ክፍት የስራ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ዴሊቨሪ ሀዋሳ ከስር በተዘረዘረው ክፍት የስራ ቦታ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
መስፈርቶች
የስራው ዘርፍ፥ ፡ ሴልስ
ደመወዝ፥ ፡ ከ2000፡ 3000 እንዲሁም ጥቅማ ጥቅም ያለው።
የትምህርት ደረጃ፥ ፡ 10 ክፍል ያጠናቀቀች
አድራሻ፥ ፡ ሀዋሳ አዋሽ ህንፃ ላይ አራተኛ ፎቆ R12
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈቶች የምታሟሉ አመልካቾች በአካል በመክረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ፩፭ ተከታታይ ቀናት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።
Check our @Deliveryhawassa

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።
በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።
ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።
ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።
@YeneTube @FikerAssefa

The dates are getting closer to witness one of Largest Global Hybrid Expo, which shall be taking place at the newly built state of the art library, Abrehot Library.
Exhibitors can take part either Onsite or Virtual, form any part of the globe.
List of Exhibitors:
Schools & Colleges/Universities
School Management Solution Providers
Software developers
App developers & Coders
Start-ups & TECH Entrepreneurs
Education Consultants
STEM Education Incubators,
Digital Service Providers
Education Material Producers & Suppliers
Digital Libraries
NGOs & related.
To Reserve Your Booth:
Call us:
+251 974 0820 36
+251 974 0820 37
Book online via:
www.backtoschoolafrica.com

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሳልጡና የሚያዘምኑ ስምምነቶችን ከቻይና ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሳልጡና የሚያዘምኑ ሁለት ስምምነቶችን በዛሬው እለት ከቻይና ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአለም ባንክ በተገኘ የ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ በዛሬው እለት የተፈረመው ውል ስምምነት የመጀመርያው ለከተማዋ የሚመጥኑ ዘመናዊና ለአገልግሎት ተስማሚ የሆኑ 110 ባሶችን ከቻይናው ዩቶንግ ባስ ካምፓኒ ጋር ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ግዥ ለመፈፀም ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ኩባንያው ባሶቹን በ8 ወራት ውስጥ የሚያቀርብ ይሆናል ተብሏል፡፡
ሁለተኛው ስምምነት ደግሞ የአንበሳ አውቶብስን አቅም የሚያዘምነውና የሚያሳድገው በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን የታገዘው የብልህ ትራንስፖርት ስርዓት (intelligent transport system) ከቻይናው ሺንዶ ሂሰንስ ትራንስ ቴክ ኩባንያ ጋር የተፈፀመ ውል መሆኑ ተገልጿል፡፡ይህ ውል ከ14 ሚሊዮን ዶላር በላይ እና በሃገር ውስጥ በተጨማሪ 9 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚደረግ ሲሆን አጠቃላይ ድርጅቱን አለም ከደረሰበት የትራንስፖርት መሰረተ ልማት እድገት ጋር የሚያቀራርብና ከወረቀት ነፃ የሆነ አገልግሎት ለደንበኞች በየተርሚናሉና የጉዞ ዲጂታል መረጃ አቀረርቦትም እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በስምምነት ስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት በ2013 ዓ.ም ምርጫ ላይ ለህዝቡ ለመፍታት ቃል ከገባናቸው ጉዳዮች አንዱ የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎትን ማሻሻል ነበር ብለዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ከ1.9 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን መንገዶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን በማስታወስ ዛሬ ደግሞ የትራንስፖርት አገልግሎቱን የሚያቀላጥፉና የሚያዘምኑ ስምምነቶችን መፈጸማቸው አስታውቀዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ለከተማ ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ኪራይ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደጉም የገለፁት ከንቲባዋ የትራንስፖርት አገልግሎትን መንግስት ብቻውን የሚፈታው አይደለም በማለት የግሉ ሴክተርን አስተዋፅኦ ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ስምምነቶቹ የእውቀት ሽግግር እና ዘመናዊነትን አለም የደረሰበትን ቀልጣፋ የአይሲቲ አገልግሎትን ያካተተ መሰረታዊ የትራንስፖርት የለውጥ ስራ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የመመሪያ ጥሰት በፈጸሙ 7 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማስተካከያ እርምጃ ተወሰደ!
የመመሪያ ጥሰት በፈጸሙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰዱን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ የኅብረተሰቡን ጥቆማዎች መነሻ በማድረግ ተቋማት ላይ ባካሄደው ድንገተኛ ጉብኝት በሰባት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶች ላይ የእርምት እርምጃዎችን መውሰዱን ገልጿል፡፡
የማስተካከያ እርምጃው የተወሰደባቸው ተቋማት (ካምፓሶች) ቢኤስቲ ኮሌጅ ጊንጪ ካምፓስ፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ሆሳዕና ካምፓስ፣ ግሬት ቪዥን ኮሌጅ ሆሳዕና ካምፓስ፣ ዛክቦን ኮሌጅ ሻሽመኔ ካምፓስ፣ ብርሃን ኮሌጅ ደብረ ብርሃን ካምፓስ፣ ዮም የድህረ ምረቃ ኮሌጅ ሀዋሳ ካምፓስ እና ለራዳ ኮሌጅ ደብረ ብርሃን ካምፓስ መሆናቸውን ገልጿል።
ተቋማቱ ከፈፀሟቸው ጥሰቶች መካከል የእውቅና ፈቃድ ባልተገኘበት መርሐ ግብር መሰማራት፣ የመግቢያ መስፈርት የማያሟሉ ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር፣ ያለባለስልጣኑ ፈቃድ የማስተማሪያ ቦታ ለውጥ ማድረግ እና እውቅና ያልተገኘበት የደረጃ ስያሜን መጠቀም ይገኙበታል።
በተቋማቱ ላይ የተወሰደው እርምጃም ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ እግድ የሚደርስ መሆኑን ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አዝናኝ ተከታታይ ኮሜዲ ድራማ
በዋሜን ኢንተር ቴመንት ዘወትር ሮብዕ 3:00 ላይ
ከወጣት እስከ አንጋፋ ተዋናይ የተሳተፉበት
ገብተው ይመልከቱት 🙏
https://youtu.be/JFZKCW5ga0Q
በዋሜን ኢንተር ቴመንት ዘወትር ሮብዕ 3:00 ላይ
ከወጣት እስከ አንጋፋ ተዋናይ የተሳተፉበት
ገብተው ይመልከቱት 🙏
https://youtu.be/JFZKCW5ga0Q
YouTube
ፍቅር አዳሽ አዲስ ተከታታይ ድራማ ክፍል 1 fikiri adashi 1
Unauthorized use, distribution, and re-upload of this content is strictly prohibited Copyright ©2021 sintayehu melaku
የሱማሌላንድ ራስ ገዝ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ለኦፊሴላዊ ጉብኝት ወደ አሜሪካ እንዳቀኑ የራስ ገዟ ውጭ ጉዴይ ሚንስቴር በትዊተር ገጹ አስታውቋል።
ፕሬዝዳንት ቢሂ በጉብኝታቸው ከአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ከሕግ አውጭ ምክር ቤቱ አባላት ጋር ይነጋገራሉ ተብሏል። ሱማሌላንድ በሐርጌሳ ወደቧ አሜሪካ ወታደራዊ ጦር ሠፈር ማቋቋም ከፈለገች ፍቃድ እንደምትሰጥ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የገለጠች ሲሆን፣ ፕሬዝዳንት ሙሴ በመጋቢት በአሜሪካ በሚያደርጉት ጉብኝት በጉዳዩ ላይ ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ በወቅቱ ተገልጦ ነበር።
[ዋዜማ ራዲዮ]
@Yenetube @Fikerassefa

በሱዳን የዳቦ ዋጋ በ40 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ የዳቦ አመጽ በመካሄድ ላይ ነው
በሱዳን የዳቦ ዋጋ መናሩን ተከትሎ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ተቀሰቀሰ፡፡
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ የተጀመረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት የዓለም ነዳጅ እና ምግብ ዋጋዎችን እንዲንር አድርጓል፡፡
በሱዳንም የዳቦ ዋጋ ከጦርነቱ በፊት ከነበረበት አሁን ላይ 50 የሱዳን ፓውንድ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም የአገሪቱን ዜጎች ለከፍተኛ ቁጣ ዳርጓል፡፡
በዚህም ምክንያት በሱዳን የዳቦ አመጽ በመካሄድ ላይ ሲሆን በሺህ የሚቆጠሩ ሱዳናዊያን ወደ አደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው፡፡
ባሳለፍነው ጥቅምት በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ (ዶ/ር) ይመራ በነበረው መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣን የተቆጣጠረው ወታደራዊ መንግስት ላይ ተጨማሪ ጫናን ይፈጥራል ተብሏል፡፡
መፈንቅለ መንግስቱን ለመቃወም ወደ አደባባይ የወጡት ሱዳናዊያን አሁን ደግሞ የዳቦ ዋጋ መናሩ ተጨማሪ ሱዳናዊያን ወደ አደባባይ ለተቃውሞ ወጥተዋል፡፡
የሱዳን የጸጥታ ሀይሎችም በአገሪቱ በርካታ ከተሞች ወደ አደባባይ የወጡ አመጸኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙን አልዓይን ከካርቱም ዘግቧል፡፡
ከዳቦ ዋጋ በተጨማሪም የነዳጅ ዋጋ በ50 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም በጀነራል አልቡርሃን ለሚመራው ወታደራዊ መንግስት ሌላኛው ፈተና ነውም ተብሏል፡፡
ተቃዋሚዎቹ ከዚህ በፊት ስልጣን በሀይል የተቆጣጠረው የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳድር እንዲመልስ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡
የዳቦ ዋጋ መናሩን ተከትሎ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ አንማርም ያሉ ተማሪዎችን ጨምሮ የባቡር መንገድ ሰራተኞችም የዳቦ አመጹን ተቀላቅለዋል፡፡
የሱዳን ጦር ስልጣን በሀይል መቆጣጠሩን ተከትሎ አሜሪካ ለሱዳን ልትሰጠው የነበረውን 700 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ማቆሟ ይታወሳል፡፡
በፈረንጆቹ 2019 በሱዳን የዳቦ ዋጋ ጨምሯል በሚል ተቃውሞ ተጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩት ፕሬዘዳንት ኦማል ሀሰን አልበሽርን ከስልጣን እንዲነሱ ዋነኛ ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም፡፡
Via:- Al ain

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ሌሊት ብሔርን መሠረት አድርጎ በተማሪዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት በበርካታ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ገለጹ።
ግጭቱን በቅርበት የተመለከቱ ተማሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት ችግሩ ከተፈጠረ ቀናት ያስቆጠረ ቢሆንም ትናንት ሌሊት ግን ወደ አካላዊ ግጭት ተሸጋግሯል። በተማሪዎቹ መካከል ወደ ብሄር ግጭት ያሸጋገረውን አጋጣሚ በተመለከተ አስተያየቱን ለዶይቼ ቬለ የሰጠው እና ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው ተማሪ« ጥላቻን የሚሰብክ ወረቀት በጊቢው መበተኑን » ይገልጻል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር ዉባቸው ማሞ በበኩላቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ቅጥር ጊቢው በመግባት ተማሪዎችን ለፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃነት ተጠቅመዋል በማለት ይከሳሉ። ኢንጅነር ውባቸው አሁን ዩኒቨርሲቲው መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባሩ እንደቀጠለ መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ያሏቸው ተማሪዎች እና ሌሎች አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን አስታውቀው ነበር።
[DW]

በኢትዮቴሌኮም እና በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መካከል መሰረተልማትን ለመጋራት የሚደረጉ ስምምነቶች በዋጋ እና የክፍያ ገንዘብ አይነት ወይም ምንዛሪ ምክንያት አለመግባባቶች ተፈጠሩ፡፡
ሁለቱ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች መሰረተ ልማትን መጋራት፤ ኢንቱ-ኮኔክቲቪቲ ማለትም የሁለቱ ደንበኞችን ማገናኘት አና ብሄራዊ ሮሚንግ ማለትም አንዳቸው የሌላኛቸውን ኔትዎርክ ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ስምምነት ለማድረግ ከመስከረም ወር ጀምሮ ሲሰሩ የነበር ቢሆንም እስካሁን ንግግራቸውን ውጤታማ መሆን አልቻለም፡፡
በሁለቱም አገልግሎቶች ሰጪዎች እንደምክንያት ከተነሱት አንዱ የኪራይ ዋጋ ሲሆን የሳፋሪኮም ሀላፊዎች በኢትዮ ቴልኮም የቀረበው ዋጋ ውድ እንደሆነ ሲገልፁ የኢትዮ ቴልኮም ሃላፊዎች በበኩላቸው የቀረበው ዋጋ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ገልፀው ለሱም ማካካሻ ኢትዮቴሌኮም በውጭ ምንዛሪ የተወሰነው እንዲከፈለው ጠይቋል፤ የሳፋሪኮም ሀላፊዎች በበኩላቸው ድርጅታቸው ሀገር ውስጥ የተመዘገበ ስለሆነ በብር መጠቀም አለበት ሲሉ ኢትዮቴልኮም በበኩሉ መሰረተልማቶችን በዶላር ከፍሎ እንደሚያሰራ እና የውጪ ምንዛሪ እንደሚያስፈልገው ይገልጻል፡፡
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አና የቁጥጥር ከፍተኛ ኦፊሰር የሆኑት ማቲው ሀሪሰን ስምምነቱ በተለያዩ ምክንያቶች ቢዘገይም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለፈው ወር ስምምነት ላይ ይደረሳል ብሎ ሲጠብቅ እንደነበር ተናግሯል፡፡የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀላፊው ለካፒታል እንደተናገሩት ጉዳዩን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በያዝነው ወር መጨረሻ መፈታት ካልተቻለ ነገሩን ወደ ኢትዮጵያ ኮምኒኬሽን ባለስልጣን እንደሚወስዱት ገልጸዋል።ባለስልጣኑ በህጉ መሰረት ጣልቃ መግባት እና የማስማማት ስልጣን አለው፡፡
[Capital]

አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🖲ሴኩሪቲ ካሚራ ከነፃ ገጠማ ጋር...
📍በተጨማሪም በቻናላችን join በማለት እቃዎችን ማየት ይችላሉ👇👇
join :- @Dawitengineering
📍የፈለጉትን ይዘዙን እኛን ለማግኘት ከታች ባለው አድራሻ ያገኙናል።
ስልክ :- 0920757958
inbox :- @Dawit757985

11 ህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ትናንት ማምሻውን ወደ እስራኤል ተጉዘዋል።
ህጻናቱ ወደ እስራኤል ያተጓዙት በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ከሴቭ ዘቻይልድ ሀርት ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ያመቻቸውን እድል በመጠቀም ነው።በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለህክምና ለሚሄዱት ህጻናት ሽኝት አድርገውላቸዋል።
አምባሳደር አለልኝ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ኤምባሲው ቪዛ ያዘገጀው ለ16 ህጻናት ቢሆንም ዛሬ ወደ እስራኤል ያቀኑት 11ዱ ናቸው ብለዋል።በቀጣይም ቀሪዎቹ ህጻናት ወደ እስራኤል የሚሄዱበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።የእስራኤል መንግሥት የልብ ህሙማን ህጻናትን ወስዶ ከማሳከም ባለፈ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች በዘርፉ የሚፈለገውን እውቀት እንዲጨብጡ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ መጋቢት 18 ላይ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔውን እንደሚያካሂድ ፓርቲው ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ በሰጠው መረጃ አስታውቋል። የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ የፓርቲውን መተዳደርያ ደንብ እንደሚያሻሽል እና አዳዲስ የፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን እንደሚመርጥ ተገልጧል።ምርጫ ቦርድ እስከ መጋቢት 10 ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያካሂዱ ካዘዛቸው ፓርቲዎች አንዱ ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
እስራኤል ለቀጣዩ ፋሲካ በዓል ለሐይማኖታዊ ተልዕኮ የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ ማገዷን ታይምስ ኦፍ እስራዔል ጋዜጣ አስነብቧል።
እስራዔል ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች እንዳይገቡባት ያገደችው፣ በኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ሳቢያ አንዴ ከገቡ ወደ አገራቸው ላይመለሱ ይችላሉ በሚል ስጋት እና ባለፉት ጥቂት ዓመታት የገቡ ኢትዮጵያዊያን ተጓዦች አልተመለሱም በማለት ነው። የአገሪቱ የኢምግሬሽን ባለሥልጣን ለእስራዔላዊያን አስጎብኝ ድርጅቶች በጻፈው ደብዳቤ፣ ተጓዥ የኢትዮጵያዊያን ክርስቲያን ቡድኖችን ወደ እስራዔል እንዳያጓጉዙ አሳስቧል።የአገሪቱ አስጎብኝ ድርጅቶች ማኅበር ግን፣ እገዳው አድሏዊ ነው ሲል ተቃውሟል።
✍️Wazema

በጉጂ ዞን ከ22 ሺ በላይ ተማሪዎች በድርቅ እና በፀጥታ ችግር የተነሳ በትምህርት ገበታ ላይ እንደማይገኙ ተነገረ!
በጉጂ ዞን በ72 ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ይከታተሉ የነበሩ ከ22 ሺ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ባለው የጸጥታ ችግር እና በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በትምህርት ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ ተገልጿል።በዞኑ ከዚህ ቀደም በነበረ የትምህርት ቤት ምገባ በርካታ ተማሪዎች ተጠቃሚ የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ምገባው በመቋረጡ እና ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በትምህርት ቤቱ ያስተምሩ የነበሩ መምህራን ባለው ችግር የተነሳ የመማር ማስተማር ሂደቱ ሊቀጥል አለመቻሉ ተጠቁሟል።በዞኑ 22 ሺ 967 ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ እና ቤተሰቦቻቸውም ባለው የፀጥታ ችግር እና ድርቅ የተነሳ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ሀላፊ የሆኑት አቶ ዮሀንስ ወርቁ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
እንደ ሀላፊው ገለፃ በአሁኑ ሰዓት የተወሰኑ ተማረዎች የዞኑ ትምህርት ቢሮ ባደረገው ክትትል ከ11 ሺ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተዘዋውረው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መደረጉ ተገልጿል፡፡በዞኑ በቂ ድጋፍ እየተደረገ አለመሆኑ እና ህብረተሰቡም በድርቅ እና በጸጥታ ችግር የተነሳ ክፉኛ መጎዳቱን አቶ ዮሀንስ ወርቁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Via Bisrat FM

ብልጽግና ፓርቲ በ10 ሺህ 658 አባላቱ ላይ ርምጃ መወሰዱን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።
ብልጽግና ፓርቲ ባካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤው የፓርቲውን ውስጣዊ አንድነት የሚያጠናክሩ ውሳኔዎች መወሰኑንና የተጣለበትን ሕዝባዊ አደራ በአግባቡ ይወጣ ዘንድ በአባላት ላይ የማጥራት እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ።በዚህም መሰረት በ108 ሺህ 258 አባላት ላይ ጥልቅ ግምገማ መደረጉን፤ በ10 ሺህ 658 አባላት ላይ ርምጃ መወሰዱን ነው ያስታወቀው።
2 ሺህ 574 አባላትም ከኃላፊነት መነሳታቸውን ፓርቲው ገልጾ፥ ሌሎች የማስተካከያ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም የፓርቲው ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ዛሬ የፖርቲውን አንደኛ ጉባኤ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በየክልሉ እታች ድረስ የተደራጀ እቅድ ተዘጋጅቶና ውይይት ተደርጎ በየአከባቢው ያሉ ችግሮች እንደሚፈቱም ነው የተገለጸው።በበርካታ ጫናዎች ኢትዮጵያን ለማበርታት፣ ለማጽናትና ለማቆም የተሄደበት ርቀት ውጤታማ የሚባል ነበር ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

152 ሺሕ ተማሪዎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን እንደሚቀላቀሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152 ሺሕ የሚሆኑት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን እንደሚቀላቀሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ይህም በአማካይ በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ፈተናውን 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ካመጡት ውስጥ 53 በመቶ ያህል መሆኑ ተነግሯል።
በመንግሥት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63 ሺሕ 833 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡የዩኒቨርሲቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135 ሺሕ 209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር እንደሚችሉም ተነግሯል።