በኢትዮጵያ ካሉ የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች 65 በመቶ ማንበብ እንደማይችሉ፤ የሚያስተምሩትን ትምህርት ከተፈተኑ መምህራን 85 በመቶ የሚሆኑት ብቁ አለመሆናቸው ተገለጸ።
ለትምህርት ስርዓቱ ውድቀትና ማነቆ ናቸው በተባሉ ተግዳሮች ላይ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጅማ ዩኒቨርሲቲ መክረዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታዉ ዶክተር ፋንታ በላይ ዛሬ የጅማ ዩኒቨርሲቲን በጎበኙበት ወቅት የትምህርት ስርዓቱ በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ በግልፅ አስቀምጠዋል።
የትምህርት ስርዓቱን ከውድቀት ለመታደግና ሀገር ከሚገጥማት ተግዳሮት ሊታደግ የሚችል ትውልድ ለመፍጠር ችግሮች ላይ ግልፅ ውይይት ማድረግና ለመፍትሄ ማስቀመጥ ወሳኝ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ካሉ የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች 65 በመቶ ማንበብ እንደማይችሉ፣ የሚያስተምሩትን ትምህርት ከተፈተኑ መምህራን 85 በመቶ የሚሆኑት ብቁ አለመሆናቸው ፣ ላለፋት ሰባት ዓመታት በየጊዜው የሀገር አቀፍ ፈተና መሰረቁም በመረጃ የተደገፈ ድክመት ሲሆን ፥ በተጨማሪ ትምህርት ቤቶችም 99 በመቶ አስፈላጊውን መስፈርት እንደማያሟሉ ተጠቁሟል ።
ለስርዓቱ ድቀት መነሻና ማነቆዎች የትምህርት ስርዓቱን ከፖለቲካው ጋር በመለየት ዩኒቨርሲቲዎች ከክልላዊና ብሄር ተኮር እሳቤ በማላቀቅ ተማሪን ማብቃት ግባቸው ሊሆን እንደሚገባ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን የኤፍቢሲ ዘገባ ያሳያል።
ዩኒቨርሲቲዎችም የሚያከናውኑት የህንፃ ግንባታ ተማሪን ከማብቃት ግብ ጋር ሲነፃፀር የላቀ በመሆኑ የሚያስተቻቸው ስለመሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ፥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተጣረሰ አሰራር መውጣትና ከፖለቲካ መነጠል የትምህርት ስርዓቱን ከውድቀት ይታደገዋል ተብሏል።በቀጣይም ምክክሩ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እንደሚቀጥል ታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa

መተሐራ "አልጌ" አካባቢ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ!
በመተሐራ "አልጌ" ተብላ በምትጠራ አካባቢ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የ10 ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።‹‹አልጌ›› የተባለችው የመኖርያ መንደር በምትገኝበት ቀበሌ ስር ባሉ ሦስት ቀጠናዎች በተመሳሳይ ሰዓት በደረሰው ጥቃት የ8 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ አንድ ሰው ከቆይታ በኋላ ህይወቱ አልፏል።ሌላ ተጨማሪ አንድ ሰውም ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል።በጥቃቱ ከሞት የተረፉ 6 ግለሰቦችም ወደ አዳማ ጀነራል ሆስፒታል ተልከው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ከታካሚዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በሆስፒታሉ በህክምና ላይ ከሚገኙ ተጠቂዎች መካከልም ህይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ ያለ ይገኙበታል ተብሏል።ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት 2 ሰዓት ላይ እንደሆነ የዓይን እማኞች ለአዲስ ዘይቤ አሳውቀዋል።በጥቃቱ ሰዓት ወዲያው ህይወታቸው ያለፈው 8 ሰዎች የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አልጌ በሚገኝ መስጊድ እና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
[Addis Zeybe]

በሶማሌ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር የሚያስችል ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።
ድርቁ በክልሉ ከአንድ ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቋረጥ አስገድዷል። በሶማሌ ክልል ድርቅ ጉዳት ባስከተለባቸው አካባቢዎች ለሚኖረው ማኅበረሰብ የምግብ ፣ የውሀ እና ሌሎች ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑንም የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። በዚህ መሀልም በክልሉ የተለያዩ ዞኖችን ለችግር ለዳረገው ድርቅ በቅርቡ የሚጠበቀው የበልግ ዝናብ መፍትሄ ያመጣል በሚል ተስፋ ተደርጓል።
Via DW

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈጸመውን ሰውን አቃጥሎ የመግደል ድርጊት የሚመረምር ቡድን ወደ አካባቢው ተሰማራ!
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈጸመውን ሰውን አቃጥሎ የመግደል ድርጊት የሚመረምር የወንጀል ምርመራ ቡድን ድርጊቱ ወደተፈጸመበት መተከል ዞን አቀና። ከፍትህ ሚኒስቴር እና ፌደራል ፖሊስ በተውጣጡ መርማሪዎች የተዋቀረው የምርመራ ቡድን ወደ መተከል ዞን የተጓዘው ከትላንት በስቲያ ረቡዕ መጋቢት 7፤ 2014 ነው።አምስት አባላት ባሉት በዚህ የምርመራ ቡድን ውስጥ ከፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሶስት ባለሙያዎች መካተታቸውን የሚኒስቴሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ቀሪ ሁለቱ አባላት ደግሞ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተወከሉ ናቸው።የወንጀል ምርመራው በሁለቱ የፌደራል ተቋማት የሚከናወን መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የገለጹት የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ፤ የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት የአጋዥነት ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል።“የኮማንድ ፖስቱ ስራ የአካባቢውን ጸጥታ ማስጠበቅ እና ተጠርጣሪዎች መያዝ ነው” ሲሉም ምክትል ኃላፊው የኮማንድ ፖስቱን ኃላፊነት አብራርተዋል።
ከመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ትላንት ሐሙስ መጋቢት 8፤ 2014 ውይይት ያደረገው የምርመራ ቡድኑ፤ “ያለውን ነገር አቅዶ ወደ ምርመራ ለመግባት” ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አቶ ሙሊሳ ተናግረዋል።“ምርመራውን ለመጀመር የሚያስችል በቂ ኃይል አለን። ትንሽ የሚያስቸግረን በአካባቢው ያለው የጸጥታ ችግር ነው። [ጸጥታው] አስተማማኝ አይደለም” ሲሉም በመተከል ዞን የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ለምርመራ ቡድኑ ስራ እንቅፋት ሊፈጥር እንደሚችል ጠቁመዋል።
Via Ethiopia Insider

አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታት የቀሩት አለም አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ
በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ
ላይ ይካሄዳል።
ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?
ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ
👉 ትምህርት ቤቶች
👉 ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች
👉 የሶፍትዌር ገንቢዎች
👉 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች
👉 ት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣
👉 አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች
👉 ኢንኩቤተሮች
👉 የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች
👉 የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች
👉 ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና
👉 ተያያዥነት ያላቸው።
ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ👇!
www.backtoschoolafrica.com
☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ
ላይ ይካሄዳል።
ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?
ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ
👉 ትምህርት ቤቶች
👉 ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች
👉 የሶፍትዌር ገንቢዎች
👉 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች
👉 ት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣
👉 አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች
👉 ኢንኩቤተሮች
👉 የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች
👉 የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች
👉 ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና
👉 ተያያዥነት ያላቸው።
ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ👇!
www.backtoschoolafrica.com
☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
🎈ለልጆችዋ ደህንነት እና ለቢሮ ለሱቅ...
↪️እንዲሁም ለእርስዎ ደህንነት መጠበቂያ ካሜራ ቻርጀር የሚመስሉ እና ሰአት የሚመስሉ ድብቅ ካሜራዎች አሉን።
↪️እንዲሁም ለ24ሰዓት መብራት ባይኖር ድምፅ እና ምስል ይቀርፃሉ።
📍በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርበናል ይደውሉ...
📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇
join :- @Dawitengineering
📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።
ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985

መንግሥት 8 የቀድሞ የትግራይ ክልል ባለሥልጣናትን እንዳሰረ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዳንዔል በቀለን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል። ከታሰሩት መካከል የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሃላፊዎች እንደሚገኙበት ዘገባው ገልጧል። ጉዳዩን የሚከታተሉ ሌሎች ጠበቆች እና ምንጮች ደሞ 12 የክልሉ የቀድሞ ኃላፊዎች፣ አንድ የመብት ተሟጋች እና አንድ ሌላ ሰው እንደታሰሩ እና በጊዜያዊው አስተዳደሩ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት እበራ ንጉስ፣ የአንድ ዞን አስተዳደሪ እና የትግራይ ቴሌቪዥን ምክትል ዳይሬክተር እንደሚገኙበት ተናግረዋል። ኮሚሽነር ዳንኤል አንዳንዶቹ እስረኞች ወደ አፋር ክልል ተወስደዋል ማለታቸውን እና የእስሩን ምክንያት ግን እንዳልጠቀሱ ዘገባው አመልክቷል።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ለማካሄድ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አስታወቁ!
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱን ተከትሎ እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ጉባኤ እንዲያካሂድ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ)፣ ኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣ እና ኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ (ኦነን) በቅርቡ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።
ትግራይ ዴሞክራቲ ፓርቲ (ትዴፓ) ጉባኤውን ማካሄድ እንደማይችል ገልጿል፡፡
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጡሩና ገምታ ድርጅታቸው ኦፌኮ መጋቢት 17 እና 18 ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚያካሂድ ገልጸዋል።አቶ ጡሩና እንዳሉትም ጉባዔው የፓርቲውን የውስጥ ጉዳዮች ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል።እንደ ፖለቲካ ፓርቲ በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋል።
Via EPA

በቤልግሬድ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አገኘች!
አትሌት ለምለም ኃይሉ በቤልግሬድ 3 ሺሕ ሜትር የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የመጀመሪያውን ወርቅ ለአገሯ አስመዘግባለች።በ18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች 3 ሺሕ ሜትር ውድድር አትሌት ለምለም ኃይሉ አሸናፊ በመሆን የመጀመሪያውን ወርቅ ለአገሯ አስመዝግባለች።
ትላንት ምሽት 4:25 ላይ በተካሄደው የሴቶች 3 ሺሕ ሜ የዓለም የቤት ውስጥ ፍፃሜ ውድድር፣ 1ኛ ለምለም ኃይሉ፣ ወርቅ፣ 3ኛ እጅጋዬሁ ታዬ፣ ነሃስ እንዲሁም 5ኛ ዳዊት ስዩም፣ ዲፕሎማ አግኝተዋል።በሴቶች ምድብ የ3 ሺሕ ሜ የፍፃሜ ውድድር የመጀመሪያ ወርቅና ነሐስ በአትሌት ለምለም ኃይሉና በአትሌት እጅጋየሁ ታዬ ስናገኝ ዳዊት ስዩም አምስተኛ በመሆን ማጠናቀቃቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሱማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ 1.1 ሚሊዮን በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸው ተገለጸ!
በክልሉ እስካሁን የዘነበ ዝናብ ባለመኖሩ ከፍተኛ የሆነ የቤት እንስሳት ሞት መኖሩን የሱማሌ ብሔራዊ ክልል አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን ኃላፊ በሽር አረብ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። አክለውም፣ እስካሁንም አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት ማለቃቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ የድርቁ ሁኔታ ምንም ዓይነት መሻሻል እያሳየ አይደለም ብለዋል።
ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ የሞቱት እንሰሳት 57 ሺሕ 731 ግመሎች፣ 328 ሺሕ 447 በጎች፣ 655 ሺሕ 951 ፍየሎች፣ እንዲሁም ከ37 ሺሕ በላይ አህዮች፣ በጥቅሉ ከአንድ ሚሊዮን 121 ሺሕ 762 በላይ የቤት እንስሳት መሆናቸውን ኃላፊው አብራርተዋል። በበረሃማ አካባቢዎች መረጃ ያልሰጡ አርብቶ አደሮች በመኖራቸው የሞቱት የቤት እንስሳት ቁጥር ከዚህም የላቀ እንደሚሆን ነው ያብራሩት።
ሙሉ ዘገባው:
https://bit.ly/3D1axmQ

The Right Time,
The Right Moves!
Join The Global Education Expo Today.
www.backtoschoolafrica.com
List of Exhibitors:
Schools & Colleges/Universities
School Management Solution Providers
Software developers
App developers & Coders
Start-ups & TECH Entrepreneurs
Education Consultants
STEM Education Incubators,
Digital Service Providers
Education Material Producers & Suppliers
Digital Libraries
NGOs & related.
To Reserve Your Booth:
Call us:
+251 974 0820 36
+251 974 0820 37

ባለፉት ስምንት ወራት ኤክስፖርት ከተደረገ ቡና 746 ሚሊዮን ዶላር ተገኘ!
በበጀት ዓመቱ መጨረሻ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚገኝበት ከሚጠበቀው የቡና ኤክስፖርት፣ ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ 746.8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የገበያ ልማትና ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክትር አቶ ሻፊ ዑመር ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ አገሪቱ በስምንት ወራት ውስጥ 157 ሺሕ ቶን መጠን ያለው ቡና ወደ ውጭ በመላክ 527 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የማግኘት ዕቅድ ነበራት፡፡
ባለሥልጣኑ ከዕቅዱ ከፍተኛ ብልጫ የተገኘበት የውጭ ምንዛሪ ገቢና ምርት በስምንት ወራቱ ውስጥ እንዳገኘ ያስረዱት አቶ ሻፊ፣ 183,155 ቶን ቡና በመላክ 746.8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡
Via Reporter

YeneTube
Photo
⬆️⬆️
በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላይ እርማት እንዲደረግ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ።
የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በዛሬው እለት ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ የ12ኛ ክፍል መግቢያ ፈተና እና ውጤት ላይ እርማት እንዲደረግ ጠይቋል።
የመግቢያ ፈተናውን ውጤት ተከትሎ የሚወጡት መረጃዎች ያልተለመዱና አስደንጋጭ ናቸው ያለው የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በተወሰኑ ተማሪዎችና ወላጆች ግፊትና ጫና የተስተካከሉ ውጤቶች ለተፈጠረው ስህተት ሁነኛ ማሳያዎች ናቸው ብሏል።
የአማራ ትምህርት ቢሮ የሁሉንም ትምህርት ቤቶች ውጤት ዝርዝር መረጃ በመሰብሰብ ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚገባው የጠቆመው ፎረሙ ትምህርት ሚኒስቴርና የፈተናዎች ድርጅት ለችግሩ ትኩረት ሰጥተው ለማረም እድል ያገኛሉ ብሎ እንደሚያምን በደብዳቤው ገልጿል።
በተማሪዎችና ወላጆች እየቀረበ ያለውን ጥያቄ ሁሉም ወገን በቅንነት ተቀብሎ የድጋሜ እርማትን እንዲሁም ተጨማሪ ማጣራት ማድረግ በዜጎች ዘንድ ፍትሐዊነትና ተአማኒነት ከማረጋገጡም በላይ ለአገር ሰላምና መረጋጋት ይጠቅማል ሲልም ፎረሙ አሳስቧል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተናውና ውጤቱ ላይ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች እንደ ፖለቲካ ጥያቄ አቻችሎና ሰምቶ በመተው የሚፈቱ ሳይሆን የትውልዱን እድል የሚወስኑ በመሆናቸው በፍጹም አካዳሚያዊ ስነ ምግባርና ከፍተኛ መሆን አለበት ብሏል ፎረሙ።
ፎረሙ በጻፈው ደብዳቤም ሁሉም አካላት ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጠይቋል።
ፈተና በደቦ እየተሠራ መልካም ትውልዶችን መፍጠር አይቻልም ያለው ተቋሙ ጉዳዩ ከብሔር አውድ ፍፁም ነጻ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እንዲሠሩ ጠይቋል።
ተማሪዎችና ወላጆች ጥያቄው መልስ እስኪያገኝ ተረጋግተው እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርቧል።
[አማራ ኮሚዩኒኬሽን]

ዩኤኢ ለትግራይ ክልል 30 ቶን እርዳታ ልካለች!
የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ (ዩኤኢ) 30 ቶን የምግብ እርዳታ ለትግራይ ክልል በአውሮፕላን ማድረሷን የሀገሪቱን ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል።