YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
“የመዲናዋ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ይቀባሉ" የሚል ዉሳኔ አልተላለፈም ተባለ፡፡

የአዲስ አበባ ህንፃዎች ሁሉ ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስታወቁ።የቢሮ ኃላፊው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የህንፃ ስታንዳርድና የውጭ ማስታወቂያ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህን መነሻ አድርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች አዲስ ከተማ ግራጫ ቀለም ልትቀባ ነው በሚል በስፋት ሲዘዋወር የታየው መረጃ የተሳሳተ ነው፡፡

እስካሁን ድረስ የከተማዋ ህንጻዎች ቀለም ምን አይነት ይሁን የሚለው ጉዳይ ለውይይት ቀረበ እንጂ የከተማ አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳላሳለፈ አመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይም ከዚህ ቀደም ‹‹ከተማችን ቡራቡሬ ሆና ባለቤት አልባ መስላለች›› ማለታቸውን ያስታወሱት የቢሮ ኃላፊው፤ ይህን ችግር ማንኛውም የመዲናዋ ነዋሪም ሊታዘብ ይችላል። የከተማ አስተዳደሩም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል።ችግሩን ለመፍታት የውጭ ማስታወቂያውና የከተ ማዋ ቀለም ሁኔታ የሚመራበት ስታንዳርድ ዝግጅት ተደረገ እንጂ ውሳኔ ላይ አለመድረሱን ጠቁመዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=73364

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ጎንደር ዞን ስር ያሉ ሁሉም ያልተፈተኑና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በቀጣይ አመት እንደሚፈተኑ ተገለጸ።

ተማሪዎቹ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሃገር አቀፍ ፈተናውን ያልወሰዱና ፈተናውንም ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በቀጣይ አመት በሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከክልል በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የቲቶሪያል ትምህርት በወረዳቸው ከሚገኘው አዲምህረት ትምህርት ቤት ከግንቦት ወር ጀምሮ እንደሚሰጡ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ አጸደ በሬ አሳውቀዋል።

በቀጣይ ሁለት የክረምት ወራቶች የማጠናከሪያ ትምህርት እንደሚሰጥ የገለጹት ወ/ሮ አጸደ በሬ በተለያዩ ምክንያት ከወረዳው ውጭ የሚገኙ ተማሪዎችንና ወደ ወረዳው መሄድ የማይችሉ ተማሪዎችን የተማሪ መታወቂያ አይዲ ካርድ ይዘው በደባርቅ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤት ከአዲ አርቃይ ከተማ ተማሪዎች ጋር መማር እንደሚችሉ አሳውቀዋል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በሰሜኑ የሃገሪቷ ክፍል በነበረው ጦርነት በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተገንዝቦ በ2013 ዓ.ም ኦንላይን ተመዝግበው ሃገር አቀፍ የ 12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱና ፈተናውን ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ከ 2014 ዓ.ም ተፈታኞች ጋር በድጋሚ ፈተናውን እንዲፈተኑ ከሃገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በጋራ መወሰናቸው የሚታወስ ነው።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በ12 አገራት ወደ 80 የሚጠጉ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ) መያዛቸው መረጋገጡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የአገራቱን ስም ሳይገልጽ ሌሎች 50 ተጠርጣሪዎችም በምርመራ ላይ መሆናቸውንም የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።መጀመሪያ በአውሮፓ መታየቱን ተከትሎ ቀደም ሲል በጣሊያን፣ በስዊድን፣ በስፔን፣ በፖርቱጋል፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሽታው መኖሩ ተረጋግጧል።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በብዛት በመካከለኛው እና በምዕራብ አፍሪካ አካባቢዎች በብዛት የሚከሰት ነው።

የእንግሊዝ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት እንደገለጸው፣ ይህ ያልተለመደ የቫይረስ ኢንፌክሽን አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ሲሆን ብዙዎች ላይም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚድን ነው።ቫይረሱ በሰዎች መካከል በቀላሉ የማይሰራጭ ሲሆን በሰፊው ሕዝብ ጤና ላይ የሚያስከትለው ስጋት በጣም ዝቅተኛ ነው ተብሏል።

ለዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተለየ ክትባት የለም። ከመደበኛው ፈንጣጣ ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው የፈንጣጣ ክትባት 85 በመቶ የመከላከል አቅም ይሰጣል።የዓለም ጤና ድርጅት አርብ ዕለት በሰጠው መግለጫ "በቅርብ ጊዜ በ11 አገሮች የተመዘገበው ወረርሽኞች ተላላፊ ባልሆኑ አገሮች ውስጥ መከሰቱ ያተለመደ ነው" ብሏል።

"ተጎጂዎችን ለማግኘት፣ ለመደገፍና የበሽታ ክትትልን ለማስፋፋት ከተጎዱት አገራት እና ከሌሎች ጋር እየሠራሁ ነው" ብሏል።በተጨማሪም ድርጅቱ በበሽታው ምክንያት ማግለል እንዳይኖር አስጠንቅቋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
“የመዲናዋ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ይቀባሉ" የሚል ዉሳኔ አልተላለፈም ተባለ፡፡ የአዲስ አበባ ህንፃዎች ሁሉ ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስታወቁ።የቢሮ ኃላፊው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ…
#update

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ ማብራሪያ ሰጠ!

አስተዳደሩ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እንድትሆን እና ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚመጥን ገፅታ እንዲኖራት ከሚሠሩ ሥራዎች አንዱ የሕንጻዎችን ቀለምና ቁመት የሚወስን አሠራርን መተግባር መሆኑን አስታውቋል።

በእስካሁኑ ሂደት የከተማዋ ሕንጻዎች ያለምንም ቁጥጥርና ወጥነት በጎደለው መንገድ የሚቀቡ ቀለማት የከተማዋን መልክ ቡራቡሬና ዥንጉርጉር ከማድረጋቸውም በላይ÷ የሚገነቡ ሕንጻዎች ዲዛይን በዘፈቀደ መሠራቱ የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ ጎድቶታልም ነው ያለው አስተዳደሩ፡፡

ስለሆነም ይህን ችግር መልክ ለማስያዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከብዙ ዓለም አቀፍና አፍሪካዊ ከተሞች ተሞክሮ በመውሰድ÷ ለከተማዋ የሚስማማ የሕንጻ ቀለማት ደረጃን አጥንቶ ለውይይት አቅርቧል፡፡በመሆኑም በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች በተሳተፉበት ሁኔታ ዝርዝር ጥናት በማድረግ ለከተማዋ የሚስማሙ 13 ዓይነት ቀለማት መለየታቸውን ገልጿል።

በዚህ መሰረት በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ለከተማዋ በመለያነት ከተመረጡ ቀለማት መካከል የሕንጻ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን÷ ይህ አሠራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ መገባቱንም ነው ያስታወቀው፡፡

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር ወጪ አዲስ ቤተ መንግሥት ሊገነባ መሆኑ ተነገረ!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር ወጪ አዲስ ቤተ መንግሥት ሊገነባ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ። ለቤተ መንግሥቱ ግንባታ የተያዘለት በጀት ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ በኋላ ከፍተኛ ወጪ የሚወጣበት የመንግስት ሜጋ ፕሮጀክት እንደሚሆን ዘገባው አመላክቷል።በየካ ክፍለ ከተማ የሚገነባው አዲስ ቤተ መንግስት ከሚያካትታቸው ግንባታዎች መካከል ልዩ ልዩ አዳራሾች፣ የመኖሪያ ቤቶች፣ ሦስት ሠው ሰራሽ ሐይቆችና መንገዶች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በመንግስት የ10 አመት ዕቅድ ውስጥ የተካተተው ይህ ፕሮጀክት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ከይዞታቸው የሚያስለቅቅ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ ቤተመንግቱ የሚገነባበትን ስፍራ ደረጃ የሚመጥን ሆኖ ከተገኘ በቦታው ላይ ራሳቸው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት ግንባታ እንዲያከናውኑ ዕድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።ዘገባው የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች መንግስት የፕሮጀክቱን የተወሰነ ወጪ በድጋፍ መልክ እንደሚሸፍን ምንጮቼ ነግረውኛል ብሏል።

በቦታው 15 ቢሊዮን ብር ያወጣል ተብሎ የሚገመተውን የ20 ኪሜ የመንገድ ግንባታ ስራ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መጀመሩ የታወቀ ሲሆን ወደ 9 ኪሜ የሚሆነውን ስራ ማጠናቀቁም ታውቋል።

ግንባታውን የሚያስተባብሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አካላት፣ አዲሱን የቤተ መንግሥት ግንባታ ፕሮጀክት 'ጫካ' ፕሮጀክት የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል፡፡የአዲሱን ቤተ መንግስት ግንባታ ተከትሎ አሁን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መኖሪያ ሆኖ የሚያገለግለውን የምኒልክ ቤተ መንግሥት እንዲሁም የኢዮቤልዩ ቤተመንግስትን ብሔራዊ ሙዝየም የማድረግ እቅድ መያዙም ተጠቅሷል።

[Reporter/✍️ Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በአራት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተዘጋጅቶ በቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ነው፡፡የፌደራል አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አስፈጻሚ ተቋማት ከተሰጣቸው ስልጣንና ተግባራቸው ጋር የሚመጣጠን የሰው ሃይል እንዲኖራቸው የሚያስችል የአደረጃጀት ማሻሻያ ማድረጋቸውን ተከትሎ በቀጣይ ሊፈጸሙ ስለሚገባቸው አቅጣጫዎች በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው ስለኢንቨስትመንት ማበረታቻ በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን የግሉ ዘርፍ ለአገር የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ድርሻ ያለው በመሆኑ ዘርፉ ያለውን ሀብት መንግሥት ትኩረት በሚሰጣቸው የልማት መስኮች ላይ በማዋል ለኢኮኖሚ ዕድገት ተገቢውን አስተዋፅኦ ማድረግ እንዲችል የሚያበረታቱ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤ በተለይም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር የውጭ ካፒታል ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት በአጠቃላይም ለማህበራዊ ኑሮ መሻሻል አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችልበትን መሠረት መጣል የሚገባ መሆኑን ከግምት በማስገባት እንዲሁም የተሰጠው ማበረታቻ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ የሚያስችል የክትትል ሥርዓት የሚዘረጋ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ግብዓቶች በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በጉምሩክ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ የአገራችንን የወጪና የገቢ ንግድ ሥርዓት ከሚመሩ ሕጐች መካከል የጉምሩክ መጋዘን አስተዳደርን እና የጉምሩክ አስተላላፊዎችን በሚመለከት የወጡ ደንቦች ይገኙበታል፡፡ እነዚህን ደንቦች በአንድ በማጠቃለል ዓለም ዐቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ጋር የሚጣጣም፣ በአገራችን እያደገ የመጣውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት የሚደግፍ እንዲሁም ሕጋዊ ንግድን እና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ፣ በስራ ላይ ካለው የጉምሩክ አዋጅ ጋር የሚጣጣም ደንብ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶች በማከል ከጸደቀበት ከዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

ቀጥሎ ምክር ቤቱ ውይይቱን ያደረገው የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን ስልጣንና ተግባር እና አደረጃጀት ለመወሰን በወጣው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የፌደራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 መሰረት የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ መብትና ግዴታዎች እንዲተላለፉለት የተደረገ በመሆኑና በተሻለ አቅም የቁጥጥር ስራውን እንዲመራ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶች በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

[PMOEthiopia]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
በአማራ ክልል የትኛውም አካባቢ ሕጋዊ ጥያቄ ያቀረበም ኾነ ፈቃድ ያገኘ ሰልፍ አለመኖሩን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የተጀመረውን
ህግ የማስከበር ስራ በአጭር ጊዜ እና በዝቅተኛ ጉዳት
ለማጠናቀቅ መላው የጸጥታ መዋቅሩ ከሰላም ወዳዱ ሕዝብ ጋር
ኾኖ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክቷል።

ሕገወጥ ፈቃድ ያላገኘ ሰልፍም ኾነ የጎዳና ላይ ትዕይንት ፈጽሞ
ተቀባይነት የሌለው መኾኑን የገለጸው ቢሮው፤ በዚህ ድርጊት ላይ
በቅስቀሳ እና አመጽ ጥሪ በሚያቀርቡ አካላት ላይ እንዲሁም
በሰልፍ ሰበብ የሕግ ማስከበር ሥራውን ለማደናቀፍ በሚደረጉ
ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊውን የሕግ የማስከበር እርምጃ
የሚወስድ መኾኑን አስታውቋል።

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው
መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል:-

የአማራ ክልል ጸጥታ ምክር ቤት የክልሉን የሰላምና እና ደኅንነት
ሁኔታ በጥልቀት ከገመገመ በኋላ የአሸባሪው ትህነግ ወረራ
ስጋትን ለመመከት ዝግጅት ማድረግ እና የክልሉን አንድነት
የሚሸረሽሩ ሕገወጥ ተግባራትን ማረም አስፈላጊ መኾኑን መወሰኑ
ይታወሳል።

ሕግ የማስከበር ሥራው ዋና ዓላማ ሊቃጣ የሚችልን የአሸባሪው
ትህነግ ድጋሚ ወረራ ለመቀልበስ፣ ለክልላችን ሕዝቦች ሰላም እና
ደኅንነት ዋስትና ለመስጠት እንዲሁም የሚታየውን ሕገ ወጥነት
መልክ በማስያዝ ሕዝቡ እየጠየቀ ያለውን የልማት እና መልካም
አሥተዳደር ጥያቄ ለመፍታት ዓላማ ያደረገ እንደኾነ የክልላችን
ርእሰ መሥተዳድር ለሕዝባችን መግለጻቸው ይታወሳል።


ካለፉት ቀናት ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ሕግ የማስከበር
ሥራ ተጠርጣሪዎች ያለምንም ግጭት እጃቸውን ለሕግ
እንዲሰጡ የማድረግ እንዲሁም እጃቸውን በሰላም ለሕግ
ለመስጠት ፈቃደኛ ያልኾኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት የመቀነስን ሥራ
በመሥራት በሰላም ወዳዱ ሕዝባችን አጋርነት ሕግ የማስከበር
ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

ይህ ሕግ የማስከር ሥራ ለሕዝባችን ሰላም እና ደኅንነት
ለክልላችን እና ሀገራችን የስላም ዋስትናን ዓላማ በማድረግ
እየተከናወነ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከዋና ጠላቶችችን ጋር በማበር
ክልላችንን እና ሀገራችንን ለማፍረስ የሚሠሩ አንዳንድ
የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች እና ግለሰቦች በአንዳንድ
የክልላችን አካባቢዎች ሰልፍ መጥራት እና ለሰላም ማስከብር
ሥራው እንቅፋት የኾኑ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።
ነገር ግን በክልላችን የትኛውም አካባቢ ሕጋዊ ጥያቄ ያቀረበም
ኾነ ፈቃድ ያገኘ ሰልፍ የለም።

ሕግ የማስከበር ሥራውን በአጭር ጊዜ እና በዝቅተኛ ጉዳት
ለማጠናቀቅ መላው የጸጥታ መዋቅራችን ከሰላም ወዳዱ
ሕዝባችን ጋር ኾኖ እየሠራ በሚገኝበት ወቅት እንዲህ አይነት
ሕገወጥ ፈቃድ ያላገኘ ሰልፍም ኾነ የጎዳና ላይ ትዕይንት ፈጽሞ
ተቀባይነት የሌለው መኾኑን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ እየገለጸ
በዚህ ድርጊት ላይ በቅስቀሳ እና አመጽ ጥሪ በሚያቀርቡ አካላት
ላይ እንዲሁም በሰልፍ ሰበብ የሕግ ማስከበር ሥራውን
ለማደናቀፍ በሚደረጉ ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊውን
የሕግ የማስከበር እርምጃ የሚወስድ መኾኑን ያሳውቃል።

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
ግንቦት 13/ 2014 ዓ.ም
ባሕር ዳር

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ ለኔትዎርክ ጥገና ስራ በአከባቢው ተሰማርተው የነበሩ ሶስት የኢትዮ ቴለኮም ሰራተኞች መገደላቸው ተሰማ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የድርጅቱ ሠራተኞች መገደላቸውን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ በኢትዮ ቴሌኮም ሆለታ ዲስትሪክት የሚያገለግሉ ባለሙያ እንደገለጹት ከሆነ ሶስቱ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ላይ ግድያ የተፈፀመው ሐሙስ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ነው፡፡

ሁለት የቴክኒክ ሰራተኞች እና አሽከርካሪያቸው ላይ ግድያው የተፈፀመው ከሆለታ ከተማ 76 ኪ.ሜ. ገደማ ርቀት ላይ እንደምገኝ በተገለጸው ሜታ ወልቂጤ ወረዳ እኩለ ቀን አከባቢ መሆኑን የተቋሙ ባልደረባ አረጋግጠዋል። “ሰራተኞቹ ለስራ እንደወጡ ሜታ ወልቂጤ በምትባል ወረዳ ከምናሬ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ መንገድ ላይ ነው በጥይት ተመተው ተገድለው የተገኙት...” መረጃ ሰጪው አክለውም የሟቾች ቀብር ትናንት እና ዛሬ በሆለታ ከተማ እና በነቀምት ከተማ መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

ግድያው በተፈጸመበት አከባቢ መንግስትን የሚፋለሙ ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱ አስቀድሞ ቢታወቅም ሰራተኞቹ ለአስቸኳይ የጥገና ስራ ወደ ስፍራው ተልከው እንደነበርም ተገልጿል፡፡የኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሳይ ውብሸት ግን የግድያውን መፈጸም አረጋግጠው ለዝርዝሩ በፖሊስ ምርመራ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞን እስር እየተከታተለ መሆኑን ኬሚሽነር ዳንዔል በቀለ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ጸጥታ ኃይሎች ሰሞኑን እየፈጸሟቸው ያሉ እስሮች እንዳሳሰቡት ዳንዔል ጨምረው ገልጸዋል።የአማራ ክልል ጸጥታ ኃይሎች በባሕርዳር ከተማ "አሻራ" ለተባለ መገናኛ ብዙኀን የሚሰሩ አምስት ጋዜጠኞችን ከትናንት ወዲያ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና ቢሮውንም እንደዘጉ ዘግቧል።ሁለት የፋኖ አባላት በባሕርዳር እና ዘጠኝ የአብን አባላት በሁለት ከተሞች መታሰራቸውንም ዘገባው ምንጮቹ ጠቅሶ ጽፏል።የአብን የፓርላማ ተወካዮችም የፓርቲው አባላት እስራት ባስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቀዋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
👉 ለጤናው ቅድሚያ እንሰጣለን


መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን
በተሰጠንና ባገኘነው ልምድና ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሔወችን እንሰጣለን።፦

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉 የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው
ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላሳይነካ
ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛ እንዳይተካ አድርጎ የፈውሳል።
👉 የእሪህ መድአኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉 ገብያ ለገረገረው ለገብያ
👉 ለመፍትሔ ስራይ
👉 ለአይነ ጥላ (ለገርጋሪ)
👉 ለስንፈተ ወሲቢ ለሚቸኩልበት
👉 የአስም (የሳይነስ)
👉 ለማይስማሙ (ለመስተፋቅር)
👉 ገንዘብ ለሚበተንበት
👉 ስራ አልሳካለት ላለ
👉 ለቡዳ
👉 ለሚጥል በሽታ
👉 ለማህጸን እንፌክሽን
👉 ህይወቱ ለሚመሰቃቀልበት
👉 ለአዕምሮ ጭንቀት
👉 ሌሊት ለሚሸና
👉 ለነገረ በትን
👉 ለሆድ ሀህመም
👉 ለስኳር መቀነሻ
👉 ለነርብ
👉 እራሱን ለሚያመው

እነዚህንና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን

መዳኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈጽማሉ

አድራሻ
ባህርዳር ቀበሌ 11
ዲያስፖራ በኮብሉ

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0917040506
📞 0912718883

ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
የሚፈልጉትን ለማግኔት ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ
🩺
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe👇
👇
በማህበራዊና በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥትን በመተቸት የምትታወቀው መስከረም አበራ ቅዳሜ እለት፣ ግንቦት 13 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር መዋሏን ባለቤቷ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

በአዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነችው መስከረም በቁጥጥር ስር የዋለችው በአዲስ አበባ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲሆን ያለችበትንም ስፍራ እንደማያውቁ ባለቤቷ ተናግረዋል።ይህም በሳምንቱ የታሰሩትን የጋዜጠኞች እና የሚዲያ አካላት ቁጥር ሰባት ያደረሰው ሲሆን ሁኔታውም የተችዎን ድምጽ በማፈኑ ረገድ አዲስ እርምጃ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

በያዝነው ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 11፣ 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ተቀማጭነቱን ያደረገውና የቅርብ ዘገባቸው በፋኖ ላይ ያተኮረው አሻራ ሚዲያ አምስት ጋዜጠኞቹ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።ጋዜጠኞቹ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ፖሊስና የአድማ በታኝ የደንብ ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት እንደተወሰዱ "ሽንት ቤት ውስጥ ተደብቄ ነበር" ያለ የስራ ባልደረባቸው ለሮይተርስ ተናግሯል።ግለሰቡ በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የአሻራ ጽህፈት ቤት መዘጋቱንም ተናግሯል።

በተጨማሪም በሃገሪቱ የተካሄደውን ጦርነት በመቃወምና የሰላምና ድርድር መንገዶች የተሻሉ አማራጮች እንደሆኑ በተደጋጋሚ አፅንኦት በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬም መታሰሩ ተዘግቧል።ቢቢሲ የአዲስ አበባን ሆነ የፌደራል ፖሊስን ለማግኘት ቢሞክርም ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ለማካተት አልተቻለም።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
መርካቶ ምን አለሽ ተራ የእሳት አደጋ ተከሰተ!

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በተለምዶ ምን አለሽ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከባድ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል በርካታ የአካባቢው ወጣቶች እና የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች ርብርብ እያደረጉ ነው ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
መርካቶ ምን አለሽ ተራ የእሳት አደጋ ተከሰተ! በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በተለምዶ ምን አለሽ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከባድ የእሳት አደጋ ተከስቷል። አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል በርካታ የአካባቢው ወጣቶች እና የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች ርብርብ እያደረጉ ነው ተብሏል። @YeneTube @FikerAssefa
#update

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መሃል መርካቶ ምን አለሽ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በተከሰተው የእሳት አደጋ የንብረት ውድመት ያጋጠመ ሲሆን የእሳትና ድንገተኛ መከላከል ሰራተኞች፣ የአካባቢው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና የፀጥታ ሃይሎች ባደረጉት ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል።

[A.A Mayor Office]
@YeneTube @FikerAssefa
ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሚንቶ ቸርቻሪዎችን ተክተው ሊሠሩ ነው!

የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ ከስርዓቱ እንዲወጡ በማድረግ በየክልሉ ያሉ የሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተክተው እንዲሠሩ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በገበያው ላይ በቂ የሲሚንቶ ምርት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በገበያ ላይ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በአማካይ እስከ አንድ ሺሕ አንድ መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሆነ እና መንግሥት ሲያደርግ የነበረው የቁጥጥር ሥራ መነሳቱም እየታየ ላለው ችግር አባባሽ ሆኖ እንደተገኘ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቁምነገር እሸቱ አስታውቀዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአራት ዓመት በፊት ያቋረጠውን የመሬት ሊዝ ጨረታ እንደገና ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል።

አስተዳደሩ ለሊዝ ጨረታው በመቶዎች የሚቆጠሩ መሬቶችን እያዘጋጀ እንደሆነ የከተማዋ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለሪፖርተር ተናግሯል። የሊዝ ጨረታ የሚወጣባቸው መሬቶች ለመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ለንግድ ሥራ እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሲሆኑ፣ አስተዳደሩም የጨረታ ሂደቱን የሚያስፈጽምለትን ቡድን አዋቅሯል። የሊዝ ጨረታው በ2010 ዓ፣ም የጨረታ ሂደታቸው ተጀምሮ የተቋረጠባቸውን መሬቶች ጭምር ያካትታል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጉራጌ ዞን የሚገኘው የእነሞርና ኤነር ወረዳ ስያሜ " እኖር " ተብሎ እንዲቀየር ተወሰነ!

የእነሞርና ኤነር ወረዳ ስያሜ " እኖር " ተብሎ ስያሜ ለመቀየር የተዘጋጀው የውይይት ሰነድ ለወረዳው ምክር ቤት አባላት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ እንዲቀየር ውሳኔ መተላለፉ ተነግሯል፡፡ነባሩ የእነሞርና ኤነር ወረዳ በተሰጡ የህዝቡ የአደረጃጀት ጥያቄዎች ምላሽ ምክንያት በስሩ ሲተዳደሩ ከነበሩ አካባቢዎች ራሳቸውን ችለው በወረዳና ከተማ አስተዳደር የተደራጁ በመኖራቸው ምክንያት በቀረው ወረዳ ስር ያሉ ነዋሪዎች ሊገልጽ የሚችል ስያሜ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል።

በእዚህ ሳቢያ በተሰጠው አዲስ ስም ቅያሪ ወረዳው "እኖር " ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል ሲሉ የእኖር ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ያዕቆብ ግርማ ሸዋ በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።የወረዳው አመሰራረትና ስያሜ በተመለከተ ከወረዳውና ከጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ወረዳውን ከዚህ ቀደም ሲያገለግሉ ከነበሩ አባቶች ጋር ውይይት መደረጉን ያነሱት ሃላፊው ወረዳው ከ1967 ዓ.ም በፊት << እኖር>> ተብሎ ሲጠራ እንደነበር ከተደረጉ በውይይቶች የተገኙ መረጃዎች ማመላከታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በሂደትም በ1967 ዓ.ም በወቅቱ የነበረው አመራር ከህዝቡ ጋር ውይይት ሳይደረግ እኖር የሚለውን ስያሜ በመቀየር "እነሞርና ኤነር " በሚል እንዲጠራ ማድረጉ ከዳሰሳዊ ጥናቱ ሊገኝ መቻሉን አስተዳዳሪው አቶ ያዕቆብ ጨምረው ተናግረዋል።በአሁኑ ሰዓትም ወረዳው ከ1967 ዓ.ም በፊት ሲጠራበት ወደነበረው ስያሜ መመለስ እንደቻለ ታውቋል ።ከውሳኔው በኋላ መንግስታዊ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ወረዳው የሚመጡ አካላት "እነሞርና ኤነር " ሳይሆን "እኖር" በሚለው በአዲሱ ስያሜ ሊጠቀሙ ይገባል ተብሏል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንብር የሆኑት የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ሩሲያና ዩክሬንን ሊጎበኙ ነው!

ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ህብተረትን በመወከል በቅርቡ ወደ ሁለቱም ሀገራት እንደሚያቀኑ መግለጻቸውን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።

የጉዞዋቸው ዋነኛ አላማም አፍሪካ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት ቆሞ በሁለቱም ሀገራ መካካል በንግር ላይ የተመሰረተ ሰላ አንዲሰፍን ያላትን ቁርጠኝነት ለማሳወቅ ነው ብለዋል።

[CGTN/Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል 4 ሺህ 552 ግለሠቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ!

በአማራ ክልል በጥምር ኃይሉ እየተከናወነ በሚገኘው የህግ ማስከበር ተግባር 4 ሺህ 552 ግለሠቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።የክልሉ የሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሠው በወቅታዊ የክልሉ ፀጥታ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሠጥተዋል።በመግለጫውም፣ ክልሉ ከግንቦት ወር መግቢያ ጀምሮ ስርአት አልበኝነትን ማስወገድ እና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ በሚል የጀመረው ዘመቻ የክልሉን አንድነት በማጠናከር የውጭ ጠላትን ማስወገድን ያለመ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል።

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮለኔል ገመቹ አያና የታሰሩበትን ሁኔታ ቀርቦ እንዲያስረዳ ቢታዘዝም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቀረ!

የኦሮሚያ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር የሆኑት ኮለኔል ገመቹ አያና የታሰሩበትን ሁኔታ ቀርቦ እንዲያስረዳ በጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት የታዘዘ ቢሆንም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቀረ።የኦሮሚያ ፖሊስ በሰበር ሰሚ ችሎቱ ቀርቦ የኮለኔል ገመቹን የእስራት ሁኔታ በጽሁፍና በአካል እንዲያብራራ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ በነበረ የችሎት ቀጠሮ መታዘዙ ይታወሳል።

በትዕዛዙ መሰረት ዛሬ ረፋድ ላይ በነበረ በችሎቱ ቀጠሮ ጥሪ ቢደረግም ከኦሮሚያ ፖሊስ ማንም አካል ሳይቀርብ ቀርቷል።የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር የሆኑት ኮለኔል ገመቹ አያና በግንቦት 09 ቀን 2013 በስር ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ነጻ ከተባሉ በኋላ፤ በነጋታው ግንቦት 10 ቀን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሲወጡ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው በገላን ፖሊስ ጣቢያ እና በወታደሪዊ ካንፕ እንዲሁም በአዋሽ መልካሳ በአንድ ጀነራል ዶሮ ዕርባታ ውስጥ ለ6 ወራት ታስረው እንደነበር እና ከስድስት ወር በኋላ ከህዳር 16 ጀምሮ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ በእስራት ላይ መሆናቸውን ከዚህ በፊት ለፍርድ ቤት አስረድተው ነበር።

ኮለኔል ገመቹ አያና ነጻ በተባሉበት የሽብር ክስ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዓቃቢህግ ይግባኝ ጠይቆ የነበረ ሲሆን፤ ይግባኝ ሰሚ ችሎቱም ኮነሬል ገመቹ ታስረው በነበሩበት የእስራት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙና አለመፈጸሙ ማረጋገጪያ ባልቀረበበት ሁኔታ ክርክር ማስቀጠል አይቻልም ሲል መዝገቡን መዝጋቱ ይታወሳል።

ይሁንና ዓቃቢህግ በድጋሚ ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በጠየቀበት በዚህ መዝገብ፤ የኮነሬል ገመቹ አያና የእስር ሁኔታ ላይ ባሳለፈው አርብ ዕለት በነበረ ቀጠሮ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በኮነሬል ገመቹ አያና ላይ ምንም አይነት የተከፈተ የወንጀል ምርመራ መዝገብ እንደሌለው ምላሽ ሰጥቷል።

ሰበር ሰሚ ችሎቱም በኮነሬል ገመቹ የእስር ሁኔታ ላይ የኦሮሚያ ፖሊስ ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ቀጠሮ ሳይቀርብ መቅረቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።ጉዳዩን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎቱ በይደር ቀጠሮ መያዙም ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa