YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የትግራይ ኃይሎች ለድርድር ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ!

የትግራይ ኃይሎች ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከ18 ወራት በላይ ሲያደርጉት የነበረውን ጦርነት ለማብቃት በኬንያ መንግሥት አሸማጋይነት በሚካሄድ ድርድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።

በህወሓት ሊቀመንበር እና በክልሉ ፕሬዝዳንት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ተፈርሞ የተሰራጨው ደብዳቤ የወጣው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው መንግሥታቸው ጦርነቱን በሰላም ለማብቃት ፍላጎት እንዳለው ካሳወቁ በኋላ ነው።

ከህወሓት በኩል የወጣው ደብዳቤ ከዚህ በፊት ቡድኑ ለድርድር ያቀረባቸውን ቅድመ ኹኔታዎች አላካተተም።

የኬንያውን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላደረጉት ጥረት አድናቆቱን የገለፀው ህወሓት፣ በድርድሩ ላይ ለመሳተፍ የሚችል ከፍተኛ የመልዕክተኞች ቡድን ወደ ኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ለመላክ ዝግጁ መሆኑን አመልክቷል።

ደብዳቤው የአፍሪካ ሕብረት የሚጠበቅበትን ያህል አለማከናወኑን በመግለጽ አጥብቆ የተቸ ሲሆን፣ ባለፉት ወራት ሰላም ለማውረድ ከመቀለ አዲስ አበባ ሲመላለሱ በነበሩት የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ላይም ጥያቄ አንስቷል።

ለድርድር ዝግጁ መሆናቸውንም በተመለከተ “ለሰላም ተጨማሪ ርቀት ለመሄድ ዝግጁ መሆናችን ከደካማነት ወይም ከስግብግብነት በመነጨ የቆምንለትን መርህ ለመተው እንደ መዘጋጀት ተደርጎ መታየት የለበትም” ብሏል።

በዚህ ድርድርም በኬንያ መንግሥት መሪነት የአፍሪካ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ተሳታፊ እንዲሆኑም መጠየቁንም ቢቢሲ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማክሰኞ ትናንት ሰኔ 07 ቀን 2014 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው እንደተናገሩት፣ መንግሥታቸው ከየትኛውም ወገን ጋር ሰላም ማውረድ እንደሚፈልግ ለዚህም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮሚቴው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ እንደሆነና በገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ መሰየሙን አመልክተው፤ ሰላሙን በተመለከተ መሳካት ያለባቸው ተግባራትን፣ እንዲሁም ስለሚጠበቁ ነገሮች እያጠና መሆኑን አመልክተዋል።

“ከህወሓትም ይሁን ከማንኛውም ሰላም ፈላጊ ጋር የምንፈልገው ሰላም ነው፤ የሚቻል ከሆነ ለሰላም መቆም ችግር የለውም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጦርነት እንደማያተርፍና ከኹለቱም ጎን የሚያለማ ወጣት እየረገፈና አገሪቱም የምታወጣው ገንዘብ ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህወሓት ጋር በሚደረገው ድርድር ይኸው ኮሚቴ ተደራዳሪ መሆኑን እና ኮሚቴው በቅርቡ የደረሰበትን ለፓርቲው ሲያቀርብ በይፋ ለሕዝብ በዝርዝር የሚቀርብ ይሆናል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ከሚገኙ 13 መድሃኒት ፋብሪካዎች ሶስቱ ስራ ማቆማቸው ተነገረ!

በኢትዮጵያ ካሉት አስራ ሶስት መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያ ፋበሪካዎች ውስጥ ሶስቱ በውጪ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ስራ ማቆማቸው ተገልጿል፡፡ ፋብሪካዎች በምስራቅ አፍሪካ ትልቅ የሚባሉ እና መሰረታዊ የነፍስ አድን መድሃኒቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ሲሆኑ ሰራተኞቹ ሙሉ ለሙሉ ስራ ማቆማቸውን የኢትዮጵያ መድኃኒት አምራቾች እና የህክምና መገልገያ ፋብሪካዎች ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ዳንኤል ዋቅቶሌ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡

ፋብሪካዎች በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙት ሳንሸንግ ፣ ካዲላ ፣ ሰሚድ ሲሆኑ ሙሉ ለሙሉ ስራ ያቆሙት ፋብሪካዎቹ የማሽን ፣የሰው ሃይል እንዲሁም የተሞላ ሰራተኛ ያሏቸዉ ሲሆን ፋብሪካው እንዲዘጋ ብቸኛ ምክንያት የሆነው የውጭ ምንዛሬ እጥረት መሆኑም ተገልጿል፡፡

አያይዘውም አቶ ዳንኤል ዋቅቶሌ እንደገጹት መድሃኒቶችን በውጪ ምንዛሬ ምክንያት በሚፈለገው መጠን ከውጪ ማስገባትም ሆነ ማምረትም አለመቻሉን ለሚመለከተው አካል ያሳወቅን ቢሆንም እስካሁን ምንም አይነት መልስ ማግኘት አለመቻላቸውን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ "ራስ ጠቆሮ" ጥብቅ ደን ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የወረዳው አካባቢና ደን ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ተወካይ ኃላፊ ወይዘሮ ዚነት መሃመድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከትናንት በስቲያ እኩለ ሌሊት ጀምሮ በጥብቅ ደኑ ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።የእሳት አደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነ ገልጸው፤ አንድ ግለሰብ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቁመዋል።የእሳት አደጋው እንዳይዛመትና የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የተለያዩ አካላት ቅንጅት ፈጥረው እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረው፤ ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አስተላልፈዋል።

አካባቢው ተራራማ ከመሆኑ ባለፈ በአሁኑ ወቅት ሀይለኛ ንፋስ በመኖሩ እሳቱ እየተስፋፋ ቢሆንም ህብረተሰቡ ጭምር በነቂስ ወጥቶ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል።"ራስ ጠቆሮ" ጥብቅ ደን ከ8 ሄክታር መሬት በላይ ስፋት ያለው ሲሆን በውስጡ የተለያዩ እንሰሳትና አዋፋትን ጨምሮ ሀገር በቀል ዛፎች እንዳሉትም አብራርተዋል፡፡

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ፍ/ቤት መስከረም አበራ በዋስ እንድትለቀቅ የተላለፈዉን ዉሳኔ አጸና!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት መስከረም አበራ በ 30 ሺ ብር ዋስ እንድትለቀቅ ቢወስንም ፖሊስ ይግባኝ ጠይቆ ነበር፡፡ይህንን ይግባኝ የተመለከተው ከፍተኛው ፍ/ቤት፤ የታችኛው ፍርድ ቤት መስከረም አበራ በ 30 ሺ ብር ዋስ ከእስር እንድትወጣ የወሰነውን ውሳኔ በማጽናት የዋስትና መብቷ እንዲጠበቅ ወስኖ ነበር።

ይሁንና ፖሊስ በድጋሚ ይግባኝ በማለቱ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዳዩን ተመልክቶ ውሳኔ ሰጥቷል።ጠቅላይ ፍ/ቤት የፖሊስን ይግባኝ ወድቅ በማድረግ መስከረም አበራ በ 30 ሺ ብር ዋስትና እንድትወጣ መወሰኑን ጠበቆቿ ሄኖክ አክሊሉ እና ሰለሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል።መምህርት መስከረም አበራ “ኢትዮ ንቃት” የተሰኘ የዮቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት ናት፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
1ሺህ 17 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ!

በሳዑዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 17 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ከተመላሾቹ ውስጥም ሶስቱ ህጻናት ሲሆኑ÷ 1 ሺህ 14ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጁላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉንም ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የባልደራስ ፓርቲ አመራሩ ስንታየሁ ቸኮል ህገ መንግስቱን በሀይል በመናድ ወንጀል ተከሰሰ!

ከ20 ቀናት ገደማ በፊት በቁጥጥር ስር የዋለው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊው ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበው ተጠርጣሪው ህገ መንግስቱን እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ሞክረሀል የሚል ክስ እንደቀረበበት ፓርቲው አስታውቋል። በተጨማሪም ህዝብን ለተቃዉሞ የሚያነሳሳ ፅሁፍ በፌስቡክ አሰራጭተሀል በመባል ተወንጅሏል።

ስንታየሁ ቸኮል በበኩሉ ባልደራስ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ጉባኤውን ለማደናቀፍ የተደረገ “አፈና” ነው ሲል ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ 12 ቀናት ይፈቀድልኝ ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ተቀብሎ ለሰኔ 20 ቀን 2014 ቀጠሮ ሰጥቷል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ግብርና ሚንስቴር የተፈለፈሉ የዶሮ ጫጩቶች እና እንቁላል ላልተወሰነ ጊዜ ለገበያ እንዳይቀርብ ማገዱን ሪፖርተር አሰነብቧል።

ዶሮ እና እንቁላል ላይ እገዳ የተጣለው፣ ምንነቱ ለጊዜው ያልታወቀ የዶሮ በሽታ በመገኘቱ እንደሆነ ሚንስቴሩ ለዶሮ አርቢዎችና ላኪዎች በጻፈው ደብዳቤ ገልጧል። የበሽታው ምንነት ታውቆ መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ እንቁላል እና የተፈለፈሉ ጫጩቶች ከውጭ አገር እና ከክልሎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እና ከአዲስ አበባም ለውጭ አገር ገበያ እንዳይቀርቡ ሚንስቴሩ አሳስቧል። በውሳኔው የዶሮ እርባታ ድርጅቶች ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተጋለጡ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው አንደኛ አመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳርፏል፡፡

1. የከተማ አስተዳደሩ መሬትን ፍትሀዊ በሆነ አግባብ ለልማት ለማዋል 89 የሚሆኑ ቦታዎችን ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለቅይጥ አገልግሎት እንዲውል የከተማውን ፕላን ባስጠበቀ አግባብ በግልፅ ጨረታ እንዲቀርቡ ውሳኔ አሳርፏል፡፡

2. በከተማችን ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በማህበር ተደራጅተው ቤት የሚገነቡበትን አሰራር ለመወሰን በተዘጋጀ ደንብ ላይ ሲሆን በዚሁ አግባብ በከተማችን የሚኖሩና የቤት ችግር ያለባቸውን ነዋሪዎች ችግር በሚቀርፍ አግባብ የከተማ አስተዳደሩ መሬት፣ የሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ህንፃዎች ዲዛይን፣ ማህበራቱን የማደራጀትና ግንባታው በሚጀመርበት ጊዜ የመቆጣጠር ሀላፊነት የሚወስድ ሆኖ በማህበር ተደራጅተው የጋራ ህንጻ የሚገነቡ ሰራተኞች፣ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች የፀጥታ አካላት ከተደራጁ በኋላ ቁጣባ በአግባቡ መቆጠብ የሚችሉና አስተዳደሩ በሚያዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ከፍታቸውን የጠበቁ ህንፃዎች ለመገንባት ዝግጁ የሆኑ ወደ ግንባታ እንዲገቡ ማድረግ የሚያስችል ደንብ ሲሆን ዝርዝር የአፈፃፀም ሂደቱ በከተማችን ካለው የቤት አቅርቦት ማህቀፍ ጋር ተጣጥሞ እንዲፈፀም ውሳኔ አሳርፏል፡፡

3. ካቢኔው በቀጣይ የተወያየበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ደህንነትን ቀድመን ለመከላከል በሚያስችል ደንብ ላይ ሲሆን በዚህም በከተማችን ለአደጋ ስጋት የሆኑ የህንፃ ዲዛይን ማስተካከያዎች፣ በግንባታ ላይ ያሉ ህንፃዎች ሊያሟሏቸው የሚገባ የደህንነት ጥንቃቄዎች፣ የተጠናቀቁ ህንፃዎች አጠቃቀም ሁኔታና ለቅድመ መከላከልም ሆነ አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ የአደጋ መውጫ አስፈላጊውን የህንፃ ዲዛይን ማስተካከያ እንዲያደርግ እንዲሁም በከተማችን የማዕድን ማውጣት ሂደት ላይ ሊሟሉ የሚገባቸው የቅድመና የአደጋ መከላከያ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት በከተማችን በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን አደጋ ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ደንብ በመሆኑ አስፈላጊውን የአፈፃፀም ሂደት ባሟላ መልኩ ወደ ተግባር እንዲገባ ደንቡን አፅድቋል፡፡

4. የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍ እስካሁን ድረስ 1 ቢሊዬን ብር መድቦ የተለያዩ ምርቶች ወደ ከተማዋ እንዲገቡ የተደረገ ቢሆንም አሁንም የዘይት አቅርቦት ላይ ያለ እጥረት መኖሩን ካቢኔው አፅንኦት ሰጥቶ ከተወያየ በኋላ ለዘይት አቅርቦት ብድር የሚሆን 400 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ድጎማ መድቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ተመድ ስለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያወጣውን ሪፖርት ኤርትራ አልቀበለውም አለች!

ኤርትራ በሀገሪቱ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን በማስመልከት በተመድ የቀረበው ሪፖርት እንደማትቀበለው አስታወቀች፡፡በኤርትራ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን ለመከታተል በተባበሩት መንግስታት የተሾሙት ሱዳናዊው ሞሃመድ አብደልሰላም ባቢከር (ዶ/ር) ሰሞኑን በኤርትራ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን የተለመከተ ሪፖርት ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡አብደልሰላም ባቢከር (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት በኤርትራ ያለው የማያቋርጥ የ”ብሄራዊ አግልገሎት” መርሃ ግብር ነቅፈዋል፡፡ይሁን እንጂ ኤርትራ አብደልሰላም ባቢከር (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ማዘኗን በተወካይዋ አማካኝነት ለምክርቤቱ ገልጻለች፡፡

ሙሉ ዘገባው:
https://am.al-ain.com/article/eriterea-says-it-doesnot-accept-un-report-on-human-rights

@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል በአዩን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ!

በሶማሌ ክልል ኖጎብ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ አደጋው በክልሉ ኖጎብ ዞን አይን ወረዳ ዳሪዳ ቀበሌ ባለ ሁለት ጋቢና ቶዮታ መኪና የኋላ ጎማ ወልቆ በመውደቁ የደረሰ ነው። በአደጋው የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰ ከሶማሌ ከልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
96 ኪሎግራም የሚመዝን ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ቁስና አደገኛ እፅ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ውጪ ሊወጣ ሲል ተያዘ!

96 ኪሎግራም የሚመዝን ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ቁስና አደገኛ እፅ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ሊወጣ ሲል ተያዘ፡፡

በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ የመንገደኞች ማስተናገጃ በኩል ደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ በሚበር አውሮፕላን ብዛታቸዉ 39 የሆነ 44 ኪሎ ግራም የሚመዝን ጠፍጣፋ ኖራ የሚመስል አደንዛዥ እፅ በፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ብዛቱ 42 የሆነ 52 ኪሎ ግራም በድምሩ 96 ኪሎግራም የሚመዝን ለግዜው ለመለየት ግልፅ ያልሆነ ጠፍጣፋ ኖራ የሚመስል ንጥረ ነገር ተይዟል።

የተያዘው አደገኛ እጽ በፌደራል ፖሊስ በምርመራ እንዲጣራ ከተላከ በኋላ፤ በውጤቱ አደገኛ እፅ እንደሆነ መረጋገጡን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
«ለሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ከተጓዙት ሦስት ሺህ 297 ተሽከርካሪዎች አንድ ሺህ 128ቱ አልተመለሱም»- የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

ሰብዓዊ ድጋፍ ጭነው ወደ ትግራይ ከተጓዙት ሦስት ሺህ 297 ተሽከርካሪዎች ውስጥ አንድ ሺህ 128ቱ እንዳልተመለሱ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለውን ሰብዓዊ ድጋፍ ሁኔታ አስመልክተው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ለትግራይ ክልል እየተደረገ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ አሁንም ቀጥሏል። በክልሉ አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ወገኖች ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። እስካሁን ድረስ ሦስት ሺህ 297 ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ ጭነው ቢሄዱም አንድ ሺህ 128ቱ አልተመለሱም።

እስካሁን ለሰብዓዊ እርዳታ የተሰማሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሦስት ሺህ 297 መሆናቸውን አቶ ደበበ ጠቁመው፤ እስካሁን የተመለሱት ተሽከርካሪዎች ሁለት ሺህ 169 ሲሆኑ፤ ያልተመለሱ ተሽከርካሪዎች ቁጥር አንድ ሺህ 128 ናቸው። ባልተመለሱ ተሽከርካሪዎች የሚመለከተው አካል ክትትል የሚያደርግ ይሆናል።

ለሰብዓዊ አገልግሎት ከአዲስ አበባ መቀሌ 236 በረራ መደረጉን አመልክተው፤ይህም በአጋር አካላት አማካኝነት ለሰውና ሰብዓዊ እርዳታ ጭነት ምልልስ የተደረገ ጉዞ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሙሉውን ለማንበብ: https://www.press.et/?p=75124

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በ11 ወራት ከተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከ97 በመቶ የሚልቀውን ማክሸፍ መቻሉ ተገለጸ!

በኢትዮጵያ በ11 ወራት ከተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከ97 በመቶ የሚልቀውን በማክሸፍ የ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ኪሳራ ማዳን መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ገለጸ።የሳይበር ምሕዳር በባህሪው ድንበር የለሽና ኢ-ተገማች በመሆኑ ዓለም በዚህ መጠነ-ሰፊና ተለዋዋጭ ወንጀል በየቀኑ በአማካይ 16 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ሀብት ታጣለች።

የሳይበር ወንጀል በ2015 በዓለም ላይ 3 ትሪሊየን ዶላር ካደረሰው ኪሳራ በእጅጉ እየላቀ መጥቶ በ2021 ደግሞ 6 ትሪሊየን ዶላር አሳጥቷል።
በየዓመቱ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣው ዓለም አቀፍ የሳይበር ወንጀል በ2025 ከ10 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር በላይ ሊያሳጣ እንደሚችል ተገምቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሰሞኑን በሰጡት ማብራሪያ በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 5 ሺህ 860 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን ገልጸዉ ነበር፡፡

በዓለም ላይ በየቀኑ በቢሊዮን ዶላር የሚያሳጣው የሳይበር ጥቃት ለኢትዮጵያም ፈተና መሆኑን ማስረዳታቸው ይታወሳል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ፤የሳይበር ወንጀል በኢትዮጵያም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ይናገራሉ።በዚህም በ2011 ዓ.ም 790፣ በ2012 ዓ.ም 1 ሺህ 80፣ 2013 ዓ.ም 2 ሺህ 900 የሳይበር ጥቃቶች መድረሳቸውን መጥቀሳቸዉን ገልጸዋል።በዘንድሮው በጀት ዓመት 11 ወራት ደግሞ 6 ሺህ የሚደርሱ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን ገልጸዋል።በኢትዮጵያ ላይ የተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከየት እንደተሞከሩና የወንጀሉን ባለቤቶች በቀላሉ ለመለየት ባይቻልም ያነጣጠሩባቸው ተቋማት መለየታቸውንም ጠቁመዋል።

በሳይበር ጥቃቱ በተለይም በባንክና የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ማነጣጠሩን ጠቅሰው፤የሚዲያ ተቋማትም ኢላማ መደረጋቸውን ተናግረዋል።የመንግሥት ቁልፍ መሰረተ-ልማቶች፣የፖለቲካ አደረጃጀቶች፣ የፌደራልና የክልል የመንግሥት ተቋማት እንዲሁም የጤና እና የትምህርት ተቋማትም በርከት ያለ ጥቃት እንደተሞከረባቸዉ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በ78 ሚሊዮን ብር የተገዙ 37 ትራክተሮች ለተለያዩ ክልሎች መከፋፈላቸው ተገለፀ!

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በ78 ሚሊዮን ብር የገዛቸውን 37 ትራክተሮች ለአማራ፣ ለኦሮሚያ፣ ለቤንሻንጉል ጉሙዝና ለሶማሌ ክልሎች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ትራክተሮቹን ለክልሎቹ ያስረከቡት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሐመድ፤ ወጣቶችን ወደ ዘመናዊ ግብርና ማስገባት፣ ስልጠና መስጠት፣ ትራክተሮችን ማቅረብ፣ የፓምፕ ድጋፍ ማድረግ ሥራዎች እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው አገራችንን በመስኖ ዘርፉ ስኬታማ ለማድረግ ከፍተኛ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፤ ተቋሙ የተለያዩ ትራክተሮችን፣ የግብርና ማቀነባበሪያዎችን፣ የጥገና ሥራዎችንና እና የመገጣጠሚያ ሥራዎችን በመሥራት የመስኖ ግብርናን ለማሳለጥ እየተጋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ድጋፍ የተደረገላቸው ክልሎችና ተጠቃሚ ወጣቶች ሚኒስቴር መ/ቤቱ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ መሰል ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡የእርሻ መሬት፣ የግብርና ማቀነባበሪያና ፓምፕ የወጣቶቹ መሰረታዊ ችግሮች መሆናቸውንም አክለው መግለፃቸውን ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢንዱስትሪው ዘርፉ 418 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱ ተገለጸ!

የህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት 6ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ላይ ይገኛል።ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ክቡር መላኩ አለበል በሪፖርታቸው ከአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፉ በበጀት ዓመቱ አስር ወራት ውስጥ 498 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 418 ሚሊዮን ዶላር ወይም የዕቅዱ 84 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።

ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 315.5 ሚሊዮን ዶላር አንጻር የ102 ሚሊዮን ዶላር (32.5%) ብልጫ ማስመዝግቡ ተገልጿል።

የተገኘው የውጭ ምንዛሪ በጨርቃጨርቅና አልባሳት 153 ሚሊዮን ዶላር፣ በምግብና መጠጥ 93.8 ሚሊዮን ዶላር፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች 33 ሚሊዮን ዶላር፣ በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች 22.6 ሚሊዮን ዶላር፣ በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ 16.7 ሚሊዮን ዶላር እና በሥጋና ወተት 98 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን ሚንስትሩ በሪፖርታቸው ተመላክተዋል።

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በዶሮዎች ላይ በተከሰተው በሽታ የተያዘ ሰው አለመኖሩን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ!

በኢትዮጵያ በዶሮዎች ላይ በተከሰተው በሽታ የተያዘ ሰው አለመኖሩን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።በኢትዮጵያ የዶሮ በሽታ መከሰቱን ከዚህ በፊት የግብርና ሚኒስቴር መናገሩ የሚታወስ ሲሆን፤ ሚኒስቴሩ በሽታው መከሰቱን ተናግሮ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስቦ ነበር።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ለአልዓይን እንዳሉት የዶሮ በሽታው በኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ከተማ መከሰቱን ገልጸዋል።በሽታው እስካሁን በቢሾፍቱ፣ በአቃቂ ቃሊቲ እና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች መከሰቱን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ ዶሮዎች መሞታቸውን አክለዋል።በሽታው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይሰራጭም ልዩ ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑን እና የሞቱ ዶሮዎችንም ሳይንሱን በጠበቀ መንገድ በማስወገድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ በበኩላቸው፤ እስካሁን በሽታው ተከስቷል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልጸው እስካሁን በሰው ላይ አለመከሰቱን ተናግረዋል።በሽታው ከተከሰተባቸው አካባቢዎች ዶሮዎች እንዳይንቀሳቀሱ ግብርና ሚኒስቴር እገዳ መጣሉ በሽታው እንዳይስፋፋ ያደርጋልም ብለዋል።የዶሮ በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችም የዶሮ ስጋ እና እንቁላል ከመመገብ እንዲቆጠቡ ዶክተር መሳይ አሳስበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የመካኒካል ምህንድስና ተመራቂ ተማሪዎች የነዳጅ ማምረቻ ማሽን መስራታቸውን የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው ይፋ ያደረገው ቴክኖሎጂ ያገለገሉ ፕላስቲኮች በመሰብሰብ በሙቀት አማካኝነት ፓይሮሊሲስ በተሰኘ ሂደት ነዳጅን በቀላሉ ማምረት መቻሉን ነው ያስታወቀው።

ቴክኖሎጂው ሀገሪቱ ያለባትን የነዳጅ እጥረት የሚቀርፍ በመሆኑ ትልቅ አስተዋፅዖ ከማድረጉም ባሻገር በሙቀት አማካኝነት የሚያዘጋጀው የነዳጅ ማምረቻ ማሽኑ በየትኛውም ቦታ በቀላሉ አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።

በተደረገ ሙከራ በሰዓት ውስጥ ሦስት ኪሎ ግራም ፕላስቲክ በመጠቀም ሁለት ሊትር ነዳጅ ማምረት የተቻለ ሲሆን ወደፊት በስፋት ከተሰራበት ከዚህ በላይ ማምረት እንደሚችል ተመራቂ ተማሪዎቹ ገልፀዋል።

አካባቢን ሊበክሉ የሚችሉ የፕላስቲክ አይነቶችን በመጠቀም የአካባቢን ውበት የመጠበቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።

የነዳጅ ምርቱ ለጀነሬተር፣ ለቀላል ተሸከርካሪዎችና ለቤት መገልገያዎች ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑምተረጋግጧል።

ከተጠቃሚው ጋር በመቀናጀት ማሽኑን በቴክኖሎጂ ማጎልበት እንደሚገባና ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ እንሰራለን ማለታቸውን የጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መረጃ ያመለክታል።

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በህንድ ሀገር ህክምና ለማግኘት ለሚሔዱ አንድ መቶ ሕፃናትና ቤተሰቦቻቸው የአየር ትራንስፓርት ወጪ ለመሸፈን ተስማማ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማሕበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት ለማጠናከር ከጤና ሚኒስቴር ፣በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ሕፃናት መርጃ እና ከሮተሪ ኢትዮጵያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

አየር መንገዱ በህንድ ሀገር ህክምና ለማግኘት የሚሔዱ አንድ መቶ ሕፃናት እና ከሕፃናቱ ጋር አብረው ለሚጓዙ አንድ መቶ ቤተሰቦቻቸው የአየር ትራንስፓርት ወጪ ለመሸፈን መስማማቱን ከአየር መንገዱ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ትናንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላይ፣ "ዳኞች አንደኛ ደረጃ ሌቦች ናቸው" በማለት ለተናገሩት ያልተገባ ንግግር ማስተካከያ እንዲያደርጉ ዛሬ ባሰራጨው ደብዳቤ መጠየቁን ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል። ልዩ ጥናትና ማስረጃ በሚፈልግ ጉዳይ ላይ ዐቢይ ዳኞችን በጅምላ በሌብነት መፈረጃቸው ተገቢ አይደለም ያለው ማኅበሩ፣ ንግግራቸው ሕዝብ በፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን አመኔታ የሚያሳጣ፣ የፍርድ ቤቶችን ገጽታ የሚያበላሽ እና የምስጉን ዳኞችን ሞራል የሚጎዳ እንደነ ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጥቂት የዶሮ እርባታ ሥፍራዎች ሰሞኑን የተከሰተው የዶሮ በሽታ እንዳይዛመት ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ!

በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ጥቂት የዶሮ እርባታ ሥፍራዎች ላይ ሰሞኑን የተከሰተው የዶሮ በሽታ እንዳይዛመት ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስድ የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ።የበሽታውን መንስኤና ምንነት ለማጥናት የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ናሙና እየተሰባሰበ በመሆኑ ውጤቱ ሲታወቅ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ባሳለፍነው ሳምንት በቢሾፍቱ እና በአዲስ አበባ ከተሞች ውስን የዶሮ እርባታ ቦታዎች የዶሮ በሽታ ተከስቷል።በሽታው በንክኪ የሚዛመት በመሆኑ በእርባታ ቦታዎች በተወሰኑ ዶሮዎች ላይ ከተከሰተ ሌሎች ዶሮዎችን ሙሉ በሙሉ ስለሚያጠፋ ጥንቃቄ ያሻል ብለዋል።በሽታው ከተከሰተ ጀምሮ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ በሽታውን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

የበሽታውን መንስኤና ምንነት ለማጥናትም የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ናሙና እየተሰባሰበ መሆኑን ገልጸው፤ ውጤቱ ሲታወቅ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።በሚኒስቴሩ የተቋቋመው ግብረ-ኃይል በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ብቻ ተወስኖ እንዲቀር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በሸታው እንዳይዛመት እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች መካከልም ዶሮ አርቢዎች ለተሻሻሉ የዶሮ ዝርያዎች እርባታ ከውጭ የሚገባውን የበሽታው መንስኤ እስኪጣራ የለማ እንቁላል ዝውውር መታገዱን ገልጸዋል።የለማ እንቁላል ሲባል ለዶሮ እርባታ ከውጭ የሚገባ እንጂ ለሰው ምግብ ፍጆታ የሚውል እንዳልሆነ ገልጸዋል።

የተከሰተው በሽታ በቅጡ መቆጣጠርና መከላከል ካልተቻለ በአገር የዶሮ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ ዶሮ አርቢዎችና ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።በዚህም በሽታውን የመከላከልና የመቆጣጠር እንዲሁም የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸው፤ አሁን ላይ ሥርጭቱና የሞት መጠኑ መቀነሱን ተናግረዋል።የታመሙ ዶሮዎችን ወደ ገበያ የማውጣት አዝማሚያዎችን በግብረ-ኃይሉ በተሰራ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሻሻሎች እንዳሉ ገልጸው፤ አሁንም የበሽታው ምንነት እስኪታወቅ ጥንቃቄ እንዲደረግ መክረዋል።

በሽታው ባልተከሰተባቸው ቦታዎች ሌሎች ዶሮዎችን ባለማስገባት እና የራሳቸውንም ወደ ሌሎች ሥፍራዎች ባለማዘዋወር ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።በዚህም በሽታው የተከሰተባቸው አርቢዎች ወደ ገበያ ባለማውጣትና የሞቱ ዶሮዎችንም በመቅበር እንዲሁም በሽታው የተከሰተባቸውን የእርባታ ጣቢያዎች ኬሚካል መርጨት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሕብረተሰቡን ከስጋት እና ሌሎች አርቢዎችን ከጉዳት እንዲሁም አካባቢን ከብክለት ለመታደግ የጋራ ትብብር ይፈልጋል ብለዋል።በሽታው በሰው ጤና ላይ ያደረሰው ጉዳት እስካሁን ባይኖርም ሕብረተሰቡም በዶሮ እና በዶሮ ውጤቶች አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።ሚኒስቴሩ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሽታው እስካሁን በሰዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም ሚኒስቴሩ ሥራ ከመጀመሩ በፊት የተንቀሳቀሱ ዶሮዎች ስለሚኖሩም ለጊዜው የዶሮ እንቅስቃሴ መገደብ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ ገልጸዋል።በየእለቱ ያለውን ሁኔታ እና የጊዜ ገደቡ የሚነሳበትን ወቅት ለመወሰን የሚያጣራ ኮሚቴ መዋቀሩን ገልጸዋል።በዶሮዎች ላይ የህመም ምልክት ካጋጠመ ዶሮ እና የዶሮ ውጤቶችን ለገበያ ባለማቅረብ ሊደርስ የሚችል ጉዳትን ለመቀነስ ማኅበረሰቡ ቀና ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa