀውስ ለመፍታት የሚያደርገውን የረዥም ጊዜ ጥረት አሜሪካ ትደግፋለች።

የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሎርድ አሕማድ በበኩላቸው “ዩኬ ከአሳድ አገዛዝ ጋር የሚደረግ ግንኙነትን በመቃወም ትቀጥላለች። አሳድ አሁንም ንጹህ ሶሪያውያንን እየገደለ፣ እያገተ እና እያሰቃየ ነው” ብለዋል።የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ የሊጉን ውሳኔ “ትልቅ ትኩረት” ሰጥቶ እንደሚመለከት ገልጾ “የአረብ አገራት ትብብርና ትስስር ያስፈልጋቸዋል” ብሏል።

ከአረብ ሊግ 22 አባል አገራት የ13ቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በካይሮ ባደረጉት ውይይት ተገኝተው ነው ውሳኔው የተላለፈው።የሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት መቆም እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። የሶሪያ የስደተኞች ቀውስ እና ስውር ዝውውር እንዲገታም አሳስበዋል።በሶሪያ የተባባሰው ድህነት እና ሥራ አጥነት ብዙዎች ወደ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እንዲገቡ አድርጓል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ የወረዳ አመራር ተገደሉ!

ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ሚያዚያ 28/2015 በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ ኡመር ለማ መገደላቸውን የአፋር ክልል የብፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አሳውቋል።

ኡመር "አሸባሪዎች በከፈቱት ተኩስ" ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፤ በኃላፊው ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ጽሕፈት ቤቱ ስለጥቃት አድራሾቹ ማንነት፣ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በሌሎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱና ስለተወሰደው እርምጃ በዝርዝር የገለጸው ነገር የለም።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ በጠራራ ፀሐይ ጅብ የአንድ ሕጻን ሕይወት መቅጠፉን ከወረዳው የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በቆሬ መንደር ሁለት ወንድማማች የሆኑ ሕጻናት ከእርሻ ማሳ ወደ ቤታቸው በሚመለሱበት ጊዜ ጅቡ ጥቃት ሊያደርስባቸው ሲሞክር ታላቅየው ሮጦ ማምለጥ ሲችል የአራት ዓመቱን ሕጻን ግን ጅቡ አንገቱ ላይ ስለነከሰው ብዙ ደም በመፍሰሱ ወድያውኑ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል ይላል ዘገባው። የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አክሎም ወላጆች ሕጻናት ልጆቻቸው ወደ ትምህርት ቤትም ሆነ ወደ ሌላ ቦታ ሲልኩ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከመጪው ዓመት ጀምሮ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት በአስገዳጅነት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት እንደሚተገበር ተገለፀ፡፡

ከሁለት ዓመታት በኋላ በ2017 ዓ.ም. በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡በዘንድሮዉ ዓመት በ74 የፌድራል ተቋማት ላይ እየተተገበረ ያለው የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ከቀጣይ አመት ጀምሮ በሁሉም የፌድራል ተቋማት ላይ በአስገዳጅነት እንደሚተገበር የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን አስታወቋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት 169 የፌዴራል ተቋማት የማኑዋል ግዥን አስቀርተው ሙሉ በሙሉ እንደሚተገበር እና የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓትን፣ በሲዳማ ክልል በማሳያነት በማስጀመር በቀጣይ በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልደአብ ደምሴ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

ወደፊት ወደ ዞንና ወረዳዎች በመውረድ የማኑዋል ግዥ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሮኒክ ግዥ የሚቀየርበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ገልፀዋል፡፡እስካሁን ስምንት ሺሕ ያህል አቅራቢዎች እንደተመዘገቡ ገልፀዉ በቀጣይ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ወደ አሠራሩ ሲገቡ ከ30 ሺሕ በላይ አቅራቢዎች ወደ አሰራሩ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓቱ ከንክኪ የፀዳ፣ ወጪ ቆጣቢና ቀልጣፋ፣ እንዲሁም ግልጽ መሆኑ ዘርፎቹ ለሙስና ያላቸውን ተጋላጭነት ከመቀነሱ በተጨማሪ፣ አቅራቢዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ያለ ውጣ ውረድ ተወዳድረው መሸጥ እንደሚያስችላቸዉ አክለዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
“ኮሚሽኑ የሚያቀርባቸው ምክረ ሐሳቦች በመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ተፈጻሚነታቸው እንዲረጋገጥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል“፡- ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሚያቀርባቸው ምክረ ሐሳቦች በመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ተፈጻሚነታቸው እንዲረጋገጥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲል አሳስቧል።ኮሚሽኑ የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወር የሥራ ክንውን ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ሚያዝያ 30/2015 አቅርቧል፡፡

በቀረበው የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይም፤ ባደራጃቸው ዘጠኝ የትኩረት መስኮች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር መካተታቸውን ኮሚሽኑ ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ አስታውቋል።በዚህም መሰረት በሪፖርቱ የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራን በተመለከተ ኮሚሽኑ በዋናው መሥሪያ ቤቱና በከተማ ጽሕፈት ቤቶቹ በ1491 ሰዎች 1680 ጉዳዮች ላይ አቤቱታ የቀረቡለት ሲሆን፤ ከነዚህም መካከል በኮሚሽኑ ሥልጣን ሥር የሚወድቁ 1084 አቤቱታዎችን ተቀብሎ ማስተናገዱ ተገልጿል፡፡

አቤቱታ ከቀረበባቸው ጉዳዮች መካከል አብዛኞቹ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶችን የተቀሩት ደግሞ የኢኮኖሚያዊና የማኅበራዊ መብቶችን የተመለከቱ መሆናቸውም ተነግሯል።

ኮሚሽኑ በ48 ማረሚያ ቤቶች እና በ323 ፖሊስ ጣቢያዎች ባካሄደው የክትትል ሥራ ለይቶ ባስቀመጣቸው ግኝቶች እና በሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች መሠረት፤ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና ያለበቂ ማስረጃ በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች መፈታታቸውን፣ የዋስትና መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው መደረጉን፣ ኢ-ሰብአዊ አያያዝ ሲፈጽሙ የነበሩ የተወሰኑ የጸጥታ አባላት ተጠያቂ መደረጋቸውን፣ በመደበኛ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ ያሉ ሰዎች መብቶች ጥበቃ እና አያያዝ መሻሻል ማሳየታቸው እና ለአብዛኛዎቹ አቤቱታዎች አወንታዊ መፍትሔ እንዲያገኙ መደረጉን ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ጠቅሷል፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በቀጨኔ መካነ መቃብር አጥር ተደርምሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ!

በዛሬው እለት ሚያዚያ 30 ከቀኑ 8:30 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የቀጨኔ  መካነ መቃብር አጥር ግንብ ተደርምሶ በአጥሩ ስር በግ ከሚነግዱ ነጋዴዎች መካከል የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ቀሪ አስከሬን ካለ በሚል በአሁኑ ሰዓት ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተለይ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ቁጥራቸዉ ለጊዜዉ በውል ያልታወቁ በግና ፍየሎች ሞተዋል የተባለ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በፍለጋ ላይ ይገኛሉ።በአደጋው ሰባት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ተልከዋል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ

ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️

የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ

ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦

🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን  ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።

ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።

በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።

አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj


For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp