YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቡርጂ ወረዳ ተነስቷል በተባለ ግጭት 9 ሰዎች ሲሞቱ 17ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን አስተዳደሩ ተናገረ፡፡

በደቡብ ክልል በቡርጂ ወረዳ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም አንድ አርሶ አደር ከጉጂ የተነሱ ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በተነሳ ግጭት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪና የወረዳው አስተዳደር ለአሻም ተናግረዋል፡፡

አሻም እንዳነጋገረቻቸው የአካባቢው ነዋሪ ከሆነ ”ይህ ግጭት የተነሳው ጉዳት የደርሰበትን አርሶ አደር ይዘው ወደ አምቡላንስ በመሄድ ላይ ሳሉ ነበር፡፡”

የወረዳው አስተዳደር ያወጣው መግለጫ ”በወረዳችን የተፈፀመው ድርጊት ሰብዓዊነት የጎደለው በመሆኑ በጥብቅ እናወግዛለን፡፡” በማለት ይጀምራል፡፡

”ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም የገበያን ቀን ጠብቆ የፀረ ሰላም ኃይሉ በማሳቸው በነበሩ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃት እና ግዲያ በመፈፀሙ ምክንያት የቡርጂን ባሕል እና ዕሴት በፍጹም በማይወክል አግባብ የሰላም መኖር የሚያንገሸግሻቸው ጥቂት ቡድኖች በገበያተኞች ላይ አሰቃቂ ግዲያ እና ጉዳት አድርሷል፡፡” ሲል ወንጅሏል፡፡

የቡርጂ ወረዳ አስተዳዳሪ ማሬ አለማየሁ ለአሻም እንደገለፁላት ”ድርጊቱ በሁለቱ ብሔረሰቦች መካከል የተከሰተ አይደለም”፡፡

አክለውም ”በዚህ አረመኒያዊ” ሲል በጠሩት” ተግባር ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ለህግ ለማቅረብ መንግስት ጠንካራ” ያሉትን ” አቋም ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡ ”

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ ነው!

በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ነገ እለተ ማክሰኞ ከቀኑ 8፡30 ላይ ለሚዲያ ተቋማት ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አፈፃፀሙ በተገቢው እንዲከወን የህግ አስከባሪ አካላት ሚና የጎላ በመሆኑ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል፡፡

ህብረተሰቡም የሚወጣውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ቢሮው መልዕክት አስተላልፏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
977 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 977 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ከእነዚህ ውስጥ ስድስት ህጻናትና 971 ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 33 ሺህ 298 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በቡርጂ ወረዳ ተነስቷል በተባለ ግጭት 9 ሰዎች ሲሞቱ 17ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን አስተዳደሩ ተናገረ፡፡ በደቡብ ክልል በቡርጂ ወረዳ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም አንድ አርሶ አደር ከጉጂ የተነሱ ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በተነሳ ግጭት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪና የወረዳው አስተዳደር ለአሻም ተናግረዋል፡፡ አሻም…
በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ከተነሳው ግጭት እና ሞት ጋር በተያያዘ 10 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል፡፡

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አለማየሁ ማሞ የሶማያ ከተማ ህዝብ በተፈጸመው አጸያፊ ድርጊት ተቆጥቷል ብለዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የአከባቢው ነዋሪዎች ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽነር አለማየሁ በግጭቱ የተጠረጠሩ ከ10 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

በአከባቢው በሚፈጠሩ ግጭቶች ፤አብዛኛው ተሳታፊ ወጣት በመሆኑ፤ይህን ወጣት ወደ ጥፋት እንዳይነዳ ፤ውይይት ከማድረግ አኳያ ክልሉ ምን እየሰራ ነው ስንል ለጠየቅናቸው ጥያቄ ኮሚሽነር አለማየ ማሞ፣ ጥረቶች እንዳሉ እና ክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ለአከባቢው ወጣቶች ትኩረት እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

የአከባቢው ነዋሪዎች ቦታው አዋሳኝ ድንበር እና ስጋት ያለበት በመሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ሃይል በቦታው ቢያሰፍር መልካም ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 19 ሰዎች ተገደሉ!

በቤኒሻንጉል ክልል፣ በካማሺ ዞን በምትገኘው ምዥጋ ወረዳ በክልሉ ልዩ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ሳቢያ 19 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ሀሩን ኡመር ለቢቢሲ ገለጹ።ባለፈው ሳምንት ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ. ም. የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች ጥቃት ሰንዝረው፣ በምላሹ ከልዩ ኃይል ጋር በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የምዥጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ መሞታቸውንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ከዋና አስተዳዳሪው ውጪ የሞቱት ሰዎች ተኩስ የከፈተው የታጣቂው ቡድን አባላት እንደሆኑም አቶ ሀሩን ገልጸዋል።ጥቃቱ በክልሉ በልዩ ኃይል አባላት ላይ መከፈቱን የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ በተደረገው የተኩስ ልውውጥም በርካታ የታጣቂው ቡድን አባላት መገደላቸውን አመልክተዋል።በክስተቱ ከልዩ ኃይሉ የሞተ የለም ያሉት ኮሚሽነሩ “ታጣቂዎቹ የሚጠቀሙበት መሣሪያ” በቤታቸው የተገኘ የተባሉ ባለሀብትም እንደሞቱ ተናግረዋል።

ግለሰቡ ቤት ውስጥ “ዲሽቃ ጥይቶች፣ 5 ክላሽና ሌላም በርካታ ታጣቂዎች የሚጠቀሙባቸው ሌሎች ነገሮች" መገኘታቸውን ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ አስረድተዋል።በግለሰቡ ቤት የተገኘውን “ለታጣቂዎች የተዘጋጀ መሣሪያ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

የምዥጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በአጋጣሚ በስፍራው እንደነበር የተናገሩት ኮሚሽነር ሀሩን በተኩስ ልውውጡ ሕይወታቸው እንዳለፈ አመልክተዋል።የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) በአካባቢው የሚንቀሳቀስ ታጣቂ ቡድን ሲሆን፣ ከክልሉ መንግሥት ጋር ዕርቅ ለመፈፀም ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር ይታወሳል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የ"ፍትህ" መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ባለቤት ተመስገን ደሳለኝን ጉዳይ ለግንቦት 30 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ቤተሰቦቹ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው ሁከት እና ብጥብጥ እንዲነሳ በዩትዩብ ንግግሮችን አድርጓል የሚለውን ቅድመ ክስ ሃሳቡ በማንሳት፣ በ"ፍትህ" መጽሄት ሁከት እና ብጥብጥ ቀስቅሷል በሚል ክስ እንዲቀየርለት ጠይቋል። ጠበቃም ችሎቱ አዲሱን ክስ ውድቅ አድርጎ ለተጠርጣሪው ዋስትና እንዲፈቅድ ጠይቀዋል። ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው፣ በአዲሱ ክስ እና በተጠርጣሪው ላይ ባለፈው ሳምንት በተፈጸመው ድብደባ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነው።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በአንድ ግለሰብ ቤት የሞርታር ተተኳሽ ተደብቆ መገኘቱ ተገለጸ!

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ 02 ቀበሌ ጢሳ አባሊማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግለሰብ መፀዳጃ ቤት ውስጥ 23 የሞርታር ተተኳሽ መገኘቱን የአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።ተተኳሹ ከኀብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ መገኘቱንም ነው የገለጸው።

የተገኘው የሞርታር ተተኳሽ አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ከአካባቢው ሽሽቶ ሲሄድ ጥሎት የሄደ ሊሆን እንደሚችል የሚገመት ሲሆን፥ ተተኳሹ የተገኘበት ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ መጠቆሙን ከአምባሰል ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
Job alert
El Aenon export and Import
Position: Junior Accountant

👉Our company wants to Hire Junior Accountant who have experience in peachtree, and knows how to handle pharmaceutical financing system.

👉Must be graduated from known university/College
Qualification: BA degree in Accounting and Financing

Job type: permanent

Salary: Based on company scale
Required Individual: 1
CGPA 3.00 and More, for both Gender

Place of Job: Tuludimtu

Those who qualify the above requirement, you can send your CV on the following address.

E-mail: elaenon11@gmail.com / Sitotawgidie11@gmail.com
Telegram: @SitotawG
Contact address: 0941483948
ፒያሳ ወርቅ ቤቶች ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ የ15 አባወራ ቤቶች ወደሙ!

በአዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ልዩ ስሙ ወርቅ ቤቶች ጀርባ ዛሬ ከቀኑ 9ሰዓት ከ37 ደቂቃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ15 አባወራዎች ቤቶች መውደማቸውን የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በአደጋው አንድ የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ እና ሁለት ነዋሪዋች ላይ በጭስ በመታፈናቸው ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

የእሳት አደጋው የደረሰበት ቦታ ከወርቅ ቤቶቹ ጀርባ ሲሆኑ ቤቶቹ እጅግ የተጠጋጉ፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋታቸው እና ቤቶቹ የተሰሩበት ግብዐቶች ውድመቱን ከባድ አድርጎታል። በተጨማሪ የቆዩ ነባር ቤቶች በመሆናቸው አደጋው ሰፊ ሆኖ የበርካታ አባወራ ቤቶች እንዲወድሙ እንዳደረገው ተነግሯል።

ወደ ወርቅ ቤቶቹ እሳቱ እንዳይዛመት እና ከፍተኛ የንብረት ውድመት እንዳይደርስ የኮሚሽኑ ሰራተኞች መትጋታቸውን አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል።አደጋውንም ለመቆጣጠር 75 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሳተፋ ሲሆን አስር የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዋች 83ሺ ሊትር ውሃ አንድ ውሃ ጫኝ ተሽከርካሪ ከመንገዶች ባለስልጣን ጥቅም ላይ ውለዋል።እሳቱን ለመቆጣጠር አንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ፈጅታል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ስማርት ቆጣሪዎች ወደ ስራ እየገቡ ነዉ፡፡

ስማርት ቆጣሪዎችን ወደ ስራ ማስገባት የተጀመረዉ ለጊዜዉ ከፍተኛ የሃይል ተጠቃሚ ለሆኑ ኢንዱስትሪዎች ሲሆን በመድናዋ ብቻ ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ ስማርት ቆጣሪዎች የመቀየር ስራ እንደተጀመረ ሰምተናል፡፡

መደበኛ ነበረውን ቆጣሪ ወደ ስማርት ቆጣሪዎች የመቀየር ስራ እየተሰራ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚውኒኬሽን ዳሬክተር ከሆኑት አቶ መላኩ ታዬ ኢትዮ ኤፍ ኤም መረጃዉን አግኝቷል፡፡

አቶ መላኩ እንዳሉት ከፍተኛ በጀት ተይዞለት ወደ ስራ የገባው ነባሩን ቆጣሪ ወደ ስማርት የመቀየር ስራው ያስፈለገው፣ የሃይል መቆራረጥ ሲኖር ለመካታተል እና ከዚህ ቀደም ከቆጣሪ አንባቢ ጋር በተያያዘ የሚነሳውን ቅሬታ ይፈታል ተብሎ መሆኑን ነግረውናል፡፡

ይህ በፓይለት ደረጃ የተጀመረው ነባሩን ቆጣሪ የመቀየር ስራ፣ ኑርፍሌክስ በተባለ የየደቡብ ኮርያ ኩባንያ እየተከናወነ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ ወደ ተግባር የገባው አሰራር በመጀመርያው ዙር 5 ሺህ የሚሆኑ ቆጣሪዎችን የመግጠም ስራ እንደሚሰራ እና በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ 45 ሺህ የሚሆኑት ነባር ቆጣሪዎች የሚተኩ መሆናቸዉን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ለፕሮጀክቱ የገንዘብ ምንጭ የአለም ባንክ መሆኑን የተናገሩት አቶ መላኩ ፡- በብድር የተገኘው 12 ሚሊዮን 546 ሺህ 54 የአሜሪካ ዶላር ሲሆን፣ ቀሪው 9 ሚሊዮን 640 ሺህ 450 ብር ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን መሆኑ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

መጋቢት 2/ 2014 ወደ ስራ የገባው ስማርት ቆጣሪዎችን የመቀየር ስራ፣ እስካሁን 107 የሚሆኑ ቆጣሪዎች መተከላቸውን ነግረዉናል፡፡

ይሁንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሲመጡ የመቀበል ልምዳችን ዝቅተኛ በመሆኑ፣ አገልግሎቱ ይህን የመቀየር ስራ ሲሰራ አንዳንድ የከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ስማርት ቆጣሪዎን ለማስቀየር ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ስራችንን እያጓተተው ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
**ባሳለፍነው ሳምንት 110 ሚሊየን 66 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡**

ኮሚሽኑ ባሳለፍነው ሳምንት በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ባደረገው ክትትል ነው 87 ነጥብ 9 ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 22 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙት፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ ጅግጅጋ እና ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ፥ በቅደም ተከተላቸው 25 ነጥብ 1 ሚሊየን ፣ 12 ነጥብ 8 ሚሊየን እና 12 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ መቻላቸው ተገልጿል ፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሃኒት ፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ እና ጥቆማ የተያዙ ሲሆን፥ ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሰባት ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 የኮንትሮባንድ ድርጊትን ለመግታትና በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመከላከልም ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ባለፉት አስር ወራት ብቻ አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊየን ሰዎች በወባ በሽታ ተይዘዋል!

ር ወራት ብቻ አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊየን ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጄ ዱጉማ የዝንጀሮ ፈንጣጣ፣ የወባ በሽታና ኮቪድ 19ን አሰመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ባለፉት አስር ወራት ብቻ አንድ ነጥብ ሶስት ሚልየን ሰዎች በወባ በሽታ ተይዘዋል።

በአፍሪካ ውስጥ 75 በመቶ አካባቢ ለወባ ወረርሽኝ ምቹ መሆኑን ያመላከቱት ዶክተር ደረጄ፤ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2021 ብቻ 14 ሚሊየን ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን 90 በመቶው ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገሪት ውስጥ መሆኑንም አመልክተዋል።እንደ ዶክተር ደረጄ ገለጻ ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ የሆነ የአየር ሁኔታ መፈጠሩ እንዲሁም የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የወባ መድሀኒት ርጭት ያለመካሄዱ ቁጥር ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ 300 ሚልየን ብር በላይ መድቦ ለክልሎች ያከፋፈለ ሲሆን አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሰዎች ሊያክም የሚችል ፀረ ወባ መድሀኒቶችን ለክልሎች አድሏልም ሲሉ ዶክተር ደረጄ ገልፀዋል።በየሳምንቱ መረጃ እየወሰዱ በፍጥነት ምላሽ የመስጠት ስራን እየከወነ ይገኛልም ብለዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መስፋፋቱን እንዲሁም 14 ስዎች በፅኑ ህሙማን ክፍል እንደሚገኙ አመላክተው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባውም ሚኒስትር ዲኤታው አሳስበዋል።ከሰሞኑ አነጋጋሪ እየሆነ የመጣው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አልተገኘም፣ ነገር ግን ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።በሀያ የድንበር ኬላዎች ላይ ቁጥጥር በመደረግ ላይ መሆኑ ተመላክቷል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ፍድ ቤቱ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በአስር ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ አዘዘ!

“ሮሃ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት መዓዛ መሐመድ በአስር ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ በፍርድ ቤት ተወሰነ።

የመዓዛን የዋስትና ጥያቄ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 የፈቀደው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

መዓዛ ከጓደኛዋ መኖሪያ ቤት በፖሊስ የተያዘችው ከአስር ቀናት በፊት ግንቦት 20 ቀን 2014 ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
ተመስገን ደሳለኝ እና ሰለሞን ሹምዬ የ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ተፈቀደላቸው::

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ሰለሞን ሹምዬ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ፤ ፖሊስ በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና በመስከረም አበራ ላይ እያደረገው ለሚገኘው ምርመራ ተጨማሪ ስድስት ቀናት ፈቅዷል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዙን ያስተላለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የብሔራዊ ቴአትር ህንፃ በድጋሚ በአዲስ መልክ ተጀመረ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ቤትን ለማዘመን በሚል ቴአትር ቤቱ በሚገኝበት ስፍራ ዘመናዊ አዲስ ህንጻ ለመገንባት ታቅዶ ወደ ተግባር ቢገባም የግንባታ ስራውን ለማከናወን ውል ወስዶ የነበረው ተቋራጩ አፍሮ ጺዮን ኮንስትራክሽ አማካይነት ግንባታው ቢጀመርም ከአንድ አመት በፊት ባጋጠመው መጓተት ሊቋረጥ እንደቻለ ተነግሮ ነበር፡፡

በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል በሚል 1.5 ቢሊዮን ብር ተመድቦለት ሲሰራ የነበረው አፍሮ ጺዮን በድጋሜ ውሉን ማደስ እንደሚፈልግ ሃሳብ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም የቀረበለትን መስፈርት ሊቀበል ባለመቻሉ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።

በአሁኑ ሰዓት ኦቢድ ኮንስትራክሽን የተሰኘው አዲስ ተቋራጭ የወጣውን ጨረታ በማሸነፍ ግንባታውን እንደጀመረ የፌደራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተክለጻዲቅ ተክለአረጋይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ተቋራጩ ከእዚህ ቀደም በነበረው ዲዛይን መሰረት የተቋረጠውን የግንባታ ሂደት በማስቀጠል በሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ህንፃውን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ውል ማሰሩን ሃላፊው ገልጸዋል፡፡አዲስ የሚገነባው ህንጻ ባለ 12 ወለል እና ከሰባት ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን ፣1.5 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚጠይቅ ብስራት ሬድዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

አዲሱ ህንጻ የቴአትር መስሪያ ቦታዎችን ቁጥር ከመጨመሩም ባለፈ የጊዜውን ዘመናዊነት የሚያሟላና ሙዚየም ጨምሮ የተለያዩ መገልገያዎችን የሚይዝ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፉን ለማገዝ የ195 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ!

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባትን ለዜጎች ለማዳረስና የጤና ዘርፉን ለማገዝ የ195 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የገንዘብ ድጋፋ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍና በግጭቶች የተጎዱ የሕዝብ ጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚረዳ ነው ተብሏል።

ወቅታዊው የገንዘብ ድጋፍ በጫና ውስጥ ላለው የኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት አጋዥ ከመሆን በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት ከ30 በመቶ በታች ያለውን የኮቪድ-19 የክትባት ሽፋን ለማሳደግና በመላ አገሪቱ የክትባት ሥራዎችን በማስፋፋት የበሽታውን ሥርጭትና ተጽዕኖ ለመቀነስ እንደሚረዳ በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተናግረዋል።

በእናቶች እና ህጻናት ጤና አጠባበቅ ረገድ፣ በሥነ-ምግብ እና ሌሎች ቁልፍ አገልግሎቶችን ተደራሽ ከማድረግ አኳያም የገንዘብ ድጋፉ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውና በግጭቱ የተጎዱ የገጠር አካባቢዎችን እና ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመድረስ ብሎም ለኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ድጋፉ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ግዢ ለማድረግ፣ የሆስፒታል የፅኑ ህሙማን ክፍል መሳሪያዎችን ለማሟላት፣ በኮቪድ-19 እና በሌሎች ህመሞች ላይ ያሉ ህመምተኞችን አያያዝ የበለጠ ለማሻሻል እንዲሁም የማኅበረሰብ ጤና ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ይውላል ተብሏል።

የገንዘብ ድጋፋ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 መጨረሻ ለ60 በመቶ ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባትን ለማዳረስ የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ ሲሆን፤ ይህ የ195 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ምላሽ የሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ከ495 ሚሊየን ዶላር ያደረሰው መሆኑም ታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጰያ የዝንጀር ፈንጣጣ በሽታን ለመለየት የሚያስችሉ 50 የላብራቶሪ ማዕከላት ተደራጅተዋል ተባለ፡፡

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኞችን ጨምሮ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።መግለጫውን የሰጡት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እንዳሉት አብዛኛው ባሉት የሀገሪቱ ክፍል ወቅቱ ለወባ በሽታ መዛመት ምቹ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር፣ በሀገሪቱ የወባ በሽታ በ16 በመቶ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

ኮቪድ-19ን በተመለከተም በአሁኑ ወቅት የበሽታው ስርጭት እየጨመረ መሆኑን አንስተው መላው ህብረተሰብ ካለምንም መዘናጋት የኮቪድ መከላከያ ዘዴዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስበዋል።የዝንጀሮ ፈንጣጣን በተመለከተም በአሁኑ ሰዓት ከ30 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ተጠቂዎች መገኘታቸውን ገልፀው፤ በኢትዮጵያ ግን እስካሁን እንዳልተከሰተ አረጋግጠዋል።ወደ ሀገሪቱ እንዳይገባም በመንግሥት በኩል አስፈላጊ ያሉት የጥንቃቄ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
“የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ የተቋቋመ ተቋም እንደሌለ የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጣና ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ እንዳስታወቀው፤ ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መቋቋም የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 እንዲሁም በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 መሰረት ከፌደራል ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ ነው ብሏል፡፡

ይሁን እንጂ “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል መጠሪያ ስያሜ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም እንደተቋቋመ የሚገልጽ መልእክት በማህበራዊ ድህረ-ገጽ እየተዋወቀ እንደሚገኝ የጠቆመው ባለሥልጣኑ፤ “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በማለት እራሱን እያስተዋወቀ የሚገኘው ይህ ተቋም ከባለሥልጣኑ ምንም አይነት ፈቃድ አልተሰጠውም።

በመሆኑም ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በጥብቅ አሳስቧል፡፡በቀጣይ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም በኢፌዲሪ የትምህርትና ሰልጠና ባለሥልጣን አስታውቋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ዝቅተኛውን ታሪፍ የ 50 ሳንቲም ጭማሪ አድርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ሰኔ 01 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል።
ቢሮው ዝቅተኛውን የታሪፍ ማሻሻያ 50 ሳንቲም ማድረጉን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ይርጋለም ብርሃኔ ተናግረዋል።

ዝቅተኛው ኪሎ ሜትር 2.5 ረጅሙ ደግሞ 30 ኪሎ ሜትር መሆኑን ያነሱት ምክትል ሀላፊው ፣በዚህም በሚኒባስ/ ኮድ 1 እና ኮድ 3/ 2.50 የነበረው አሁን 3 ብር እንዲሁም 30 ብር የነበረው ደግሞ 33.50 መሆኑን እንዲሁም በሚዲ-ባስ/ሃይገር እና ቅጥቅጥ/ ደግሞ ከ1 እስከ 2 ብር ጭማሪ ተደርጓል ብለዋል።

አዲሱ የዋጋ ጭማሪ ከነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጋር ብቻ የተያያዘ መሆኑን አንስተዋል።አሊያንስ አዉቶቡሶች ከሚዲባስ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ጭማሪው እንደሚመለከታቸው እና አንበሳ እና ሸገር አዉቶቡሶች ግን በመንግሥት ድጎማ ስር በመሆናቸው ማሻሻያ እንዳልተደረገባቸው ተገልጿል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa