YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ሀብት_ያለው_አእምሮህ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የእለት ጉርስህን ለማግኘት እየተጣጣርክ ወይም ያለህ ሀብት እንዲበዛ የምታደርግበትን መንገድ እየፈለግክ ነው?

እንግዲያውስ ሀብት ያለው አእምሮህ የተሰኘው አዲሱ የዶ/ር ጆሴፍ መርፊ መጽሀፍ ይረዳሀል፡፡ መጽሐፉ “የሁሉም ሀብት መነሻ አእምሮ ነው” ይለናል፡፡

“የምትኖረው በአእምሮህ ውስጥ ነው፡፡ ሀብታም ወይም ደሀ፣ ለማኝ ወይም ሌባ የምትሆነው እዚያ ነው፡፡ በህይወት ውስጥ የምትፈልጋቸውን ነገሮች የመፍጠር ኃይል እንዳለህ ስትገነዘብ ታላቅ ዋጋ ያለው እንቁ እንዳለህ ታውቃለህ፡፡ በውስጥህ ያለው ሀብት እና ኃይል በጭራሽ የሚቀንስ ስላልሆነ አንተ ከምታስቀምጠው ገደብ በስተቀር የአእምሮህ ሀብት ገደብ አያውቅም፡፡”

ከዝቅታ ህይወት ወደ ከፍታ ህይወት ተሸጋግረህ አንገትህን ቀና ለማድረግም ሆነ፣ በሕይወትህ ውስጥ የሚገባህን ብልጽግና ለማግኘት ይህ መጽሐፍ እንዴት የድብቁን አእምሮህን ኃይል መጠቀም እንዳለብህ ያስተምርሀል፡፡

#ሀብት_ያለው_አእምሮህ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
አዲስ አበባ ከተማ ሊገባ የነበረ 2500 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ!

ትናንት ከሱሉልታ ወደ አዲስ አበባ በኤፍኤስአር የጭነት መኪና ተጭኖ ሊገባ የነበረው 2500 የክላሽ ጥይት ኬላ ፍተሻ ላይ መያዙን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ ገልፀዋል።

አቶ ጌታሁን አክለውም በፍተሻው ወቅት የጥይቱ አዘዋዋሪና ሹፌሩ ለጊዜው ሲሰወሩ መኪናው እና ጥይቶቹን ቁጥጥር ሥር በማዋል በኤግዚቢትነት ተይዘው በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን የሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላንድ ሳምንት አቋርጦት የነበረውን የስኳር ምርት እንደገና ማምረት እንደጀመረ ለመንግሥት ዜና አውታሮች ተናግሯል። ፋብሪካው ምርቱን ላንድ ሳምንት ያቋረጠው ባካባቢው ባለው የጸጥታ ስጋት ሳቢያ የነዳጅ አቅርቦቱ በመስተጓጎሉ እንደነበር ገልጦ፣ አሁን ግን የነዳጅ አቅርቦት ችግሩ ስለተፈታለት ምርት መጀመሩን ነው ያስታወቀው። የፋብሪካው ምርት ካለፈው የካቲት 2 ጀምሮ የተቋረጠው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሳቢያ እንደሆነ ተደርጎ የተሠራጨውን ዘገባ ፋብሪካው አስተባብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
Forwarded from YeneTube
🇭🇺የስራ ጉዞ ወደ #Hungary 🇭🇺
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - Budapest, Hungary
👉 የስራው አይነት - Construction work
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - 8 - 10 hr/day
👉 የወር ደሞዝ - €1500 and more
👉 ፆታ - ወንድ
👉 ዕድሜ - 18 እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#30_persons

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo


Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com
http://Sabinaadvisor.com
https://tttttt.me/sabinavisaa
Forwarded from YeneTube
🎁 #ArtLand_gifts 🎁

✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌

✔️እንዲሁም MUG, PUZZLE, ሀብል እና ፕላስቲክ MDF ላይ የወደዱትን ፎቶ ወይም ፅሁፍ ያሰሩ 🎁


🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

Join our telegram channel👇
@artlandengraving
ከአዲስ አበባ ወደ ወልቂጤ ከተማ ሽጉጥና የክላሽንኮቭ ጥይቶችን ይዞ ሊሄድ ሲል በቁጥጥር ሥር የዋለው ተከሳሽ የ9 ዓመት ፅኑ እስራትና የ80 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተወሰነበት!

ከአዲስ አበባ ወደ ወልቂጤ ከተማ ሽጉጥና የክላሽንኮቭ ጥይቶችን ይዞ ሊሄድ ሲል እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በ9 ዓመት ፅኑ እስራትና በ80 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት አንዲቀጣ ተወስኖበታል።

የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው አበበ ቦጋለ የተባለው ተከሳሽ የጦር መሳርያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀፅ 4/1 እና 22/3 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ መጋቢት 22/2013 ከቀኑ 4:00 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አውቶብስ ተራ ውስጥ ወደ ወልቂጤ ከተማ ለመጓዝ ቅጥቅጥ አውቶብስ ላይ ተሳፍሮ እያለ፤ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ተጠራጥረው ድንገት ሲፈትሹት ይዞት በነበረው ሻንጣ ውስጥ “ሪታይ ፍልከን” የተባለ ሽጉጥ ከመሰል 4 ጥይቶች እና ብዛታቸው 300 (ሶስት መቶ ) የሆኑ የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይቶች ይዞ እጅ ከፍንጅ በመገኘቱ በፈፀመው የፀና ፍቃድ ሳይኖረው የጦር መሳርያ መያዝና ማዘዋወር ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርቧል።

ተከሳሹ በተመሰረተበት ክስ ላይ የእምነት ክህደት ቃሉን ተጠይቆ ወንጀሉን መፈፀሙን ሙሉ በሙሉ ባለማመን ክዶ የተከራከረ ሲሆን፤ ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዳሉ ያላቸውን ዝርዝር የሰው፣ የሰነድና በክሱ ላይ የተጠቀሰው የጦር መሳርያ በኢግዚቪት ማስረጃነት አቅርቦ አሰምቷል።

ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤት ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም ተከሳሹ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ጥፋተኛ ነህ ሲል ፍርድ በመስጠት ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊዎችን ያስተምራል ያለውን በ9 ዓመት ፅኑ እስራትና በ80 ሺህ ብር የገንዘብ እንዲቀጣ እንደወሰነበት ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ በኢትዮጵያ ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱን በበጎ እንደምትመለከተው አስታወቀች!

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የአዋጁ መነሳት ብሔራዊ ምክክርን ለማፋጠን ያግዛል ብሏል።መንግስት አዋጁ እንዲነሳ ማድረጉ እየተካሄደ ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ተጨማሪ ጠቃሚ እርምጃ እንደሚሆንም ዋሸንግተን አስታውቃለች።ይህ እርምጃም በአዋጁ የታሰሩ ሰዎችን በአስቸኳይ በመፍታት ሊቀጥል እንደሚገባም ነው የአሜሪካ መንግስት የጠየቀው።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
በእንግዳ ማረፍያ (ፔኒስዮን) የተነሳው እሳት እስካሁን ማንነታቸው ያልታወቀ የጥንዶችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

በአቃቂ ክ/ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ ዛምባባ ጠጅ ቤት አካባቢ በሚገኙ የንግድ ቤቶች ላይ የካቲት 9/2014 ሌሊት 8፡42 ገደማ የተነሳው የእሳት አደጋ በአንድ የመኝታ ክፍል ውስጥ ተኝተው የነበሩ ሁለት ሰዎችን ህይወት አሳጥቷል፡፡የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈውን የሁለቱን ግለሰቦች ማንነት እንዲሁም የአደጋውን መነሻ ምክንያት ፖሊስ እያጣራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ግለሰቦች ህይወታቸው ያለፈበት “ፔኒሲዮን” ወይንም የእንግዳ ማረፊያ ክፍል ላይ ድንገተኛ እሳቱ በመነሳት ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

በተጨማሪም፤ በአካባቢው ተያይዘው በሚገኙት አራት የንግድ ሱቆች፣ የሸቀጣሸቀጥ መደብር፣ ምግብ ቤት፣ ፀጉር ቤት እንዲሁም ግሮሰሪ ላይ ድንገተኛ እሳቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

በአደጋው ምክንያት በአንድ መኝታ ክፍል ውስጥ ተኝተው የነበሩ ሁለት ጥንዶች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ በአደጋው የሶስት ሰዎች ህይወትን ማትረፍ የተቻለ ሲሆን ሰባት መቶ ሺ ብር የሚገመት ንብረት ሊወድም እንደቻለ ኢትዮ ኤፍኤም ሰምቻለሁ ብሏል፡፡

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ሶስት የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎች የተሰማሩ ሲሆን ሰላሳ በሚሆኑ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ እሳቱን ለመቆጣጠር መቻሉንም አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የካቲት 9 /2014 ዓ/ም ምሽት 11፡50 በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አየር ጤና አካባቢ በመኖሪያ ቤት ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ከ አንድ መቶ ሺ በላይ የሚገመት ንብረት ሲወድም ከ ሁለት መቶ ሺ በላይ ንብረት ደግሞ ማትረፍ መቻሉንም አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው አደጋ የሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የነገሩን አቶ ንጋቱ ህብረተሰቡ እንዲሁም የንግድ ድርጅቶች ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች ላይ የተለየ ጥንቃቄን በማድረግ እራሳቸውንና ንብረታቸውን እንዲጠብቁ ጠይቀዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ነፃነታቸውን የተነፈጉ ሰዎችን መብት በሚመለከት ብሔራዊ ምርመራ ሊያደርግ ነው!

ኢሰመኮ የብሔራዊ ምርመራውን መጀመር አሰመልክቶ ዛሬ ሐሙስ የካቲት 10/2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከባለድርሻዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

ኢሰመኮ ነፃነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች መብቶች ዙርያ የሚደረገው ብሔራዊ ምርመራ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚቆይ ነው ብሏል።

ምርመራው በአስፈጻሚ አካላትና በሌሎችም፣ ስልታዊና ውስብስብ በሆኑ መንገዶች ነፃነታቸውን የተነፈጉ፣ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎችን ጉዳይ የሚመለከት ነው ብሏል።

ለዚህ ብሔራዊ ምርመራ መነሻ የሆነው ኢሰመኮ በስፋት የተቀበላቸው ጥቆማዎችና ያደረጋቸው ምርመራዊ ጥናቶች መሆናቸውን የኢሰመኮ የሲቪል፣ የፖለቲካዊ፣ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ኮሚሽነር አብዲ ጅብሪል (ዶ/ር) ለአሻም ነግረዋታል።

ብሔራዊ ምርመራው የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ነፃነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች፣ ባለ ግዴታውችን እና የመብት ተሟጋቾችን በማሳተፍ በውይይት ላይ የተመሠረተ ፍትሕን ለማስፈን ይረዳል ተብሏል።

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
ህወኃትን ከአሸባሪ ዝርዝር ውስጥ ይውጣ ለሚለው ጥያቄ መንግስት ምንም ምላሽ የለውም ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ!

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውን ህወኃት ከአሸባሪ ዝርዝር ውስጥ ይውጣ ለሚሉ ጥያቄዎች መንግስት ምንም አይነት ምላሽ የለውም ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።አምባሳደር ዲና በዛሬው እለት ሳምንታዊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የስራ ማብራሪያ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ የደህንነት ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አካላት ተደራደሩ እያሉ ነው፤ ለምን አላችሁ የምንለው ነገረ የለም መንግስት ግን የራሱን አቋም ያራምዳል ለጥያቄው ምንም ምላሽ  የለውም ሲሉ አስረድተዋል።ከተለያዩ አካላት ህወሃትን ከአሸባሪ ዝርዝር ውስር ይወጣ እያሉ ጥያቄ ቢያቀርቡሙ በመንግስት በኩል ምንም ምላሸ የለም ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ስለ አፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላም ስለመጠናቀቅ ያነሱ ሲሆን በጉባኤው የ23 ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ፣ ሶስት ጠቅላይ ሚኒስትሮችና ሶስት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መገኘታቸውን ገልጣልቃ ።ጉባኤው ካተኮረባቸው  ጉዳዮች መካከል ኮቪድ እና መፍትሄው ፥ ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚዊ እና የልማት  አጀንዳ መሆናቸውን አስታውሰዋል።

በጉባኤው የሰላም እና ጸጥታ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የጠመንጃ ድምጽ በአፍሪካ አህጉር እንዳይሰማ የተያዘው እቅድ  ሊሳካ አለመቻሉ አሳዛኝ ሲሉ አምባሳደር ዲና ገልፀውታል።እንዲሁም በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት መፈንቅለ መንግስት መብዛቱ አሳሳቢ መሆኑ የተነሳ ሲሆን እንዲሁም በአፍሪካ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ ስለሚኖር ጣልቃ ገብነት የጉባኤው ተሳታፊዎች ነቅፈውታል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከስሎቪኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቻቸው ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገለፁ!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ ከስሎቪኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጃኔዝ ጃንሳ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት "ከጠቅላይ ሚኒስትር ጃኔዝ ጃንሳ ጋር ለረዥም ጊዜ የዘለቀውን የኢትዮጵያና የስሎቪኒያ ወዳጅነት ስለማጠናከር እንዲሁም ስለቴክኒክ እና ኢኮኖሚ ትብብር ተወያይተናል።" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ!

በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ በሰዉና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።ከያቤሎ ወደ አዲስ አበባ 65 ሰዉ ጪኖ ስጓዙ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 34983 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ ማድረሱን የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ ገልጸዋል።ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በይርጋጨፌና በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአደጋ መንሴና ፖሊስ እያጣራ መሆኑን የዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል ።

@YeneTube @FikerAssefa
በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶቹን ሰኞ የካቲት 14 2014 ዓ.ም እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው ሰኞ በሚጀምረው አገልግሎቱ ከአዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ውጭ ያሉ መደበኛ አገልግሎቶቹን መስጠት እንደሚጀምር ይፋ አድርጓል፡፡

ኤጀንሲው አገልግሎቶችን በሁሉም ክ/ከተማ እና ወረዳው በተዘጋጀ መርሃ ግብር ነዋሪው እንዲስተናገዱ እንደሚደረግ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ኤጀንሲው አዲስ ሴኪውርድ የሰርተፍኬት ፕሪንተር ለክ/ከተማ እና ወረዳ እያሰረጨ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ከ2013ዓ.ም ጀምሮ ፎርጀሪን ሙሉ ለሙሉ ያስቀርልኛል እንዲሁም የውስጥ ሌብነትንም ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለውን “የሴኪውርድ “ ፕሪንተር ወደ ስራ በማስገባት የማሰራጨት እና የኮንፊግሬሽን ስራ በክ/ከተማ እና በወረዳ ጽ/ቤቶች ሲሰራ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

የከተማውን የወሳኝ ኩነት ማስረጃዎች አለም ዓቀፍ ደረጃ እንዲኖራቸው፣ የሰርተፍኬቶቹን ደህንነት ከፍ የሚያዱርግ፣ እና ሲስተም ባለባቸው እና በሌለባቸው ወረዳዎች አገልግሎት በመስጠት የእጅ ፅሁፍ ንክኪን ለመጨረሻ ግዜ የሚያስቀር ነው ተብሎለታል።

ከዚህ ቀደም ከነበረው መደበኛ ሰርተፍኬት በውስጡ የባለማስረጃውን ስም እንዲሁም ፎቶግራፍ በምስጢራዊ ህትመት ይዞ የሚወጣ ሲሆን በ UV ማሽኖች ተፈትሾ በቀላሉ ኦርጅናል መሆን አለመሆኑን ከባለማስረጃው ስምና ሌሎች መረጃዎች ጋር በማመሳከር መለየት የሚያስችል ሲሆን በውጭ የሚሰራ የፎርጀሪ ስራን ከማስቀረት ባሻገር በሰርተፍኬቱ ላይ በሚኖር ልዩ Licensed QR ኮድ ፈቃድ የሚሰጣቸው ተቋማት ሰርተፍኬቱ ትክክለኛ ስለመሆኑ ማረጋገጥ የሚችሉበት ስርዓት እንደያዘ ኤጀንሲው አስታውቋል።

በአልግሎት ወቅት ታትመው የሚሰጡት የወሳኝ ኩነት እና የያላገባ የምስክር ወረቀቶች በዋናነት ማስረጃው (ሰርተፍኬቱ) በየትኛው ወረዳ፣ በየትኛው ባለሙያ (User) እና ለማን እንደታተመ መረጃ በመያዝ በማዕከል ቁጥጥር የሚያደርግ አሰራር ያለው ከመሆኑ ባሻገር በምን አይነት ኮምፒውተር የህትመት ትዕዛዝ እንደተሰጠው መለየት የሚያስችል ዘመናዊ አስራርን እንደሚያካትት የአዲስ አበባ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአይኤምኤፍ ኒውስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከከዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ኒውስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤"ከክሪስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ኢትዮጵያ ተቋም ጋር ያላትን ትብብር ስለ ማጠናከር እና የለውጡን ሂደት በቀጣይነት ስለ መደገፍ ተወያይተናል" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብ/ጄኔራል ተፈራ የርዕሰ መሥተዳደሩ አማካሪ ሆነው ተመደቡ!

የአማራ ክልል መንግሥት በፀጥታ ዘርፍ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ ማድረጉን ተከትሎ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የርዕሰ መሥተዳደሩ አማካሪ ሆነው ተመደቡ።

ክልሉ የገጠመው የሰላምና የፀጥታ ችግሮችን በአግባቡ ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ በክልሉ ያሉ የፀጥታ መዋቅሩ ላይ ያሉ ጉድለቶችን እና ጥንካሬዎችን በዝርዝር መገምገሙን ክልሉ አስታውቋል።

ክልሉ የገጠመውን የኅልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የሕዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያው አስፈልጓል ነው የተባለው።

ይህን ተከትሎ ወበዚህምው የልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴ ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የፀጥታ አማካሪ ሲደረጉ፤ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል መሠለ በለጠ የልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ሆነው መሾማቸው ነው የተገለፀው።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት፣ ነፃነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች መብቶችን በተመለከተ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ብሔራዊ ምርመራ (National Inquiry) ለማካሄድ ከፌዴራልና ከዘጠኝ ክልሎች የተወጣጡ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የፍትሕ ተቋማት ተወካዮች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ስብሰባ ተካሂዷል።

ውይይቱ ነፃነታቸውን በተነፈጉ ሰዎች መብቶች ጉዳይ የሚደረገውን የመጀመሪያውን ብሔራዊ ምርመራ ያስተዋወቀ ሲሆን፤ ብሔራዊ ምርመራን ለማካሄድ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል መግባባትን ፈጥሯል።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
#ሀብት_ያለው_አእምሮህ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የእለት ጉርስህን ለማግኘት እየተጣጣርክ ወይም ያለህ ሀብት እንዲበዛ የምታደርግበትን መንገድ እየፈለግክ ነው?

እንግዲያውስ ሀብት ያለው አእምሮህ የተሰኘው አዲሱ የዶ/ር ጆሴፍ መርፊ መጽሀፍ ይረዳሀል፡፡ መጽሐፉ “የሁሉም ሀብት መነሻ አእምሮ ነው” ይለናል፡፡

“የምትኖረው በአእምሮህ ውስጥ ነው፡፡ ሀብታም ወይም ደሀ፣ ለማኝ ወይም ሌባ የምትሆነው እዚያ ነው፡፡ በህይወት ውስጥ የምትፈልጋቸውን ነገሮች የመፍጠር ኃይል እንዳለህ ስትገነዘብ ታላቅ ዋጋ ያለው እንቁ እንዳለህ ታውቃለህ፡፡ በውስጥህ ያለው ሀብት እና ኃይል በጭራሽ የሚቀንስ ስላልሆነ አንተ ከምታስቀምጠው ገደብ በስተቀር የአእምሮህ ሀብት ገደብ አያውቅም፡፡”

ከዝቅታ ህይወት ወደ ከፍታ ህይወት ተሸጋግረህ አንገትህን ቀና ለማድረግም ሆነ፣ በሕይወትህ ውስጥ የሚገባህን ብልጽግና ለማግኘት ይህ መጽሐፍ እንዴት የድብቁን አእምሮህን ኃይል መጠቀም እንዳለብህ ያስተምርሀል፡፡

#ሀብት_ያለው_አእምሮህ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
ኢሰመኮ፤ የጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እስር “ስልጣንን አላግባብ የመጠቀምና ፍትሕን የማጉደል ነው” አለ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፤ የጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እስር “ስልጣንን አላግባብ የመጠቀም እና ግልፅ የሆነ የፍትሕን መጓደል መሆኑን አስታወቀ።ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ሁለት ወር ከ 10 ቀን ለሚሆን ገሂዜ በእስር ላይ መቆየቱን የገለጸው ኢሰመኮ ጋዜጠኛውን ጨምሮ ልክ እንደ እርሱ ሁሉ ያለአግባብ የታሰሩ አካላት ያለቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስቧል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa