ሩሲያ በታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ከነዳጅ እንደምታገኝ ገለጸች
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገባችበት ጦርነት የዓለም ነዳጅ ዋጋን በማናር ላይ ይገኛል
ሩሲያ በታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ከነዳጅ እንደምታገኝ ገለጸች።
የሩሲያ ፋይናንስ ሚኒስትር እንዳሉት በተያዘው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት ተጨማሪ 14 ቢሊዮን ዶላር ነዳጅ እንደምታገኝ ይጠበቃል።
ሚኒስትሩ አንተን ሲሉአኖቭ እንደተናገሩት ባለፈው ዓመት ሩሲያ ከነዳጅ ገበያ ያገኘችው ዓመታዊ ገቢ 9 ቢሊየን ዶላር ነበር።
በተያዘው ዓመት ተጨማሪ 14 ቢሊየን ዶላር ነዳጅ እንደምታገኝ የገለጸችው ሩሲያ፤ ገቢውን የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚዋን ለማረጋጋት እንደምታውለውም ሚኒስትሩ አክለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ከዩክሬን ጋር ለጀመረችው ጦርነት ወጪ እንደምታውለውም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከጀመረች ሶስት ወራት አልፎታል።
ጦርነቱን ተከትሎም በአሜሪካ አስተባባሪነት ከ6 ሺህ በላይ ማዕቀቦችን የተለያዩ ሀገራት በሩሲያ ላይ ጥለዋል።
ሩሲያም ወዳጅ አይደሉም ያለቻቸውን ሀገራት ነዳጇን በሩብል እንዲከፍሉ ትዕዛዝ ማስተላለፏን ተከትሎ የአውሮፓ ኩባንያዎች ነዳጅ በሩብል መግዛት ጀምረዋል።
ጀርመን እና ጣልያን ከሩሲያ ነዳጅን በሩብል ለመግዛት ወሰኑ 40 በመቶ የአውሮፓ ሀገራትን ነዳጅ ፍላጎት የምታሟላው ሩሲያ ነዳጇን እንዳትሸጥ ማዕቀብ ቢጣልባትም ሀገራት ግን ምርጫ አጥተው አሁንም የሩሲያን ነዳጅ በመግዛት ላይ ናቸው።
በዚህ ጦርነት ምክንያት የዩክሬን ዋና ዋና የሚባሉ ከተሞችን ጨምሮ የንግድ ማሳለጫ ወደቦች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ወድመዋል።
Via:- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa

በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ!
በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡የትራፊክ አደጋው የደረሰው 13 ሰዎችን አሳፍሮ ከእንጦጦ ወደ ቁስቋም ይጓዝ የነበረ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ገደል ውስጥ በመግባቱ ነው፡፡
በዚህም የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ÷ አሽከርካሪዎች በኃላፊነት ስሜት ፍጥነታቸውን ቀንሰው በማሽከርከር የዜጎችን ህይወትና ንብረት ከአደጋ መጠበቅ አለባቸው ብለዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

በመዲናዋ የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ ነው!
በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰቶችን በተሻለ መልኩ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለ አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አስታወቀ።የህዝቡ ተሳትፎ ማነስ፣ የአንዳንድ ደንብ ተቆጣጣሪዎች የግንዛቤ ማነስና የሥነ ምግባር መጓደል እንዲሁም የአንዳንድ አስፈፃሚ አካላት ጣልቃ ገብነት ለደንብ ማስከበር በችግርነት ከሚነሱት መካከል እንደሚጠቀሱ ተገልጿል።
የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ደሳለኝ ፉፋ፤ የደንብ መተላለፍ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት አዲስ የአሠራር ሥርአት መዘርጋት ማስፈለጉን ገልጸዋል።
የመሬት ወረራ፣ ህገ ወጥ ግንባታ፣ የጎዳና ላይ ንግድን ጨምሮ ሌሎችንም ለመከላከልና ለመቆጣጠር የደንቡ መዘጋጀት ወሳኝ መሆኑንም አብራርተዋል።በሰው ኃይል እስከ ታችኛው እርከን በባለሥልጣኑ አዲስ አደረጃጀት ተሠርቶ መጠናቀቁን ጠቁመው ይህም የደንብ መተላለፎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያግዛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሳምንት ለ240 ሺሕ ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለለት የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ!
በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው እና በሳምንት ለ240 ሺሕ ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።ማዕከሉ በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን ባሟላው አዲስ ህንፃ ላይ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ነው የተገለፀው።
በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ዜጎች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል የተባለለት ማዕከሉ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች በነፃ አገልግሎቱን በመስጠት ተስፋ እንደሚሆንም ተጠቁሟል።ማዕከሉ በነገው ዕለት እንደሚመረቅም ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አትሌት አንዷለም በላይ የኦታዋ ማራቶን የቦታውን ሰዓት በማሻሻል ጭምር አሸነፈ
*
አትሌት አንዷለም በላይ በካናዳ የኦታዋ ማራቶን የቦታውን ሰዓት በማሻሻል ጭምር አሸንፏል፡፡
አትሌት አንዷለም ውድድሩን በበላይነት የጨረሰው 02:06:03 በሆነ ሰዓት በመጨረስ ነው፡፡
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ተሾመ መኮንን ውድድሩን 4ኛ ሆኖ ጨርሷል።
ለባህሬን የሚሮጠው አብዲ ዓሊ እና ጃፓናዊ ዩታ ሺሞዳ ውድድሩን በሁለተኛ እና ሶስተኛነት አጠናቀዋል፡፡
Via EBC

👍1
በአሜሪካ "ባልሽን እንዴት መግደል ይቻላል" የሚል ድርሰት የጻፈችው ግለሰብ ባሏን በመግደል ወንጀል ጥፋተኛ ተባለች
ደራሲዋ ክራምፕተን-ብሮፊ በአንድ ወቅት "ባልሽን እንዴት መግደል ይቻላል" በሚል ርዕስ አንድ ዝነኛ ድርሰት የፃፈች ሴት ስትሆን ፤ ይህችው አሜሪካዊት የፍቅር ታሪክ ደራሲ የትዳር ጓደኛዋን በመግደል ወንጀል ተቀጥታለች።
በፖርትላንድ ኦሪገን ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ መሰረት
በምግብ ዝግጅት ላይ የነበረውን ባለቤቷን ዳንኤል ብሮፊን በመግደል ናንሲ ክራምፕተን ብሮፊ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመስጠት ስምንት ሰአት ፈጅቷል።ሁለት ጊዜ ልቧ ላይ ተኩሳ ከመምታቷ በፊት በደራሲዋ እና በባለቤቷ መካከል የፋይናንስ ውዝግብ እንደነበራቸው አቃቤ ህግ ተናግሯል።
የባለቤቷ ሞት ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ የህይወት ኢንሹራንስ ካሳ እና ሌሎች ንብረቶችን እንድታገኝ ያስችላይ እንደነበር በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ተብራርቷል።
[ ዳጉ ጆርናል]

በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮችን ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊየን ብር በላይ መመዝበሩን በፍትህ ሚኒስቴር የተደረገ ጥናት አመላከተ።
ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው በዚህ ጥናት ከ370 ቢሊየን ብር በላይ በባንኮች ላይ ማጭበርበር ተሞክሮ እንደነበር ተመላክቷል።
ጥናቱን ተከትሎ የፍትህ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የተለያዩ ባንኮች ፕሬዚዳንቶች፣ የኢትዮ ቴሌኮምና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።
ጥናቱ በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች መንስኤዎቻቸው እና የአፈጻጸም ዘዴያቸውን በመለየት የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማቅረብ በፍትህ ሚኒስቴር የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውይይቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮችን ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊየን ብር በላይ መመዝበሩን የተደረገው ጥናት አመላክቷል።
Via :- FBC

በሀሰተኛ ማስረጃ የ276 ሚሊዮን ብር የግልግል ዳኝነት ያልተገባ ውሳኔ ሰጥተዋል ተብለው የተከሰሱት ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ።
በሀሰተኛ ማስረጃ የ276 ሚሊዮን ብር የግልግል ዳኝነት ያልተገባ ውሳኔ ሰጥተዋል ተብሎ በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱት ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችና ግብረአበሮቻቸው ላይ የዐቃቤ ህግን ማስረጃዎች መርምሮ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጧል።
ተለዋጭ ቀጠሮውን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት ነው።
ዐቃቤ ህግ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በነበሩት አዱኛ ነጋሲ߹ አክሊሉ ዘሪሁንና ግብረ አበሮቹ ላይ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ክስ መመስረቱ ይታወሳል ።
ዐቃቤ ህግ በሀሰተኛ ማስረጃ የ276 ሚሊዮን ብር የግልግል ዳኝነት ያልተገባ ውሳኔ ሰጥተዋል ብሎ በከባድ የሙስና ወንጀል የከሰሳቸው ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችና ግብረአበሮቻቸው ላይ አስር (10) የምስክሮችን ቃል ሲያሰማ ሌሎች ገላጭ ማስረጃዎችን ደግሞ ዛሬ ግንቦት 15/2014 ዓ.ም በፅ/ቤት እንዲደርሳቸው ተደርጓል ።
በዚህ የዐቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመላከተው 1ኛ ተከሳሽ አዱኛ ነጋሲ ሲመለከት ነበር በተባለው 11ኛ የፍታብሔር የአፈጻጸም ችሎት በዳዊት ገ/እግዛብሔርና በቱፋ ጣፋ መካከል በስራ ግንኙነት ሳይከፈል የቀረ 276 ሚሊዮን ብር እና 9 ከመቶ ወለድ 250 ሺህ የግልግል ዳኝነት ክፍያ በጥቅምት 10 ቀን 2009 ዓ/ም የተከፈተ መስሎ በሀሰተኛ ሥም በተዘጋጀ ሀሰተኛ የግልግል ዳኝነት መዝገብ ለአንደኛ ተከሳሽ ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ ከዐቃቤ ህግ 1ኛ ምስክር ጋር በ2ኛ ተከሳሽ አክሊሉ ዘሪሁን አደራዳሪነት በተለያዩ ቀናትና ቦታዎች በመገናኘት 3 ሚሊዮን ብር እና የ2 ሚሊዮን ብር ቼክ ከ4ኛ ተከሳሽ በመቀበል እንዲሁም ዐቃቤ ህግ ጓደኛቸው ነው ባለው እስከዳር አሰፋ በተባለ ግለሰብ የንግድ ባንክ ሒሳብ 400 ሺህ ብር ገቢ እንደተደረገላቸው ዐቃቤ ህግ በክሱ ላይ መጥቀሱ ይታወሳል ።
በተጨማሪም በአቶ ዳዊት ገ/እግዛብሔር ሥም በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የነበረ 276 ሚሊዮን ብር “ቱሉ ጣፉ” ተብሎ በሀሰት ሥም በተከፈተ ቡና ባንክ እንዲገባ ያለአግባብ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሎ በዐቃቤ ህግ ክስ መመስረቱ ይታወሳል ።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት ዐቃቤ ህግ በክሱ ላይ የጠቀሳቸው ገላጭ ማስረጃዎችን ለመጠባበቅ ደግሞ ለዛሬ ግንቦት 15/2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር በዚህም መሰረት ዐቃቤ ህግ በክሱ ላይ የጠቀሳቸውን ገላጭ የሰነድ ማስረጃዎች በፅ/ቤት ለተከሳሾች እንዲደርሳቸው ተደርጓል ።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች በቀረበባቸው ማስረጃዎች ላይ አስተያየታቸውን ከቀጠሮ በፊት እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሲሰጥ ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ያቀረባቸውን ማስረጃዎች መርምሮ ብይን ለመስጠት ደግሞ ለግንቦት 30/2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት የዕለቱ ችሎት ተጠናቋል ።
(ፍትህ ሚኒስቴር)

ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በዋስትና እንዲለቀቁ የቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገ!
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ዛሬ ተመልክቷል።የመርማሪ ቡድኑ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ እና የተለያዩ ማስረጃዎችን ከባንክ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከኢሳት እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት የሚሰበስባቸው መረጃዎች በመኖራቸው ለ14 ቀናት ተጨማሪ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው አስፈላጊ ናቸው የተባሉት መረጃዎች የሚሰበሰብባቸው ተቋማት የመንግስት ስለሆኑ እና ጊዜ የሚወስዱ ስላልሆኑ ተከሳሽ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ በዋስትና እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።
ይሁን እንጂ የምርመራ ቡድኑ የጠበቃውን በዋስትና ይለቀቁልኝ ክርክር በመቃዎም ተከሳሹ ከእስር ቢለቀቁ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያጠፉብናል፤ በዚህ ምክኒያት በእስር ሊቆዩ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ካደመጠ በኋላ ከተጠየቀው 14 ቀን የ10 ቀናት ብቻ ተጨማሪ ቀጠሮ በመስጠት ለሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ቀጥሯል።
[Addis Zeybe]

የቤንዚን፣ ናፍጣ እና ኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተባለ!
በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ ናፍጣ እና ኬሮሲን (ነጭ ጋዝ) የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የተጠቀሱት ምርቶች መሸጫ ዋጋ በዓለም ገበያ ቢጨምርም መንግሥት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል የምርቶቹ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዓለም ዐቀፍ ዋጋ ተሰልቶ የመጣው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።

በመጪው የክረምት ወቅት ጎርፍና መሰል አደጋዎች ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።
ሰሞኑን የታየው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የመጣ መሆኑ ተጠቁሟል።በኢንስቲትዩቱ የአየር ሁኔታና የአየር ጠባይ ትንበያ ባለሙያው ታምሩ ከበደ እንደገለጹት፤በቀጣዩ ክረምት ወቅት ከመደበኛው በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ትንበያዎች ያመለክታሉ።
የላሊና የአየር ጠባይ ለውጥ ሳቢያ በአገሪቱ በበልግም ሆነ በመኸር ወቅቶች ደረቅ ወራት በዝተው መስተዋላቸውን የገለጹት ባለሙያው ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሓምሌና ነሀሴ ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ይችላል ብለዋል።በተለይም በአገሪቱ በሰሜን ምስራቅና በምስራቅ አካባቢዎች ላይ ዝናቡ እየጨመረ እንደሚሄድ ጠቁመዋል።
ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው ከፍተኛ የሙቀት መጠን የላሊኖ ተፅእኖ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ጋር ተያያዥ መሆኑን ለጎርፍ አደጋ ሥጋት እንደሚሆንም አብራርተዋል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ የጎርፍ አደጋ ሥጋት ያለባቸው አካባቢዎች ከወዲሁ አደጋዎች እንዳይፈጠር ኅብረተሰቡም ሆነ ተቋማት ከወዲሁ የመከላከል ሥራ ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል።በተለይ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ፣በወንዞችና ተዳፋታማ አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተጠናከረ የጥንቃቄ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በአገሪቱ የተከሰተው ላሊና የመኸርና በልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑትን የቦረና፣ባሌ ሶማሌና ደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች በቂ ዝናብ እንዳያገኙ ምክንያት መሆኑንም አስታውሰዋል።የአደጋ ሥጋትና አመራር፣ ጤና ሚኒስትር፣ ግብርናና ሌሎች መሰል የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላሊኖ የሚፈጥረውን አደጋ ለመመከት ከወዲሁ አስፈላጊ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ከግንቦት ወር መጀመሪያ ጀምሮ የሙቀቱ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በከተሞች መስፋፋትና የውኃ አካላት መመናመን ምክንያት መሆኑንም ነው ያነሱት።ኅብረተሰቡም የተለያዩ ተክሎችን በመትከልና በመንከባከብ የአየር ንብረት ለውጥን የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች መቋቋም እንደሚገባ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ባለሀብቶችን በማገት እና በማስፈራራት ብር በጠየቁ የሰራዊቱ አባላት ላይ ክስ ተመሠረተ!
ባለሀብቶችን በመሰለል፣ በማገት እና በማስፈራራት 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በጠየቁ እና በተቀበሉ አራት የመከላከያ ሚኒስቴር አባላት እና ግብረ-አበሮቻቸው ላይ ሥልጣንን አላግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ስር ክስ መመሥረቱን ፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ክሱ የተመሠረተው የመከላከያ መኪና በመያዝ “ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሀብት ማስመለስ የመጣን ዐቃቤ ሕጎች ነን፤ ሕገ-ወጥ ዘይት፣ ስኳር እና የጦር መሣርያ ስለምትሸጡ በወንጀል ትፈለጋላችሁ” በማለት 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በጠየቁ የመከላከያ ሚኒስቴር አባላት እና ግብረ-አበሮቻቸው ላይ ነው።
የተለያዩ የምርምራ ሂዶትችን ከፖሊስ ጋር ሲያከናውን ቆይቶ በግለሰቦች ላይ ክሱን የመሠረተው ደግሞ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል መሆኑ ተገልጿል።
ወንጀሉን ፈጽመዋል በሚል ክስ የተመሠረተባቸው በመከላከያ ሚኒስቴር በ93ኛ እና 94ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር አባል የሆኑት 1ኛ) መቶ አለቃ ሀጂ ቱሉ߹ 2ኛ) ኦፊሰር መንግሥቱ በቀለ߹ 3ኛ) ሻምበል ካህሊ መላክ߹ 4ኛ) ሻለቃ ዱጉማ ዲምሳ እና በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ውስጥ ተሰማርተው የሚገኙት ግብረ-አበሮቻቸው ከ5ኛ-8ኛ ስማቸው በክሱ የተጠቀሰው ተከሳሾች ሹምበዛ ፍቃዱ፣ አዲስ ዓለሙ፣ ተስፋዬ ለሚ እና አሸናፊ ወልደ ሰማያት መሆናቸውን ከፍትሕ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ችሎቱ በቁጥጥር ስር ያልዋሉትን 7ኛ እና 8ኛ ተከሳሽን ፖሊስ አፈላልጎ አንዲያቀርብ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን ተከሳሾች በተመሰረተባቸው ክስ ላይ የመጀመርያ የክስ መቃወሚያና ባልተያዙ ተከሳሾች ላይ የፖሊስን ምላሽ ለመጠባበቅ ለግንቦት 29/2014 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል።

የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ በሮሃ ሜዲያ የየትዩብ ብዙኀን መገናኛ አዘጋጅ መዓዛ ሞሐመድ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንደፈቀደ ሮሃ ሜዲያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ገልጧል።
መርማሪ ፖሊስ መዓዛን "ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት" ወንጀል እንደጠረጠራት ካስረዳ በኋላ፣ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል። የተጠርጣሪዋ ጠበቆች በበኩላቸው፣ ተጠርጣሪዋ ከጋዜጠኝነት ሥራዋ ውጭ የሰራችው ወንጀል እንደሌለ በመጥቀስ ጉዳዩ በመገናኛ ብዙኀን አዋጁ መታየት አለበት ሲሉ ተከራክረዋል። ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው በሁለቱ ወገኖች ክርክር ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነው።

1ሺህ 76 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!
ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 76 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።ከእነዚህ ውስጥ ሶስት ህጻናትና 1073 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 30 ሺህ 198 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

የትግራይ ክልል መንግሥት የኤርትራ ሠራዊት ትናንት እና ከትናንት ወዲያ የሽራሮ ከተማን በከባድ ጦር መሳሪያ ደብድቧል ሲል ዛሬ ማምሻውን በኮምንኬሽን ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ ከሷል።
የክልሉ መንግሥት መግለጫ በሽራሮው የከባድ መሳሪያ ድብደባው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል።
የክልሉ መንግሥት መግለጫ ባለፉት ሁለት ቀናት የኤርትራ ጦር በሽራሮ በኩል ጥቃት የከፈተው፣ ባለፈው ግንቦት 16 በምዕራብ ትግራይ ዓዲ አውዓላ አካባቢ የከፈተው ጥቃት የትግራይ ኃይሎች በወሰዱት አጸፋ ከሽፎ ጦሩ ክፉኛ በመመታቱ ነው ብሏል። የትግራይ ኃይሎች በውጊያው አንድ የኤርትራ ጦር ብርጌድ አዛዥ እና ሦስት የሻለቃ አዛዦች የሚገኙባቸው 120 ወታደሮችን ገድለው 195 ያህሉን እንዳቆሰሉ እና አራት ወታደሮችን እንደማረኩ ገልጧል። አንድ ድሽቃ፣ አምስት የወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛዎች እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እንደተማረከም መግለጫው ጨምሮ አውስቷል።
የክልሉ መንግሥት በዚሁ መግለጫው፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኤርትራን መንግሥት ድርጊት በቃ ለማለት እጅጉን ቢረፍድበትም፣ ፈጽሞ ግን አልመሸበትም በማለት መግለጫውን ቋጭቷል።
[ዋዜማ ራዲዮ]

በደሴ በተከሰተ የእሳት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ!
በደሴ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ አራዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በድርጅትና መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የተከሰተ የእሳት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ ገለጸ፡፡የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ጥላሁን ፈንታው ለኢዜአ እንደገለጹት ፥ ከለሊቱ 6 ሰዓት ገደማ የተቀሰቀሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ርብርብ ሲያደርጉ በነበሩ ሰዎች ላይም ጉዳት አስከትሏል።
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሰዓቱ ወደ ህክምና ተቋም ሄደው እርዳታ እንዲያገኙ እንደተደረገም ተናግረዋል።“የእሳት አደጋው የተነሳበት አካባቢ አሮጌ እቃዎች የሚከማቹበትና ያረጁ ቤቶች ያሉበት በመሆኑ በቀላሉ ለማጥፋት ፈታኝ ቢሆንም በህብረተሰቡ ርብርብ እሳቱ ሳይስፋፋ መቆጣጠር ተችሏል” ብለዋል፡፡የእሳት አደጋ ማጥፊያ ተሸከርካሪ ከኮምቦልቻ ከተማ ጭምር መጥቶ ለማጥፋት ርብርብ መደረጉን ጠቁመው ፥ በቅንጅት አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።የአደጋው መንስኤ፣ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት፣ የተቃጠሉ ቤቶችና ሌሎችንም የሚያጣራ ቡድን ወደ ቦታው ተልኮ ስራ መጀመሩን ኃላፊው ተናግረዋል።

መንግስት፤ የህወሃት እና የኤርትራ ግጭት ወደ ኢትዮ- ኤርትራ ግጭት እንደማያመራ ገለጸ!
የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ቅዳሜ እና ዕሁድ ዕለት የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ በኩል ጥቃት ከፍቶ እንደነበር ቢገልጹም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ቀድሞ ትንኮሳ ያደረገው ህወሃት እንደሆነና በዚህም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ብሏል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናገሩት ህወሃት የኤርትራ ጦር ጥቃት ከፈተ በሚል የሚያሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም፡፡
በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወሃት ኤርትራን እየተነኮስ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ገልጿል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:
https://am.al-ain.com/article/ethiopia-says-eriterea-tplf-clash-won-t-evolve-into-ethio-eriterea-conflict

በሰበታ የተገነባው የኮካኮላ ፋብሪካ ተመረቀ!
ፋብሪካው የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተመረቀው።ዛሬ በሰበታ ከተማ የተመረቀው ፋብሪካ ኮካኮላ ምርት ከሚያመርትባቸው ፋብሪካዎች 5ኛው ቅርንጫፍ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ በኢድ አል ፈጥር በዓል ላይ ከፈነዳው የአስለቃሽ ጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር የዋለው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ለአንድ ሳምንት በር ተዘግቶበት መታሰሩን ለፍርድ ቤት አስታወቀ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል የመከላከል አድማ ብተና አባል የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ሶስተኛ ጊዜ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀረቦ ጉዳዩ ታይቷል።
መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት ከግንቦት 10 ቀን ጀምሮ በተሰጠው የ13 ቀን የምርመራ ጊዜ ውስጥ የሰራውን የምርመራ ስራ ሪፖርት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
በዚህም የተጠርጣሪው ቃል የመቀበል ስራ መሰራቱን ለተጠርጣሪው የገንዘብ ድጋፍ መኖርና አለመኖሩን ለማጣራት ለ18 ባንኮች ደብዳቤ መላኩን :የግል ስልኩ ላይ ለኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለብሔራዊ መረጃ ደህንነት ተቋም ደብዳቤ ልከው ውጤት እየተጠባበቁ መሆናቸውን እና የስልክ ቁጥር በማን ስም እንደወጣ ለማጣራት በኢትዮ ቴሌኮም በኩል እንዲጣራ መጠየቁን እንዲሁም የፈነዳውን አስለቃሽ ጭስ ቦንብ ፍንጣሪ በፎረንሲክ ምርመራ እንዲደረግ መላኩንና የምስክር ቃል መቀበሉን ለችሎቱ አስረድተዋል።
በፍርድ ቤቱ ዳኛ በኩል የስንት ምስክር ቃል እንደተቀበለ ለመርማሪ ፖሊስ ለቀረበ ጥያቄ የአንድ ሰው ምስክር ቃል ተቀብለናል የ3 ምስክር ቃል ይቀረናል በማለት ምላሽ ሰቷል።
ምስክሮቹ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከሆኑ አስካሁን ለምን አልተቀበላችሁም ለሚለው ጥያቄ ደግሞ አንደኛው ምስክር ለስራ ሌላ ቦታ በመሄዳቸውና ሌሎቹም ስራ ላይ በመሆናቸው ምክንያት መቀበል አለመቻሉን መርማሪ መልስ ሰቷል።
ተጠርጣሪው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በበኩሉ ከሻንጣዬ ጀምሮ ብርበራ ተደርጎል ነገር ግን ምንም ማስረጃ አላገኙብኝም እኔ ምንም ወንጀል አልሰራሁም ከታሰርኩበት ጊዜ ጀምሮ ውሃ እንኳን የሚሰጠኝ ጠያቂ የለኝም አንድ ሳምንት በር ተዘግቶብኝ ታስሬ ነበር ሲል ለችሎቱ ገልጿል።
በአሁን ወቅት ያለበት የስር ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በችሎቱ ዳኛ የተጠየቀው ኮንስታብል አንቡላ አሁን አ/አ ፖሊስ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዲሆን መደረጉን መልስ ሰቷል።
ፍርድ ቤቱ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ አስቀርቦ ከተመለከተ በኋላ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ማስረጃ ማሰባሰቡን እንዲሁም የ3 ሰዎች ምስክር ቃል መቀበልና ቀሪ ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረው ማረጋገጡን ገልጿል።በዚህ መልኩ የጀመረውን ምርመራውን ፖሊስ አጠናቆ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ የ10 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል።የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቆ ለሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።
Via Tarik Adugna

ሶስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በአማራ ክልል አለ ያሉት “አፈና” እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ!
ሶስት ተቃዋሚ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአማራ ክልል እየተደረገ ነው ያሉት “መንግስታዊ አፈና” እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ። ፓርቲዎቹ በጋራ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 23፤ 2014 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሌላ ውድመት እንዳያደርስ የሰላም አማራጮች ሁሉ እንዲተገበሩም ጠይቀዋል።
የጋራ መግለጫውን የሰጡት እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ናቸው። ሶስቱ ፓርቲዎች በአዲስ አበባ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የመኢአድ ዋና ጽህፈት ቤት የሰጡት መግለጫ ዋነኛ ትኩረቱ መንግስት ከሰሞኑ እያካሄደው የሚገኘው “የህግ ማስከበር ዘመቻ” ነው።
ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ጋዜጠኞች፣ ማህበረሰብ አንቂዎች፣ የፋኖ አባላት፣ ምሁራን፣ ተመላሽ የጸጥታ አባላት እና የፖለቲካ አመራር አባላት “በህግ ማስከበር ሰበብ ታፍነዋል” ሲሉ ወንጅለዋል። መንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻውን “የማህበረሰቡን ቅስም ለመስበር፣ የኃይል ሚዛንን ለማስጠበቅ፣ መሪ ለማሳጣት እና በዚሁ አጋጣሚ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ምሁራንን፣ ጋዜጠኞችን፣ የማህበረሰብ አንቂዎችን ከመከላከያና ልዩ ኃይል ተመላሾችን ለማሳደድ እየተጠቀመበት ነው” ሲሉም ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ከስሰዋል።
[Ethiopia Insider]