YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በመዲናዋ ሕዝባዊ ሰራዊቱ የሚመራበት አዲስ ደንብና ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለጸ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕዝባዊ ሰራዊት የሚመራበት አዲስ ደንብና ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱን የከተማዋ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የሰላም እሴት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በሰጡት ማብራሪያ÷ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ከ246 ሺህ በላይ የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ከፖሊስ ጋር በቅንጅት ለመሥራት በሚያስችል መልክ ከጓድ እስከ ብርጌድ ፖሊሳዊ አደረጃጀትን በተከተለ መንገድ የሪፎርም ሥራ ተከናውኗል ብለዋል፡፡

ከሕልውና ዘመቻው ወቅት አንስቶ የሕዝባዊ ሠራዊት አባላት የከተማችንን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥና የሽብር ቡድኖችን አፍራሽ እንቅስቃሴ ለመግታት ከፖሊስ ጋር በቅንጅት እስከ መስዋዕትነት የደረሰ ዋጋ መክፈላቸውን ተናግረዋል፡፡ሕገ ወጥ ጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል፣ ለሽብር ተግባር የተዘጋጁ የክልል ፖሊስ የደንብ ልብሶችን መያዝ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ለእኩይ ዓላማ የተከማቹ የልዩ ልዩ ሀገራት የገንዘብ ኖቶች፣ ለሽብር እንቅስቃሴ የተዘጋጁ ሀሰተኛ መታወቂያዎችን ጨምሮ በርካታ የተደራጁ ወንጀለኞችንና የሽብር ድርጊቶችን ሕዝባዊ ኃይሉ ከጸጥታ ተቋማት ጋር በጋራ ሲከላከል መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡

የፖሊሳዊ አደረጃጀት ሪፎርሙ ያስፈለገው÷ አገልግሎቱን በዘላቂነት አጠናክሮ ለማስቀጠል መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡ፖሊስ ከሕዝባዊ ሠራዊቱ ጋር በቅንጅት እየሰራ ባለው ስራ÷ የመኪና ስርቆት፣ የተደራጀ ዘረፋና መሠል ደረቅ ወንጀሎች 50 ከመቶ መቀነሳቸውንም ወ/ሮ ሊዲያበማብራሪያቸው አንስተዋል፡፡አዲስ የተዘጋጀው የሕዝባዊ ሠራዊት ረቂቅ ደንብና መመሪያ ትዕዛዝ ከበላይ የሚወርድበት የራሱ የዕዝ ሰንሰለት እንዲኖረው ተደርጎ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡በአዲሱ የሕዝባዊ ሠራዊት ረቂቅ ደንብና መመሪያ መሠረት የሠራዊቱ አባላት ማንነታቸውን የሚገልጽ የደንብ ልብስና ኃላፊነታቸውን በዝርዝር የሚገልጽ የመታወቂያ ካርድ እየተዘጋጀላቸው መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ከአፋር ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እራሱን አገለለ!

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ የአፋር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ያልተሳተፍኩበትና ከአቋሜ የሚጻረር መግለጫ በማውጣቱ እራሴን ከምክር ቤቱ አግልያለሁ ሲል ዛሬ ባወጣው መግለለጫ አስታውቋል፡፡

የአፋር ህዝብ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤቱ አባል በመሆን እየተንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም፣ ጉዳዩ ከአብሮነት ወደ ግለኝነት ያዘነበሉ አካሄዶችን ላለፉት ሦስት ዓመታት ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡ ምክር ቤቱ በግልጽ የህዝብን ስብራቶች በመደበቅ ላይ የተሰማራ በመሆኑ፤ ከጋራ ምክርቤቱ ጋር በዚህ መልኩ መቀጠል ለአፋር ሕዝብና ለፓርቲው ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዘነ መሆኑን ተመልክቻለሁ ብሏል ፓርቲው በመግለጫው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
⬆️⬆️

የአዲስ አበባ ፖሊስ በጉለሌ ክ/ከተማ በአንድ ተማሪ ላይ የድብደባ ወንጀል የፈፀሙ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገለፀ፡፡

የፓሊስ አባላት የህግ በላይነትን ለማስጠበቅ በሚያከናውኑት የትኛውም አይነት እንቅስቃሴ የሰው ልጆች ሰብዓዊ መብቶችን አክብሮ በማስከበር ህጋዊ አግባብ መሆን እንዳለበት የአ/አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር ሆቴል በሚባል አካባቢ ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ በክፍል ውስጥ ርንቺት ተኩሶ ከት/ቤት ውስጥ አምልጦ የሄደ አንድ ተማሪን አራት የፖሊስ አባላት ተከታትለው በመያዝ የድብደባ ወንጀል ፈጽመውበታል፡፡

ህገ- ወጥ ድርጊቱ እንደተፈፀመ ፖሊስ በደረሰው መረጃ እና ባደረገው ማጣራት ድል በር 2ኛ ደረጃ በሚባል ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ነው በሚል ፕሮግራም ላይ በክፍል ውስጥ በተደረገ ዝግጅት አንድ ተማሪ ርችት እንደተኮስ እና በትምህርት ቤት ውስጥ ርችት መተኮሱ ሌሎች ተማሪዎችን እንደረበሻቸው ለፖሊስ መረጃ ይደርሰዋል፡፡በእለቱ ድርጊቱን ፈፅሟልየተባለው ተማሪ ከት/ቤቱ ቅጥር ግቢ እንደወጣ የተነገራቸው 4 የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት ክትትል በማድረግ ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር የሚባል ሆቴል አካባቢ ተማሪውን ይዘውት ተገቢ ያልሆነ ድብደባ ፈፅመውበታል፡፡

የአ/አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ፖሊስ መረጃው ካደርሰው በኋላ ተጠርጣሪ የፖሊስ አባላቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራይገኛል፡፡በማነኛውም ሁኔታ ውስጥ የህግ አስከባሪነት መነሻው ህግን ማክበር መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ የዜጎችን ህጋዊ መብት በሚፃረሩ የፖሊስ አባላት ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በማንኛውም ሁኔታ ህገወጥ ተግባራት ሲፈፀሙ ህ/ሰቡ በያገባኛል ስሜት የሚሰጠውን መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መዓዛ መሃመድና ሰለሞን ሹምዬ በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ወሰነ።

የፈደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንድትለቀቅ መወሰኑ ይታወሳል።ይሁን እንጂ ፖሊስ በጠየቀው ይግባኝ መሰረት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጨማሪ 5 ቀናትን ለፖሊስ መፍቀዱ አይዘነጋም።የጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ ጠበቆች ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ፍርድ ቤቱ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ ወስኗል።

በተመሳሳይ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጣ የፈቀደለት ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ ፖሊስ በጠየቀው ይግባኝ መሰረት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለፖሊስ የምርመራ ጊዜ ዳግም የ5 ቀን የገከዜ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወቃል።ይሁን እንጂ በጠበቆቹ በኩል በጠየቀው ይግባኝ መሰረት ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የታችኛው ፍ/ቤት ውሳኔ ተከብሮ በ10 ሺህ ብር ዋስ እስር እንዲወጣ ወስኗል።በሌላ በኩል ደግሞ የጠበቃ አዲሱ ጌታነህን ጉዳይ የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በ30 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጣ ፈቅዷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ405 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ!

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ405 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኦስማን ዲዬ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

ገንዘቡ ለአርብቶ አደርና ደረቃማ አካባቢ የከርሰ ምድር ውሃ ልማት እንዲሁም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡በዚህም 210 ሚሊዮን ዶላሩ በአርብቶ አደርና ደረቃማ አካባቢ የከርሰ ምድር ውሃ ልማት የሚውል ሲሆን ቀሪው ደግሞ የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ይውላል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
1ሺሕ 127 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ!

በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺሕ 127 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከተመላሾቹ መካከል ስድስት ህጻናትና 1 ሺሕ 121 ወንዶች መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉ ተገልጿል፡፡እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው 38 ሺሕ 853 ኢትዮጵያዊያንን መመለስ ተችሏል ተብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ከ12,000 ለሚበልጡ ምርቶችና አገልግሎቶች ደረጃ የተዘጋጀ ቢሆንም ብዙዎቹ ግን በሰዉ ዘንድ አይታወቁም ተባለ፡፡

የወጡ ደረጃዎች አለመታወቅ ደግሞ ምርቶችና አገልግሎቶች የተቀመጠውን የጥራት መስፈርት ስለማሟላት አለማሟላታቸው ለማረጋገጥ የሚከወነውን ስራ አስቸጋሪ እንዳደረገው ተነግሯል፡፡የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት በደረጃ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አሰናድቶ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ተመክሮበታል፡፡

የኢንስትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ እንዳሉት ከተዘጋጁት ደረጃዎች 296ቱ አስገዳጅ ናቸው፡፡የተቀሩትና የሚበዙት ደግሞ አስገዳጅ ያልሆኑ ደረጃዎች ናቸው ብለዋል፡፡

አስገዳጅ የሆኑትም ሆኑ ያልሆኑት ግን ብዙ በሰዉ ዘንድ እንደማይታወቁ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡በመድረኩ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጣዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ እንዳለው መኮንን በበኩላቸው በኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ንግድ መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት ለማጥበብ አንዱ መንገድ የወጡ ደረጃዎችን ጠብቆ ማምረት ነው ብለዋል፡፡

ጥራትና ደረጃ የአገርን ገፅታ የሚወስኑ ጉዳዮች እንደሆኑ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡መንግስት ምርቶችና አገልግሎቶች የተዘጋጀላቸውን ደረጃ አሟልተው እንዲገኙ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡ከጊዜው ጋር የሚሄዱ የፍተሻ መሳሪያዎች እንዲሟሉና ዘመናዊ ማዕከላት እንዲገነቡ ከፍተኛ ገንዘብ የመደበው በዚሁ ምክንያት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በዜጎች ላይ ያልተመጣጠነ እርምጃ መወሰዳቸውን ኢሰመኮ ገለጸ!

በጋምቤላ ከተማ በዜጎች ላይ ያልተመጣጠነ እርምጃ መወሰዱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ገለጸ፡፡ኢሰመኮ መምሻውን ባሳለፍነው ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም በጋምቤላ ከተማ ከተፈጠረው ጉዳይ ጋር ተያይዞ እየተከሰቱ ባሉ ድርጊት ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል፡፡ድርጅቱ እንዳለው ከሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ምክንያት ነዋሪዎች ከሕግ ውጭ ግድያ ስለመፈጸሙ መረጃዎች ደርሰውኛል ብሏል፡፡

በተለይም በጥቃቱ ተሳትፈዋል ወይም ተባብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ቤት ለቤት በመሄድ ጭምር ግድያዎች እንደተፈጸሙ ኢሰመኮ ከምስክሮችና የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃዎች ጭምር ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን አስታውቋል።የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሰዎችን ደኅንነትና የከተማዋን ሰላም ማረጋገጥ የመንግስት ቀዳሚው ተግባር መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ የሰብአዊ መብቶች መርሆች ሊከተሉ እንደሚገባ ያሳሰቡት ዶ/ር ዳንኤል በተለይም የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡና በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ በአስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥም አሳስበዋል።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ታጣቂዎች በመንግሥት የፀጥታ አካላት እና አስተዳዳሪዎች ላይ በከፈቱት የጦር መሣሪያ ጥቃት የወረዳው አስተዳዳሪ እና የወረዳው የፖሊስ ምክትል አዛዥ መገደላቸው ተገለጠ።

ግድያው ባለፈው እሑድ ሰኔ 05 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. በወረዳው ጋሌማ በተባለ ደናማ አከባቢ ጠዋት በግምት ከ3 እስከ 4 ሰዓት ገደማ መፈፀሙን ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን ያልገለጡ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ (DW) ተናግረዋል። እንደ ነዋሪው አስተያየት፦ የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል አዛዡ ከወረዳው ከተማ ጎቤሳ የተወሰኑ የፖሊስ አባላትን አስከትለው የአርሲ ብሔራዊ መካነ-አራዊት አካል ወደ ሆነው ጋሌማ ሲያመሩ ነው ጥቃቱ በታጣቂዎች የተከፈተው።በጥቃቱም የወረዳው አስተዳዳሪ፣ የወረዳው ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል አዛዥ እና አንድ የሚሊሻ አባል መገደላቸውን ነው ነዋሪው የገለጹት።

«የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል አዛዡ ባለፈው ከዚህ የሔዱት ዘመቻ ተብሎ ነው።ዝም ብሎ ፖሊሶች እና ቀለል ያለ ኃይል ይዘው ነው የኼዱት። ጋሌማ ውስጥ ድንኳን ተጥሏል ተብሎ ከዚህ በፊት መረጃ ደርሷቸዋል።»
ነዋሪው እንዳሉት በዕለቱ ታጣቂዎች ሰዎች አግተዋል፤ የጦር መሣሪያና ገንዘብ ዘርፈዋል። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዘመዱ ኃይሉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ እና የፖሊስ ምክትል አዛዥ በጥቃቱ መገደላቸውን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል፡፡

«በታጣቂዎች እና በሰላም አስከባሪዎች መካከል የሰው ሕይወት አልፏል። ይህ መኾኑ የታወቀ ነው። በሺርካ ወረዳ እና በሳቡሬ ድንበር ላይ ነው። ቦታው ደግሞ አስቸጋሪ ነው። የሌሎችም የወደቁ ሰዎች ሬሳ ይኖራል ብለን እናስባለን።»የአርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ ዋና ከተማ ጎቤሳ ከአዲስ አበባ 264 ኪ.ሜ ገደማ ርቀት ላይ ስትገኝ፤ ከበቆጂ ከተማ ደግሞ 35 ኪ.ሜ. ትርቃለች። ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች በአከባቢው እንደማይንቀሳቀሱና መሰል የፀጥታ ስጋትም ሲያዩ የመጀመሪያቸው መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ለአገር ውስጥ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ዘንድሮ ለማቅረብ ከታሰበው የጥጥ ምርት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ጥጥ ምርት ሊቀርብ እንዳልቻለ ኢንዱስትሪ ሚንስቴር መናገሩን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ባለፉት 10 ወራት ለጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች 35 ሺህ ቶን ጥጥ ለማቅረብ ታስቦ የነበረ ሲሆንም፣ በጸጥታ ችግር ሳቢያ ምርቱ በመቀነሱ ማቅረብ የተቻለው ከግማሽ በታች እንደሆነ ሚንስቴሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው የ10 ወራት ሪፖርት ላይ ተናግሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በዛሬው ዕለት ተመርቆ ሥራውን በይፋ ጀምሯል።

የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የምረቃ እና ስራ ማስጀመሪያ ሰነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተካሂዷል።በምረቃ ስነ ስርዓቱ የብሔራዊ ባንግ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።አማራ ባንክ በዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ተመርቆ በ70 ቅርንጫፎቹ በይፋ ስራ መጀመሩ በስነ ሰርዓቱ ላይ ተገልጿል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአሜሪካ የአጎዋ ጥቅም ለኢትዮጵያ እንዲፈቀድ እና እንዲታደስ ተጠየቀ!

የአጎዋን ስምምነት መሰረት በማድረግ የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶችን ከቀረጥ ነፃ በማድረግ በአሜሪካ ገበያ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት የሚገያኙትን ጥቅም ለኢትዮጵያ እንዲፈቀድ እና እንዲታደስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠየቀ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።አምባሳደር ተስፋዬ በመንግሥት በኩል እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ዙሪያ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል የቆየ ግንኙነት መኖሩን እና ይህ ግንኙነት ደግሞ እስካሁን ድረስ በተለያዩ መስኮች ትብብሩ ተጠናክሮ መቀጠሉን በማስታወስ በመንግሥት በኩል ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያለውን ግንኘነት በአዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ፍላጉት እንዳለው ጠቅሰዋል።የሀገሪቱን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ሀላፊነት የመንግሥት ዋነኛ ተግባር መሆኑን ገልፀው የሕወሓት ቡድን ከጎረቤት አገራት ላይ የሚያሳየው ጠብ ጫሪ ባህሪያት እንዲሁም ከአጎራባች ክልሎች ላይ የሚያደርገው ትንኮሳ በሰላም ጥረቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
በመስቀል አደባባይ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማዘጋጀት 2 ሚሊዮን ብር ይከፈላል ተባለ!

በመስቀል አደባባይ የሙዚቃ ድግስ (ኮንሰርት) ለማዘጋጀት እስከ ኹለት ሚሊዮን ብር እንደሚያስከፍል የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።

በአደባባዩ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ለማድረግ የኪራዩ ዋጋ የተለያየ ነው የተባለ ሲሆን፤ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማድረግ ክፍያው እስከ ኹለት ሚሊዮን ብር መሆኑን የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የገበያ ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ታደሰ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ክፍያው ኹለት ሚሊዮን የሆነው ኮንሰርት ብዙ ወጪ ስለሚጠይቅ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው አክለው ተናግረዋል። ኮንሰርቶችን በተመለከተም ብዙ ሰዎች እየጠየቁና ፕሮግራም እየተያዘላቸው መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው አንስተዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በ2015 በጀት ዓመት የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በውጤታማነት ማጠናቀቅ እንጂ አዲስ ፕሮጀክት የመጀመር እቅድ እንደሌለው የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ።

በ2014 በጀት ዓመት ሊጀመሩ ታቅደው በጸጥታና በተለያዩ ምክንያቶች ያልተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ማስገባትም ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ÷ መንግሥት በ2015 በጀት ዓመት ምንም ዓይነት አዲስ የልማት ፕሮጀክት አይጀምርም፡፡

እቅድ ወጥቶላቸው በተለያዩ ምክንያቶች ያልተጀመሩ እንዲሁም ተጀምረው ላልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ትኩረት መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡በ2014 በጀት ዓመት ሊጀመሩ ታቅደው በጸጥታና በተለያዩ ምክንያቶች ያልተጀመሩ ፕሮጀክቶች በ2015 በጀት ዓመት ሊጀመሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።በቀጣይ ለፕሮጀክቶች በጀት የሚመደበው ከአሥር ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ጋር በማናበብ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ በ2016 በጀት ዓመት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር በመካከለኛ ዘመን ማዕቀፉ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡መንግሥት ከፕሮጀክት አፈጻጸም በተጓዳኝ ቁጠባ ላይ ትኩረት ማድረጉን ጠቁመው፥ ተቋማትን በማዋሃድ እስከ 40 በመቶ ወጪን ለመቀነስ መታቀዱን አብራርተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ፕሮጀክቶች የሚታቀዱበትና የሚተዳደሩበት የሕግ መመሪያ እንዳልነበረ ጠቅሰው÷ በ2013 ዓ.ም የመንግሥት የልማት ፕሮጀክቶች አስተዳደር አዋጅ መጽደቁን ገልጸዋል።አዋጁን መሰረት በማድረግም÷ ፕሮጀክቶችን ከሀሳብ ቀረጻ ጀምሮ እስከ ግንባታ ፍጻሜ ድረስ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ ክትትል ያደርጋሉ ብለዋል፡፡በተለይም ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው እቅድ መሰረት መከናወናቸውን ከተጠናቀቁ በኋላም የታለመላቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ስለማምጣታቸው በትኩረት እንደሚገመገም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 9 ሺህ ያህል የትግራይ ተወላጆች ያለ ፍርድ እስር ላይ ይገኛሉ ሲል ሮይተርስ ባወጣው አዲስ የምርመራ ሪፖርት ገልጧል። ከታሰሩት እስረኞች መካከል 17ቱ ለሞት እንደተዳረጉ ዘገባው አመልክቷል። ሦስት ሺህ እስረኞች በደቡብ ክልል ሚዛን ተፈሪ ከተማ በሚገኝ 18 ጊዜያዊ ማቆያዎች እንደሚገኙ የገለጠው ዘገባው፣ ማቆያዎቹ የቆሸሹ እና የእስረኞቹ አያያዝም ዓለማቀፍ ሕግን ያልተከተለ ነው ብሏል። ሮይተርስ ስለታሳሪዎች ለፌደራል ፖሊስ፣ ለፍትህ ሚንስቴር እና ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ እንዳላገኘ ጨምሮ ገልጧል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ከሩሲያ ጋር መነጋጋር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ተናገሩ፡፡ ለዲ ፒ ኤ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ከበርካታ የአውሮፓ ሀገራት ትችት ቢደርስባቸውም ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ግንኙነት መፍጠርና መነጋገር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
1
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ቤት አልባ ናቸው ተባለ


በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ 12 ሚሊዮን ዜጎች የሚጠጣ ውሃ እጥረት አለባቸውም ተብሏል
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ቤት አልባ መሆናቸውን ተመድ ገለጸ፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ባሉ ሀገራት የተወሰኑ አካባቢዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ ድርቅ ተጋልጠዋል፡፡

የተመድ ቃል አቀባይ ፋርሃን ሀቅ እንዳሉት በአፍሪካ ቀንድ ከ1 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ቤት አልባ ሆነዋል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ፣ኬንያ እና ሶማሊያ 12 ሚሊዮን ዜጎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር ገጥሟቸዋልም ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡

በምስራቅ አፍሪካ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በኑሮ ውድነትና ግጭት ምክንያቶች እየሞተ ነው ተባለ

በድርቁ በተለይም ሴቶች እና ህጻናት የበለጠ ጉዳት እያስተናገዱ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ለተጎጂዎች በቶሎ ድጋፍ ማድረግ ካልተቻለ በታሪክ አስከፊውን ጉዳት ያስተናግዳሉም ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ በአጠቃላይ 18 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች አስከፊ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው ድርጅቱ የተናገረ ሲሆን 200 ሺህ ሶማሊያዊያን መራባቸው ተገልጿል፡፡
ከዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በተገኘ ድጋፍ እስካሁን 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎችን መርዳት የተቻለ ሲሆን ለተቀሩት ዜጎች በጀት ባለመገኘቱ ምክንያት ለረሃብ የሚጋለጡ ዜጎች መኖራቸውን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

Via:- Alain
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ግርምት ከፈጠሩት ውስጥ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ አንድ እራቁቱን የሆነ ግለሰብ የፖሊስ መኪና ጣሪያ ላይ ወጥቶ መደነሱ ነው። ግለሰቡ ፖሊሶች ለምነውት ከመኪናው የወረደ ሲሆን ወደ እስር ቤትም አምርቷል። ክስም ይጠብቅዋል ተብሏል።
ቪዲዮው የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ”ኦነግ ሽኔ” በተባሉ ሰዎች ላይ ጅምላ ግድያ ሲፈጽሙ ያሳያል - ኢሰመኮ
ኢሰመኮ በጉዳዩ ላይ የተሟላ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ አሳስቧል**

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፤ በትናንትነው እለት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ሲዘዋወር የነበረው በርካታ ግለሰቦች ከመኪና እየወረዱ ሲደበደቡና በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳየው ቪዲዮ "ኦነግ ሸኔ" በተባሉ ሰዎች ላይ የተፈጸመ እንደሆነ አስታወቀ ።

ድርጊቱ የተፈጸመው በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ ልዩ ቦታው እንቶሊ በሚባል ስፍራ በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም የተፈጸመደ መሆኑም ኢሰመኮ በመግለጫው አመላክቷል፡፡

የጅምላ ግድያው የተፈጸመው " በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ’’ ነውም ብሏል። ኢሰመኮ ይህን ይበል እንጅ የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም፡፡
ኢሰመኮ፡ "ከህግ ውጭ የተፈጸመ ወንጀል" ሲል የገለጸው የጅምላ ግድያ ፤ ተቋሙ ከዚህ ቀደም ባወጣው “በኢትዮጵያ የአፋር እና የአማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች እና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ህግ ጥሰቶች ላይ የተደረገ ምርመራ” በሚል መጋቢት 2፣ 2014 ዓ.ም ያወጣው ሪፖርት ከተካተቱ ከህግ ውጭ የተፈጸመ የግድያ ድርጊት ክስተቶች አንዱ መሆኑም አስታውሷል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተሟላ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነትም እንዲረጋገጥ በድጋሚ አሳስቧል።

በዚሁ ሪፖርት ላይ ኢሰመኮ ከምስክሮች እና በስፍራው በመገኘት በመስክ ምልከታ ያሰባሰበውን መረጃ መሰረት በማድረግ ድርጊቱ የተፈጸመበትን ስፍራ ጠቅሶ ወቅቱም በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት ቀኑ በትክክል ያልታወቀ መሆኑንም አስፍሯል።

የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በሁለት የጭነት መኪኖች ያመጡዋቸውን እና ወደ 30 የሚጠጉ የ”ኦነግ ሸኔ አባላት” ናቸው ያሏቸውን ሰዎች በጅምላ በጥይት ደብድበው መግደላቸውን ገልጿል።

 ኢሰመኮ ቪዲዮውን ላይ ተጨማሪ ማጣራትና የቴክኒክ ምርመራ ካደረገ በኋላ ከዚህ ቀደም በመስክ ምርመራ በለየው ስፍራና በቪዲዮው ላይ ያለውን ስፍራ ማነጻጸሩን አስታውቋል።

ምስሉ የተቀረጸበት ቦታ ለማነጻጸርና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የቴክኒክ ምርመራዎችን ማድረጉን ገልጾ ቪዲዮው ላይ ያለው ከፍርድ ውጭ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ ከዚህ ቀደም ኢሰመኮ በሪፖርቱ ያካተተው ስለመሆኑ በአሳማኝ ደረጃ ማስረጃ ማግኘቱንና ማረጋገጡን አስታውቋል።

Via :- Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa