ባሳለፍነው ቅዳሜ ማለትም በቀን #21/08/2015 ከጥዋቱ 1፡50 ላይ በእንጅባራ ዩንቨርሲቲ በተምዶ ኪዳነምህረት መግቢያ በመባል በሚታወቀው በር በኩል የዩንቨርሲቲው የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ኤደን ገብሩ ከቤተክርስቲያን መልስ የግቢ መታወቂያ ( ID Card ) #አለመያዟን ተከትሎ ከዩንቨርሲቲው ተረኛ የጥበቃ ሠራተኞች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በደረሰባት አካላዊ ጥቃት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ተማሪዋ ከባድ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በርካታ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጥቆማ አድርሰውናል።
ይህንን ጥቆማ በመቀበል ጉዳዩን ለማረጋገጥ ጉዳት የደረሰባት ተማሪ ጋር እንዲሁም የዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረትን አናግረናል።
ተማሪ ኤደን ገብሩ ጋር በደወልንበት ጊዜ ተማሪዋ በስልክ ለማውራት አቅም ስላጠራት አጠገቧ ከነበሩት ጓደኞቿ ነው መረጃውን ያገኘነው>
ጉዳት በደረሰባት ተማሪ የእጅ ስልክ ደውለን ያገኘነውን መረጃ በአጭሩ ለመግለፅ
ተማሪዋ ወደ ቤተክርስትያን ስትሄድ የግቢ መታወቂያ ትረሳለች።
ወደ ግቢ ስትመለስ የግቢ መታወቂያ እንዳልያዘች በመንገር በመመገቢያ ካርድ ያስገቧት ዘንድ የጥበቃ ሠራተኞችን ስትጠይቅ አንዱ ጥበቃ ይገፈትራታል።
አትገፍትረኝ ብላ እጁን ለማስለቀቅ ስትሞክር በጥፊ ይመታታል። ለምን በጥፊ ትመታኛለህ ስትለው በድጋሚ ገፍትሮ ጥሎ ጭኗ አካባቢ ይረግጣታል።
ጭኗ አካባቢ የረገጣት ህመም ሲበረታባት ሌሌች ጥበቃዎች ጣልቃ ገብተው ወደ ግቢ እንድትገባ ይፈቅዱላታል። ዶርም ገብታ መታወቂያዋን ይዛ ክስ ለመመስረት ዲሲፕሊን ቢሮ ሄዳ ሰኞ ትመለስ ዘንድ ነግረዋት ከቢሮ ስትወጣ ራሷን ሳተች።
አሁን ላይ ማህፀኗ አካባቢ የተቋጠረ ደም እንዳለ እንደተነገራትና ህመሙ ምናልባትም ቀዶ ህክምና ሊያስፈልገው እንደሚችል በእጅ ስልኳ መረጃ የሰጡን ከጎኗ ያሉ ጓደኞቿ ነግረውናል። ጓደኞቿ በተጨማሪ እንደነገሩን ከሆነ ተማሪዋ ሽንት ለመሽናትና ለመንቀሳቀስ እጅጉን እየተቸገረች እንደሆነ ገልፀው ዩንቨርሲቲው ጉዳዩን አለባብሶ ለማለፍ እንዳይሞክር ድምፅ እንሆንላት ዘንድ ጠይቀዋል።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳንት የሰጠን ምላሽ
ዩንቨርሲቲው መረጃው የደረሰው ቢሆንም ጉዳዩ በመጣራት ሂደት ላይ እንዳለ ፕሬዝዳንቱ ነግረውናል።
አሁን ላይ ተማሪዋ የህክምና እርዳታ እያገኘች እንዳለ ገልፀው የህመሟን ምክንያት ማለትም ተማሪዋ ያቀረበችውን ምክንያት በተጨማሪም ራሷን ስታ በምትወድቅበት ጊዜ የመታት ነገር መኖር አለመኖሩን የባለሙያ ማረጋገጫ እንደሚያስፈልግና እንደ ፀጥታም መጠየቅ ያለባቸው ነገሮች በመኖራቸው ጉዳዩን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እያጣሩ እንደሚገኙና በሚናፈሱ ወሬዎች ላይ ብቻ ተመስርቶ የግል አስተያየት መስጠት እንደማይገባ ገልፀውልናል።
@Yenetube @Fikerassefa

የጀርመን መራኄ መንግሥት አዲስ አበባ ገቡ!
የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። መራኄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ርእሠ ብሔር፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጋር በሁለትዮሽ ፣ አካባቢያዊ እና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።DW እንደዘገበው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ እና ጀርመን ጠንካራ ግንኙነት ያላቸውና በብዙ የኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅቶች ጀርመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆየች አገር ናት ብለዋል።
የኢትዮጵያ እና የጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ አንድ ምዕተ ዓመት ተሻግሯል። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ሲደርሱ የንግድ ተቋማት ባለቤቶችን እና ኃላፊዎች አስከትለው ነበር።ከጀርመን ሰፊ ቁጥር ያለው ባለሃብት የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስዓለም ጀርመን የኢትዮጵያ ሰፊ የልማት አጋር መሆኗን ጠቅሰዋል። በትምህርት እና በስልጠና ከምታደርገው ሰፊ ድጋፍ ባለፈ አሁን የሰላም ስምምነት ሒደቱ በላቀ እንዲሳካ ፣ ለመልሶ ግንባታ ሥራዎችም ድጋፍ ያደርጋሉ ብለዋል።
በሌላ በኩል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ ላይ ችግር የሚፈጥር ነው የተባለው የሱዳን ቀውስ ክስተቱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ነው ተብሏል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም እንዳሉት እስካሁን 61 አገሮች 7726 ዜጎቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል ከሰዳን ማስወጣታቸውንና ከነዚህም 3517ቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገልፀዋል።
[DW]
@YeneTube @FikerAssefa

የመቀሌ ወደብና ተርሚናል ወደ አገልግሎት ተመለሰ፡፡
የመቀሌ ወደብና ተርሚናል ወደ አገልግሎት የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ)የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል፡፡በነበረው የፀጥታ ችግር ተቋርጦ የቆየው የመቀሌ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት የመጀመሩን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡መዳረሻቸው መቀሌ ወደብና ተርሚናል ለሆኑ ገቢ ጭነቶች ከዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከመነሻ የባሕር ወደብ ለመቀሌ ኦፕሬሽን መክፈት የሚቻል መሆኑንም ነው ድርጅቱ ለደንበኞቹ ያስታወቀው፡፡
[ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8]

የሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ አከፋፋዮች እና የችርቻሮ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማዋ የሚታዩ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በዚህ መሰረት ቢሮው በሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ ከማሸግ ጀምሮ ሌሎች ህጋዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስታውቋል።
ህብረተሰቡ በተለይም ሸማቾች ከተተመነው ዋጋ በላይ ከፍለው መሸመት የሌለባቸው ሲሆን፣ ጉዳዩ ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ መስመር 8588 በመደወል ጥቆማ አድርሱኝ ሲል ቢሮው አሳውቋል፡፡
የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋን በተመለከተ ደርባ በ1067.36 ፣ ዳንጎቴ 1106.85፣ ሀበሻ በ1305 ብር፣ ሙገር በ1016 ብር፣ ኢትዮ 1056.80 ሳንቲም የመሸጫ ዋጋው መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።
Via:- ዳጉ ጆርናል

በአማራ ክልል መከላከያ ሰራዊትና ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት ውስጥ ሙግባታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ
የክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት በሚመለከት የተቃውሞ ሰልፍን አስተባብረዋል የተባሉ ወጣቶች እየታሰሩ መሆኑንም ኢሰመኩ ገልጿል
በአማራ ክልል የሀገር መከላከያ እና በአካባቢው ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት ውስጥ ሙግባታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው “የሕግ ማስከበር ዘመቻ”ን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
ኮሚሽኑ ይህ ድርጊት በሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን አንድምታና ተጽእኖ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑ አስታውቋል።
ኮሚሽኑ አደረኩት ባለው ክትትል በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት አለ ብሏል።
በተለይም ሸዋ ሮቢት፣ አርማኒያ፣ አንጾኪያ፣ ገምዛ እና ማጀቴ በመከላከያ ሰራዊት እና በአካባቢው ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥና በከባድ መሣሪያ ጭምር የታገዘ ጥቃት መኖሩን ደርሼበታለሁም ብሏል።
በዚህ የተኩስ ልውውጥ ምክንያትም በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ከመድረሱ ባለፈ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱን እንዳረጋገጠ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተወሰኑ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና የማዋቀር ውሳኔን በመቃወም የተካሄዱ ሰልፎችን መርተዋል የተባሉ የተወሰኑ ወጣቶች እና ከፋኖ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች እንደታሰሩ ኢሰመኮ መረዳቱንም አስታውቋል።
በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚፈጠሩ ተጨማሪ ግጭቶች ሰብአዊ መብቶች ላይ አስከፊ ወይም ከባድ ጥሰቶች የሚያስከትሉ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም የሚመለከታቸው ወገኖች ችግሩን በሰላማዊ መንገድና በውይይት እንዲፈቱ አሳስቧል።
ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡ፣ ስለደረሰው ጉዳት ሁሉ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥም ኢሰመኮ ጥቋል።
እንዲሁም በማናቸውም ሁኔታ የሚፈጸሙ እስራቶች ሕግን መሠረት ያደረጉ በተለይም “የጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነጻ መሆን” የሚሉትን የሰብአዊ መብቶች መርሆችን ያከበሩ መሆናቸውን መንግሥት እንዲያረጋግጥ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

👍1
ቀድመው ይዘጋጁ
ከመጪው ግንቦት አንድ ጀምሮ የድረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቶች እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
ዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቱ በቴሌ ብር፣ ሲቢኢ ብር እንዲሁም በሞባይል ባንኪንግ አማራጮች በኩል የሚተገበር ሲሆን ደንበኞች ይህንን በመገንዘብ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያቸውን በወቅቱ እንዲያከናውኑ አገልግሎቱ አሳስቧል።
በአገልግሎቱ የደንበኞች አገልግሎት ሽያጭ እና ቅሬታ ሰሚ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሪት ስምረት በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የድህረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የክፍያ ሥርዓትን ለማዘመን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ስትራቴጂካዊ ትግበራ መጀመሩን አስታውሰዋል።
በዚህም፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት 72 በመቶ የሚሆኑ የድረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ወደ ዘመናዊ የክፍያ ሥርዓት መቀላቀላቸውን ጠቅሰው አሁን የቀሩት 28 በመቶ የሚሆኑ ተጠቃሚዎች ወደ ሥርዓቱ የሚካተቱ ይሆናል ብለዋል።
በመላ አዲስ አበባ 30 የድረ-ክፍያ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቅሰው በመጪው የግንቦት ወር 21 የሚሆኑት የድረ-ክፍያ ማዕከላት ሙሉ በሙሉ በቀጥታ ወደ ዘመናዊ ሥርዓት ይገባሉ ብለዋል።
እንደ ሥራ አስኪያጇ ማብራሪያ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የሚገኙ ዘጠኝ የድረ-ክፍያ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት ለግንቦት ወር ብቻ የቢል የአከፋፈል ሥርዓትን የሚሰጡ ይሆናሉ።
የክፍያ ሥርዓቱን በዘመናዊ የአከፋፈል ሥርዓቶች ማድረጉ ደንበኞች ከዚህ ቀደም በክፍያ ማዕከላት ሲያጋጥማቸው የነበሩ መጉላላቶችን ከማስቀረቱ ባሻገር ፈጣን እና ተደራሽ የሚሆን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።
አገልግሎቱ ከዚህ ቀደም የፍጆታ ክፍያ አገልግሎትን ይሰጥ በነበረበት የጊዜ ገደብ መሰረት የዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቱ እንደሚሰጥ አስታውቀው ደንበኞች ወር በገባ ከ26 እስከ ቀጣይ ወር 15 ባሉ ቀናቶች ፍጆታቸውን በመክፈል ከተጨማሪ የቅጣት ወጪ ራሳቸውን እንዲታደጉም ጥሪ አቅርበዋል።
የዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቱ ለተጠቃሚዎች ምቹና ቀላል እንዲሁም በማንኛውን አይነት የስልክ ቀፎ የሚሰራና በተለይም አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች ወደ ማዕከላቱ በሚመጡበት ሂደት ሊያጋጥማቸው የሚችለውን እንግልት የሚያስቀር መሆኑንም አብራርተዋል።
EBC

በወላይታ ዞን በድጋሚ የሚደረገው ህዝበ ውሳኔ ሰኔ 12 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልልን ለመመስረት በወላይታ ዞን በድጋሚ የሚደረገው ህዝበ ውሳኔ፤ በመጪው ሰኔ 12፤ 2015 እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ለህዝበ ውሳኔው የመራጮች ምዝገባ የሚካሄደው፤ ድምጽ በሚሰጥበት ቀን እንደሆነም ቦርዱ ገልጿል።
ምርጫ ቦርድ ይህንን ያስታወቀው በወላይታ ዞን በድጋሚ የሚካሄደውን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ፤ ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 26፤ 2015 በአዲስ አበባ ሳፋየር ሆቴል እያደረገ ባለው የባለድርሻ አካላት ውይይት ላይ ነው። በዚህ ምክክር ላይ የነባሩ ደቡብ ክልል እና የወላይታ ዞን አመራሮች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በዚህ ውይይት ላይ በድጋሚ ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ፤ ቦርዱ ያዘጋጀውን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል። በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ህዝበ ውሳኔው ከአንድ ወር ከ15 ቀናት በኋላ የሚካሄድ ሲሆን ውጤቱ ደግሞ በሰኔ 19 ይገለጻል።
በዚህ ህዝበ ውሳኔ 998,00 መራጮች ይሳተፋሉ የሚል ግምቱን ያስቀመጠው ቦርዱ፤ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወነው በድምጽ መስጫው ዕለት ሰኔ 12 መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወርቅ መግዣ ዋጋ ላይ ማሻያ አደረገ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወርቅ መግዣ ዋጋ ላይ ማሻያ ማድረጉን አስታወቀ።ባንኩ በላከው መግለጫ በወርቅ ንግድ በሚታየው ህገ ወጥ ወርቅ ንግድ ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለባንኩ እየቀረበ ያለው የወርቅ መጠን የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑን አስታውቋል።
በመሆኑም ባንኩ በወርቅ መግዣ ዋጋ ላይ ከዚህ ቀደም ለአቅራቢዎች የሚከፈለው 35 በመቶ ክፍያ ቀርቶ በየዕለቱ በሚወጣው ዓለም አቀፍ ዋጋ ላይ ለአቅራቢዎች ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፈል ወስኗል።

አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️
በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።
ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ
✅ ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️
✅ የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ
✅ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦
🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።
ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።
በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።
✅ አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!
For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj
For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
#Nedaj #nedajapp

ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር ፣
ላንጋኖ ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች
✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን
✔️ ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን
✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር
✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን
✔️ ዘመናዊ ኪችኖች
✔️ የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣
♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣
♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን
♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን
♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣
♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡
🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ
በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511
ይደውሉልን,ይጎበኙን!
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት

❤1
Meri Geta Tibebu
👉አስደሳች ዜና ማየት ማመን ነው
መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሔ ስራይ
👉ለአስም (ለሳይነስ)
👉 ለአይነጥላ ለሰው እጅ ለገርጋሪ👇
እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች መቶ ተመርምሮ የለብወትን ችግር አውቆ መታከም ይችላሉ
እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል
👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።
ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ
👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah
👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

የሠራተኞችን ደመወዝ ለማዳበሪያ ዕዳ ግዢ በዋስትና ያስያዙ የወረዳ አስተዳደር ሓላፊዎች ተከሠሡ!
በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን ምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳ፣ ከመምህራን በስተቀር አብዛኛው የመንግሥት ሠራተኛ፣ ለተከታታይ ሦስት ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸውና ከዚኽም የተነሣ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ተናገሩ። የተቋረጠው ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው፣ በሰላማዊ ሰልፍ ከጠየቁ ሠራተኞች መካከል፣ ከ200 በላይ የሚኾኑቱ መታሰራቸውን፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።የምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት፣ ከግለሰቦች እና ከባለሀብቶች ተበድሮ ለተወሰኑት መክፈሉንና ከ200 በላይ የሚኾኑ የ16 መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ግን እንዳልተከፈላቸው አስታውቀዋል።
የሃዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ፣ በመጠኑ ቢለያይም ችግሩ በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች መኖሩን አረጋግጠዋል።የክልሉ መንግሥት፣ የአፈር ማዳበርያ በብድር ሲገዛ፣ የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ አካውንት በዋስትና በማስያዙ የተፈጠረ ችግር መኾኑን ጠቅሰው፣ የአሠራር ጥሰት ተፈጽሟል፤ ጥሰቱን የፈጸሙ የዞንና የወረዳ አመራሮች እና ባለሞያዎች በሕግ እንዲጠየቁ መደረጋቸውን፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አብርተዋል፡፡
የዞኑ የመንግሥት ሠራተኞች በማይመለከታቸው ጉዳይ ለምን እንዲቸገሩ ይደረጋል በሚል የተጠየቀው፣ የክልል ፋይናንስ ቢሮ፣ የዞንና የወረዳ ደመወዝ መክፈል እንደማይመለከተው ምላሽ ሰጥቷል፡፡ የሁሉንም ሠራተኞች ዓመታዊ ደመወዝ ጨምሮ የዞኖቹ ሁሉም ወረዳዎች አጠቃላይ በጀት፣ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ መላኩን ያወሳው የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ፣ ለአርሶ አደሮች የተሠራጨውን የአፈር ማዳበርያ ገንዘብ ሰብስቦ መመለስ፣ የዞኖቹ እና የወረዳዎቹ ሓላፊነት እንደኾነ አመልክቷል፡፡
ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁን፣ በሃዲያ ዞን የምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኛ የኾኑ አስተያየት ሰጪ፣ ለተከታታይ ሦስት ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል።በወረዳው የግብርና ጽሕፈት ቤት ሠራተኛ መኾናቸውን የተናገሩት ወይዘሮ ምኞት አለነ፣ ከሁለት ወራት መዘግየት በኋላ ደመወዝ እንደተከፈላቸው ጠቅሰው፣ ያልተከፈላቸው ሠራተኞች መኖራቸውን ጠቁመዋል። ለወራት ያለደመወዝ የቆዩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ከመቸገራቸው የተነሣ፣ የቤት ዕቃዎቻቸውን ለመሸጥ እየተገደዱ መኾናቸውን ገልጸዋል።
በወረዳው የተለያዩ ዘርፎች ሠራተኞች፣ አስከፊ ሲሉ ወደገለጹት ኢኮኖሚያው እና ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ መግባታቸውን የሚያመለክቱት ሌላው ቅሬታ አቅራቢ አቶ ብሩክ ነዳሞ፣ ደመወዛቸው በወቅቱ እንደማይከፈላቸው ተናግረዋል።የሃዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ፣ ችግሩ በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች መኖሩን አረጋግጠው፣ የምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳን ተነጋግረን፣ ሰሞኑን ለሁሉም ሠራተኞች ከፍለናቸዋል፤ ሲሉ ተናግረዋል።
የምን ያህል ሠራተኞች ደመወዝ እንደተከፈለ የተጠየቁት የምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳ የፋይናንስ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ አብርሃም ለራሞ፣ ከግለሰብ እና ከባለሀብቶች ተበድረው ለተወሰኑ ሠራተኞች ክፍያ መፈጸማቸውንና አሁንም ያልተከፈላቸው ስለ መኖራቸው ገልጸዋል።ከተቋረጠባቸው የሦስት ወር ደመወዝ ውስጥ፣ የአንድ ወሩ ብቻ ለተወሰኑ ሠራተኞች ሰሞኑን እንደተከፈላቸው የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ አብዛኞቹ እንዳልተከፈላቸውና ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎም ሠራተኞቹ፣ ደረሰብን ያሉትን በደል፣ ሕዝብ እና የመንግሥት አካላት እንዲያውቁት ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው ለእስር መዳረጋቸውንገልጸዋል።የሃዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሩ አቶ አብርሃም ቁጥራቸውን ባይጠቅሱም፣ የታሰሩ ሠራተኞች ስለመኖራቸው ጠቅሰው፣ የታሰሩት ግን በወንጀል ድርጊት በመሳተፋቸው ነው፤ ብለዋል።
አቶ ብሩክ ግን፣ ደመወዛችን በወቅቱ ይከፈለን ከማለት በቀር የፈጸምነው የወንጀል ድርጊት የለም፤ ሲሉ ይከራከራሉ።የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም፣ የችግሩ መነሻ፥ ከውዝፍ የአፈር ማዳበርያ ዕዳ ጋራ የተገናኘ መኾኑንና የኦዲት ግኝት ስለመኖሩም አስረድተዋል፡፡ ይህም፣ ከአምስት ዓመታት በፊት አንሥቶ ሲንከባለል የመጣ ችግር የተፈጠረው፣ በወቅቱ የወረዳው ሥራ አስፈጻሚዎች እና አመራሮች ስሕተት እንደኾነና በሕግ እንዲጠየቁ መደረጉን አቶ አብርሃም ገልጸዋል፡፡
አቶ አብርሃም፣ አርሶ አደሩ በተጠቀመው ማዳበሪያ እና የወረዳውአመራሮች በፈጸሙት የአሠራር ስሕተት፣ ስለምን የመንግሥት ሠራተኞች ይበደላሉ፤ በሚል ለተጠየቁት፣ የክልሉን የፋይናንስ ቢሮ ተወቃሽ ያደርጋሉ።የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዲሬክተር አቶ አማን ሬሽድ፣ ቢሮው፥ የዞንና የወረዳ ደመወዝ ክፍያ አይመለከተውም፤ ብለዋል።
በዓመቱ መጀመሪያ፣ የሁሉም ሠራተኞች ዓመታዊ ደመወዝ ጨምሮ አጠቃላይ በጀት ተልኳል፤ ለአርሶ አደሮች የተሠራጨውን አፈር ማዳበርያ ገንዘብ ሰብስቦ መመለስ፣ የዞኖች እና የወረዳዎች ሓላፊነት ነው፤ ሲሉ ተናግረዋል።የቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል(ሲዳማን ጨምሮ) ከመበታተኑ በፊት፣ ከ2005 እስከ 2010 ዓ.ም. የተወዘፈው 5ነጥብ6 ቢሊዮን ብር የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ እንደነበረበት ተገልጿል።በዕዳ ውዝፉ የተነሣ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ መክፈል የተሳነው የምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳም፣ ተከፍሏል የተባለውን ጨምሮ ከአጠቃላይ ውዝፉ 61 ሚሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተመልክቷል፡፡
Via VoA

በኡባ ደብረፀሃይ ዛባ ከተማ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ!
በጎፋ ዞን ኡባ ደብረፀሃይ ወረዳ ዛባ ከተማ ላይ ትናንት ምሽት በጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እስካሁን የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚንኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሳሁን አባይነህ እንደገለጹት፣ በጎፋ ዞን ኡባ ደብረፀሃይ ወረዳ ዛባ ከተማ ትናንት ምሽት የዘነበው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እስካሁን የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጸዋል።
በአደጋው በርካታ መኖሪያ ቤቶች የፈራረሱ ሲሆን፣ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረትም ወድሟል ብለዋል።