YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አዝናኝ ተከታታይ ኮሜዲ ድራማ
በዋሜን ኢንተር ቴመንት ዘወትር ሮብዕ 3:00 ላይ
ከወጣት እስከ አንጋፋ ተዋናይ የተሳተፉበት
ገብተው ይመልከቱት 🙏

https://youtu.be/JFZKCW5ga0Q
ዛሬ በዓለም ገበያ የአንድ በርሜል ድግድፍ ነዳጅ ዋጋ ከ100 ዶላር በታች መውረዱን ዓለማቀፍ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የዩክሬኑን ግጭት ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 140 ዶላር ደርሶ ነበር። ሆኖም ዩክሬን እና ሩሲያ ግጭቱን ለመፍታት የጀመሩት ድርድር ተስፋ በመፈንጠቁ የነዳጅ ዋጋ በፍጥነት ሊወርድ እንደቻለ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ አስተዳደር 110 ዘመናዊ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ከቻይና ሊገዛ እንደሆነ የአስተዳደሩ ቃል አቀባይ ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። አስተዳደሩ ትናንት ዘመናዊዎቹን አውቶብሶች በ15 ሚሊዮን ዶላር ወጭ ለመግዛት ከአንድ የቻይና ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። በስምምነቱ መሠረት የቻይናው ኩባንያ አውቶብሶቹን በ8 ወራት ውስጥ ያስረክባል ተብሏል።

አስተዳደሩ ለከተማዋ በኪራይ ለሚያቀርባቸው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን በዓመት እስከ 2 ቢሊዮን ብር ድረስ ድጎማ ይሰጣል።

@Yenetube @Fikerassefa
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የምግብ ዘይትና ነዳጅ በማከማቸት እጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል ያላቸውን ከ120 በላይ ንግድ ቤቶችን ማሸጉን አስታወቀ።

ከ58 ሺህ በላይ ሊትር ነዳጅና 7000 ሊትር የምግብ ዘይት ተከማችቶ መገኘቱን ከተማ አስተዳደሩ አመልክቷል። ለሕገወጥ ንግድ መባባስ የአንዳንድ አመራር እጅ እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል። ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የሚከታተል ግብረኃይል መቋቋሙም ተመልክቷል።የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከፀጥታ፣ ከንግድና ገበያ ልማትና አዲስ ከተቋቋመው «የገበያ አረጋጊ፣ ፀረ ኮንትሮባንድና ሕገወጥ ንግድ ጥምር ግብረ ኃይል» ጋር የጋራ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ወቅት አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎቹ አንዳመለከቱት የኑሮ ውድነቱና የዋጋ ጭማሪው በተወሰኑ እቃዎች ላይ በሁሉም ሸቀጦች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ መንግስት ለንግዱ ማኅበረሰብ ድጎማ እንደሚያደርገው ሁሉ በዋጋ ትመና ላይም አስተዋፅዖ ሊኖረው እንደሚገባ አሳስበዋል። 

ለዋጋ መጨመሩና ለሕገወጥ ንግዱ መባባስ አንዱ ትልቁ ምክንያት የላይኛው የአስተዳደር እርከን ጣልቃ ገብነት እንደሆነ ተወያዮቹ አመልክተዋል።በውይይቱ ላይ የተገኙት የባህር ዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ባየ አለባቸው ንግዱ በሕገወጥ ደላላ እየተመራ እንደሆነ አመልክተው በዚህ ሂደት የአንዳንድ አመራርና ባለሞያዎች ተሳትፎ አለበት ብለዋል።ችግሩን ለመቀነስ ይህን ጉዳይ የሚከታተል ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ግብረኃይ መቋቋሙን አብራርተዋል።የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ንግድ መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ አጥናፉ እስካሁን የምግብና ሌሎች ሸቀጦችን ያላግባብ አከማችተው ገበያው እንዲንር ባደረጉ 128 የንግድ ድርጅቶች ላይ ርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

በባሕር ዳር ከተማ «የገበያ አረጋጊ፣ ፀረ ኮንትሮባንድና ሕገወጥ ንግድ ጥምር ግብረ ኃይል» መቋቋሙንና ግብረኃይሉም የሕገወጥ እንቅስቃሴዎችን እየተከታተለ ርምጃ ይወስዳል ብለዋል።ሰሞኑን በዋናነት የተከሰተውን የምግብ ዘይት እጥረት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ለመቅረፍ 883 ሺህ ሊትር ዘይት ለክፍለ ከተሞች እየተከፋፈለ ቢሆንም፤ በቂ እንዳልሆነ ነው መምሪያ ኃላፊው የገለፁት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የምግብ ሸቀጦች ላይ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ንረት በኑሯቸው ላይ ብርቱ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሆነ በተለይም በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖች ሲያማርሩ ተሰምተዋል። 

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተለያዩ ለሴት እና ለወንድ እንዲሁም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን የሚያገኙበት ድረ-ገጽ 👇
shein.com SHEIN.COM shein.com

ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን (SHEIN.COM)

Contact @kiru04
☎️ 0931607806

Join 👇👇👇
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
🖲ሴኩሪቲ ካሚራ ከነፃ ገጠማ ጋር...

📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇

join :- @Dawitengineering

📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።


ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሳምንታት የቀሩት አለም አቀፍ የትምህርት ኤክስፖ
በታላቁ አብርሆት ቤተ መፃህፍትና በቨርቹዋል መድረክ
ላይ ይካሄዳል።

ብዙዎች ተመዝግበዋል! እርሶስ?

ከነዚህ መሃል ከሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ

👉 ትምህርት ቤቶች
👉 ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች
👉 የሶፍትዌር ገንቢዎች
👉 ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች
👉 ት/ቤት አስተዳደር ዲጂታል መፍትሔ አቅራቢዎች፣
👉 አለም አቅፍ የትምህርት እድል አማካሪዎች
👉 ኢንኩቤተሮች
👉 የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢዎች
👉 የትምህርት ቁሳቁስ አምራቾች እና አቅራቢዎች
👉 ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና
👉 ተያያዥነት ያላቸው።

ለመመዝገብ ይህችን ሊንክ ይጫኑ👇!
www.backtoschoolafrica.com

☎️ : +251 974 08 2036
+251 974 08 2037
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም፡-   አቶ ፀጋ አራጌ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

እንዲሁም ዶክተር ንጉሴ ምትኩ የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የጦላይ ማሰልጠኛ ት/ቤት የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ያጠናቀቁ ወታደሮችን በማስመረቅ ላይ ነው!

የጦላይ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኞች ማሰልጠኛ ት/ቤት የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ያጠናቀቁ ወታደሮችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የመከላከያ ጄነራል ኢንስፔክተር ኃላፊ ሌተና ጄነራል ድሪባ መኮንን በክብር እንግድነት መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁለት ዙር መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን÷ የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብም እንደየዙሩ የተለያየ ነው።

በዚህ መሠረትም በመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች የሲቪክስ ትምህርት ፈተና ውጤት ያልተያዘ ሲሆን÷ ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ መሆኑን ተመላክቷል፡፡

ለመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 500፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 400 ተይዟል፡፡

ለሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ደግሞ ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 500 ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት መያዙ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በሁለት ዙር በተሰጠው ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ የውጤት አያያዝ እና የማለፍያ ነጥብን ከተያያዘው ምስል ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከዩክሬን መውጣት ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ወደ ፖላንድ እዲገቡ ሊደረግ ነዉ ተባለ!

አዲስ አበባ የሚገኘው የዩክሬን ኤምባሲ ዩክሬን ውስጥ ባለ አንድ ካምፕ ተዘግቶባቸው ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ፖላንድ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀምሯል ተብሏል።ከኢትዮጵያዊያን ዜጎች የደረሰውን ጥቆማ በመቀበል ኤምባሲው ይህንን ስራ ጀምሯል።

ኤምባሲው ዜጎቻችንን ከካምፑ በማውጣት ወደ ፖላንድ ድንበር ሊወስዱ ንግግር እንደጀመሩ እንዳሳወቀው ጋዜጠኛ ኤልያሰ መሠረት የዘገበ ሲሆን ፣ የካምፑ ሀላፊ ስልክ ተደውሎለት ይህን እንዲያስፈፅም ታዟል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዋሽንግተን ለግብፅ F-15 ጄቶች ልታቀርብ ነው!

የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ የአሜሪካ ጦር ጄኔራል ዩናይትድ ስቴትስ ለግብፅ ኤፍ-15 አውሮፕላኖችን እንደምትሰጥ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡የዩናይትድ ስቴትስ የማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ ጄኔራል ፍራንክ ማኬንዚ በኮንግረሱ ላይ ‘‘ረጅም ጠንካራ እና ኢላማውን በአግባቡ የሚመታ F-15 ልንሰጣቸው መሆኑ መልካም ዜና ነው'' ማለታቸው ተሰምቷል ፡፡

ማክኬንዚ በምን ያህል ጊዜ ወይም በቁጥር ስንት F-15 አውሮፕላኖች እንደሚሰጡ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።ባለፈው ወር የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለሀገሪቱ የሚሰጠውን 130 ሚሊዮን ዶላር በሰብአዊ መብት ስጋት ምክንያት ማቋጡን ማናገሩ የሚታወስ ነው፡፡

ማክኬንዚ በግብፅ ጎብኝት ማድረጋቸው ተከትሉ ግን ለግብፅ “በጣም ጠንካራ” ወታደራዊ እርዳታን እንዲሰጥ አፅንዖት በመስጠት ሲናገሩ ተደምጧል።በሕዝብ ብዛት የምትታወቀው ግብፅ በአረብ ሀገራት ወሳኝ አጋር እና ቁልፍ ድምጽ ነች።የአሜሪካ የጦር መርከቦች በስዊዝ ካናል በኩል እንዲያልፉ እና ለአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ያለገደብ በረራ በመስጠትም ግብፅ ሚናዋ ከፍተኛ መሆነን የዋሽንግተን ወታደራዊ ባለስልጣናት ሲናገሩ ቆይተዋል።

✍️Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ክልል ባለዉ ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ የመንግስት የስራ መግቢያ እና መዉጫ ሰዓት ተቀየረ!

በጋምቤላ ክልል ባለዉ ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ለውጥ የተደረገበት የመንግስት የስራ መግቢያ እና መዉጫ ሰዓት ለዉጥ እስከ ግንቦት 30 እንደሚቆይ የክልሉ ፕሬስ ሴክረታሪያት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል። ዉሳኔዉ ከ የካቲት 1 ጀምሮ መተግበር መጀመሩን የተናገሩት አቶ ኡገቱ በክልሉ ባለዉ ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ የስራ ሰዓት ለዉጡን ማድረግ እንዳስፈለገ ተናግረዋል።

በመሆኑም የስራ ሰዓት መግቢያ ጠዋት 1 ሰዓት እስከ 5:30 ከሰዓት መግቢያ 10 ሰዓት እንዲሁም ከስራ መዉጫ 12 ሰዓት ከ 30 እንደሆነ ተናግረዋል። አክለዉም ቅዳሜ እና እሁድ የእረፍት ቀናት እንደሆኑም ገልጸዋል።

ሆኖም የስራ ሰዓት ለዉጡ በስራ ሂደት ላይ ጫናን እየፈጠረ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊዉ የስራ ሰዓቱን በማያከብሩ ሰራተኞች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝም የጋምቤላ ክልል ፕረስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ አክለዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።በክልሉ በያዝነዉ ሳምንት እስከ 41° ሴንቲግሬድ የሚደርስ ሙቀት ሊኖር እንደሚችል ተሰምቷል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ ታዩ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ መታየታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገለጹ።ቢቢሲ አቶ ዳውድ ዛሬ ረፋድ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አምርተው እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ተረድቷል።ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት የኦነግ የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልጾ ነበር።

ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ መሆኑን በመጥቀስ በሊቀ መንበሩ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን እና ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን በደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል።ከአቶ ዳውድ የቁም እስር በተጨማሪ በርካታ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በእስር ላይ ይገኛሉ።የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ሚካኤል ቦረን እና አብዲ ረጋሳን ጨምሮ ኬነሳ አያና፣ ኮሎኔል ገመቹ አያና፣ ዳዊት አብደታ እና ለሚ ቤኛ በእስር ላይ ይገኛሉ።

የኦነግ ቃል አቀባይ በቴ ኡርጌሳ ደግሞ ከጥቂት ቀናት በፊት ከእስር ቢለቀቁም፤ በእስር ላይ ሳሉ ያጋጠማቸውን የጤና መታወክ ተከትሎ በጤና ተቋም ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።የፖለቲከኞቹ ጠበቆች ደንበኞቻችን በፍርድ ቤት በነጻ ቢለቀቁም ፖሊስ ነጻ ለማሰናበት ፍቃደኛ አይደለም ሲሉ ከዚህ በፊት ለቢቢሲ ተናግረዋል።የአቶ ዳውድ ኢብሳን ከቁም እስር መለቀቅ በተመለከተ ፓርቲያቸው እስካሁን ያለው ነገር የለም።

BBC
@Yenetube @Fikerassefa
12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስታወቁ!

ሰሞኑን የተከሰተውን የዘይት አቅርቦትና ዋጋ መወደድ ዙሪያ መንግስት ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ገበያዉን ለማረጋጋት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አስታወቁ። ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር አገር ውስጥ የገባ ገብቶ እየተከፋፈለ መሆኑን ጠቁመዋል። ቀሪዉ 7 ነጥብ 7 ሚሊየን ሊትሩ እየተጓጓዘ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም በየወሩ 50 ሚሊየን ሊትር በሶስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር በተከታታይ ግዢ ይፈጸማል ብለዋል።ባለፈው አመት 1ነጥብ 1 ቢሊየን ሊትር ወደ አገር ውስጥ መግባቱንና በቀጣይ ገበያዉን ለማረጋጋት የተለያዩ ውሳኔዎች መተላለፋቸዉንና ወደ ትግበራ መገባቱንም ገልጸዋል።መንግስት በዘይት ላይ የሚያደርገውን ድጎማ በሌሎች ዘርፎች ላይ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።በየወሩ 50 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ አገር ውስጥ ውሳኔ ላይ መደረሱን ገልፀዋል።

Via EBC/EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ቦሌ ድልድይ አከባቢ ረፋድ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

አደጋዉ የደረሰዉ በሲኖ ትራክ እና የቤት መኪና መሃል በተፈጠረ ግጭት ሲሆን ፣ መብራት ይዞት ቆሞ የነበረ የቤት መኪና ላይ ከፍጥነት ገደብ በላይ እያሽከረከረ የነበረ ሲኖ ትራክ መብራት ጥሶ በማለፍ መኪናዉን ገጭቶ አደጋው እንደደረሰ የቦሌ ክፍለከተማ ቡድን መሪ ዋና ሳጅን ወንድሙ አሻግሬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡

በዚህም በቤት መኪናዉ ዉስጥ ከነበሩ 4 ሰዎች መካከል ሁለቱ በዕድሜ ገፋ ያሉ ወንድ እና ሴት ወዲያዉ ህይወታቸዉ ሲያልፍ ፣ ሹፌሩ እና ከጀርባ የነበረች ሌላ ሴት ደግሞ ወደ ህክምና መወሰዳቸውን ዋና ሳጅን ወንድሙ ተናግረዋል፡፡ዋና ሳጅን ወንድሙ አሻግሬ እንደገለጹት በመኪናዉ ዉስጥ ከነበሩት 4 ሰዎች መካከል ሹፌሩን ጨምሮ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል እናት፣ አክስት እና ልጅ ሲሆኑ ሌላዉ አንድ ግለሰብ ግን ያለዉ ዝምድና እየተጣራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ዋና ሳጅኑ እንደገለጹት በመብራት ዙሪያ ያለ ሁኔታን በጣም በጥንቃቄ መተግበር እንዳለበት እና መብራት ጥሶ ማለፍ ለብዙ ጉዳቶች የሚያጋልጥ በመሆኑ ሁሉም አሽከርካሪ በጥንቃቄ እንዲያሽከረክር መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስታወቁ! ሰሞኑን የተከሰተውን የዘይት አቅርቦትና ዋጋ መወደድ ዙሪያ መንግስት ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ገበያዉን ለማረጋጋት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ጂቡቲ ከሚገኝ አምራች ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አስታወቁ። ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር አገር ውስጥ የገባ ገብቶ እየተከፋፈለ…
4 ሚሊዮን 316 ሺሕ ሊትር የምግብ ዘይት በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ሳርቃ ለዋልታ እንደገለጹት ባቡር በመጠቀም በአንድ ቀን 4 ሚሊዮን 316 ሺሕ ሊትር ዘይት ገብቷል፡፡ባቡሩ በአንድ ዙር 2 ሚሊዮን ሊትር እንደሚያጓጉዝ ገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው አሁንም ተጨማሪ ዘይት በባቡር በመጓጓዝ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን የምግብ ዘይት በአስቸኳይ ሁኔታ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ እንደሆነ ማሳወቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa